Telegram Web Link
ዘመነ ጽጌ
 
ዘመነ ጽጌ የሚባለው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያለው ነው። ይህ ወቅት ዐቢይ የምስጋና ቀናት ያለው ሊቃውንቱ በማሕሌት፣ ምእመናን በፍቅር ሆነው የእናታችን የድንግል ማርያምን ስደት ከተወዳጅ ልጇ ጋር የሚያዘክሩበት ወር ነው። ከማሕሌቱም በተጨማሪ ምንም እንኳን የዐዋጅ ጾም ባይሆንም የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው በጾም ሆነው የሚያሳልፉት ዐቢይ የምስጋና ወቅት ነው።
 
ጽጌ ማለት ጸገየ አበበ ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን አበባ፣ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው። አበቦች ውብ፣ ማራኪና አስደሳች ከመሆናቸው የተነሣ የሰው ልጆች በሙሉ አበቦችን ይፈልጋሉ። ምድርም በአበቦች አጊጣ ተሸልማ ስትታይ ክረምት ከለበሰችው ልምላሜ ይበልጥ ታስደስታለች። ዘመነ ጽጌ ዝናምና ወጨፎ፣ ዶፍና ጎርፍ፣ መብረቅና ነጎድጓድ የሚፈራረቅበት የክረምት ቀናት አልፎ ምድር በአበቦች የምትሸለምበት፣ ደመናው ከሰማይ ተወግዶ ሰማይ በከዋከብት የሚያሸበርቅበት፣ የሰው ልጆች ይህንን በማየት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ወር ነው።
 
ወርኃ ጽጌ የዘመናት ባለቤት ዘመነ ክረምቱን አሳልፎ የደስታ እና የመልካም ምኞት መግለጫ በሆኑ አበቦች ወደ አሸበረቀው ዘመነ ጸደይ ስላደረሰን "ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፤ ክረምት አለፈ በረከት ተተካ ምድርም በአበቦች አጌጠች” እየተባለ የሚዘመርበት ወቅት ነው። በዚህ ወራት ሰውም ዕድሜው እንደ አበባ አጭር በመሆኑ ሞቱን ማሰብ እንዳለበት ማስገንዘብ ተገቢ ነው። አበባ የሚወድቀው የሚረግፈው ፍሬ ለማፍራት ነው፤ አበባ ሲኖር በመዓዛው፣ ሲረግፍ በፍሬው ያስደስታል።
👍44
ሰውም ሲኖርም ሲሞትም ፈጣሪውን ማስደሰት አለበት እንጅ ያለ ፍሬ ንስሓ መሞት የለበትም፤ "ግበሩኬ እንከ ፍሬ ሠናየ ዘይደልወክሙ ለንስሓ፤ እንግዲህስ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ እንዲል፡፡ (ማቴ.፫፥፰)
 
ወርኃ ጽጌ የእናታችንን ስደት ከተወደደው ልጇ ጋር የምናስብበት ነው። በተለይም ማሕሌተ ጽጌ በተባለው ድርሰት ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል እርሷን በአበባ ጌታችንን በፍሬ፣ እርሷን በፍሬ ጌታን በአበባ እየመለሰ ብሉይን ከሐዲስ አጣጥሞ የተናገረው ምሥጢር ድንቅ ነው። ክርስቶስን በአበባ ሲመስለው ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ትወፅእ በትር እም ሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እም ጉንዱ" በማለት ድንግል ማርያምን በጉንድ ክርስቶስን በጽጌ መስሎ ይናገራል። እርሷን በአበባ ሲመስልም ከአበባ ፍሬ እንዲገኝ ፍሬ ሕይወት ፍሬ መድኃኒት ክርስቶስ ከእርሷ እንደሚገኝ ለማመልከት ነው። (ኢሳ.፲፩፥፩)
 
ከማሕሌተ ጽጌ አንድ ማሳያ አቅርበን ክርስቶስ ለምን ተሰደደ የሚለውን እንመልከት፤ “በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፊ ዘዐፀዋ፣ እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኀዋ፣ ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ፣ ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ሔዋ፤በአዳምና በሔዋን በደል ሱራፊ የዘጋውን የገነትን በር ከጽጌ ልጅሽ በቀር ማን ከፈተው? አዳምን ከምርኮ የመለስሽው ድንግል! ደስ ይበልሽ  በተአምርሽ ወደ አበባይቱ ምድር ገብታለችና ሔዋን እንደ እንቦሳ ዘለለች።” ሊቁ በዚች ክፍል ብቻ ሐዲስን ከብሉይ እንዴት እንዳገናኘው ልብ ይሏል።
 
በሰውነቱ መሰደድ፣ መራብ፣ መጠማትን ገንዘብ ያደረገው ክርስቶስ እንደ አምላክነቱ ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ነቢዩ ዕንባቆም እንደተናገረው “እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ጸዳሉም እንደ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሯል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አወካት ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፤ የዘለዓለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘለዓለምም ኮረብቶች ቀለጡ፤ መንገዱ ከዘለዓለም ነው” (ዕን ፫፥፴፮)  በማለት የገለጸው አምላክ ለምን ተሰደደ ቢሉ፡-
 
ለካሣ፦ የመጀመርያውን ሰው አዳምን በበደሉ ምክንያት ከገነት አስወጥቶት ነበርና ካሣ ይሆነው ዘንድ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ተሰደደ። በገድለ አዳም ተመዝግቦ እንደምናገኘው አዳም ገነት ከወጣ በኋላ ተራበ ተጠማ ክርስቶስም በግብጽ ምድር ተራበ ተጠማ፣ አዳም ከገነት ሲወጣ ከሔዋን በቀር አብሮት ማንም አልነበረም፤ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ከዳግማዊት ሔዋን ከድንግል ማርያም በቀር ማንም አልነበረውም፤ “ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፣ ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዝኀ ሠናይታ፣ ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፣ ተአወዩ በኀጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ እናንተ ኀዘንተኞች የእመቤታችንን ስደቷን አስባችሁ አልቅሱ፣ እናንተ ደስተኞች የቸርነቷን  ብዛት አስባችሁ አልቅሱ። ድንግል ማርያም እንደ ወፍ በግብፅ ተራራዎች ብቻዋን ትዞራለች የአባቷ የኢያቄም ሀገር የምትሆን ኤፍራታን አጥታ ታለቅሳለችና እናተ ኀዘንተኞች አልቅሱ።” እንዲል (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ስደትን ለሰማዕታት ለመባረክ፦ ሰማዕትነት እሳት፣ ስለት ብቻ መቀበል አይደለም ሀገር ጥሎ መሰደድም ሰማዕትነት ነውና። በመዋዕለ ስብከቱ  “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” ብሎ የሚያመጣው ነውና። (ማቴ.፲፥፳፫) የስደተኞች ተስፋ ክርስቶስ ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ ስደትን ባረከው። “ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን፤ኢየሱስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ፣ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ሆነ” እንዳለ ሊቁ (ሰቆቃወ ድንግል) ለዚህም ነው ዛሬ ቅዱሳን ፍቅሩ አገብሮቸው ከዘመድ ባዳ ከሀገር ምድረ በዳ አሰኝቶ በዱር በጫካ ከአራዊትና ከእንስሳት ጋር እየታገሉ መኖርን የሚመርጡት።
 
ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደው ልጇ ጋር በስደት ሳለች ያጋጠማትን መከራዎች ከሰቆቃወ ድንግል አንዲትን ቃል አንሥተን እንመልከት። ገና የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና ሳለች ሕፃን ታቅፋ መሰደዷን ተመልክቶ “ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ ማርያም ብዙኀ በሐዚ ለሕፃን ደከምኪ ሶበኑ የሐውር  በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ” በማለት አንድ ጊዜ በጀርባዋ አንድ ጊዜ በጎኗ እያለች ልጅ አዝላ በግብጽ በርኃ ስትንከራተት የሚዘክራት ሰው አጥታ ይልቁንም የልጇን የወርቅ ጫማ ሲወስዱባት ምርር ብላ ስታለቅስ፣ ክርስቶስን ታቅፋ ይዛ ዓይኑን እየተመለከተች ስታልቅስ ልብ በሉ። ሊቁ ይህን ተመልክቶ እናንተ የገሊላ ሰዎች እንቦሳይቱ ማርያም ወዴት ሔደች በለቅሶ እከተላት ዘንድ  መንገዷን ነገሩኝ በማለት ይማጸናል። (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ዛሬም ሊቃውንቱ ስደቷን እያሰቡ ሌሊቱን በማሕሌት ወደ ግብጽ እየወረዱ ያድራሉ። የቤተ ክርስቲያን ልጆች አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! በእውኑ ዛሬስ ድንግል ማርያም ከስደት ተመልሳለችን? በልባችን ላይ ያነገስነው ሄሮድስን ወይስ ክርስቶስን? የቤተ ክርስቲያን ልጆች ዛሬም ድንግል ማርያም ተመልሳ የምታርፍበት የንጹሕ ልቡና ሀገር ያስፈልጋልና ማረፊያ ለመሆን እንዘጋጀ፡፡ ቅድስት ድንግል ወደ ሀገሯ ስትመለስ ከናዝሬት መልካም ሰው ይወጣልን የተባለላት ናዝሬት የተወደደ የተመሰገነ ክርስቶስን አስገኘች። ይህን ሳስብ ዛሬ የእኛ ሀገርም ድንግል ከስደት ከመመለሷ በፊት ያለችዋ ናዝሬት ትመስለኛለች፤ መልካም ሰው ደግ ሰው የለባትምና። "አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር ወውኅደ ሃይማኖት እም እጓለ መሕያው፤ አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና አድነኝ ከሰው ልጆችም መተማመን ጠፍቶአልና” እንዳለ ነቢዩ ዳዊት (መዝ.፲፩፥፩)
 
በመጨረሻም በየቀኑ የምትሰደደውን ድንግል ዓመት ጠብቀን ስደቷን ከምናስብ አሳዳጁን ሄሮድስን አስወግደን ዘወትር ሕፃኑንና እናቱን በልባችን ጽላት አንግሠን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን።የልባችን ንጉሥ ክርስቶስ ሲሰደድ አብራ ትሰደዳለችና። ድንግል ሆይ "እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ በምድረ ነኪር ሀገረኪ ገሊላ እትዊ፤ እስከመቼ ድረስ በባዕድ ሀገር ትኖሪአለሽ? ወደ ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ።” የሰላም መገኛ ሰላማዊት ርግብ ሱላማጢስ ሆይ፥ ሰላምን ትሰጭን ዘንድ ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ገሊላ ኢትዮጵያ ተመለሽ።
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
 
 
 
👍43👎2
በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ በፍራንክፈርት እየተካሄደ ይገኛል።
*

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፳፮ - ፳፯ ቀን  ፳፻፲፭ ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ጠቅላላ ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላትና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ ዛሬ ጠዋት መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም (October 7, 2023) በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል።

ምንጭ: የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ
👍39
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት ሁሉ አቀፍ ትሥሥርን በሚመለከት ምክክር አደረገ።

በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት ሁሉ አቀፍ ትሥሥርን በሚመለከት ከሊቃውንት ፣ ከባለሙያዎች፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ምክክር ተካሂዷል።

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ምክትል ሰብሳቢ ዲያቆን ስንታየሁ ምስጋና ሥርዓተ ትምህቱን በሚመለከት ገለጻ ካደረጉ በኋላ ሥርዓተ ትምህርቱ ከሁሉም የቤተ ክርስቲያን የትምህርት ተቋማት ጋር የሚኖረውን መስተጋብር መነሻ ፤ ከመደበኛ የአስኳላ ትምህርት አንጻር ሥርዓተ ትምህርቱ ሊያያቸው የሚገባውን ሐሳቦች ጥሩ እድሎችና ተግዳሮቶች ተነስተዋል።

በ2016 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ የሚጀምረው የቅድመ መደበኛ (ዕድሜያቸው ከአራት እስከ ስድስት) ላሉ ሕፃናት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ገለጻ ተደርጎ በቀረቡት መነሻ መሠረት በማድረግም ተሳታፊዎች ያላቸውን ሃሳብንና ልምዶች በሰፊው አጋርተዋል።

በመጨረሻም ተተኪውን ትውልድ ለማፍራት ዘመኑን የዋጀ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የተሟላ ሁሉ አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሥርዓተ ትምህርት ለቅድመ መደበኛ ሕፃናት ራሱን የቻለ ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት ፣ ዝግጅት ላይ ያለውን ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርት ማጠናቀቅ እና ከ12ኛ ክፍል በኋላ ወደ ቀጣይ ተቋማት የትምህርትና የአገልግሎት ስምሪት አጠቃላይ ማኅቀፍ ላይ ከሊቃውንት፣ ባለሙያዎች ና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክርና በየዘርፉ ጥናት እየተጠና በተደራጀ መልኩ ዝግጅትና ትግበራው ላይ በስፋት እንደሚሳተፉ በመግለጽ ቀጣይ መርሐ ግብሮች ተይዘው ምክክሩ ተፈጽሟል።
👍19
በምክክሩ ላይም የሰንበት ትምህር ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አባላት ፣ የማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ ፣ የሊቃውንት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለ ፣ ከአንጋፋ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ መምህራን መካከል መልአከ ሰላም መምህር ታዬ አብርሃም ፣ መምህር ያረጋል አበጋዝን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው መምህራንና የሥርዓተ ትምህርት ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

© የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
👍5
‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፤፩)

ክፍል አንድ

ይህ ቃል የሚተረጎመው ለእመቤታችን ነው፡፡ ይኸውም በብሥራተ መልአክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችውን አንድያ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት በፈለገው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዷን የሚያመለክተውን ስደቷን ከስደት እንድትመለስ ጠቢቡ በትንቢት ቀድሞ የተናገረው ይህን ቃል ነው፡፡ ወቅቱ አብዝተን ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች የምንማርበት፣ የምንጸልይበት፣ የምናስተምርበትና የምንዘምርበት ወቅት በመሆኑ በዚህ ርእስ ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፤ እንድትከታተሉን እናሳስባችኋለን፤ ምልጃዋ አይለየን!!!
ቤተ ክርስቲያናችን መቼም ይህ ቀረሽ የማትባል ስንዱ እመቤት መሆኗን ሁሉን በዓይነቱና በፈርጁ ያዘጋጀች ለሁሉ የሚሆን፣ ከሁሉ የሆነ ነገር ያላት እመቤት ናት፡፡ ትምህርቷን በወቅትና በሁኔታ ከፋፍላ እንደሚመች እንደሚመች፣ ለመብላት፣ ለመጠጣትና ለማጣጣም እንዲመች አድርጋ እንደምታቀርብ ወርኃ ክረምት ላይ አንድ ጽሑፍ አጋርተናችሁ ነበር፡፡ ስለ እመቤታችን ስደትና መከራ ስለተነሣንበት እርስ ከማብራራታችን በፊት ስለወቅቱ ትንሽ ማለት የግድ ነውና ስለ ወርኃ ጽጌ/ዘመነ ጽጌ/ የተወሰነ እንላለን፡፡

ጽጌ የሚለው ቃል በቁሙ ሲፈታም አበባ የሚል የአማርኛ ትርጉም አለው፡፡ ወርኃ ጽጌ የክረምቱን ማለፍ፣ የውኃውን መጉደል፣ የነገድጓዱን፣ የጎርፉን፣ የጨለማውን፣ የመከራ ምልክት የሆነውን የክረምቱን ማለፍ፣ የምድሩን መርጋት፣ የውኆችን መጥራት፣ የጨለማውን መገፈፍ፣ የብርሃንን መውጣት፣ የአበቦችን መፍካት፣ የምድርን ውበት የሚያመለክት፣ አዕዋፍ በዝማሬ የሚደሰቱበት ወቅት ነው፡፡
👍26
የጽጌ ወር ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፡፡ ጽጌ፣ ምድር በአበባ፣ ማኅሌቱ በያሬዳዊ ዜማ የሚፈካበት ልዩ ወቅት፣ ምድር የምትዋብበትና የምትቆነጅበት፣ ተራሮች የሚንቆጠቆጡበት የጌጥ፥ የውበት ወቅት እንደሆነ ጠቢቡ ሲገልጽ “እነሆ ክረምቱ አለፈ፤ ዝናቡም አልፎ ሄደ፤ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ” ይላል፡፡ (መሓ. ፪፥፲፩) “አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም፤ አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳን በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም” እንዲል፤ (ሉቃ.፲፪፥፳፯) ተራሮችና ኮረብቶች በሰው እጅ ያልተጌጠውን  ውብ የሆነ ልብሳቸውን ተጎናጽፈው የሚመለከታቸውን ሁሉ ትኩረት የሚስቡበት፣ ለአፍንጫ ተስማሚ የሆነውን ጥዑም መዓዛቸውንም እንካችሁ ብለው ያለስስት የሚቸሩበት፣ አዕዋፍ ዝማሬያቸውን ከወትሮው በላቀ ሁኔቴ  የሚያንቆረቁሩበት፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየባረሩ ጣፋጭ ማርን የሚያዘጋጁበት፣ ሁሉ አምሮ፣ ሁሉ ደምቆ፣ አዲስ ሆኖ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ ይህ ጊዜ ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ በመባል ይታወቃል፡፡

ቤተ ክርስቲያንም ዝማሬዋን፣ ትምህርቷን፣ ዜማዋን፣ ንባቧን፣ ለወቅቱ እንዲስማማ እያደረገች በምሳሌና በኅብር፣ በሰምና ወርቅ እያዋዛች ለጀሮ እንዲስማማ፣ ለልብ እንዲያረካ፣ ለሥጋ ስክነትን ለነፍስ ዕረፍትን እንዲሰጥ አድርጋ ታቀርብበታለች፡፡ በሰማዩ ፍካት፣ በውኃው ጥራት፣ በኮከቦች መውጣት፣ በአበቦች ውበት፣ በተዘሩት አዝርዕት፣ በጸደቁት አትክልት፣ በዛፎቹ ልምላሜ፣ በአዝርዕቶቹ ፍሬ ሁሉ ቃሉን እየመሰለች ታስተምራለች፤ ትዘምራለች፤ ትቀድሳለች፤ በጥበብ ረቅቃ ታራቅቃለች ተቀኝታ ታስቀኛለች፡፡

ቤተ ክርስቲያን በምልዓትና በሙላት ያለች ናት፡፡ ይህን ዘመነ ጽጌንም እንደ ሌሎች ወቅቶች/ወንጌልን ለማስተማር፣ የራቀውን አቅርባ የረቀቀውን አጉልታ፣ የጎደለውን ሞልታ፣ የጠመመውን አቅንታ ለማስተማር በብዙ መልኩ ትጠቀምበታለች፡፡ በልዩ ሁኔታ ነገረ ማርያምም ነገረ ክርስቶስም በስፋት የሚሰበክበት ወቅት በመሆኑ ዘመነ ጽጌ እጅግ ተወዳጅ ወቅት ነው፡፡

ወርኃ ጽጌን ልዩ የሚያደርገው አንዱና ዋናው የእመቤታችን እና የተወዳጅ ልጇ ስደት የሚታሰብበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡

ውድ የዚህ ጽሑፍ ተከታታዮች ‹‹ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ተመለሺ›› በሚል ርእስ ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች በቀጣይ ክፍል ሰፋ አድርገን እናቀርብላችኋለን፡፡
እስከዚያው ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን!
👍54
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

ከነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።

የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን

ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
👍121
#አደራ_አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 1ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

ቀን፡ ኅዳር 2/2016 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ

ጉባኤው በሁሉም ማእከላት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከናወናል።

ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
👍47
2025/07/14 13:51:32
Back to Top
HTML Embed Code: