Telegram Web Link
የማኅበረ ቅዱሳን 33ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ሥር የሚገኝ አገልግሎት ማኅበር ነው።
ማኅበሩ እግዚአብሔር ያከበራቸው የሐዋርያት የነቢያት የጻድቃን የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ይህን ስያሜውን አግኝቷል።
የ33ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉ በማኅበሩ ዋና ማእከል 3ኛ ወለል ላይ በመከበር ላ የሚገኝ ሲሆን መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማንአየ "አሸናፊ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶምና ገሞራ በሆንን ነበር!" በሚል ኃይለ ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ማርያምን ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪምየማኅበሩ መዘመራን ወረብ እና የበገና ዝማሬ አቅርበዋል፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የማኅበሩ መሥራች፣የአሁን እና የቀድሞ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
19👍4🕊1
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአሜሪካ ማእከል የፖርትላድ ግንኙነት  ጣቢያ አባላት በድምቀት አክብረዋል።
  
9🕊3
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 33 ዓመታት ሀገር እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅሙ ሥራዎችን መሥራቱ ተገለጸ።

ግንቦት ፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበሩን 33ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ አመራሮቹ ከማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

መምህር ዋሲሁን በላይ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በ33 ዓመታት ውስጥ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ገዳማትንና አድባራትን በማጠናከር፣በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች በሚማሩ ተማሪዎች፣ቤተ ክርስቲያን በሚገጥሟት ውስጣዊ፣ውጫዊ ፈተናዎች እና በሌሎችም ዙሪያ ባለን ሙያዊ አገልግሎት አገልግለናል ብለዋል፡፡

የማኅበሩ ሰብሳቢ  አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም በበኩላቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች  ትምህረተ ወንጌል እንድትሰጥ ማኅበረ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመተርጎም ፈር ቀዳጅ ነው ያሉ ሲሆን በሚዲያውም ዘርፍ መረጃዎችን ለምእመናን እያሰራጨ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 33 ዓመታት ውስጥ ሃይማኖታቸውን እና ሀገራቸውን ያስቀደሙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዓለም ዙሪያ መብዛት የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ትልቁ ውጤት እንደሆነም በነበራቸው ቆይታ ላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አንሥተዋል፡፡

አቶ ካሳሁን አክለውም ገዳማት በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ፣ከምእመናን ጋር ያላቸው ግንኙት እንዲጠናከር በርካታ ተግባራትን አከናውነናል አሁንም እያከናወንን እንገኛል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት፣አስተምህሮ፣ዶግማ እና ቀኖና ለመጣስ በሚጥሩ አካላት ላይ መረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ለቅዱስ ሲኖዶስ እና ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ ያሉባትን ጫናዎችን በመቀነስ ረገድ  ምእመናንን ለመጠበቅ ማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ሥራዎችን ሠርቷል ሲሉ መምህር ዋሲሁን ገልጸዋል፡፡
12👍8🙏1🕊1
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት 33ተኛ ዓመቱ ድረስ ሀገርን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅሙ ብሎም ተጨባች ወጤት ያስመዘገቡ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
16🕊2👍1
2025/07/13 12:17:30
Back to Top
HTML Embed Code: