Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን የደም ልገሳ መርሐ ግብር በነገው ዕለት ሊያከናውን መሆኑ ተገለጸ

ግንቦት ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ከሚያከናውናቸው መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ በማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ተሳትፎ ያደርጋል።

ከእነዚህ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የሆነው እና በየዓመቱ የሚከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ዘንድሮም በማኅበሩ ሁሉም መዋቅሮች ላይ ተግባራዊ አንደሚሆን ተገልጿል።

የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት በሚያስተባብረው በዚህ መርሐ ግብር ላይ የማኅበሩ አባላት በየማእከላቶቻቸው በተዘጋጁ የደም መለገሻ ቦታዎች በመገኘት ደም እንደሚለግሱ ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ምእመናን እና የማኅበሩ አባላትም 5ኪሎ በሚገኘው በዋናው ማእከል ሕንጻ በመገኘት ደም እንዲለግሱ ጥሪ የቀረበ ሲሆን
ማኅበረ ቅዱሳን ከብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ መርሐ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ በነገው ዕለት በሁሉም የማኅበሩ ማእከላት አማካኝነት ይከናወናል።
18👍3
በደብረ ብርሃን ማእከል የደም ልገሳው መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።
11
ማኅበረ ቅዱሳን ጭሮ ማእከል የደም ልገሳ መርሐ ግብር እያከናወነ ነው።
1
የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል ደም በመለገስ ላይ ይገኛሉ
3
2025/07/08 15:28:06
Back to Top
HTML Embed Code: