Telegram Web Link
ሻሸመኔ ማእከል በተለያዩ ኮሌጆች ያስተማራቸውን የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች አስመረቀ

ሐምሌ ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል በተለያዩ ኮሌጆች ሲያስተምራቸው የቆዩትን የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።

በምርቃት መርሐግብሩ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ በቃሉ ታመነ ፣የደብሩ አገልጋዮች እንዲሁም የማኀበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ፍርዱ አያኖ ተገኝተዋል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ መዝሙር፣ ስብከተ ወንጌል የተከናወነ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል ተበርክቷል።
18🕊2
የሐምሌ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ?

የሐምሌ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#የተሰጠህን አደራ #ጠብቅ ›› በሚል ግቢ ጉባኤያትን በተመለከተ አደራን ስለመወጣት በመልእክቱ ዐምዱ ይዛለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” የክርስቶስን ደቀመዛሙርት እከተላቸው ዘንድ ፍቅረ እግዚአብሔር ያስገድደኛል"
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር "ሐዋርያው #ቅዱስ ጴጥሮስ "በሚል ርእስ ትውልዱእና እድገቱ ፣የቅዱስ ጴጥሮስ መጠራት ሰፊ ትምህርት ያስጨብጣል። #በመልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ ሺፈራው የተዘጋጀ ግሩም ጹሑፍ ትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች።

#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# ዛሬ ሳንሠራ ቀርተን ነገን እንዳንቸገር ልዩ ትኩረት ለግቢ ጉባኤያት " በሚል ርእስ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ፣የመምህራን ችግር፣የቋንቋ ጉዳይ ፣የየዮኒቨርቲዎች የትምህርት የጊዜ ሠሌዳ፣ሀገሪቱ ያለችበት የጸጥታ ችግር ፣እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ፣መፍትሔ ከማን ምን ይጠበቃል ? የሚሉትን መሠረታዊ ጉዳዩች ይዟል።
"#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ #ኦርቶዶክሳውያን በማኅበረሰብ ውስጥ ቦታችን የት ነው _ክፍል _፫" በሚል ርእሰ #በጎ አድራጎት እና ኦርቶዶክሳውያን ምንና ምን ናቸው ? በማለት በጎ ማድረግ ዘርፈ ብዙ መሆኑን ያሳያል ።

#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ "በሚል ርእስ የስሙ ትርጓሜ፣ልደቱና እድገቱ፣የትምህርት ሕይወቱ የሹመት ዘመኑ፣ማስተማር ሕይወቱን በተመለከተ ፣የቅዱስ ቄርሎስ ሥራዎች፣መዓርገ ቅድስና በማንሳት ስለ ቅዱሱ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ።

#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ክርስቲያናዊ ሕይወትን በዕቅድ መምራት "በሚል ጥሩ ነገር ታስነብባለች።
17
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ከፍቅረኛህ ጋር ታረቅ " በሚል ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ "#ዘመነ ክረምት"ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ አዘጋጅተናል።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፯ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
18👍1
“ዘመኑን የዋጀ ንቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ትኬት መዘጋጀቱን ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ

ሐምሌ ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ  “ዘመኑን የዋጀ ንቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን” በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ማሰባሰቢያ ትኬት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ማኅበሩ የተቋማዊ ለውጥ ትግበራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ለ2ተኛ ጊዜ በተከለሰው የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት በግቢ ጉባኤያት ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሃይማኖት እና በሥነ ምግባር አንጾ ለማውጣት ለሚተገብራቸው የመምህራን ማፍራት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት፣ እንዲሁም የቨርቹዋል ሥልጠና ማእከል ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች የሚውል የድጋፍ ማሰባበሰቢያ ቲኬት ማዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡

የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አበበ በዳዳ ከሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ትኬቱ ሥርጭት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ትኬቱም ለግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ለማኅበሩ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሌሎች የአገልግሎቱ ደጋፊ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን የቀረበ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው አክለውም  የአንድ ትኬት ዋጋ 100 (አንድ መቶ ብር) ብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ትኬቱን ከግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፣ ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንዲሁም በማኅበሩ የልማት ተቋማት ሱቆች ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡
3
እንደሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው ኃላፊነት መሠረት በዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ኦርቶዶክሳዊያን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የሃይማኖት ትምህርት እያስተማረና በአባቶች ቡራቄ እያስመረቀ ይገኛል፡፡
"ኑ እንሰባሰብ " መርሐ ግብር በአሜሪካ ተካሄደ
“ኑ እንሰባሰብ” በአሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የቀድሞ የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን በአንድነት ለማሰባሰብና በግቢ ጉባኤ ቆይታቸው የነበረውን አገልግሎት ለማስታዎስና የተፈጠረውን ትስስር ለማደስ ያለመ መርሐ ግብር ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአሜሪካ ማእከል የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር እገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ተካሄደ፡፡
በመርሐ ግብሩም የግቢ ጉባኤ መንፈሳዊ ሕይዎት በሦስቱ አስርት ዓመታት  ምን  ይመስል  እንደነበር የተቃኘበት ሲሆን ዘመኑን የሚወክሉ  ለእለቱ መርሐ ግብር የተመረጡ አባላት ትውስታቸውን፤ ልምዳቸውንና ያገኙትን ትምህርት፤ የነበረውን የመደጋገፍ፤ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ሁኔታ በማጋራት ጉባኤተኛውን በትዉስታ ወስደውት ነበር ያመሹት፡፡ እግዚአብሔር ለትውልዱ ያደረገውና የሰጠው የአገልግሎት እድልም ከህሊና በላይ እንደሆነ ከትውስታ ጋር ቀርቧል፡፡
እንዲህ ዓይነቱ  መርሐ ግብር  ቀጣይ  እንደሚሆን  አባላት ልምዳቸውንና ለክርስቲያናዊ ሕይዎታቸው ማደግ፤ ለሙያ እድገትና ምክክር እንዲሁም ትብብር የሚደግፍ ቀጣይነት ያለው ትስስር ለመገባንት መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል  ከአዘጋጅ ክፍሉ ለማዎቅ ችለናል፡፡
2025/07/13 02:51:08
Back to Top
HTML Embed Code: