Telegram Web Link
ከሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ደቀ መዛሙርት ተመረቁ

ማኅበረ ቅዱሳን ከደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ገብረ ክርስቶስ ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት እና ከደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ደቀ መዛሙርትን አሠልጥኖ አስመርቋል።

ለአንድ ወር በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ዙሪያ ሥልጠና ሲወስዱ ለቆዩት ሠልጣኞች በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የምርቃት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የደብሩ ሰ/ት/ቤት የሠልጣኞችን የትራንስፖርት እና የምግብ ወጪ ከመሸፈን ጀምሮ የመኝታ እና የሕክምና አገልግሎቶች በሙሉ በማሟላት ሥልጠናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ተገልጿል።

የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ሥልጠናው እንዲከናወን ፈቃድ ከመሥጠት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱም በመርሐ ግብሩ ላይ ተነግሯል።

የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶ/ር ሄኖክ ፍቅሬ እንደተናገሩት ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎቶች የምታከናውነውን አገልግሎት ለማጠናከር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ያሉ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ሰ/ት/ቤቶች በዚህ አገልግሎት ላይ ከማኅበሩ ጋር በመተባበር እየሠሩ በመሆናቸው ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል።
👍61
ምክትል ሰብሳቢው ጨምረው እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ሠልጣኞቹን ከመመልመል ጀምሮ  መምህራን በመመደብ ተሳትፎ እንዳደረገ አንስተው  የደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት እና የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት ሥልጠናው በታቀደለት መልኩ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለሠልጣኞቹ አባታዊ የአገልግሎት መመሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ  በጠረፋማ አካባቢ ያለውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መደገፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም አካላት ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባው ገልጸው የደብሩ አስተዳደር እና ሰ/ት/ቤት ያከናወኑት ተግባር ሊበረታታ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሥልጠናውን ለተከታተሉ ተተኪ መምህራን የመጽሐፍ ቅዱስ እና የምስክር ወረቀት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
👍10🙏2
“የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መካሄዱ ተገለጸ

“የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ለገዳማትና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያና ማስፋፊያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በዮድ አብሲኒያ የባህል አዳራሽ ተካሄዷል።

በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ ና የማኅበረ ቅዱሳን ስራ አመራር አባል ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም (ዶ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ምእመናን ተገኝተዋል።

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ የሩቅ ምስራቅ ሰዎች የእጅ መንሻ፣ እንሰሳት እስትንፋሳቸውን እንደሰጡ እኛም የእርሱን አስተምህሮ ላስቀጠሉልን ለገዳማትና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ካለን ላይ ማካፈል ይጠበቅብናል” በማለት ገልጸዋል።

ህዳር 15 የተጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን ምእመናን የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለገዳማትና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ስጦታቸውን መለገስ እንደሚችሉ ተጠቁማል።
👍10
በማኅበረ ቅዱሳን የደሴ ወረዳ ማእከል “ወደ ቀደመው አገልግሎታችን እንመለስ!!” በሚል መሪ ቃል የአባላት የማነቀቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

በማኅበረ ቅዱሳን የደሴ ወረዳ ማእከል በትላንትናው ዕለት ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት አዳራሽ “ወደ ቀደመው አገልግሎታችን እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የማነቀቂያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም ከማኅበረ ቅዱሳን መሥራች ከነበሩት አባላት አንዱ መ/ታ ዶ/ር ይቻለዋል ጎሽሜ ስለ ማኅበረ ቅዱሳንና አገልግሎቱን አስመልክቶ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በፈቃደኝነት፣በቂ ጊዜ በመስጠት፣በዓላማ ጽናት፣በመንፈሳዊ ሕይወት በመጠንከር፣ አርዓያ በመሆን፣የሚከሰቱ ፈተናዎችን ለመቋቋም ዝግጁ በመሆንና በአገልግሎት የሚገኝ ዋጋን ተስፋ በማድረግ መንፈሳዊ ስራዎችን በመሥራት ማገልገል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የደሴ ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያቆን ሞላ ንጉሥ በበኩላቸው አጠቃላይ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት፣ ተቋማዊ እሴት የገለጹ ሲሆን አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማኅበሩን እና ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በመርሐ ግብሩ ላይ የደሴ ማእከል እያከናወናቸው ስለሚገኙት ተግባራት፣ስላጋጠሙ ችግሮች፣ማኅበረ ቅዱሳን ስላደረገው ተቋማዊ ለውጥ እና በአባላት የአገልግሎት ተሳትፎ ዙሪያ ሐሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
👍162
2025/07/14 06:48:48
Back to Top
HTML Embed Code: