Telegram Web Link
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአሜሪካ ማእከል በዴንቨር የሚገኙ አባላት በድምቀት አክብረዋል።
13👍1
#✍️ሐመር መጽሔት በግንቦት ወር እትሟ !

✍️" ክርስቶስን መምሰል ማለትም ሌሎችን ዝቅ ብሎ ማገልገልን እንጂ ሄሮድሳዊ ዙፋን መሻት አይደሉም " #ሐመር #መጽሔት ግንቦት ፳፻፲፯ ዓ.ም ✍️
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ግንቦት ፳፻፲፯ ዓ.ም

#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር

•ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

•ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት ቁጥር ፭ # የግንቦት ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#ሥልጣን #ለአገልግሎት እንጂ #ለግል ጥቅም አይሁን ›› በሚል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀደሰ ሕይወት ውስጥ አባቶች የሚያደርጉት የአክሊለ ሦክ ምሳሌ የሆነውን አስኬማ እንጂ የዓለማውያን ገዢዎችን ዘውድ እንዳልሆነ ትጥቁማለች።
በአሁኑ ሰዓት ግን ከፍተኛውን የአገልግሎት መዋቅር ለመያዝ ከፍተኛ እሽቅድምድም እንዳለ ሁሉ በየአንዳንዱ አጥቢያም ከቤተ መቅደሱ አገልግሎት እየወጡ ወደ አስተዳደር ቦታ ለመግባት ከፍተኛ ሽሚያ እየታየ ይገኛል በማለት ሐመር በመልእክት ዐምድ ያስነብበናል ።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” #ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገስጿቸው ” በሚል ርእስ በስፋት ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ክፍል _፩" በሚል ዐቢይ ርእስ ትምህርት ይሰጣል ።
👍41
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# ለማገልገል እንጂ ለመገልገል አንቅደም " በሚል ርእስ ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያስነብባል።

#ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ኦርቶዶክሳውያን በማኅበረሰብ ውስጥ ቦታችን የት ነው _ክፍል _፩" በሚል ርእስ ዐቢይ ርእስ ሰፊት ትምህርት ታሰተምራለች።

#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ብርሃን ደብረ ገነት ቅዱስ ዑራኤልና አኔቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን _ክፍል ፩" በሚል ርእስ ስለ አመሠራረት ፣ስለ ስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴው ፣ስለ ልማት አገልግሎት፣ ስለ ጉባኤ ቤት : በስፋት ታስቃኛለች ።

#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ህልውና #ምንጩን ማጥራትና መጠበቅ " የመንጋው እረኞች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ ለዓለም ሁሉ ሰላምን የሚለምኑ ትጉሃን ባሕታውያን የሚፈልቁባቸው ጉባኤ ቤቶች ከሚደርስባቸው ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ተኵላ ዛሬውኑ ካልተጠበቁ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ማሰብ የሕልም እንጀራ እንደ መብላት ይሆናል በማለት በስፋት ይዛለች ።

#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ድምፀ ቤተ ክርስቲያን "በሚል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድም በሌላም መንገድ የራቁትን ልጆቿን ስትጠራ ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ቤዛና ቤዛነትን” በተመለከተ ክፍል _፩ /ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የሆኑትን #መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ ቀሲስ #መንግሥቱ አማረ ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች። መሠረታዊ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ ተሰጥቷል።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፭ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
👍7
ለዕጣ እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ።

በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የተዘጋጀው የበረከት ዕጣ ዕድለኞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

ዕድለኞች የወጣላቸውን ዕጣ ትኬት በመያዝ ከማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ማእከሉ ጽሕፈት ቤት 4ኛ ፎቅ በመቅረብ ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ :-ከተጠቀሰው ቀን ዉጪ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረዉም::
👍8
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአሜሪካ ማእከል በሎስአንጀለስ የሚገኙ  አባላት በድምቀት አክብረዋል።
1
2025/07/13 19:20:39
Back to Top
HTML Embed Code: