Telegram Web Link
ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐናም የእግዚአብሔርን ስእለት ለመፈጸም ዘመዶቻቸውንና ባልንጀሮቻቸውን በመጥራት ልጃቸውን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ በዚያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ከካህናቱ ጋር በመሆን እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ፡፡
 
በቤተ መቅደሱ ባሉት የሊቀ ካህናቱ መግቢያ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ነበሩ፤ በእነዚያም በእያንዳንዱ ደረጃዎች መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ የሚደረስባቸው ናቸው፤ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐናም ልጃቸው እመቤታችን ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯት መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወዳለበት ስፍራ ሄደች፤ እርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት፤ በዚያን ጊዜም ለሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መንፈስ ቅዱስ ምሥጢርን ገለጠለት፤ ነቢያት ትንቢት የተናገሩላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ አስገነዘበው፤ መኖሪያዋም በዚሁ ቤተ መቅደስ እንዲሆን የአምላክ ፈቃድ መሆኑን አወቀ፡፡
 
እርሱም ይህንን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ‹‹ይህቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን?›› ብሎ ሲጨነቅ ቸርነቱ የማያልቅ ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤልም ኅብስት ሰማያዊን በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ ታየ፤ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ ኅብስተ መና እንደሆነ አስቦ ታጥቆና እጅ ነሥቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ በተራ በተራ ቢሞክሩም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡  ሐና እና ኢያቄምም ለእነርሱ የመጣ እንደሆነ ለማወቅ ቢቀርቡም ወደ ላይ ከፍ አለባቸው፤ ከዚህ በኋላ ካህኑ ዘካርያስ ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፡፡ በዚህ ጊዜም መልአኩ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ፣ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያህል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መገባት፤ ጽዋውን አጠጣት፤ በኋላም ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ሊቀ ካህናቱም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን  ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን›› ብለው ምንጣፉን አንጥፈው፣ መክዳውን ግራና ቀኝ፣ መጋረጃውን አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፤ ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡
 
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስት እየተመገበች፣ ስቴ ሕይወት እየጠጣችና ከመላእክት ጋር እየተጫወተች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ሆኖም ግን በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ተሰብስበው ክፉ ምክርን መከሩባት፤  “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለችና እርሷም እንደ ባሪያ ልትገዛን ነው” በሚል ለማስገደል ሰዎችን ላኩ፡፡ እነዚያም አይሁድ የላኳቸው ሰዎች ሊገድሏት ሲሄዱ ቤተ መቅደሱ አራት ማዕዘን እሳት ሆኖ፣ መላእክትም ሰይፋቸውን መዘው፣ ረበው ታዩአቸው፡፡ ይህን ሲመለከቱ እመቤታችን በእሳት እንደ ተቃጠለች አስበው በመደሰት ወደ መጡበት ተመልሱ፤ በማግስቱ ግን በቤተ መቅዱስ በደኅና አገኟት፡፡   
 
