" ..በዚህ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በስፋት የሚሰማውን ብልሹ አሠራር ማረምና ለቀጣዩ አገልግሎት መልክ ማስያዝ የካህናቱ ትልቅ ድርሻ ነው፡ ፡ ፡"#ሐመር መጽሔት
ሐመር መጽሔት #የኀዳር ወር ዕትም በሁሉም የማኅበሩ ሱቆች ትገኛለች
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ ፩
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

👍13❤8
• ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲፩ ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ “#እናንተ ግን የሌቦችና የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት፤” በሚል ዐቢይ ርእስ በሁሉም መስክ ከወሬ ባለፈ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን በተግባር የሚፀየፍ አገልጋይ በታሰበው መጠንና ፍጥነት መፍጠር እንዳልተቻለ ፤በተቀደሰው ሥፍራ የጥፋት ርኵሰትን ማከናወን ሊቋቋሙት የማይችሉትን የእግዚአብሔር ቍጣ በራስ ላይ መጥራት ነው።
ሲገሠጹም ከመመለስ ይልቅ ለምን ታወቀብኝ ብሎ ሌላ በደል ለመጨመር መሯሯጣቸውና የእግዚአብሔርን ትዕግሥት መፈታተን መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ ሌላው ጉዳይ እንደሆነ ፤ ችግር ዳር ሆኖ በማውራት፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማንሸራሸር፣ ከንፈር በመምጠጥና በተናጠልም እዚህም እዚያም በማለት የሚፈታ እንዳልሆነ ልንገነዘብና ሁላችንም ተገቢውን ሥራ ልንሠራ እንደሚገባ ፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለአጥፊዎች መከታ፣ ሽፋንና ዋሻ የሆኑ አካላትም ከእነርሱ ጋር ከተሳሰሩበት ምድራዊ ማሰሪያ ይልቅ አባታቸው እግዚአብሔርና እናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደምትበልጥባቸው አስታውሰው አካሄዳቸውን በማስተካከል ከእውነት ጐን እንዲቆሙ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
. #ዐውደ ስብከት ሥር ‹‹ወዳጄ በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ ነሽ››(መኃ.፪፥፪) በሚልርእስ ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን ጻድቃን ስለ እውነተኞቹ ምእመናን (ክርስቲያኖች)፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ወዘተ. የተናገረው ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ትንቢቱን ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ተናግሮታል፡ መሆኑን ያሳያል።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ (ዕብ.፲፫፥፰)" በሚል ዐቢይ ርእስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን በኦሪት፣በነቢያት ፣በወንጌል፣ እንዴት እንደምስብከው ሰፊ ትምህርት ይሰጣል፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮቷ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በልዩ ልዩ መልኩ ታስረዳለች።
በሥርዓተ ቅዳሴዋ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብከው ሁሉ ሥርዓተ ቅዳሴዋን እና ማኅሌት በምትፈጽምባቸው ንዋየ ቅድሳትም ትሰብከዋለች ።ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ሰዎች ስሟን እንዲሁ እናጠፋለን ብለው የሚያስቡበትን ልቡናቸውን ሽህ ጊዜ እንደገና መልሰው መላልሰው ሊያስቡበት ይገባል ። ይህን ሁሉ ቤተክርስቲያን ስታስተምር እየታየች ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ አታስተምርም ማለት ባላዩት ምስክር መሆን፤ ለራሱ ሳያውቅ እኔ ላሳውቅህ ማለትና ከአንተ ይልቅ እኔ ስለ አንተ አዋቂ ነኝ እንደ ማለት ይቆጠራል፡፡
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “‹‹ወይሠረዉ መፍቀርያነ ወርቅ፤ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ›› (ቅዳሴ እግዚእ ቁ.፭) በሚል ዐቢይ ርእስ የወቅቱ የቤተ ክህነታችን ፈተና በጥልቀት ትዳስሳለች ።በአሁኑ ዘመን አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት እንደ መንፈሳዊ መሪነት ሚናቸውን መወጣት ተስኗቸው እንደሚታዩ በመረጃ ትሞግታለች፡፡አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር አገልጋይነት ይልቅ እንደ ምድራዊ ምንደኛ፣ እንደ ፖለቲከኛ፣ እንደ ቢዝነስ ሰው ያለ የአካሄድ ዝንባሌን የሚያሳዩም መኖራቸውን ትጠቁማለች፡፡
በተለይ ገንዘብን በመሰብሰብና በማከማቸት ጥማት የታወሩትን ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፈተና ሆነውብኛል ብላ እስከ ማወጅ ደርሳለች፡፡-አንዳንድ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት የቅድስት ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ኃላፊነት ቦታዎችን፣ የአገልጋዮችን ቦታ ገንዘብ ለሚሹ ሰዎች በገንዘብ የሚሸጡ እየተበራከቱ እንደሆነ በመረጃ ትሞግታለች፡፡-በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት መደቦችንና የክህነትን ሥልጣን እንደ ቢዝነስ የሥራ መደቦችን የመሸጥ እና የመግዛት አካሄድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ እየፈተናት ነው፡፡
የካህናት ቅጥርና ዝውውር፣ ስእለትና የምጽዋት ገንዘብ አስተዳደር፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰበሰበችው ገንዘብ የምታውልበት ዓላማ፣ የጥቂት አገልጋዮች ማካበት የብዙ አገልጋይ ካህናት መጎስቆል፣ የገንዘቡ አወጣጥና አገባብ፣ በግንባታ ሥራዎች ላይ ያለው የግዢና የገንዘብ አወጣጥ ሥርዓት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የኪራይ ቤቶች አስተዳደር፣ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማቀላጠፊያ ብለው የሚሰጡት ገንዘብ የሚተዳደርበት መንገድ፣ የቤተ ክህነቱ የአገልግሎት መደቦች ስያሜና ቁጥር፣ የንዋየ ቅድሳት አስተዳደር ጥያቄ፣ የሚነሣበት እየሆነ መምጣቱን ታሳያለች ፡፡ ሙሉውን #ከመጽሔቱ ይነበብ
#ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_፪ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ መንፈሳዊ ጭንቀት ስለሰማያዊው እና ዘለዓለማዊው ሕይወት መጨነቅና ማሰብ እንደሆነ በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡ከመንፈሳዊ ጭንቀቶች ስቀምጣሉ፡፡ ሙሉውን ከሐመር መጽሔት ታገኛላችሁ፡፡
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ከገነተ ልዑል እስከ መንበረ ልዑል”በሚል ዐቢይ ርእስ በሚል ርእስ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን የሰንበትትምህርት ቤቱ አመሠራረት፣ የሊቃውንት አሻራ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የምረቃ መጽሔትን በምንጭነት በመጠቀም ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ምሩቃን ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አስተዋፅኦ" በሚል ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በመላው ዓለም በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ጉባኤያትን በመመሥረት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዶግማ እና ቀኖና እንዲሁም ሥርዓት እንዲያውቁ፣ ራሳቸውንም ከክፉ ነገር በመጠበቅ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማነጽ እንዲችሉ አገልገሎቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ያሳያል ። የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ከምረቃ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ድርሻ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዓበይት የሆኑትን ሐመር መጽሔት ታስቃኛለች፡:
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#በፍላጻ የተወጋ ልብ-ክፍል ፩ "በሚል እጅብ ባሉ ሀገር በቀል የተፈጥሮ ዛፎች በተከበበ ዐፀደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መጸለይ እጅግ ይወዳል፡፡ ከዚያ ውጣ ውጣ አያሰኘውም፡፡ አንድ ቀን እንደልማዱ ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ሲያበቃ ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ አለ፡፡ እጅግ የሚያስደስት መዐዛ ቢያውደው የትመጣውን ለማወቅ ከአንገቱ ተቃንቶ ዙሪያውን ሊቃኝ ጀመረ በማለት ግሩም የኪነጥበብ ጹሑፍ ታስነብባለች ።
• #በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኀ ጽጌን” ክፍል አንድን በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ መጋቤ ሐዲስ ተስፋ ሚካኤል ታከለን በወርኃ ጥቅምት ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ቀጣይና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ ጌታ ወደ ግብፅ የተሰደደበት ምክንያት ለምንድ ነው?

👍20❤4
በስደቱ ጊዜ እነ ኮቲባ ወደ ዝንጀሮና ጦጣ እንደተለወጡ ይነገራል ከሥነ ፍጥረት አንጻር ይስማማልን? የስደት ዐቢይ ምክንያቶችን እና ስደቱን ለምን በወርኀ ጥቅምት እናስባለን? ከወቅቱ ጋር የተሳሰረ ምሥጢር አለው የሚሉ ጉዳዮችን በሊቃውንት ምላሽ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

👍21❤2
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር
በዕለቱም፦
👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 አባላት የአገልግሎት ቃል ኪዳናቸውን ያድሳሉ
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።
እርስዎም ከማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!
ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990

👍17❤13
ደብረ ቁስቋም
ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡
ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብጽ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)
በስደቱም ጣዖታተ ግብጽ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፤ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቡና አውጥቶ አሳደደ፡፡

👍27❤6🙏5
እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)
ጌታችን ኢየሱስ በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቁርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮ የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም (ትርጉም ፳፻፫ ዓ.ም)
ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር

❤31👍8🙏8
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በዕለቱም፦
👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።
እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!
ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በዕለቱም፦
👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።
እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!
ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
👍37❤5
ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ፡፡
የቀደመ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጥበብና ዕውቀት ለማስፋፋት እየሠራ የሚገኘው የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ለነበረው ስኬታማ ጉዞ ጉልህ ሚና የነበራቸው ባለ ድርሻ አካላትን የሚያመሰግንበት መርሐ ግብር ነው ያካሄደው፡፡
በመርሐ ግብሩም ላይ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕርዳርና ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ አቡነ እንድርያስ ፣ የዴንቨርና እና ኮሎራዶ አካባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ተገኝተዋል።

👍17
በዕለቱ የመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የጓንቻ ገዳም አቡነ ተጠምቀ መድኅን ገዳም ፣ደብረ ድማኅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ፤ ማኅበረ ቅዱሳን እና ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ተቋማት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እጅ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የሐመረ ብርሃን የብራና የመጽሐፍት ሥራ ድርጅት የብራና ፣ የዕደ ጥበብ፣የስዕል፣የሕጻናት የአብነት ትምሕርት እና በሌሎቹም ዘርፍች በርካታ ሥራዎች እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ከ5 በላይ ቅርንጫፎች ከፍቶ እየሠራ የሚገኝ መሆኑም ተገልጿል።
ድርጅቱ ከንጹሕ ምንጭ በተቀዳ ዕውቀትና ጥበብ ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላትና የተግባረ ዕድ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኝ ሲሆን በ2010 ዓ.ም በ10 አገልጋዮች የተጀመረው የሐመረ ብርሃን የብራናና የመጽሐፍ ሥራ ድርጅት ከቤተ ክርስቲያን ጎን ለጎን ከመንግሥት አካላት ጋር እንደሚሠራም ተገልጿል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሕጻናት የትምህርት መርሐ ግብር ሥነ ምግባርን ከዕውቀት ጋር የተዋሐዱለት ትውልድ በመፍጠር ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ተጠቅሷል።
በመርሐ ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የብራና ዝግጅት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም ዛሬ ላይ በዚህ መልክ እያደገ መምጣቱ የሚያስደስት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አባቶቻችን በድካም ያቆዩልንን ትውፊትና ታሪክ አንዱም ሳይዛባ እንዲቀጥል አጥብቃችሁ ያዙ ሲሉም አባታዊ ምክርና መመሪያ ሰጥተዋል።

👍32❤9
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት:-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/
ኢንስታግራም፡- http://www.instagram.com/pr.deputy/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ትዊተር፡- http://www.twitter.com/@kidusanpr/
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905

👍8