የብፁእ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል።
👍41
ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ የሊባኖስ፣የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስዕ በስኮላርሺፕ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዩኒቨርስቲ ለተጓዙ ተማሪዎች አቀባበል አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ በስኮላርሺፕ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዩኒቨርስቲ ለተጓዙ ተማሪዎች አቀባበል አድርገው ሕጻናቱን ጎብኝተዋል።
እንዲሁም ብፁዕነታቸው በስኮላርሺፕ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ራስ አልኬማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ተማሪዎች አቀባበል ያደረጉ ሲሆን አድባራት ከየግዛቱ የመጡትን ተማሪዎችን እንዲያስተምሩና እንዲንከባከቡ መመሪያ ሰጥተዋል።
ዘገባው የማዕዶት ሚዲያ ነው።

👍68
ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም!
በሚሊኒየም አዳራሽ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ!
የቻለ ሁሉ የማይቀርበት ልዩ ጉባኤ!
ኑ! አንድ ሁነን ቅዱስ ያሬድን ዘክረን ከበረከቱ እንካፈል!
በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ መምህራነ ወንጌል፣መዘምራንና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ።
መግቢያ ዋጋ 100 ብር!
ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000560510091
አቢሲኒያ ባንክ
145735858
አባይ ባንክ
146-101-9959527-013(9959527)

👍49
ማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማኅሌት አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የማኅሌተ ጽጌ መጽሐፍ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ።
ይህንን የአባ ጽጌ ድንግል ድርሰት የሆነው መጽሐፍ የተረጎሙት የፊንላንድ ሀገር ዜጋ የሆኑት እና ከሃምሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቆይታ ያደረጉት አቶ ኒሎ ሆንካነን ናቸው።
ተርጓሚው መጽሐፉ ወደ ፊንላንድኛ ለመተርጎም ከ10 ዓመት በላይ ሲያጠኑ እንደቆዩና ዋና ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት በ1919 ዓ.ም በዶ/ር አዶልፍ ግሮህማን የተተረጎመውን የጀርመንኛ ቅጅ እንደሆነ ነው የገለጹት።
አቶ ኒሎ ማኅሌተ ጽጌን ለምን ለመተርጎም እንዳነሳሳቸው ሲጠየቁ "ማኅሌተ ጽጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካሏት የመዝሙር መጻሕፍት ውስጥ በትንሽ ጥራዝ መጽሐፍ ሆኖ መታተም የሚችል እና መንፈስን የሚያረካ ይዘት ያለው ስለሆነ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
መጽሐፉ በያዝነው መስከረም ወር ውስጥ በፊንላንድ ርዕሰ ከተማ ሄልሲንኪ ከተማ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ፣ የደብሩ ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ እና የተርጓሚው ቤተሰቦችና ወዳጆች በተገኙበት ተመርቋል
ምንጭ: የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

👍70
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
(ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት)
በኤልሳቤጥ ቤተ
+++++++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በጥይት መገደላቸው ተገለጸ፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን ከተገደሉት አንድ ካህን እና ዲያቆን በተጨማሪ ሁለት ካህናትና አንድ ምእመን በታጣቂ ኃይሎቹ መታገታቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
የታገቱት ካህናትና ምእመኑ ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ያሉበት አልታወቀም፡፡
ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልጠቀሱት መረጃ ሰጭያችን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ ጊዜ ካህናትና ምእመናን ላይ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ገልፀዋል ።
በዚህም ምክንያት በርካታ ምእመናን አካባበቢውን እየለቀቁ መሰደዳቸውንም ነግረውናል፡፡
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 የተፈጠረውን ግድያና አፈና በተመለከተ የሚመለከተው የጸጥታ አካላት የወሰደው እርምጃ አለ ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄም የጸጥታ አካሉ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በአዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚፈጠረውን የንጹሃን ግድያ ማስቆም የመንግስት ዋና ሥራ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል፡፡

👍33👎3
የሰማዕታቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል።
በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በአርቱ መካነ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፡፡
---------------------------------------------
መስከረም 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቁ የጸሎት አባት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን መሪጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮችን ታፍነው ባልታወቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን የሀገረስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።
በአዳማ ወረዳ ዙሪያ በቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በታላቋ የጸበል ቦታ በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ የተፈጸመው ይኼ አሰቃቂ ድርጊት ነውርና ግፍ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃት ስለሆነ አሁንም መሰል ጥቃት እንዳይስተናገድ የሚመለከተው አካል በርካታ ጸበልተኛ በቦታው ስለሚገኝ አስፈላጊ ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።
በተፈጸመው ግፍና በደል የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ማዘኑን የገለጸ ሲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ዙሪያና ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት ዙሪያ እየተነጋገረ መሆኑን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ገልጿል::

👍43