አይሁድ በዚህን ጊዜ እንዲገድሏት ወዳዘዙአቸው ሰዎች በመሄድ ለምን እንዳልገደሉአት ጠየቁአቸው፤ እነርሱም የሆነውን ባለ መረዳት በድጋሜ ሊገድሉአት ሄዱ፤ ዳግመኛም መንገዳቸው ዱር፣ ገደልና ባሕር ሆነባቸው፡፡ ይህን ጊዜ በአስማት እንዲህ የምታደርጋቸው እንደሆነ በማሰብ የእርሷን አስማት የሚበልጥ ለመፈለግ ተስማምተው መጥቁል የሚባል መተተኛ ጋር ሄዱ፡፡ እርሱም ‹‹ዋጋዬን ከሰጣችሁኝ እሺ፤ እርሷንስ አጠፋላችኋለሁ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ብዙ ወርቅ፣ ፈረስ፣ በግ፣ ፍየል፣ ጊደርና አልባሳት ሰጡት፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ ሀብት ለማግኘት መለስ ቢል ብሩ፣ ወርቁና ሁሉ ነገር ዝጎና አፈር በልቶት አገኘው፡፡ ይህን ጊዜ ‹‹የኢያቄምና የሐና ልጅ ሳልቀድማት ቀደመችኝ›› ብሎ እጅን ጸፋ፡፡ ከዚያም ለእነርሱ ሲያሳያቸው ‹‹እኛማ ቀድመን አላልንህምን?  አንተ ነህ እንጂ ሁሉን ማድረግ ይቻለኛል ያልከው›› አሉት፡፡ ገንዘባቸውንም እንዲመልስላቸው አስጨንቀው ያዙት፤ መጥቁልም ‹‹ቆዩኝ፥ የእርሷንስ ነገር አሁን በመንፈቀ ሌሊት አሳያችኋለሁ›› ብሎ ከእነርሱ መካከል ጎበዝ ጎበዙን መርጠው ፫፻፸ ሰው እንዲሰዱለት በጠየቃቸው መሠረት ሰጡት፤ ከእነርሱም መካከል ወንዝ ወርዶ አንዱን አርዶ ፫፻፸ አጋንንት ስቦ ካወጣ በኋላ እንዲረዱት ጠየቃቸው፤ በጠየቃቸው ነገር ደስ በመሰኘትም አጋንንቱ ከፊት፣ መጥቁል በመካከል አይሁድ በኋላ ሆነው ነጋሪት እየተመታ፣ እምቢልታ እየተነፋ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመግደል ቤተ መቅደስ ሊደርሱ ሁለት ምንዳፈ ሐጽ ሲቀራቸው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ድረስ ያልተደረገ መብረቅና ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትን፣ መጥቁልንና አይሁድን ቀጥቅጦ አጠፋቸው፡፡
    
እመቤታችን ድንግል ማርያምም በማግስቱ ይህን አይታ ‹‹መጥቁል ሆይ፥ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንክ? ከአንተ መከራና መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ አመሰገነች፡፡ ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የጌታን ኅቡእ ስሙን ብትጸልይበትም መሬት ተከፍቶ ከእነ ሥጋቸው ዋጣቸው፡፡
 
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከዚህ በኋላ ተፈራች፤ ለመልካም ሰው ወዳጅ ለክፉ ሰዎችም ጭምር አማላጅ የሆነችው እናታችን ለጠንቋይና ለአስጠንቋይ ግን በሕይወተ ሥጋ እስካሉ ድረስ ንስሓ ካልገቡ በስተቀር እንደማታማልዳቸው ከዚህ ታሪክ እንረዳለን፡፡
  
እናታችን፣ አማላጃችንና ተራዳኢያችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠላት የተነሡባት በዚህ ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላትም ‹‹ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ መውጣት አለባት›› በሚልም አይሁድ በጠላትነት ተነሥተውባት ነበር፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን እንዲህ ብሎ ጠየቃት፤ «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም «ከእግዚአብሔር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናትና አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ አምላካችን እግዚአብሔርም ለካህኑ ዘካርያስ ከነገደ ይሁዳ መካከል ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሰዎች በመምረጥ በትራቸውን ሰብስቦ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብቶ ሲጸልይ እንዲያድር እንዲሁም በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጥቶ ምልክቱን እንዲመለከት ነገረው፡፡ እርሱም እንደታዘዘው አድርጎ በማግስቱ ካህናቱን ሰብስበው በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይም «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት» የሚል ጽሑፍ በመገኘቱ ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋ ነበርና ለእርሱ ተጠሰች፡፡
 
እመቤታችን ድንግል ማርያምም ከዚህ በኋላ ከቤተ መቅደስ ወጥታ ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ኖረች፡፡ እርሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ ስትወልድ፣ በስዳቷ ወቅትም ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ስትጓዝ እንዲሁም መከራ ስትቀበል ሁሉ ከጎና ሳይለይ የጠበቃት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ግን አምላካችን እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኛ ድኅነት ሲል ያደረገው በመሆኑ በእመቤታችን በኩል የተፈጸመውን የክርስቶስ የማዳን ሥራ በእምነት በመቀበል አማላጀነቷንና ተራዳኢነቷን ተስፋ በማድረግ ልንኖር ይገባል፡፡
 
በዓሉን የምሕረት፣ የበረከትና የረድኤት ያድርግልን፤ አሜን!
    
ምንጭ፡- “ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን” በመጋቤ ሐዲስ መምህር ሮዳስ ታደሰ
 
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለሚያስገነባው ባለ ዐስራ ሁለት ወለል ሕንጻ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)፣ የጅጅጋ ሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም(ዶ/ር)፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ እና የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን እንዲሁም  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የሚገነባው አዲሱ ሕንጻ ማእከሉ ወጣት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሙሉ አቅሙ በማስተማር የቤተ ክርስቲያን እና የሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እና በማእከሉ ለሚከናወኑ ልዩ ልዩ የሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የሙያ አገልግሎት፣የሚዲያ ተደራሽነት እና ለቅዱሳት መካናት ተግባራት አቅም የሚፈጥር መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።


በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለሁሉ ነገር መሠረት እና ለምንፈልገው ለውጥ የምርምር እና የትምህርት ተቋማት ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አክለውም የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ትልልቅ ተቋማትን ለማቋቋም የማንንም ርዳታ ሳንጠብቅ ዐሥር ሚልዮን የምንሆን ኦርቶዶክሳውያን በዓመት ውስጥ ባሉን የፆም ወቅቶች ብቻ ለቁርስ ወጪ የምናደርገውን ብናዋጣ ዓላማችንን ማሳካት እንችላለን ብለዋል፡፡
በመልዕክታቸው መጨረሻ ላይም ይህ የአዲስ አበባ ማእከል ሕንጻ የዚህ ስኬት አካል ስለሆነ ሁላችንም የድርሻችንን ብንወጣ በአንድ ዓመት ውስጥ መጨረስ እንችላለን በማለት ተናግረዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በበኩላቸው ይህ ዛሬ በአዲስ አበባ ማእከል እየተገነባ ያለው የወጣቶች ማእከል በአጠቃላይ ወጣቱ ትውልድ ስለ አገሩና ስለቤተ ክርስቲያኑ የሚመራመርበት፣ ዘመኑ ከሚያመጣቸው ፈተናዎች ተጠብቆ ለበጎ ነገር የሚነሳሳበት መሆኑን ተገንዝበን ምዕመናን ሁሉ ተረባርበን በአጭር ጊዜ ልናጠናቅቀው ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሰብሳቢው አክለውም ማኅበሩ ባለፉት 32 ዓመታት  በሀገር ውስጥ እና በውጪ፣ በገጠርና በከተማ ውጤታማ ተግባራትን ማሳካት የቻለው በአባቶች ቡራኬ፣ በአባላቱ ጠንካራ ሥራ እና በምዕመናን ድጋፍ በመሆኑ ይህ ፕሮጀክት እንዲሳካ የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ ከተገኙት ታዳሚዎች 7,500,000.00 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) ቃል የተገባ ሲሆን ለዚህ በጎ ዓላማ ምዕመናን ሁሉ እንዲሳተፉ የሕንጻ ግንባታ ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የጾም ቁርሳችን ለወገናችን
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰው ከፍተኛ ድርቅና ማኅበራዊ ቀውስ ወገኖቻችን ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል።
ስለዚህ እርስዎ ከታኅሣሥ 1 -27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የጾም ቁርስዎን በመስጠት የሰው ሕይወትን ያትርፉ።
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400
ማኅበረ ቅዱሳን
09 84 18 15 44
09 43 00 04 03
የጾም ቁርሳችን ለወገናችን
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ከፍተኛ ድርቅና ማኅበራዊ ቀውስ ወገኖቻችን ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል።
ስለዚህ እርስዎ ከታኅሣሥ 1 -27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የጾም ቁርስዎን በመስጠት የሰው ሕይወትን ያትርፉ።
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 በወገን ፈንድ ለመለገስ የተያያዘውን ሊንክ ይጫኑ።
https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/
ማኅበረ ቅዱሳን
09 84 18 15 44
09 43 00 04 03
ማኅበረ ቅዱሳን በድርቅ ለተጎዱ የሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃና አሞራ አካባቢዎች 1.5 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት ድጋፍ አደረገ 
+++

በሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠመ ባለው ድርቅ፣ ጦርነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳዊያን ጨምሮ የሀገራችን ሕዝቦችን ለከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ተጋላጭ እየሆኑ እንዳለ ይታወቃል። 

ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 5 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት፣ በመቐለ እንዲሁም በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣በወልዲያ፣በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስና በሌሎች የሀገራችን ክፍል ያጋጠሙ ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶችን መረጃ በማደራጀት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።

በአሁኑ ወቅት በሰሜን ጎንደር ባጋጠመው  ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ  ለሚያስፈልጋቸው በደባርቅ ወረዳ አርግንጆና እና በአደባባይ ጽዮን ቀበሌዎች ለሚገኙ 1 ሽህ 860 ወገኖች 235 ኩንታል አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በጃና አሞራ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ አደጋው ምክንያት ለተጎዱ 29 ገዳማት አድባራት 500, 000 ብር የፈጀ ዕጣን ጧፍና ዘቢብ ድጋፍ ተደርጓል። 
በአጠቃላይ ለድጋፉ ከ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ወጭ ተደርጓል። በድጋፉም ርክክቡ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የደባርቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ጌትነት፣ የጎንደርና ደባርቅ ማእከላት ተወካዮች ታኅሣሥ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው ተገኝተው ድጋፉን ለተጎጅዎች እጅ በእጅ አስረክበዋል።  

ድጋፉ የሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከልና ሌሎች በጎ አድራጊ ምእመናንና ተቋማት ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው። በተመሳሳይ መረጃ በቅርብ ጊዜያት ብቻ በዋግሕምራ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ ከቅበት ተፈናቅለው ቡታጅራ ይገኙ ለነበሩ ተጎጅዎች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣይ ጊዜያትም በድርቅና ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱ አካባቢዎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ የሚያከናውናቸው የአስቸኳይ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል።

ለእነዚህ መሰል ሰብአዊ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ለማድረግም፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-

በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
6. በአዋሽ ባንክ 01329817420400                                                                                                   7. በወገን ፈንድ፡- https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/  መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን።                                                        
ለበለጠ መረጃ
•  09 43 00 04 03
•  09 84 18 15 44 
ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን

ክፍል አንድ


ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንዴት ሰነበታችሁ? እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ‹‹መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን›› በሚል ርእስ ተከታታይ ጽሑፍ እናደርሳችኋለንና ተከታተሉን፡፡

መልካም አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው የሚሠራ ሳይሆን ተሠርቶ የተጠናቀቀ መዋቅር ባለቤት ናት፡፡ የመንግሥት መዋቅር በሌለበት ቦታ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አለች፡፡ ከአጥቢያ እስከ አንድ ግለሰብ መኖሪያ ድረስ ቤተ ክርስቲያን አለች፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሊቃውንትን፣ ካህናትን፣ መነኮሳትን፣ ዲያቆናትን፣ መዘምራንን፣ ምእመናንንና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የምታስተዳድር ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ብዙ የሰው ኃይል በማስተዳደር የሀገር ሸክምን ያቃለለች፣ የብዙ ሰዎችን ሥጋዊና መንፈሳዊ ሕይወት የቀየረች፣ ለተራቡ ሁሉ ምግበ ሥጋ፥ ምግበ ነፍስ የምትመግብ ናት፡፡ የታመሙ የሚፈወሱባት፣ ያዘኑ የሚጽናኑባት፣ የተሰበሩ የሚጠገኑባት፣ የፈውስ፣ የድኅነት መገኛ መሆኗን ዓለም ያወቀው እውነት ነው፡፡

ለበርካታ ዓመታት ይህን ጽኑ ተግባር ስትፈጽም ከዚህ የደረሰችው ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥበብ በተሞሉ መሪዎችና አገልጋዮች ከፍተኛ አስተዳደራዊ ጥበብና መሥዋዕትነት ነው፡፡ ሥርዓተ መንግሥት አንድ ሺህ አንድ ጊዜ ፈርሶ ተሠርቷል፡፡ ምክንያቱም የሚመሩት ሥጋዊ ጥበብ ቢኖራቸው መንፈሳዊ ጥበብ የሚድጎላቸው ናቸውና፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ጥበብ የጎደላቸው እና ፍቅረ ንዋይ የሚገዳደራቸው አገልጋዮች በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ በመኖራቸው እየተፈተነች በከፋ የአስተዳደር ችግር ውስጥ ትገኛለች፡፡
መልካም አስተዳደር ማለት ምን ማለት ነው?

ዓለም በአሁኑ ጊዜ ትልቅ አጀንዳ ከሚያደርጋቸው ጉዳዮች ዋናው መልካም አስተዳደር ነው፡፡ መልካም አስተዳደር መገለጫው ብዙ ነው፤ እንደ የተቋማቱ ባሕርይ፣ የሥራ ሁኔታ በልዩ ልዩ ሁኔታ ሊገለጽ የሚችል ቢሆንም የጋራ ባሕርያት ይኖሩታል፡፡

ይሁን እንጂ መልካም አስተዳደር ውጤታማነት፣ ጥራት፣ የተገልጋዮችን ነጻነት የሚያከብር፣ አድልዎ የሌለባት፣ የሕግ የበላይነት፣ ተጠያቂነትና ግልጸኝነት፣ ያለው አገልግሎት መስጠትን፣ መልስ ሰጭነትን፣ ኃላፊነት መውሰድን፣ አሳታፊነት፣ ፍትሐዊነትና ስልታዊ የሆነ ርእይ መያዝን የሚያካትት እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ መልካም አስተዳደር ካለ ሥልጣን ለያዙ ሰዎች ላይ ሕጋዊ ገደብ የሚያስቀጥ እና ሥልጣን በተወሰኑ በተጨማሪም መልካም አስተዳደር ግለሰቦች ሥር እንዳይሆን የሚያደርግ ነው፡፡

መልካም አስተዳደርን ከቤተ ክርስቲያን አኳያ ብፁዕ አቡነ አስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ለሥራ ኃላፊዎች በሐምሌ ፳፻፭ ዓ.ም በተሰጠ ሥልጠና ላይ ተገኝተው እንዲህ ገልጸውት ነበር፡፡

‹‹መልካም አስተዳደር ማለት ከእግዚአብሔር በተሰጠን ሥልጣንና ኃላፊነት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት በሁሉም መስክ በጎ አርአያነት ያለው መልካም እረኛ መሆን ነው፡፡›› የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በድረ ገጹ በለቀቀው አንድ ጽሑፍ ላይ ደግሞ ‹‹መልካም አስተዳደር ማለት በአገልጋይና በተገልጋይ መካከል በመተማመን ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠር›› ማለት እንደሆነ ያትታል፡፡ ጠቅለል ብሎ ሲገለጽ መልካም አስተዳደር የሚባለው ሐሳብ ከውሳኔ አሰጣጥ ሂደትና የተወሰነውን ውሳኔ ከማስፈጸም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለሆነም ለተገልጋዮች ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ፣ መብታቸውን የሚያስጠብቅ፣ አገልግሎት የሚያቀርብ እና ሕጎችን ተግባራዊ የሚያደርግ የአስተዳደር ሥርዓት ሁሉ መልካም አስተዳደር ሊባል እንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የምንለው ምኑን ነው?

በዓለም ያሉ ተቋማት ቢያስተዳድሩ የተወሰነ ጉዳይን ነው፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ግን ሥጋውንም፣ መንፈሳዊውንም ያቀፍ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ ይህም ከሰው ሀብት አስተዳደር፣ ከፋይናንስ አስተዳደር እና የንብረት አስተዳደር በተጨማሪ መንፈሳዊ አስተምህሮውም ያካተተ በመሆኑ ነው፡፡

ሀ. የሰው ሀብት አስተዳደር

የአንድ ተቋም ህልውናው የሚረጋገጠው ዋናውና የመጀመሪያው የሰው ሀብት አስተዳደሩ ነው፤ ተቋም ውጤታማ ለመሆን በጠንካራ፣ በብቁና በሥነ ምግባሩ ምስጉን የሆነ የሰው ኃይል መዋቀር አለበት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ መነኮሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራንና ሌሎችም በልዩ ልዩ ሙያ የሚያገለግሎ ምእመናንን በርካታ የሰው ኃይል ታስተዳድራለች፡፡ እነዚህ አገልጋዮች ብዙኃኑ ጠንካሮችና በጥብቅ ሥነ ምግባር የሚመሩ፣ የሥጋዊና መንፈሳዊ ዕውቀት ባለቤቶች ስለ ነበሩ ቤተ ክርስቲያኗ በማዕበልና በወጀብ ውስጥ አልፋ ለእኛ ልትደርስ ችላለች፡፡

ለ. የንብረት አስተዳደር

ቤተ ክርስቲያን እጅግ ግዙፍ መንፈሳዊና ሥጋዊ ሀብት ባለቤት ናት፡፡ ቁጥራቸው ከአርባ ሺህ በላይ አድባራትና ገዳማትን፣ በርካታ የመሬት ይዞታዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ኮሌጆችን፣ ልማት ተቋማትን፣ ሕንፃዎችን፣ የጸበል ቦታዎችን እና ተሽከሪካረዎችን የአገልግሎት መስጫዎችን፣ መኪኖችን ከመንበረ ፓትርያሪክ እስከ አጥቢያ ድረስ ታስተዳድራለች፡፡

ሐ. የፋይናንስ አስተዳደር

በገንዘብ አስተዳደር በኩልም በስእለት፣ በዐሥራት በኩራት፣ በልማት፣ በኪራይ፣ በርዳታ፣ በስጦታ፣ በጸበል እና በልዩ ልዩ አገልግሎት ምክንያት የሚሰበሰብ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ታስተዳድራለች፤ ታንቀሳቅሳለች፡፡

መ. የምእመናን አስተዳደር

መንግሥትም ሕዝብን ቢያስተዳድር በኃይል ታግዞ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ከዚህ በተለየ መንገድ ምእመናንን ታስተዳድራለች፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድ ተቋም እንደሚያደርገው በሥሯ የሚያገለግሉትን ብቻ ሳይሆን ምእመናንን በሥጋዊና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ትልቅ ኃላፊነት ወስዳ በኃይል ሳይሆን በሰላም በጠብ ያይደለ በፍቅር ታሰተዳድራለች፤ ትጠብቃለች፡፡

ሠ. የመንፈሳዊ ሀብት አሰተዳደር

ቤተ ክርስቲያን ሌላም ድርብ አስተዳደራዊ ኃላፊነት አለባት፡፡ እርሱም የማይዳሰሰውንና በቁሳዊ ዋጋ የማይተመነውን መንፈሳዊ ሀብት ማስተዳደር ነው፡፡ ይህም ዜማውን፣ ቅኔውን፣ ሥነ ጥበባዊ ዕውቀቱን፣ ሥነ ጽሑፋዊ ሀብቱ፣ ሥነ ሥዕሉን ሁሉ መንፈሳዊ ዋጋ ያለውን፣ መለያዋ የሆነውን ትጠብቃለች፤ ታስተዳድራለች፡፡ ከምንም በላይ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮውን፣ ትውፊቱን፣ ዶግማውን ከቀኖና አስተባብራ ትጠብቃለች፤ እንዳይቀሰጥና እንዳይሸራረፍ ታሰተዳድራለች፡፡

የተወዳጆችሁ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! ለዛሬ በዚህ አበቃን! ‹‹የመልካም አስተዳደር እጦት በቤተ ክርስቲያን›› በሚል ርእስ ሁለተኛውን ክፍል ይዘንላችሁ እስክንቀርብ ቸር እንሰንብት! አሜን!
2024/09/30 12:22:24
Back to Top
HTML Embed Code: