Telegram Web Link
#ተከታታይ_ኮርስ

ውድ ተከታታዮቻችን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እና ሰኞ በግሩፓችን (የተዋህዶ ልጆች) ላይ ኮርስ የምንሰጥ ይሆናል።ስለዚህም እናንተም ግሩፕ ውስጥ በመቀላቀል መማር ይችላሉ።ሌሎች ወንድምና እህቶቻችሁን በመጋበዝ ፤ በመጠየቅና መማር ይቀጥሉ።

ኮርሱ ሁሌ ቅዳሜ እና ሰኞ ከ 2:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ ይሆናል።

ለመመዝገብ የእርሶን ስልክ ቁጥር ፤ ሙሉ ስሞትን ፤ Username ወደዚህ ቦት ይላኩ @Tewahido_lijoch_course_bot

ግሩፑ ለመቀላቀል ይህን ሊንክ ይጠቀሙ የተዋህዶ ልጆች
በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው  የሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፊልም ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ታዘዘ።
***

ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
==============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲነርጂ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ የስማዕትነት ተጋድሎ ዙሪያ የሚያጠነጥን ፊልም ለመስራት የሚያደርገው እንቅስቃሴ
ታሪክን የሚያጎድፍ ሆኖ ስለተገኘ ሊቆም እንደሚገባ በመግለጽ ኅዳር 25 ቀን 2016ዓ.ም  በቁጥር 1673/2789/2016 በተጻፈ ደብዳቤ መግለጹ ይታወሳል።


ይህንን ተከትሎ የፊልሙ ጸሐፊ እና ዳይሬክተር  ሞገስ  ታፈሰ ዶ/ር  እየተዘጋጀ የሚገኘውን  ፊልም ቤተክርስቲያናችን በሊቃውንቶቿ አማካኝነት  መርምራ፣ የሚታረም ካለ አርማና የሚቃናውን አቅንታ በምትሰጠን አስተያየትና ማስተካከያ መሠረት ፊልሙን የምንሠራ መሆኑ  ታውቆ አስፈላጊው ትብብር ሁሉ ይደረግልን። በማለት በጽሑፍና በአካል  ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመገኘት  በፊልሙ ዝግጅት ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ ጠይቀዋል።

ብፁዕ  አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም  ዶ/ርሞገስ ታፈሰ ያቀረቡትን ይቅርታ  በመቀበል በአካልና በጽሑፍ በፊልሙ ጽሑፍ ዝግጅት ዙሪያ  መረጃ ከመስጠት ባለፈ በቤተ ክርስቲያናችን በኩል የፊልሙ ጽሑፍ እንዲመረመርላቸውና እርማት በሚያስፈልገው ጉዳይ ዙሪያ እርማት እንዲደረግበት መጠየቃቸው የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎም  የፊልም ጽሑፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጉባኤ በሚገባ ተመርምሮና መታረም ያለበት ሁሉ ታርሞ እንዲቀርብ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን የፊልም ጽሑፉም በሊቃውንት ጉባኤ እየተመረመረ መሆኑ ታውቋል። ሊቃውንት ጉባኤ የፊልሙን  ጽሑፍ መመርመሮ ሲያጠናቅቅም ውጤቱን የምንገልጽ ይሆናል።

ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
" ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኃላ ህክምና ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም " - ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ተገደሉ።

ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ሊተርፉ ሳይችሉ ቀርቶ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው የግድያው ምክንያት እንደማይታወቅ ገልጸው በክስተቱ የተሰማቸውን መሪር ኃዘን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢኦተቤ ቴቪ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስታባበሪያ በርቀት ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩትን 155 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አስመረቀ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++

በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋህዶ በነበረው የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም (ዶ/ር)፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋስይሁን በላይ፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎች፣ ተመራቂዎች እና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

121 ወንዶችና 34 ሴት ተመራቂ ተማሪዎች በኢ ለርኒግና በሞጁል በስምንት ማእከላት ትምህርታቸውን መከታተላቸው በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በዋናነት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ፍላጎት ላላቸው ኦርቶዶክሳውያን እና በሌላ እምነት ውስጥ ላሉ ወገኖች ባሉበት ቦታ በአመቺ ቴክኖሎጂ ትምህርቱ እንደሚሰጥም ተጠቁማል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስታባበሪያ በኩል ምእመናን በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ፣ የጠፉትን ወገኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን መመለስና አዳዲስ አማንያንን ማስተማር የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው። በማለት መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሰብሳቢው አክለውም ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣ የስብከት ኬላ መሥራት፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ማስከፈት፣ ጠረፋማ በሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመምህራን ወርሀዊ ድጎማ በማድረግ ረገድ ዘርፈ ብዙ ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ክርስትና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን የሚያቀውን በሕይወት መግለጥ አለበት ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በተጨማሪ እንደገለጹት ቅድስት ቤተክርስቲያን የታሪክ ባለቤት በመሆኗ የሐዋርያትን ሕይወት ዛሬ በመኖር ልንደግመው ይገባል ብለዋል፡፡

በዕለቱ ያነጋገርናቸው ተመራቂዎች በበኩላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ላመቻቸላቸው የትምህርት እድል በማመስገን ትምህርቱ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፣ ቀኖና ፣ ሥርዓትና ትውፊት ላይ የካበተ እውቀት እንዳስጨበጣቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ በተመቻቸላቸው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የሥነ ፍጥረት ትምህርት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፣ ትምህርተ ክርስትና፣ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ የክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር መግቢያ መከታተላቸው ታውቋል፡፡
2024/09/30 12:19:31
Back to Top
HTML Embed Code: