Telegram Web Link
በእቅበተ አእምሮ እና በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለወጣቶቾ እና ለጽዋዕ ማኅበራት ሥልጠና ተሰጠ።

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የዋድላ ወረዳ ቤተ ክህነት የኮን ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከዋድላ ወረዳ ቤተ ክህነትና ከማኅበረ ቅዱሳን ኮን ወረዳ ማእከል ጋር በመቀናጀት “እቅበተ አእምሮ” በሚል ርዕሠ ጉዳይ በተለያየ ዘርፍ ለተሰማሩ ወጣቶች እና ለጽዋዕ ማኅበራት ሥልጠና ተሰጥቷል።

ሥልጠናው በዋናነት ወጣቱ ራሱን ከመናፍቃን እንዲጠበቅ እና የጽዋዕ ማኅበራትም እምነታቸውን ብሎም ቤተክርስትያናቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የሐዲስ ኪዳን መምህር የሆኑት መምህር ኪነ ጥበብ ጌታሁን እንደገለጹት “ወጣቱ እራሱን ከሀሰተኛ ትምህርት ጠብቆ የእግዚአብሐርን መንግስት ለመውረስ መዘጋጀት አለበት” ሲሉ ተናግረው የጽዋዕ ማኅበራትም ቤተክርስትያን አሁን ያለችበትን ፈተና ተረድተው ለተለየ አገልግሎት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ኮን ወረዳ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ሻንበል አበራ በበኩላቸው ወጣቶች ሃይማኖታችውን አውቀው፤ቤተክርስትያናችውን እንዲጠብቁ አሳስበው የጽዋዕ ማኅበራትም ዘመኑን የዋጀ ትምህርትና የጽዋዕ መርሐ ግብር በማዘጋጀት አባላቶቻቸው የሥርአተ ቤተክርስቲያን አክባሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በሥልጠናው 134 ሠልጣኞች እንደተሳተፉ ታውቋል።
👍15
ለቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ 600 ሕጻናትና ለ4 የጤና ተቋማት የማኅበረ ቅዱሳን ላልይበላ ወረዳ ማዕከል ድጋፍ አደረገ።

ታኅሣሥ ፳፬/ ፳፻፲፯ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን

በዛሬው ዕለት በማኅበረ ቅዱሳን ላልይበላ ወረዳ ማእከል በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገር ከሚገኙ በጎ ፍቃደኞች የተገኘውን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አስቸኳይ የዕለት ምግብ በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ 600 ሕጻናትና ለ4 የጤና ተቋማት ድጋፍ አድርጓል።

መምህር አበበ ሰጥአርጌ የላልይበላ ወረዳ ማእከል የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ክፍል ኃላፊ እንዳሉት በቡግና ወረዳ ከሚገኙት ቀበሌዎች መካከል በብርኮ ቀበሌ ለ250 ሕጻናት እና በጉልሀ ቀበሌ ለ350 ሕጻናት በአጠቃላይ ለ600 ሕጻናት የዕለት ምግብ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በ4 የጤና ጣቢያዎች በሕክምና ላይ ለሚገኙ ሕጻናት አገልግሎት የሚዉል፣ ለአይና፣ለቅዱስ ሀርቤና ለቆብ እንዲሁም በርካታ ታካሚዎች በሚገኙበት የብርኮ ጤና ጣቢያ ድጋፍ መደረጉን መምህር አበበ ገልጸዋል፡፡

የላልይበላ ወረዳ ማእከልና የድጋፉ አስተባባሪ ግብረ ኃይል አባላት ድጋፍ ያበረከቱትን በሀገር ውስጥና በዉጭ ሀገር የሚገኙ በጎ ፍቃደኞችን በሕጻናቱና በጤና ተቋማቱ ስም አመስግነው አሁን በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያት በርካታ ሕጻናት ከፍተኛ ለሆነ የጤና ችግርና ለሞት ተጋላጭ በመሆናቸው ሌሎች አካላት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
🙏17👍134
✍️ሐመር መጽሔት በጥር  ወር እትሟ!✍️
✍️".. እኛም ጥምቀትን እንፈልጋለን የሚሉ ምእመናን  ብዙ ናቸው ..) #ሐመር #መጽሔት  በጥር  በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ  ✍️      
                   ༺ ༻ 
  #የኅትመት ዘመን ፦#ጥር ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት  ቁጥር-፩    #ጥር  ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " #ጥምቀትን የተጠሙ ነፍሳት "በሚል ዐቢይ መልእክት
አገልግሎቱን ከሚፈልጉት ምእመናን ቍጥር ጋር ባለመጣጠኑ የተጠመቁትም  ምእመናን የሚያነሡት ጥያቄ  “አጠመቃችሁን ነገር ግን እግዚአብሔርን የምናመልክበት፣ ሥጋ ወደሙን የምንቀበልበት ቤተ ክርስቲያን የለንም፤ የሚያስተምሩን መምህራን፣ ቀድሰው የሚያቈርቡን ካህናትና ዲያቆናትም የሉንም” የሚለውን ነው።
👍111
በአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ሥር የሚገኙ አንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለአብነት ያህል ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ትጉሃን ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የዘነብ ወርቅ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የቤተል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት እና እንደእነዚህ ያሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የሚሰብኩ ሰባክያንን አገልግሎቱ ከሚፈለግበት አካባቢ እያስመጡ ያሠለጥናሉ፤ የአገልግሎት ተሞክሯቸውንም እያሳዩ ይገኛሉ። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይህን ከሠሩ ሁሉም ቢተባበሩ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ይቻላል። መልካም እየሠሩ ያሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን አብነት በማድረግ ሁሉ ለእንደዚህ ያለው ተግባር መረባረብ “እኛም መጠመቅ እንፈልጋለን” ብለው ጥሪ ለሚያቀርቡ ምእመናን የድርሻቸውን ምላሽ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።
“እኛም መጠመቅ እንፈልጋለን፤ እኛም እንደ እናንተ ኦርቶዶክስ መሆን እንፈልጋለን” ብለው ለሚጣሩት ወገኖቻችን ፈጥኖ ከመድረስ አኳያ ያለውን ጫና (ተግዳሮት) ሁሉም የየድርሻውን ቢወጣ የእነዚህን ጥምቀትን የተጠሙ ነፍሳት ጥያቄዎችን በሚገባ መመለስ  እንደሚቻል ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል" በሚል ርእስ  ባልንጀራ የሚለውን ቃል ትርጉምና አከፋፈል ፣ከክፉ ባልንጀራ መራቅ አሰፈላጊ  እንደሆነና ክፋት ለሰው ልጅ የባሕርዩ  እንደአልሆነ ና ለማሳያ ያህል የተወሰኑትን በማንሳት ከክፉ ባልንጅርነት ተጠብቀን በመልካም ባልንጅረነት እንድንጠቀም መንገድ ታሳያለች ።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “ቃል ሥጋ  ሆነ” (ዮሐ.፩፥፲፬)  ክፍል ሁለት  " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ጌታ ለምን እንደተወለደ  በዝርዝር ተዳሶበታል።
#ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ችግር በመፍታት ረገድ የምእመናን ድርሻ   " በሚል ርእስ  ዓለምን ሊሞላ በሚገባው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ቦታ ሊጠባቸው አይገባም፡፡ ‹‹ክርስትናችሁን ጠብቁ፣ ሲሞላላችሁ ጸበል ረጭተን፣ አጥምቀን፣ አቊርበን እናስተናግዳችኋለን፤›› ብቻ ተብለው የሚገፉ፣ ዘልቀው የመጡ ብቻ ተጨንቀውም ቢሆን በአገልግሎቱ ውስጥ ብልጭ፣ ብልጭ እንዲሉ ብቻ ማድረግ ሕዝባውያን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ቅርበት እንዲኖራቸው አያደርግም፡፡ ስለዚህ ከዚህ የተሻገረ ተሳትፎ እንደሚፈልጉ  ያሳያል።
በአፈጻጸም  ችግር ምእመናን የሰበካ ጉባኤ ተወካይ ሁነው ተመርጠው ግን ቢሮ አካባቢ ባሉት ሠራተኞች  ሥራው  ይያዝና የተመረጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት አዝነው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዕውቀትና በሙያ ምንምአገልግሎት ሳይሰጡ ከተመረጡበት የፈቃድ አገልገሎት  እንደሚወጡ፤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት  ቤተ ክርስቲያን አባላት የሆኑ ምእመናን በተወሰነ መልኩ በሰበካ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ ለቍጥር መሙያ ያህል እንጂ በወሳኝነት ሚና ላይ ሲሳተፉ  ብዙ እንደማይታዩ ታስነብባለች ፡፡ሙሉውን ጥር ሐመር ያንብቡ !
•  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#“ድኾችንና ጦም አዳሪዎችን…ጥራ” "በሚል ርእስ 
በርካታ ሰዎች ቤታቸው ፈርሶባቸው፣ ሀብት ንብረታቸው ተወስዶባቸው፣  ሲያበሉ ሲያጠጡ የነበሩ አሁን አብሉኝ አጠጡኝ የሚሉ ሆነው፣ እንግዳ ሲቀበሉ የነበሩት የሚቀበላቸው አጥተው በየመጠለያው ወድቀው፣ አንዳንዶች ደግሞ ያንኑም እያጡት  በችግር ላይ ችግር ተደራርቦባቸዋልና እንደነዚህ ያሉትን በፍቅር ማስተናገድ እጅግ የበለጠ ዋጋ  እንዳለው በአጽንዖት ታሰተምራለች።
#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የስደተኞች መጠጊያ ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን " ክፍል ሁለት በሚል ርእስ  ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ያለውን ግንኙነት ፣ ከሀገረ ስብከቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ፣ በሀገር ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር ያለ ግንኙነት ፣የነበሩ ተግዳሮቶችን  ታስቃኛለች ።
•  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን" በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ሁለት   በሚል ርእስ ስለ መንፈሳዊ ማኅበራት በዓለማውያን ዘንድ ፣ መንፈሳውያን ማኅበራት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ መንፈሳውያን ማኅበራት የአገልግሎት ተሳትፎ፤ በእኛ ዘመን ለጽዋ ማኅበር የሰጠነው ትርጉም መስተካከል እንዳለበት  በተለይም በአሁኑ ዘመን መልካም ማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሚያስፈልግበት ወቅት ይህንን ብናደርግ ትርጉም  እንደሚኖረው  ሰፊ ጉዳይይዛለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ጥሪ" ክፍል -፩"በሚል የሴቶች አለባበስን  በተለይም ራቁታቸውን ስለሚሄዱ  ለመንፈሳዊ ሕይወት አጠራራችን እንደሚለያይ ታስነብባለች።
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “በዐልና አከባበሩ- # ክፍል ፪ " በሚል ርእስ #“በዓልንና የበዓል  አከባበርን” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚእ አሰፋ ጋር የተደረገ የመጨረሻ   ጥያቄና መልስ ይዛለች  ። ለምሳሌ፦የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን በዓል አንድነትና ልዩነት ።፤የበዓል አከባበር እንዴት መሆን እንዳለበት ፤በዓል ማክራችን ለምን እንደሚጠቅመን ፣ባናከብርስ ምን እንደሚቀርብን፣በዓል አከባበር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ፤እነዚህን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደሚቻል ከሊቁ ጋር የተደረገውን ምልልስ ይዛለች
   ሐመር መጽሔት #፴፪  ኛ ዓመት   ቁጥር ፩  በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
👍205
በደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ታኅሣሥ ፳፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ለምትገኘው ለደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የቅዳሴ ጉባኤ ቤት ተማሪዎች የምግብ ቁሳቁስ በትናንትናው ዕለት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ አያሌው እንደገለጹት  ማእከሉ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ምእመናን የሰበሰበውን  ድጋፍ ማድረጉን  የገለጹ ሲሆን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና የሰላም እጦት አንጻር ጉባኤ ቤቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆናቸው በተጠናከረ ሁኔታ ተጨማሪ ድጋፎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።

በተመሳሳይም መሰል ድጋፍ በጋዞ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው የዋሮ ቅዱስ ሚካኤል ለ30 የዜማ ጉባኤ ቤት የአብነት ተማሪዎችም ተበርክቷል በዚህም በአጠቃላይ ለሁለቱም ጉባኤ ቤቶች 170‚000 (ከአንድ መቶ ሰባ ሺ ብር በላይ ወጭ መደረጉን ተገልጿል፡፡
33👍9
የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ምክክር ተደረገ።

ማኅበረ ቅዱሳን በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ተግባር ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ  ሰ/ት/ቤቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

በጠረፋማ አካባቢዎች ያለውን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማገዝ በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተተኪ መምህራንን በማስመጣት ሥልጠናዎችን ሲሰጡ እንደነበር ይታወቃል።

ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ እና አገልግሎቱን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ካሉ ሰ/ት/ቤቶች ጋር በትናንትናው ዕለት በማኅበሩ ሕንጻ ላይ ውይይት አከናውኗል።

በውይይቱ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይፈ ዓለማየሁ እንደገለጹት የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን ሁሉም አካላት በትብብር መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዲ/ን ሙሉጌታ ነጋ ለተሳታፊዎች በአገልግሎቱ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን እስካሁን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥልጠና የተከታተሉ ተተኪ መምህራን በየአካባቢዎቻቸው የሠሯቸውን ተግባራት በሪፖርት መልክ አቅርበዋል።
👍13
2025/07/14 10:32:59
Back to Top
HTML Embed Code: