Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን የታንዛኒያ ግንኙነት ጣቢያ ተመሠረተ

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን የጣለችበትን ኃላፊነት ለመወጣት  የሚያስችል ተቋማዊ አቅም እየገነባ ይገኛል። በተለይም ዘመኑ የሚጠይቀውን የአገልግሎት ተደራሽነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቋማዊ ለውጥ ሂደት ላይ ይገኛል።

የማኅበሩን አገልግሎት ከሚያጠናክሩት መዋቅሮች መካክል በግንባር ቀደምትንት የሚጠቀሱት ማእከላቱ ሲሆኑማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ 52 እና በውጭ አገራት ደግሞ 7 ማእከላትን በመመሥረት አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል።

ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም የማኅበሩን አገልግሎት ለማስፋት እንደሚያግዝ እምነት የተጣለበት  የታንዛኒያ ግንኙነት ጣቢያ  ተመሥርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ምሥረታውን ያደረገው ግንኙነት ጣቢያው በኬንያ ማእከል ሥር በመሆን እንደሚያገለግል ታውቋል።

በምሥረታው ዕለት የኬንያ ማእክል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር መኳንንት መለሰ እንደገለጹት በታንዛኒያ የሚገኙ ምእመናንን ለማጽናት እና ላላመኑት ደግሞ ወንጌልን ለማድረስ የግንኙነት ጣቢያው መመሥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል። በተጨማሪም ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የተቋማዊ ለውጥ ጉዞ ለታዳሚዎች ሰፊ ማብራሪያ እናገለጻ ተደርጓል።

በመጨረሻም የግንኙነት ጣቢያውን ሥራ አስፈጻሚ በመምረጥ የምሥረታው መርሐ  ግብር ተጠናቋል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ፣ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ርሐብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” ሮሜ 8፡35-36

ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራን፣ ሞትንና ስደትን፣ የመቀበል ታሪኳ ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ  ይኽንና መሰል መተኪያ የሌለው ሕይወት የሚያጠፋና ሥጋት ላይ የሚጥሉ ተፈጥሯዊ፣ ሰብዓዊ ክብሩን የሚያራክስ ተግባራት እንዳይደገሙ ለማድረግ በሚጥርበት ዓለም ችግሩ በተለይም በሀገራችን እየተባባሰ መቀጠሉ እጅግ ያሳስበናል፡፡
በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ሠላሳ ስድስት፣ እንዲሁም በሶሌ ዲገሉና ጢጆለቡ በተባሉ ቀበሌዎች ሃያ ስምንት ኦርቶዶክሳዊውያን ከየቤታቸው ተለቅመው ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ከእነዚህም ሰባቱ ሴቶችና ሃያ አንዱ ወንዶች ናቸው፡፡ በዚህ ጥቃት የሰባ ዓመት አዛውንትና የሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት ይገኛሉ፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን አምስት ምእመናን ሰማዕት ሲሆኑ የሦስት ምእመናን ቤት ተቃጥሏል። በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም አጥቢያ በዓለ ድንግል ማርያምን አክብረው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ገዳዮች ሰማዕትነት የተቀበሉ መሆኑን ከሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ደርሶን ከሐዘናችን ገና ሳንጽናና ይባስ ብሎ በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት የአቋቋም መምህር የሆኑት መምህር ፍሥሐ ዓለምነው ባልታወቀ ግለሰብ በድንጋይ ተወግረው መገደላቸው እና ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሌሊቱ 11፡00 ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት በኲረ ትጉሃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመተው መገደላቸው በእጅጉ ከማዘናችንም በላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያረጋግጥ አድራጎት ሆኗል፡፡ 

በዚህ መግለጫ በቅርብ የተፈጸመውን ለማቅረብ ተሞከረ እንጅ ተመሳሳይ ግድያና፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል የየዕለት ዜናችን ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ለአብነትም ያህል በወለጋ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በመሳሰሉት እየተፈጸመ ያለው ድርጊት መንግሥትና ሕገ መንግሥት ባለበት ሀገር፣ የውጭ ወራሪና ድንበር ተሻጋሪ ጠላት ሳይኖርብን፣ እርስ በርሳችን በምናደርገው መጠፋፋት፣ ሃይማኖት ተኮር ጥላቻዎች፣ የንፁሐን ሕይወት መቀጠፉና የሀገርን ሀብት መውደሙ እኛንም ሆነ በመላው ዓለም መፍቀሬ ሰብእ የሆኑ የሰብዓዊ ክብር አስጠባቂ ተቋማትን ሳይቀር ማሳዘኑ ቀጥሏል፡፡ 

ይህ ሁኔታ በታሪክ ከመመዝገቡ በላይ የዜጎች በሕይወት የመኖር፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት፣ የአካልና የንብረት ደኅንነታቸው መጠበቅ፣ የሃይማኖትና የእምነት ነፃነት መከበር፤ የዜጎች ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ ያለባቸውን አካላት በሙሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ እየተፈጠረ ባለው አስከፊ መከራ፣ በጭካኔ የተሞላ ድርጊት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ማጣት የዜጎችን ሕይወት፣ አካልና ንብረት፣ የእምነት ተቋማትን፣ መተኪያ የሌላቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶችና መስሕቦችን ሲያወድም፣ በሀገር ሁለንተናዊ ደኅንነትና በሕዝቦች ትሥሥር ላይ የፈጠረው አለመተማመን በቀላሉ የማይመለስ አደጋ ነው፡፡ 

ይኽ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከሰተው ረሀብ፣ ድርቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት በተጨማሪ በየቦታው በተፈጠሩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ምክንያት በርካቶች ቀያቸውን ለቀው፣ መነኰሳት ገዳማትን ትተው ተሰደዋል፤ ወላድ እናቶች፣ ሕሙማንና አረጋውያን በሕክምና እጦት እያለቁ ነው፣ ሕፃናትና ወጣቶች ከጤናማ እድገትና ከትምህርት ገበታ ተደናቅፈዋል፣ 

በመሆኑም

፩. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ከግጭትና ከጦርነት፣ ከእርስ በርስ መገዳደል ወጥተው በውይይትና በምክክር፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት የታላቋን ሀገር መልካም ስምና ክብር እንዲሁም የዜጎቿን ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ተግባር ቅድሚያ እንዲሰጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡  

፪. በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንፁሐን ምእመናንና ተቋማት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች  በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ መንግሥትና የሚመለከታችሁ ሁሉ ዋስትና እንድትሰጡ፣ ወንጀል ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ድርጊቱንም መላው ዓለም እንዲያወግዘው ቋሚ ሲኖዶስ በአጽንዖት ይጠይቃል፡፡ 

፫. ከቤተ ክርስቲያን አልፎ የሀገርና የዓለም ሀብት የሆኑ ቅዱሳን መካናት፣ እንደ ዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም፣ አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም እና አካባቢው፣ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳምና አካባቢው የመሳሰሉ ሁሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት አደጋ የተጋረጠባቸው በመሆኑ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን።

፬. በመጨረሻም በየቦታው የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለማስቀረት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራ ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብን ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራው መሳካትም  በየደረጃው ያላችሁ አህጉረ ስብከት የስጋት መረጃዎችን ለሚመለከተው ሁሉ በማሳወቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡   
 
ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ለሞቱት የተዋሕዶ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ዐስበ ሰማዕትታን እንዲከፍልልን፣ ለወገኖቻቸው ሁሉ መጽናናት እንዲሰጥልን፣ ስለስሙና ስለሰብዓዊ ማንነታቸው በመከራና ስጋት ወስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ ጽናቱንና ብርታቱን እንዲሰጥልን፣ አጥፊዎችን እንዲገስጽልን፣ ስደትና አለመረጋጋትን እንዲያርቅልን፤ የሀገራችንን አንድነትና ሰላም፣ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሕልውና እንዲጠብቅልን የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ 

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር

          እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

            ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.
                አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በየ3 ወሩ የሚካሄድ "ቦሩ ሜዳ መርሐ ግብር በኦሮምኛ ቋንቋ ጀመረ።

ከማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የፊት ለፊት የጥያቄና መልስ መድረክም የመጀመሪያ ጉዳዩን ነገረ ማርያም ላይ አድርጓል።

በዕለቱ መነሻ ሃሳብ ካቀረቡ በኋላ ከምእመናን ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ቀሲስ ዶ/ር ደሳለኝ ዋቅጋሪ የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና መምህር እሱባለው ደምሴ ናቸው።

በመድረኩም የእመቤታችን መልኳ እንደ አምላክ መልክ ነው፡፡ ሐሳቧም እንደ አምላክ ሐሳብ ነው፡፡  የሚለው ሰው እንደ አምላክ ማሰብ ይችላልን?  ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠሩ፡፡ የሚለው ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን አምላክ አያደርጋትም ወይ የሚልና ሌሎች ጥያቄዎች ቀርበው በመምህራን መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ይህ "ቦሩ ሜዳ" የተሰኘው በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጀው መርሐ ግብር በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩ በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በቅርብ ቀን ወደ ተመልካች የሚደርስ ይሆናል።

"ቦሩ ሜዳ" በአማርኛ ዝግጅት ክፍል ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተለያዩ የእቅበተ እምነት ጉዳዮች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በመጋበዝ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
"ሙያችን ለቤተ ክርስቲያናችን" በሚል ልዩ የኦርቶዶክሳውያን ባለሙያዎች ምክክር ጉባኤ ተካሄደ
+++
መርሐ ግብሩ ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ  የተካሄደ ሲሆን፣ ኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ዕውቀት ከዘመኑ ጥበብ ጋር አጣምረው ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚያውሉበት መንገድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊ ዲ/ን አንድነት ተፈራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፍዋል።
በምክክር መርሐ ግብሩም ከስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በተጨማሪ የመርሐ ግብሩ ዋና አካል የሆነው “ኦርቶዶክሳዊ የሙያ አገልግሎት ምንነት፣ልምዶችና የቀጣይ ትኩረቶች” የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ በዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ የሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ ቀርቧል። በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት የአገልግሎት ዘመናት በሰጠው የሙያ አገልግሎት የተገኙ ውጤቶች በማሳያነት ቀርበዋል። በተጨማሪም በሙያ በማገልገል ሂደት ያሉ ችግሮችና መፍትሔዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብሪያ ተሰጦባቸዋል።
በቀጣይነትም ከማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ አንጻርና ቤተ ክርስቲያን ከሙያተኞች ልታገኘው የሚገባውን አገልግሎት በተመለከተ ከጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢዎችና አወያዮችዎች ማጠቃለያ ተሰጥቶበታል።
መሠል መርሐ ግብራት በቀጣይ ጊዜ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ሙያተኞች በሙያቸው ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉባቸው የሚችሉ አደረጃጀቶችና ሥልታዊ ተግባራት ተለይተው የተቀመጡ መሆናቸው ተገልጿል
‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› ቅዱስ ያሬድ
 
ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት፣ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች፣ ንጽሕናዋንም ይሁን ቅድስናዋን ፍጥረት በአንደበቱ ተናግሮም ሆነ ጽፎ የማይጨርሰው፣ የአምላክ ማደሪያ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብዙኃን፣ ሰዓሊተ ምሕረት፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡፡
 
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› በማለት ስለ እርሷ የቅድስናና የንጽሕና ሕይወት ገልጿል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፈቃደ እግዚአብሔር ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄምና ከእናቷ ቅድስት ሐና በስእለት የተገኘች መሆኗ ታሪኳ የተመዘገበበት የነገረ ማርያም መጽሐፍ ይገልጻል፡፡
 
ቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም በተለወደች በስድስት ወሯ ከእናቷ እቅፍ ወርዳ በመቆምና  ሰባት እርምጃን ተራምዳ ዳግም ወደ እናቷ እቅፍ ውስጥ በመግባት ሐናን አስደንቃታለች፡፡ አንድ ዓመት ሲሆናትም አባቷ ኢያቄም ታላቅ ድግስ አዘጋጅቶ ካህናቱንና ሕዝብን ጠርቶ ጋበዘ፡፡
 
ከዚህም በኋላ እመቤታችን ሦስት ዓመት በሆናት ጊዜ እናቷ ሐና የልጇን ስእለት አስታውሳ ለቤተ መቅደስ አገልጋይ እንድትሆን መስጠት እንዳለባቸው ለባሏ ለኢያቄም እንዲህ ብላ አወሳችው፤  ‹‹ይህቺ ብላቴና የስእለት ገንዘብ እንደሆነች ታውቃለህ፤ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጣት፤›› እርሱም ‹‹ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማ ፈቃዴ ነው›› አለ፤ ኢያቄም ይህን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኖራ ያገኘቻት አንዲት ልጇ ናትና ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው፡፡
 
2024/09/30 10:35:57
Back to Top
HTML Embed Code: