Telegram Web Link
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።
*****
**

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ከድርገውላቸዋል።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምም ለቤተ ክርስቲያንና ለቅዱስነታቸው ክብር የሚመጥን የእንኳን ደህና መጡ መርሐ ግብር ከሰዓታት በኋላ የሚከናወን ይሆናል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አሜሪካ ያቀኑት ከአንድ ዓመት በፊት ተይዞላቸው በነበረ የሕክምና ቀጠሮ ምክንያት ነው።
አንዳንድ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ከቅዱስነታቸው ጉዞ ጋር በተያያዘ ቅዱስነታቸው ተመርዘው ወደ አሜሪካን ለሕክምና እንደ ተጓዙ አስመስለው መሠረተ ቢስና ከእውነት የራቀ መረጃዎችን በማስተላለፍ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሲያደናግሩ መክረማቸውም ይታወሳል።

ምንጭ: የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👍66👎1
ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም
በሚሊኒየም አዳራሽ

የቻለ ሁሉ የማይቀርበት ልዩ ጉባኤ
ኑ! አንድ ሁነን ቅዱስ ያሬድን ዘክረን ከበረከቱ እንካፈል

በዕለቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ መምህራነ ወንጌል፣መዘምራን እና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ

መግቢያ ዋጋ 100 ብር

ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም አካውንት ንግድ 1000560510091 አቢሲኒያ 145735858 ዓባይ 1461019959527013 አሐዱ 0003488720301
አዋሽ 013040800017700 ዳሽን 0088872166011
አሐዱ 0003488720301

ወገን ፈንድ
https://www.wegenfund.com/causes/semeka-hheyaawe/
👍39👎1
https://youtu.be/eku36lz5-lg?si=mQIf5jPITODv4MYD

የስደት ዘመንሽ

መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ

በጠላት ፈተና ከሀገር ተሰደሽ
 ስትንከራተቺ አምላክን ታቅፈሽ
 ከገሊላ አንስቶ እስከ ግብፅ በረሃ
የሚያዝንልሽ አጣሽ የሚሰጥሽ ዉኃ
   አዝ
ሰሎሜ ትመስክር ያየሽውን ጭንቀት
 ዮሴፍም ይናገር የሀዘንሽን ብዛት
 እመቤቴ ማርያም ከአንድ ልጅሽ ጋራ
 በግብፅ በረሃ ያየሽዉ መከራ
    አዝ
  ውርጭና ፀሓዩ ሲፈራረቅብሽ
  ረሀብና ጥሙ እንዲያ ሲያንገላታሽ     
  በለጋነት ዕድሜ በሄሮድስ ቅናት
  ከልጅሽ ጋር አየሽ መከራ ስደት
         አዝ
   ልጅሽ አንዲምረን ስለእኛ እንዲራራ         
   ለበረከት ሆነ ያየሽው መከራ    
   መልካም ፍሬ አፈራ ያነባሽው ዕንባ
   ምክንያት ለኛ ሆነ ገነት እንድንገባ
       አዝ
👍24
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
👍68
የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6ና በ10ኛ ክፍል ያስተማራቸውን ከ4500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ


የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6 እና በ10ኛ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል አስመርቋል። በመርሐ ግብሩ ላይም ብፁእ አቡነ አብርሃም የባህርዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁእ አቡነ ጴጥሮስ የሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁእ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት  የየክፍሉ ኃላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመራሮች ተመራቂ ተማሪዎችና  ወላጆቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ "ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም" በሚል መሪ ቃል መከበሩን አንድነቱ አሳውቋል። በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ  በአዲስ አበባ ከሚገኙ 250 አድባራት 157 የሚሆኑት በ2015 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርቱን መተግበራቸውንና በዛሬው ዕለት ግን 77 የሚሆኑ አድባራት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ እርከኖች ተማሪዎቻቸውን ማስመዘናቸውን ገልጸዋል።
👍18
2025/07/14 17:46:23
Back to Top
HTML Embed Code: