በጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል እና የአብነት ትምህርት አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር ተከናወነ።
በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ የተመራ ልዑክ ከጌዲኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና ከሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደርጓል።
በዲላ ከተማ በተደረገው ውይይት ማኅበረ ቅዱሳን በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ብፁዕነታችው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉ እጅግ እንዳስደሰታቸው የተናገሩ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ በተጠናከረ ሁኔታ ለቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመናን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም የአቅም ውስንነት አለበት ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ጨምረው እንደተናገሩት ማኅበሩ አሁን በሀገረ ስብከቱ ሊያከናውናቸው ያሰባቸው ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
በዕለቱ ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ የተከናወኑ ተግባራትን ለልዑካኑ ያስጎበኙ ሲሆን ማኅበሩ በሀገረ ስብከቱ የመጀመርያ የሆነና በ2018 ዓ.ም ለሚያስገነባው የአብነት ትምህርት ቤት የሚሆን 450 ካሬ ሜትር ቦታ መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የደቡብ ማእከላት ማስተባበርያ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ቀሲስ አሰፋ በበኩላቸው ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው በተለይም በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉ ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት እየዞሩ በመመልከት የተዘጉት እንዲከፈቱ አድርገዋል ብለዋል።

👍26
“የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያና የስጦታ ዘመቻ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ተገለጸ::
የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ወልደ እግዚአብሔር ፍጹም ሰው ሆኖ ዓለሙን ለማዳን መምጣቱን አሕዛብ ዓይተው ያመኑበት ዕለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሰብአሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እጅ መንሻ ያቀረቡት በዚህ ታላቅ ዕለት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ምእመናን በጾመ ነቢያት “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን ይደግፉ ዘንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተሰናድቷል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማት እና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የሚያከናውናቸውን ፕሮጀክቶች ለማጠናከር “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መርሐ ግብር እያካሄደ እንደሆነ ማስተባበሪያው ቀደም ሲል ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
የስጦታ መርሐ ግብሩም ከ፳፻፲፬ ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን የ፳፻፲፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል “ስጦታዬን ለእራሴ” ሳይሉ ሁለ ነገራቸውን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰጥተው ለሚያገለግሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ገዳማውያን እንድናበርክት ማስተባበሪያው ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
ማኅበሩ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚኖሩ ምእመናንን በማስተባበር በገዳማትና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ከመቶ ስልሳ አምስት በላይ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንደቻለና በዚህም በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ማፍራት እንዲሁም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ ማድረጉ ይታወቃል።

👍50❤16🕊4
የደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የመጡ ደቀ መዛሙርትን እያስተማረ እንደሆነ ተገለጸ።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከደቡብ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት የመጡ ሠላሳ አራት ደቀ መዛሙርትን ከኅዳር ሃያ ሰባት ቀን ጀምሮ እያስተማረ መሆኑን በአዲሰ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ አርያም መንግሥቱ ዘለዓለም ገልጸዋል።
የደብሩ አስተዳዳሪ አክለውም በ፳፻፲፮ ዓ.ም ከጠረፋማ አከባቢ የመጡ ሃያ አምስት ደቀ መዛሙርትን ተቀብለው ማስተማራቸውን በመግለጽ በ ፳፻፲፯ ሰባ ሁለት ተማሪዎች ለመቀበል በዕቅድ ከተያዘው ውስጥ ጥሪ ከተደረገላቸው ሠላሳ ስድስት ተማሪዎች መካከል ሠላሳ አራቱን ተቀብለው እያሠለጠኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት የፕሮጀክቱ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋይ የሆኑት ተመስገን ቶማስ በበኩላቸው “ማኅበረ ቅዱሳን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ጠረፋማ አከባቢዎች የሚገኙ ተተኪ መምህራንን በማፍራት በርካታ ሥራዎችን መሥራቱን በመግለጽ የዚህን ዓመት ሥልጠና ልዩ የሚያደርገው ሠልጣኞች በቋንቋቸው ጭምር እየተማሩ መሆኑ ነው” ብለዋል።
ሥልጠናው ለ ሁለት ሳምንት እንደሚቀጥል የገለጹት አስተባባሪው ታኅሣሥ ፳/፳፻፲፯ ዓ.ም ሠልጣኞቹ በደብሩ ዐውደ ምሕረት ላይ በልዩ ድምቀት እንደሚመረቁ አሳውቀዋል።

👍5
የሥልጠና ኮሚቴው ጸሐፊ እና የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት አባል የሆኑት አቶ ማስተዋል አንዱዓለም በበኩላቸው ሰ/ት/ቤቶች በመሰል አገልግሎቶች ላይ ቢሳተፉ ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚቻል ገልጸው በደብሩ ባለፈው ዓመት ሥልጠናውን የወሰዱ ደቀ መዛሙርት በተሠማሩባቸው አከባቢዎች ስምንት መቶ ሃምሳ ኢ-አማንያን ማስጠመቅ በመቻላቸው ሥልጠናው አመርቂ ውጤት ማምጣቱን ያሳያል ብለዋል።
❤6
ማኅበረ ቅዱሳን በሐድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ስልጤ ወረዳ ቤተ ክህነት ለቅበት አገልጋዮች ማቋቋሚያ ድጋፍ አደረገ፡፡
+++
በነሐሴ 2015 ዓ.ም በቅበት ከተማ በተከሰተ ጥቃት ከ1500 በላይ ምእመናን ከአካባቢው ተፈናቅለው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ተጠልለው ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በወቅቱም ማኅበረ ቅዱሳን ለእነዚህ ምእመናን በተጠለሉበት ቦታጅራ ከተማ በመገኘት ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጪ የሆነበት የምግብ ግብዓትና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ከወራት በኃላም በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም ወደ ቀያቸው ተመልሰው ኑሯቸውን የጀመሩ ቢሆንም የቅበት ደብረ ስብሐት ቅድስት ማርያም፣ ደብረ ሰላም ቅድስት አርሴማና የቆቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮች በገጠማቸው የገቢ እጥረት በቦታው ጸንተው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረው ቆይተዋል፡፡ ለዚህም ለአገልጋይ ካህናት ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲሆንና ለሌሎችም የገቢ ማስገኛ የልማት ለተግባራት መነሻ እንዲሆን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ያለውን አቅም ታሳቢ በማድረግ የከብት ድለባ ፕሮጀክት ተግግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፣ ከአሜሪካ ሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተገኘ 333,0000 (ሦስት መቶ ሠላሳ ሦሰት ሺህ) ብር እና በአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል አገልጋይ ከሆኑት መልአከ መንክራት ቀሲስ ስብሐት ሊቁ የንስሐ ልጆች በተገኘ 180,000 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ) ብር የገንዘብ ድጋፍ በድምሩ 5 በሬዎችን በመግዛት ከሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ጋር ቦታው ድረስ ተገኝቶ አስረክቧል፡፡
በዕለቱም ድጋፍ የተደረገላቸው አገልጋዮች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይ ተረጋግተው ለማገልገል እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡

❤6👍6
✝️የጾም ቁርሳችን፣
ለወገኖቻችን✝️ +++
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስ ብዙ ወገኖቻችን ለችግር ተጋልጠዋል።
እርስዎም ለእነዚህ ወገኖች የጾም ቁርስዎን በመለገስ ቸርነትን ያድርጉ!
ድጋፍ ለማድረግ
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
09 84 18 15 44 ወይም
09 20 27 42 98 ይደውሉ።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

👍3
ለደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት የመጽሐፍ ስጦታ ተበረከተ።
በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል በሀገረ አሜሪካ ሜኒሶታ እና አትላንታ የሚኖሩ ምዕመናንን በማስተባበር ለደብረ ምሕረት አቡን ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት የመጽሐፍ ስጦታ በዛሬው ዐለት አበርክቷል።
የምስክር ጉባኤ ቤቱ መምህር የኔታ ነቅዓ ጥበብ እሸቴ እንደገለጹት ደቀ መዛሙቱ በመጽሐፍት ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ማቋረጥ የለባቸውም በማለት የተናገሩ ሲሆን ድጋፍ ያደረጉትን የሚኖሶታ እና አትላንታ ምዕመናንን አመስግነው መጽሐፍት በማንበብ ከጉባኤ ቤቱ ተመርቀው የሚወጡ ደቀ መዛሙርት ቤተክርስቲያንንና ሀገርን ለማገልገል ሙሉ ሰው እንዲኾኑ እንዲሁም የሚጠበቅባቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ አሳስበዋል።
የተበረከተው የመጽሐፍ ድጋፍ ከ212 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት እንደሆነም ታውቋል።

❤5