Telegram Web Link
ግእዝ ክፍል 67
የውስጠዘ እና የባዕድ ቅጽል ትርጉም
እሙር፥ማእምር፥መስተአምር ብሎ ያወቀ የታወቀ ያሳወቀ የተዋወቀ ያስተዋወቀ የሚያውቅ የሚታወቅ የሚያሳውቅ የሚተዋወቅ የሚያስተዋውቅ አዋቂ ታዋቂ አሳዋቂ ተዋዋቂ አስተዋዋቂ ያውቅ ነበር አዋቂ ነው ተብሎ ይተረጎማል።ለምሳሌ በሌላ ቃል ብንመለከተው ቅዱስ ብሎ ያመሰገነ የተመሰገነ ያስመሰገነ የተመሰጋገነ ያመሰጋገነ የሚያመሰግን የሚመሰገን የሚያስመሰግን የሚያመሰጋግን የሚመሰጋገን አመስጋኝ ተመስጋኝ ተመሰጋጋኝ አመሰጋጋኝ አስመስጋኝ ተብሎ ይተረጎማል።ይህን የመሰሉ ቃላት በዚህ መልኩ ይሄዳሉ።ለአንድ ሴት ቅድስት መቀድስት መስተቀድስት መስተቃድስት ይላል።ለብዙ ወንዶች ደግሞ ቅዱሳን መቀድሳን መስተቀድሳን መስተቃድሳን ይላል።ለብዙ ሴቶች ቅዱሳት መቀድሳት መስተቀድሳት መስተቃድሳት ይላል። መድበል ቀደስት ይላል ትርጉሙ እንደ ብዙ ወንዶችና ሶቶች ነው።

የሣልስ ቅጽል ትርጉም
አእማሪ ብሎ የሚያውቅ አዋቂ ያውቅ የነበረ አዋቂ ነው ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ ይህንን የመሰለ ቃል ሲመጣ እንድህ እንድህ እያለ ይተረጎማል። ለምሳሌ ጸሓፊ፥ሠዓሊ የሚለው ሣልስ ቅጽል ስለሆነ የላይኛውን መስሎ ይተረጎማል። ጸሐፊ ብሎ የሚጽፍ ጸሐፊ ይጽፍ የነበረ ጸሐፊ ነው ተብሎ ይተረጎማል።ሠዓሊ ደግሚ የሚሥል ሠዓሊ ይሥል የነበረ ሠዓሊ ነው ተብሎ ይተረጎማል።ይህንን የመሰለ ብዙ ቃላት አሉ።

ይህ ውስጠዘ እና ሣልስ ውስጠዘ በዝርዝር እርባታ ይረባል ይኽውም ለምሳሌ ውእቱን ብቻ ብንመለከት ውእቱ ውእቱን ሲያውቅ

ውእቱ ብእሲ እሙሩ ማእምሩ መስተአምሩ ውእቱ ለውእቱ ብእሲ ይልና ሲተረጎም ያ ሰውየ ለዚያ ሰው አዋቂው ተዋዋቂው አስተዋዋቂው ታዋቂው አሳዋቂው ያወቀው የታወቀው ያሳወቀው የተዋወቀው ያስተዋወቀው የሚያውቀው የሚታወቀው የሚያሳውቀው የሚተዋወቀው የሚያስተዋውቀው ያውቀው የነበረ አዋቂው ነው ተብሎ ይተረጎማል። እንዲህ እያልክ እስከመጨረሻው ዝለቅ።

ሣልስ ቅጽልም በዝርዝር ይሄዳል ይሄውም ውእቱ ብእሲ አእማሪሁ ውእቱ ለውእቱ ብእሲ ሲል ያ ሰውየ ለዚያ ሰው አዋቂው የሚያውቀው ያውቀው የነበረ አዋቂው ነው ተብሎ ይተረጎማል። እንዲህ እያለ እስከ መጨረሻው ይዘልቃል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 68
የሳቢዘር እና የንዑስ አንቀጽ ዝርዝር
እኒህም እያንዳንዳቸው በ10ሩ መራሕያን ይዘረዘራሉ።ሐይወ ኖረ ብሎ ሕይወት ሳቢ ዘር ይወጣል።ይህ ሕይወት ደግሞ ሲዘረዘር ሕይወቱ ሕይወታ ሕይወቶሙ ሕይወቶን ሕይወትከ ሕይወትክሙ ሕይወትክን ሕይወትኪ ሕይወትየ ሕይወትነ እያለ መኖሩ መኖሯ መኖራችን መኖሬ እያለ ይተረጎማል።

የአርመመ ዝም አለ ለሚለው ንኡስ አንቀጹ አርምሞ ወይም አርምሞት ትርጉሙ ዝም ማለት የሚል ሲሆን ይህ በ10ሩ መራሕያን ሲዘረዘር አርምሞቱ አርምሞታ አርምሞቶሙ አርምሞቶን አርምሞትየ አርምሞትነ አርምሞትከ አርምሞትኪ አርምሞትክሙ አርምሞትክን እያለ ዝም ማለትህ ዝም ማለትሽ ዝም ማለታችሁ እያለ እያለ ይተረጎማል።

ከዚህ ቀደም ባሉ ክፍሎ እንዳየነው አጠቃላይ ዘመድ ዘር ጥሬ ዘር ምእላድ ባእድ ከምእላድ ወዘተ እንድህ በ10 በ10 እየተተረጎሙ ይሄዳሉ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 69
የቦዝ አንቀጽ ዝርዝር
አእሚርየ አውቄ አእሚረከ አውቀህ አእሚረኪ አውቀሽ አእሚረክሙ አውቃችሁ አእሚረክን አውቃችሁ አእሚረነ አውቀን አእሚሮሙ አውቀው አእሚሮን አውቀው እያለ በ10ሩ መራሕያን ከዘረዘረ በኋላ እንደገና በዝርዝር እርባታ አንዱ መራሒ አንዱን መራሒ እየሳበ አንዱ ባለቤት አንዱ ተሳቢ እየሆነ ይዘረዘራል። ለምሳሌ አውቆት የሚለውን አማርኛ ስንመረምረው ባለቤቱ እርሱ ወይም ውእቱ እንደሆነና ታዋቂውም እርሱ ወይም ውእቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። ስለዚህ አውቆ የሚለው አእሚሮ ነው። ውእቱን ሲስብ ግን ሁን ይጨምርና አእሚሮሁ ይላል።

ውእቱ ሲታውቅ "ሁ"ን መጨመር
ይእቲ ስትታወቅ "ሃ"ን መጨመር
ውእቶሙ ሲታወቁ "ሆሙ"ን መጨመር
ውእቶን ሲታወቁ "ሆን"ን መጨመር
አንተ ስትታወቅ "ከ"ን መጨመር
አንቲ ስትታወቂ "ኪ"ን መጨመር
አንትሙ ስትታወቁ "ክሙ"ን መጨመር
አንትን ስትታወቁ "ክን"ን መጨመር
ንሕነ ስንታወቅ "ነ"ን መጨመር
አነ ስታወቅ "ኒ"ን እየጨመርን በዝርዝር እርባታ እናረባዋለን ማለት ነው።ለምሳሌ አውቃችሁኝ ብል ባለቤቱ እነርሱ ወይም ውእቶሙ ናቸው ታዋቂው ደግሞ እኔ ወይም አነ ነኝ። ከላይ ባለቤቱ ውእቶሙ ቀቲሎሙ እነርሱ ገድለው ይል ነበር።ገድለውኝ ለማለት ግን በአነ ጊዜ "ኒ"ን መጨመር እንዳልነው ቀቲሎሙ ባለው ላይ ቀጥታ "ኒ" ሲጨመር ቀቲሎሚነ ገድለውኝ ይላል ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 70
የዓዲ ዝርዝር
ዓዲ ማለት ገና ማለት ነው።ይህ በ10ሩ መራሕያን ይረባል።ይኽውም ዓዲ ብሎ ገና ነው፥ገና ይሆናል ገና ይሁን ብሎ በውእቱ እንደገና ዓዲ ብሎ ገና ነህ፥ ገና ትሆናለህ፥ ገና ሁን እያለ በ10ሩም ይተረጎማል።

እንደገና ይኽው ዓዲ በዝርዝር እርባታ ይረባል ይኽውም።ዓዲሁ ብሎ ገናው ነው ገናው ይሆናል ገናው ይሁን ይላል። ዓዲከ ብሎ ደግሞ ገናህ ነው ገናህ ይሆናል ገናህ ይሁን ይላል። ዓዲክሙ ብሎ ገናችሁ ነው ነው ገናችሁ ይሆናል ገናችሁ ይሁን እያለ ይዘረዘራል።

በምሳሌ ለማጎልበት ያህል።
ዓዲ ኢመጽአ ሐሳዊ መሲሕ ሲል ወደ አማርኛ ሲተረጎም ሐሳዊ መሲሕ ገና አልመጣም ማለት ነው።እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቃና ዘገሊላ ሰርግ ወይናቸውኮ አልቋል ባለችው ጊዜ ጊዜየ ገና አልደረሰም ብሏታል።ይህ በግእዝ ሲጻፍ ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ ይላል ማለት ነው።

የእለቱ ጥያቄዎች
አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም/ሚ

1ኛ ገና አላወቅንም
2ኛ ገና አልታገስንም

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
በቀጣይ የባሕረ ሐሳብ ትምህርት እንቀጥላለን ‼️ ሼር በማድረግ ለሁሉም ያዳርሱ!!!

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 1
ቤተክርስቲያን ከሰከንድም ከማይክሮ ሰከንድም እጅግ በጣም የረቀቀ የዘመን የጊዜ መለኪያ አላት።
1ኛ ሳድሲት ይህ ቁጥር 0.00000185 ሰከንድ ነው።አስበውማ ከሰከንድ እጅግ ያነሰ መለኪያ ነው።
2ኛ ኀምሲት ይህ ቁጥር 0.00011 ሰከንድ ነው።
3ኛ ራብዒት ይህ ደግሞ 0.0067 ሰከንድ ነው።
4ኛ ሣልሲት ይህ ደግሞ 0.4 ሰከንድ ነው።
5ኛ ካልዒት ይህ ደግሞ 24 ሰከንድ ነው
6ኛ ኬክሮስ ይህ ደግሞ 24 ደቂቃ ነው።

በሌላ አገላለጽ
60 ሳድሲት=1 ኃምሲት
60 ኃምሲት=1 ራብዒት
60 ራብዒት=1 ሣልሲት
60 ሣልሲት=1 ካልዒት
60 ካልዒት=1 ኬክሮስ
60 ኬክሮስ=1 ዕለት ወይም 24 ሰዓት ነው። ይህ ማለት ደግሞ 1 ሰዓት 2.5 ኬክሮስ ነው ማለት ነው።ስለዚህ ይህንን ካየን ካልዒትን ወደ ሣልሲት እንዲሁም አንዱን ወደ አንዱ መለወጥ አያቅተንም ማለት ነው።

እንደሚታወቀው ፀሐይ ዓመቱን ሙሉ ብርሃኗን ትሰጣለች።በአንጻሩ ጨረቃ በቀን በቀን ከፀሐይ 1 ኬክሮስ ከ 52 ካልዒት ከ31 ሣልሲት በአነሰ መጠን ታበራለች።ይህንን እያንዳንዱን እንመልከተው።
በቀን 1 ኬክሮስ በ30 ቀን 30 ኬክሮስ ይሆናል።በ2 ወር 60 ኬክሮስ ይሆናል።60 ኬክሮስ ደግሞ 1 እለት ስለሆነ።በ2 ወር 1 እለት በ12 ወር 6 እለት ይገኛል።
52 ካልዒት 31 ሣልሲት በ12 ወር 5 ቀንና 15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ይሆናል።52 ካልዒት×30 ቀን×12 ወር=18720 ካልዒት ይገኛል።ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንለውጠው 312 ኬክሮስ ይመጣል።በመቀጠል 30 ሣልሲት×30 ቀን×12 ወር 10800 ሣልሲት ይመጣል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 3 ኬክሮስ ይሆናል።ከላይኛው ጋር 312+3=315 ኬክሮስ ይሆናል።ይህንን ወደ እለት ስንቀይረው 5 ቀን ከ15 ኬክሮስ ይሆናል።
ይህች 5 ቀን ጷግሜን ናት።ከዝያ 15 ኬክሮስ በ4 ዓመት 4×15=60 ኬክሮስ ወይም አንድ እለት ይሆናል። በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 6 የምትሆን በዚህ ምክንያት ነው።አንዷ ሣልሲት በ600 ዓመት 1 ቀን ትሆናለች።ይኽውም 1 ሣልሲት×30 ቀን×12 ወር×600 ዓመት 216000 ሣልሲት ይገኛል ይህንን ወደ ኬክሮስ ስንቀይረው 60 ኬክሮስ ይሆናል።60 ኬክሮስ ደግሞ አንድ ቀን ወይም እለት ነው። ስለዚህም በ600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 7 ትሆናለች ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄ
1ኛ 6 ቀን ስንት ካልዒት ይሆናል
2ኛ 1 ቀን ስንት ሳድሲት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 2
የዓለም እድሜ ስንት ነው በሚልየን ይቆጠራል ወይስ እንዴት ነው? ለሚለው ብዙ አስተያየቶች አሉ።እኒህን ከስር መሰረቱ እንመልከት እንግዲህ ይህች ዓለም የተፈጠረች በእለተ እሑድ ነው።ይህም እሁድ ጥንተ እለት ወይም የእለታት መጀመሪያ ይባላል።ማክሰኞ ጥንተ ቀመር ይባላል።ረቡዕ ደግሞ ጥንተ ዖን ይባላል።ዖን ማለት ፀሐይ ማለት ነው።ፀሐይ የተፈጠረች በዕለተ ረቡዕ ስለሆነ።ጥንተ ዖን ማለት ፀሐይ የተፈጠረችበት የመጀመሪያ እለት እንደማለት ነው ጥንተ ዖን ማለት።ዓለም የተፈጠረ መጋቢት 29 እሑድ ቀን ነው።ፀሐይ የተፈጠረች ረቡዕ ስለሆነ ከረቡዕ በፊት ያለው ቀን በፀሐይ አቆጣጠር ስላልተቆጠረ ምናልባት በሚልየን በቢልየን የሚቆጠር ዘመን ሊሆን ይችላል ወይም በአንጻሩ በሰከንድ በደቂቃ የሚቆጠር ሊሆን ይችላል የሚሉ አሉ።ነገር ግን ከረቡዕ በኋላ ያለውን ቀንና ከረቡዕ በፊት ያለውን ቀን ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አንድ ቀን እያለ ቀን በማለት ስለሚያስተባብረው ምንም እንኳ ፀሐይ ረቡእ ብትፈጠርም ከረቡዕ በፊትም ጨለማንና ቀንን የሚለይ ብርሃን ነበረ።ስለዝህ ተመሳሳይ አቆጣጠር ይኖረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ። አዳም በእለተ አርብ ተፈጠረ።ከ40 ቀን በኋላም ወደ ገነት እግዚአብሔር አስገባው።አዳምም የእግዚአብሔርን ሕግ እየጠበቀ 7 ዓመት ከ1 ወር ከ17 ቀን በገነት ተቀመጠ።ከዚያ በኋላ አትብላ የተባለውን እጸበለስ ስለበላ ተፈረደበት። አዳምም ንሥሓ በገባ ጊዜ እግዚአብሔር ከ5500 ዘመን በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ የሚል ተስፋ ሰጠው።የአዳም ልጆችም ይህን ይዘው ጌታ ሰውን ለማዳን የሚመጣበትን ጊዜ በፀሐይ በጨረቃ በከዋክብት እየቆጠሩ ይኖሩ ነበር። የዘመን ቁጥር የተጀመረበት ምክንያቱ ይህ ነው።ጌታም
1ኛ በ5500 ዘመን በዘመነ ዮሐንስ መጋቢት 29 እሑድ ቀን በ3 ሰዓት ተፀነሰ
2ኛ በ5501 ዘመን ወይም በ1 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ታህሳስ 29 ማክሰኞ መንፈቀ ሌሊት ተወለደ።
3ኛ 31 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ ጥር 11 ማክሰኞ መንፈቀ ሌሊት ተጠመቀ።
4ኛ በ33 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ነሐሴ 13 እሑድ ቀን በቀትር ጊዜ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት በደብረ ታቦር ገለጠ።
5ኛ በ34 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማርቆስ መጋቢት 27 አርብ በቀትር ጊዜ ተሰቀለ።።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 3
ባሕረ ሀሳብን የአጽዋማትና የበዓላት መውጫ እንዲሆን የደረሰው ቅዱስ ዲሜጥሮስ 11ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ነው።ባሕረ ሐሳብ ማለት የዘመን ቁጥር ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ 40 ቀን ጾመ።ይህም ማለት ጥር 11 ተጠምቆ ጥር 12 ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ድረስ ጾመ ይህን ጾም ጌታ የጾመው በመሆኑ ዐቢይ ጾም ወይም ጾመ ኢየሱስ እንለዋለን።ከሐዋርያት ጀምረው እስከ 241 ዓመተ ምሕረት ድረስ አካባቢ ምእመናን ዐቢይ ጾምን ጥር 12 ጀምረው የካቲት 21 ድረስ ይጾሙና።እንደገና ሰሙነ ሕማማትን ከመጋቢት 22 እስከ መጋቢት 27 ይጾሙ ነበረ።ትንሳኤንም ሰኞም ይሁን ማክሰኞም ይሁን ብቻ መጋቢት 29 ቀን በዋለበት ቀን ያከብሩ ነበር።ሐዋርያት ግን በዲድስቅሊያ የትንሳኤ በዓል እሑድን መልቀቅ የለበትም ብለው ስርዓት ሰርተው ስለነበር ቅዱስ ድሜጥሮስ የነነዌ ጾም የዐቢይ ጾም እና ጾመ ሐዋርያት ከሰኞ።ደብረ ዘይት ሆሳእና ትንሳኤ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ።ስቅለት ከአርብ።ዕርገት ከሐሙስ።ርክበ ካህናት፥ጾመ ድኅነት ከረቡዕ ባይወጡ በወደድኩ ነበር።ብሎ ተመኘ።መልአኩም መጥቶ ባሕረ ሀሳብን ገለጸለት።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 4
©©አበቅቴ እና መጥቅእ©©
ከዚህ በኋላ መልአኩ አበቅቴን እና መጥቅእን ለዲሜጥሮስ ገለጸለት።አበቅቴ ማለት ተረፈ ዘመን ማለት ነው።ይህም ማለት ጨረቃ ከፀሐይ ባነሰ የምታበራበት የጊዜ መጠን ነው።ፀሐይ በዓመት 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ ከ1 ሣልሲት ታበራለች።ጨረቃ ደግሞ 11 ቀን አንሳ 354 ቀን ታበራለች።በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት አበቅቴ ይባላል።መልአኩ ለዲሜጥሮስ የገለጸለት አበቅቴ ዓለም ከተፈጠረ የመጀመሪያውን ዓመት ነው።ስለዝህ 11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል።ሌላው መጥቅዕ ማለት ነጋሪት ደወል ማለት ነው።ደወል ሲመታ ከሩቅ ያሉት ተሰብስበው መጥተው እንዲገኙ ይህ መጥቅእም አጽዋማትን እና በዓላትን የሚያስገኝ ስለሆነ ነው።መልአኩ ለዲሜጥሮስ የገለጸለት ጥንተ መጥቅእ 19 ነው።አበቅቴ እና መጥቅእ ሁለቱ ተደምረው ሁልጊዜም 30 ይሆናሉ።

ስለዚህ በመጀመሪያው ዓመት 11 አበቅቴ ከሆነ በሁለተኛው 22 ይሆናል በሦስተኛው 33 ይሆናል።ከ30 በላይ ሲሆን በ30 አካፍለን ቀሪውን እየያዝን አበቅቴን እናወጣለን ስለዚህ 3 ይሆናል።ከዚያ በአራተኛው 14 እያለ ይሄዳል።አበቅቴና መጥቅእ ሁለቱ ተደምረው 30 ስለሚሆኑ አንዱ ከተገኘ ሌላኛውን ከ30 በመቀነስ እናገኘዋለን።ምሳሌ አበቅቴ 6 ከሆነ መጥቅእ 24 ይሆናል ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 5
©©ሰባቱ አዕዋዳት®®
1ኛ ዓውደ እለት፦ይህ ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት እለታት ናቸው።ይህም ማለት ቅዳሜን መልሰን የምናገኘው ከሰባት ቀን በኋላ ነው።
2ኛ ዓውደ ፀሐይ፦በየ 28 ዓመቱ የሚገኝ ሲሆን ይህም ዕለትና ወንጌላዊ ይገናኙበታል። ይህም ማለት ለምሳሌ ዛሬ ታኅሣሥ 17 ቅዳሜ ቀን ዘመነ ማቴዎስ ተመልሶ ይኽው ቀን ማለትም ታኅሣሥ 17 ቀን ዘመነ ማቴዎስ እለተ ቅዳሜ የሚገኘው የዛሬ 28 ዓመት ነው ማለት ነው።
3ኛ ዓውደ ወርኅ፦በፀሐይ 30 ቀን በጨረቃ አንድ ጊዜ 29 አንድ ጊዜ 30 የሚሆነው ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ሐምሌ 21 ማርያምን ከ30 ቀን በኋላ ነሐሴ 21 እናገኛታለን ይህ ዓውደ ወርኅ ይባላል።
4ኛ ዓውደ ዓመት፦ይህ በፀሐይ 365.25 ቀን ነው።ይህም ማለት ለምሳሌ ዛሬ ታኅሣሥ 17ን መልሰን የምናገኘው ከ365.25 ቀን በኋላ ነው ማለት ነው።
5ኛ ዓውደ ንኡስ ቀመር ወይም ዓውደ አበቅቴ የሚባለው ደግሞ ከ19 ዓመት በኋላ የሚመላለስ ነው።ይህም ማለት ለምሳሌ ዛሬ ይህን በምታነብበት ጊዜ ፀሐይም ካለችበት ቦታ ጨረቃም ካለችበት ቦታ በዚያው ቦታ የሚገኙት ከ19 ዓመት በኋላ ነው።ከዚያ በፊት ግን ፀሐይ ባለችበት ብትገኝ ጨረቃ ከሌላ።ጨረቃ ባለችበት ስትገኝ ፀሐይ በሌላ እየሆኑ ይኖራሉ።በየ 19 ዓመት ግን መጀመርያ ከየነበሩበት ይገናኛሉ።
6ኛ ዓውደ ማእከላዊ ቀመር ወይም ዓውደ ማኅተም፦ይህ በየ 76 ዓመቱ ይከሰታል።በዚህም ለምሳሌ ዛሬ ዘመነ ማቴዎስ ታኅሣሥ 17 ቀን አሁን ፀሐይ እና ጨረቃ ካሉበት መልሰን ዘመኑም ዘመነ ማቴዎስ ሆኖ የሚገኘው ከ76 ዓመት በኋላ ነው።ይህም 4×19=76 ነው
7ኛ ዓውደ ዐቢይ ቀመር፦ይህ ደግሞ 532 ዓመት ሲሆን በዚህ ወንጌላዊ እለት እና አበቅቴ ይገናኙበታል።ይህም ማለት ለምሳሌ ዛሬ ታኅሣሥ 17 ቀን ቅዳሜ ዘመነ ማቴዎስ ላይ አሁን ወጥታችሁ ፀሐይም ያለችበትን ቦታ ጨረቃም ያለችበትን ቦታ ብትመለከቱ።ከዛሬ በኋላ እለቱም ቅዳሜ ቀኑ ታኅሣሥ 17 ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ሆኖ ጨረቃ እና ፀሐይን አሁን ባያችኋቸው መልኩ ልታዩዋቸው የምትችሉ ከ532 ዓመት በኋላ ነው። 4×7×19=532 ያልነው ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 6
©® ዓመተ ምሕረትና ዓመተ ኩነኔ©®
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ክርስቶስ የተጸነሰበት ጊዜ ያለው ዓመት ዓመተ ኩነኔ ይባላል።መጠኑም 5500 ዓመት ነው።ክርስቶስ ከተፀነሰበት ጀምሮ ወደዚህ ያለው ዘመን ደግሞ ዓመተ ምሕረት ይባላል።መጠኑም ባለፈው መስከረም 2013 ዓመተ ምሕረት ነው።
ዓመተ ዓለም=ዓመተ ኩነኔ+ዓመተ ምሕረት
=5500+2013
=7513 ዓመት
ይህ ማለት ዓለም ከተፈጠረ እስካሁን ያለው እድሜ 7513 ዓመት ነው ማለት ነው።
ዓመተ ወንጌላዊ
ወንጌላውያን 4 ናቸው።ወንጌልን ለ4 ተካፍለው እንደጻፉት ሁሉ።ዘመናትንም ለ4 ተካፍለው ይመግቡታል።ስለዚህ ዘንድሮ ዘመኑ ዘመነ ማን ነው የሚለውን ለማወቅ ስንፈልግ ዓመተ ዓለሙን ለ4 አካፍለን
ቀሪው 1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው 2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው 3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ
ያለ ቀሪ ከተካፈለ ዘመነ ዮሐንስ ነው።
ስለዚህ በዚህ መሰረት።7513÷4=1878 ቀሪ 1 ይሆናል።1878 ወይም ደራሹ መጠነ ራብዒት ይባላል።ስለዚህ ቀሪው 1 ከሆነ ማቴዎስ ነው እንዳልነው ዘንድሮ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ይባላል።
የዓመቱ መስከረም 1 ቀን መቼ መቼ ትውላለች?
መስከረም አንድ ቀን መቼ እንደዋለ ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከመጠነ ራብዒት ጋራ ደምረን በእለታቱ ልክ በ7 አካፍለን
ቀሪው 1 ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው 2 ከሆነ ረቡእ
ቀሪው 3 ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው 4 ከሆነ አርብ
ቀሪው 5 ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው 6 ከሆነ እሑድ
ያለ ቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል።
ስለዚህ ዘንድሮ መስከረም 1 መቼ ዋለ የሚለውን ለማወቅ።(7513+1878)÷7=1341 ቀሪ 4 ይሆናል።ቀሪው 4 ከሆነ አርብ ይውላል።ስለዚህ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም አርብ ውሏል ማለት ነው።
መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል
ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል
ህዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል
ታሕሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል
ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል።
ይህም ማለት ለምሳሌ መስከረም 1 ቀን አርብ ከዋለ ሚያዝያ 1 ቀንም አርብ ይውላል ማለት ነው።ታህሣሥ 19 ቅዳሜ ከዋለ ሐምሌ 19ም ቅዳሜ ይውላል ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 7
የ2013 መጥቅእ እና አበቅቴን እንዴት እናገኛለን??
ዓመተ ዓለምን በንኡስ ቀመር ወይም በ19 ብናካፍለው።ይህም ማለት 7513÷19=395 ቀሪ 8 ይሆናል።አሐደ አእትት ለዘመን እንዲል 8-1=7 ይሆናል።ይህ 7 ወንበር ይባላል። አበቅቴውን ለማግኘት ይህንን ወንበር በጥንተ አበቅቴ ስናባዛው ማለትም 7×11=77 ይሆናል።ይህንን ቁጥር ለ30 ስናካፍለው 2 ጊዜ ደርሶ 17 ይተርፋል።ይህ 17 የዘንድሮው ዓመት ማለትም የ2013 አበቅቴ ነው።

መጥቅእን ለማግኘት አጭሩ መንገድ ከ30 ላይ 17 ስንቀንስ 13 እናገኛለን ስለዚህ የ 2013 ዓ.ም መጥቅእ 13 ነው።በሌላ መልኩ ወንበሩን በጥንተ መጥቅእ ስናባዛው 7×19=133 ይሆናል ይህንን ለ30 ስናካፍለው 4 ጊዜ ደርሶ 13 ይተርፋል።ይህ መጥቅእ ይባላል። መጥቅእ 14ን አይነካም ከ14 በላይ ከዋለ በመስከረም ይውላል።ከ14 በታች ከዋለ በጥቅምት ይውላል።በዚህም ምሳሌ ዘንድሮ መጥቅእ 13 ከሆነ ከ14 በታች ስለሆነ በጥቅምት ውሏል ማለት ነው።ስለዚህ የዘንድሮ መጥቅእ ጥቅምት 13 ውሏል።መስከረም 1 ቀን አርብ ከዋለ ጥቅምት 1 ቀን እሑድ ይውላል።ጥቅምት 8 እሑድ ይውላል።9 ሰኞ 10 ማክሰኞ 11 ረቡእ 12 ሐሙስ 13 አርብ ይውላል።ስለዚህ ጥቅምት 13 ቀን አርብ ውሏል ማለት ነው።

መባጃ ሐመር
መባጃ ሐመር አጽዋማትና በዓላት መቼ እንደሚውሉ የሚያሳውቀን ሲሆን የምናገኘውም መጥቅእ+መጥቅእ የዋለበት የእለት ተውሳክ ነው።ይህም 13+የአርብ ተውሳክ =13+2 ይህም 15 ይመጣል።15 መባጃ ሐመር ነው። መጥቅእ በጥቅምት ከዋለ የነነዌ ጾም በየካቲት ትጀምራለች።ይህም የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም የነነዌ ጾም ይገባል ማለት ነው።መጥቅእ በመስከረም ከዋለ እና መባጃ ሐመሩ ከ30 በታች ከሆነ በጥር ይገባል።ከ30 በላይ ከሆነ ግን ገድፎ በየካቲት ይውላል።
የእለታት ተውሳክም እንደሚከተለው ነው።
የቅዳሜ ተውሳክ 8
የእሑድ ተውሳክ 7
የሰኞ ተውሳክ 6
የማክሰኞ ተውሳክ 5
የረቡእ ተውሳክ 4
የሐሙስ ተውሳክ 3
የአርብ ተውሳክ 2
ነው።ይህ ከመጥቅእ ጋር መጥቅእ የዋለበት እለት ተደምሮ መባጃ ሐመርን ለማግኘት ይጠቅመናል።
መጥቅእ በዓላትና አጽዋማት መቼ እንደሚውሉ ሲያሳውቁን አበቅቴ ደግሞ ሠርቀ ወርኅ እና ሠርቀ ሌሊትን ለማግኘት ይጠቅመናል።

© ሠርቀ መዓልት የሚባለው ራሱ ቀኑ ነው።ለምሳሌ የመስከረም 1 ሠርቀ መዓልት ራሱ 1 ነው።
© ሠርቀ ሌሊት=አበቅቴ+ሠርቀ መዓልት+ሕፀፅ
=17+1+1
=19
© ሠርቀ ወርኅ=ሠርቀ ሌሊት+4
=19+4
=23
ሕጸጽ ያልነው።
የመስከረምና የጥቅምት 1
የህዳርና የታህሳስ 2
የጥር እና የየካቲት 3
የመጋቢት እና የሚያዝያ 4
የግንቦትና የሰኔ 5
የሐምሌ እና የነሐሴ 6 ነው

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 8
የበዓላትና የአጽዋማት ተውሳክ።መባጃ ሐመር 15 እንደመጣ ክፍል 7 ላይ አይተናል።ይኽውም የካቲት 15 ቀን የነነዌ ጾም ትገባለች ማለት ነው።ሌሎቹ መቼ እንደሚውሉ ለማወቅ ይህን መባጃ ሐመር ከተውሳኮቻቸው ጋር እየደመርን እናገኘዋለን።የአጽዋማትና የበዓላት ተውሳክ እነሆ
የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14
የደብረ ዘይት ተውሳክ 11
የሆሳእና ተውሳክ 2
የስቅለት ተውሳክ 7
የትንሳኤ ተውሳክ 9
የርክበ ካህናት ተውሳክ 3
የዕርገት ተውሳክ 18
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28
የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29
የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1
ነው።ስለዚህ እኒህን ተውሳኮች ከመባጃ ሐመሩ ጋር እየደመርን በአላቱ አጽዋማቱ መቼ እንደሚውሉ ያሳውቁናል።ስለዚህ
ዐቢይ ጾም=14+መባጃ ሐመር
=14+15
=29
ስለዚህ ዓቢይ ጾም የካቲት 29 ይውላል ማለት ነው።መጥቅእ ጥቅምት ውሎ ስንደምረው ከ30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን መጋቢት ላይ ይውላል።በ2013 ዐቢይ ጾም የካቲት 29 ይውላል።
ደብረ ዘይት=11+መባጃ ሐመር
=11+15
=26
መጋቢት 26 ደብረ ዘይት ይውላል ማለት ነው።መጥቅእ ጥቅምት ውሎ ይህ ድምር ከ30 ከፍ ካለ ግን በ30 ገድፈን ሆሳእና ሚያዝያ ላይ ይውላል ማለት ነው።
ሆሣዕና=2+መባጃ ሐመር
=2+15
=17
ሚያዝያ 17 ሆሳእና ይውላል ማለት ነው።
ስቅለት=7+መባጃ ሐመር
=7+15
=22
ሚያዝያ 22 ስቅለት ይውላል ማለት ነው
ትንሳኤ=9+መባጃ ሐመር
=9+15
=24
ሚያዝያ 24 ትንሳኤ ይውላል ማለት ነው።
ርክበ ካህናት=3+መባጃ ሐመር
=3+15
=18
ግንቦት 18 ቀን ርክበ ካህናት ይሆናል ማለት ነው
ዕርገት=18+መባጃ ሐመር
=18+15
=33
33 ከ30 በላይ ስለሆነ በ30 ስንከፍለው አንድ ደርሶ 3 ይተርፋል።ይህም ዕርገት ሰኔ 3 ይሆናል ማለት ነው።ከ30 በላይ ባይሆን ግንቦት ላይ ይውል ነበር።
ጰራቅሊጦስ=28+መባጃ ሐመር
=28+15
=43
ይህ ከ30 በላይ ስለሆነ በ30 ስናካፍለው 1 ደርሶ 13 ይተርፋል።ስለዚህ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 13 ይውላል ማለት ነው።ደምረነው ከ30 በላይ ካልሆነ በግንቦት ይውላል።
ጾመ ሐዋርያት=29+መባጃ ሐመር
=29+15
=44
ይሆናል በ30 ስንገድፈው 1 ጊዜ ደርሶ 14 ይተርፋል።ስለዚህ ሰኔ 14 ጾመ ሐዋርያት ይገባል ማለት ነው።ከ30 በታች ቢሆን ኖሮ ግንቦት ላይ ይውል ነበር።
ጾመ ድኅነት=1+መባጃ ሐመር
=1+15
=16
ስለዚህ ጾመ ድኅነት ሰኔ 16 ይጀምራል ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ ክፍል 9
©® ኢየዐርግ እና ኢይወርድ ©®
እነዚህ በዓላት ኢየዐርግ (አይወጣም) እና ኢይወርድ (አይወርድም) አላቸው ለምሳሌ የነነዌ ጾም ቢወርድ ቢወርድ ጥር 17 ይሆናል እንጂ ጥር 16 አይሆንም።እንዲሁም ቢወጣ ቢወጣ የካቲት 21 ይሆናል እንጂ የካቲት 22 ሊሆን አይችልም።ይህ ማለት የነነዌ ጾም ከጥር 17 እስከ የካቲት 21 ባለው ብቻ ይውላል ማለት ነው።በዚህ መሰረት የሌሎችንም እንመልከት
ኢይወርድ.......ኢየዐርግ
የነነዌ ጾም.............ጥር 17........የካቲት 21
ዓቢይ ጾም..............የካቲት 1......መጋቢት 5
ደብረ ዘይት.............የካቲት 28....ሚያዝያ 2
ሆሳእና....................መጋቢት 19...ሚያዝያ 23
ስቅለት...................መጋቢት 24....ሚያዝያ 28
ትንሳኤ..................መጋቢት 26.....ሚያዝያ 30
ርክበ ካህናት.........ሚያዝያ 20.......ግንቦት 24
ዕርገት..................ግንቦት 5..........ሰኔ 9
ጰራቅሊጦስ............ግንቦት 15.......ሰኔ 19
ጾመ ሐዋርያት...........ግንቦት 16.......ሰኔ 20
ጾመ ድኅነት.............ግንቦት 18..........ሰኔ 22
የበዓላትና የአጽዋማት ኢየዐርግና ኢይወርድ ይህንን ይመስላል።

በነገራችን ላይ የእኛ የዘመን መለወጫ መስከረም 1 ቀን ነው።እስራኤላውያንን በኦሪት እንደተጻፈው ጌታ ከግብጽ የወጣችሁበት ወር ሚያዝያ የዘመን መለወጫ ይሁናችሁ ብሏቸዋል።በእስራኤል ጥር የካቲት መጋቢት ክረምት ነው።ሚያዝያ የክረምት መውጫ ነው።የእኛ ክረምት ግን ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ ነው።ክረምት የሚወጣበት መስከረም ስለሆነ የዘመን መለወጫችን መስከረም ነው።በነገራችን ላይ እስራኤል ከግብጽ ከመውጣታቸው ዘመን የሚቆጥሩት ከጥቅምት ጀምረው እንደሆነና የዘመን መለወጫቸው ጥቅምት እንደነበረ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ጽፈዋል።ፈረንጆቹ ደግሞ ጌታ የተወለደበትን ታህሣስ 29 ጀምረው ዘመንን ይለውጣሉ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ባሕረ ሐሳብ 10
©የዘመን መለወጫ መስከረም ወይስ ጥር©
በነገራችን ላይ የእኛ የዘመን መለወጫ መስከረም 1 ቀን ነው።እስራኤላውያንን በኦሪት እንደተጻፈው ጌታ ከግብጽ የወጣችሁበት ወር ሚያዝያ የዘመን መለወጫ ይሁናችሁ ብሏቸዋል።በእስራኤል ጥር የካቲት መጋቢት ክረምት ነው።ሚያዝያ የክረምት መውጫ ነው።የእኛ ክረምት ግን ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ ነው። ክረምት የሚወጣበት መስከረም ስለሆነ
የዘመን መለወጫችን መስከረም ነው።ፈረንጆቹ ደግሞ ጌታ የተወለደበትን ታህሣስ 29 ጀምረው ዘመንን ይለውጣሉ። ያም ሆነ ይህ በአቡሻኽር ትምህርት እንደምናገኘው በዓለም ላይ በጣም ብዙ የዘመን አቆጣጠሮች አሉ።ስለዚህ የሁሉንም ከመቀበል ውጭ ይህ ስህተት ነው ይህ ልክ ነው ማለት አንችልም።ጌታ ግን የዘመን መለወጫ በሚያዝያ ይሁን ብሎ ስለዘመን መለወጫ የተናገረው ብቸኛው ቃል በኦሪት ይገኛል።
ይህ ሁሉ መደከሙ የዘመናትን ባለቤት እግዚአብሔርን ዘመኑን እያስታወስን ለማመስገን (ለአሥርቆት) ነው።ሁልጊዜ ቢሆን ጸሎታችንን የምንጀምረው ከዚህ በኋላ በሚገኘው መንገድ ነው።ውዳሴ ማርያምም ይሁን ሌላ ጸሎት ከአሥርቆት በኋላ ነው።አሥርቆቱም ይህ ነው።
ሃሌ ሉያ በዘንዜከር ሐሳባተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሳበ ነቢያት ወሐዋርያት ሐሳበ ጻድቃን ወሰማእት ሐሳበ ደናግል ወመነኮሳት ሐሳበ ኄራን መላእክት እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ (አስተውል ማቴዎስ ጸሎት እያደረግክበት ያለው ዘመን ነው) ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ማርቆስ ዜናዊ።ካልክ በኋላ ያለህበትን ዘመን ዓመተ ምህረት ዓመተ ዓለም አስበህ በ፸፻ወ፭፻፲፫ ኮነ ዓመተ ዓለም።በ፶፻ወ፭፻ ኮነ ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ።በ፳፩፲፫ ኮነ ዓመተ ምሕረት።ትልና በመቀጠል ያለህበትን ወር አንስተህ ለቀጣዩ ወር በሰላም ያድርሰኝ ለማለት ዮም ሠረቀ ለነ ወርኀ መስከረም (በመስከረም ወር ከሆነ እየጸለይክ ያለኽው) ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኀ ጥቅምት በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን ትላለህ።በመቀጠል የእለቱ ሠርቀ መዓልት ሠርቀ ሌሊት እና ሠርቀ ወርኅ አስበህ እንዲህ ትላለህ።መስከረም 1 ላይ ከሆነ እየጸለይክ ያለኽው አሚሩ (፩) ሠርቀ መዓልት። አሡሩ ወተሱኡ (፲፱) ሠርቀ ሌሊት (19ኝን ያገኘነው አበቅቴ+ሠርቀ መዓልት+ሕጸጽ አድርገን ነው) እሥራ ወሠሉሱ (፳፫) ሠርቀ ወርኅ።ሠርቀ ወርኅን ያገኘነው ሠርቀ ሌሊት ላይ 4 በመጨመር ነው።ከዚያ እየጸለይክ ያለኽው ረቡእ ከሆነ አሚሩ ጥንተ ዖን ረቡዑ ሠርቀ ዕለት ሰቡኡ ጥንተ ቀመር ብለህ ዝ ጸሎት ወዝ አስተብቁዖት ይዕርግ በእንተ ስመ አብ ወበእንተ ተዝካረ ወልዱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ስሙ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ወበእንተ ስማ ለእግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ አሜን ብለን እንጨርስና ይህም ጸሎት ነው ከዚያ ወደ ሌላው ጸሎት እንገባለን ማለት ነው።የምትጸልየው
ረቡእ ከሆነ ጥንተ ዖን 1 ጥንተ ቀመር 2 ጥንተ ዕለት 4 ይሆናል።
ሐሙስ ከሆነ ጥንተ ዖን 2 ጥንተ ቀመር 3 ጥንተ ዕለት 5 ይሆናል።
አርብ ከሆነ ጥንተ ዖን 3 ጥንተ ቀመር 4 ጥንተ እለት 6 ይሆናል።
ቅዳሜ ከሆነ ጥንተ ዖን 4 ጥንተ ቀመር 5 ጥንተ እለት 7 ይሆናል።
እሑድ ከሆነ ጥንተ ዖን 5 ጥንተ ቀመር 6 ጥንተ እለት 1 ይሆናል።
ሰኞ ከሆነ ጥንተ ዖን 6 ጥንተ ቀመር 7 ጥንተ እለት 2 ይሆናል።
ማክሰኞ ከሆነ ጥንተ ዖን 7 ጥንተ ቀመር 1 ጥንተ እለት 3 ይሆናል።
በዚህ መሰረት ዘመኑን እያስታወስን እግዚአብሔርን እያመሰገንን እንኖራለን።

አነሳስቶ ላስጀመረን
አስጀምሮ ላስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይገባል
አሜን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
Photo
1ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው።
17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
25 ሰናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
26 ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
27 መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
28 መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
29 ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
30 ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
31 ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
32 ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
33 ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
34 ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
35 አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
36 ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
37 ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
38 ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
39 ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
40 ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።
41 አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
42 ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
43 ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
44 ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
45 ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
46 ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
47 ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
48 ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
49 በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
50 መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
51 ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
52 ትንሳኤ፦መነሳት ማለት ነው።
53 ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
54 ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
55 ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
56 ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
57 ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
58 ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
59 ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
60 መርአዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርአዊት ለሴት ነው።
61 ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
62 ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
63 ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
64 ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
65 ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
66 ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
67 ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
68 ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
69 ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
70 ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
71 ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
72 መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
73 ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
74 ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
75 ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
76 ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
77 አማን፦እውነት ማለት ነው።
78 አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
79 ተንከተም፦ድልድይ ማለት ነው። ሰዋስው መሰላል ነው።
80 ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈


በቀጣይ የግእዝ ትምሀርት በአዲስ መልኩ በአዲስ ክፍል እንቀጥላለን‼️ ሼር በማድረግ ለሁሉም ተደራሽነቱን እናስፋ ‼️ በጽሑፍ እና በድምፅ ሪከርድ እንገናኛለን‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 1🌹
የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቁጥር አለው።ዛሬ ከ1 እስከ 100 ያሉ ቁጥሮችን እንመለከታለን።የአማርኛ ቁጥሮች ከአረብኛ የመጡ ናቸው።

አማርኛ ግእዝ ሲነበብ English
1 ፩ አሐዱ One
2 ፪ ክልኤቱ Two
3 ፫ ሠለስቱ Three
4 ፬ አርባዕቱ Four
5 ፭ ኀመስቱ Five
6 ፮ ስድስቱ Six
7 ፯ ሰብዓቱ Seven
8 ፰ ሰመንቱ Eight
9 ፱ ተሰዓቱ Nine
10 ፲ አሠርቱ Ten
20 ፳ ዕሥራ Twenty
30 ፴ ሠላሳ Thirty
40 ፵ አርብዓ Forty
50 ፶ ኀምሳ Fifty
60 ፷ ስድሳ Sixty
70 ፸ ሰብዓ Seventy
80 ፹ ሰማንያ Eighty
90 ፺ ተስዓ Ninety
100 ፻ ምእት Hundred

የግእዝ መስራች ቁጥሮች እኒህ ናቸው።ሌላው ቁጥር እነዚህን መሠረት አድርጎ ነው የሚጻፈው።ምሳሌ 16ን በግእዝ ለመጻፍ ከፈለግን እንተነትነዋለን ማለት 10+6 እናደርገውና በግእዝ እንለውጠዋለን ይኽውም ፲+፮=፲፮ ይሆናል ሲነበብ አሠርቱ ወስድስቱ ይሆናል ማለት ነው።ሌላ ምሳሌዎችንም ቀጥለን እንመልከት።

1, 48=40+8=፵+፰=፵፰
በአማርኛ፦አርባ ስምንት።
በግእዝ፦አርብዓ ወሰመንቱ።
English፦Forty eight.
2 74=70+4=፸+፬=፸፬
በግእዝ፦ሰብዓ ወአርባዕቱ።
በአማርኛ፦ሰባ አራት።
English፦Seventy four.
3 99=90+9=፺+፱=፺፱
በግእዝ፦ተስዓ ወተስዓቱ።
በአማርኛ፦ዘጠና ዘጠኝ።
English፦Ninety Nine.

ሌሎችንም ቁጥሮች በዚህ መልኩ መመሥረት ትችላላችሁ።አስተውሉ በመደመሩ ምትክ "ወ"ን አስገብተን ተናግረናል። በሚቀጥለው ክፍል ከ100 በላይ ያለውን ቁጥር እናያለን እዚህ ላይ ግልጽ ያልሆነ ካለ በአስተያየት መስጫው መጠየቅ ይቻላል።

#መልመጃ
የማከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ቁጥር ለውጡ።የለወጣችሁትንም በንባብ አስቀምጡ።
1, 44
2, 68
3, 83
4, 21
5, 39
የሚከተሉትን የግእዝ ቁጥሮች ወደ አማርኛ ለውጡ
6,፹፫
7, ፷፩
8, ፶፱
9, ፸፰
10, ፲፭

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ሁለት ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
ግእዝ ክፍል-፩ ቁጥር

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ሁለት ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 2(፪)
🌹


ክፍል 2 እና ክፍል 3 ሊከብዷችሁ ይችላሉ። ቁጥር ስለሆነ ታላላቅ መምህራንም ይቸገሩባቸዋል። በተለይ ነገ የምለቀው ክፍል ሦስት በጣም ሊከብዳችሁ ይችላል። ከክፍል አራት ጀምሮ ቀለል ስለሚል በዚህ ተስፋ ቆርጣችሁ እንዳትጠፉ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ።
አማርኛ ግእዙ ንባቡ
100 ፻ ምእት
10000 ፼ እልፍ
100000 ፲፼ አእላፍ
1000000 ፻፼ አእላፋት
10000000 ፲፻፼ ትእልፊት
100000000 ፼፼ ትእልፊታት
1000000000 ፲፼፼ ምእልፊት
10000000000፻፼፼ ምእልፊታት

እንግሊዘኛው ከላይ ወደታች በቅደም ተከተል one hundred, ten thousand, one hundred thousand, one million, ten million, one hunderd million, one billion, ten billion ነው።

በእነዚህ መካከል ያሉ ቁጥሮችን ለማወቅና ለመጻፍ የመደመር እና የማባዛት ምልክትን ተጠቅመን ቁጥሩን ተንትነን ማወቅ እንችላለን። ለምሳሌ 108 በግእዝ ለመጻፍ 100+8 ነው።፻+፰=፻፰ ምእት ወሰመንቱ ይላል። 208ን በግእዝ ለመጻፍ ደግሞ 2*100+8=፪*፻+፰=፪፻፰ ክልኤቱ ምእት ወሰመንቱ ይላል ማለት ነው። በእንደዚህ ዓይነት ስሌት የመጨረሻውን መደመር "ወ" ብለን እያስገባን ማንበብ እንችላለን ማለት ነው።ጉዳዩን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ያህል።የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንመልከት።

456=4*100+50+6=፬*፻+፶+፮=፬፻፶፮
በአማርኛ፦አራት መቶ ሃምሳ ስድስት
በግእዝ፦አርባዕቱ ምእት ኀምሳ ወስድስቱ።
English፦Four hundred fifty six.

999=9*100+90+9=፱*፻+፺+፱=፱፻፺፱
በአማርኛ፦ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ።
በግእዝ፦ተስዓቱ ምእት ተስዓ ወተስዓቱ።
English፦ Nine hundred ninety nine.

1000=10*100=፲*፻=፲፻
በአማርኛ፦አንድ ሺህ
በግእዝ፦አሠርቱ ምእት
English፦One thousand.

2589=25*100+80+9=፳፭*፻+፹+፱=፳፭፻፹፱
በአማርኛ፦ሁለት ሺ አምስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ።
በግእዝ፦እሥራ ወኀምስቱ ምእት ሰማንያ ወተስዓቱ።
English፦Two thousand five hundred eighty nine.

7832=78*100+30+2=፸፰*፻+፴+፪=፸፰፻፴፪
በአማርኛ፦ሰባት ሺ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት።
በግእዝ፦ሰብዓ ወሰመንቱ ምእት ሠላሳ ወክልኤቱ።
English፦Seven thousand eight hundred thirty two.

10757=10000+7*100+50+7=፼+፯*፻+፶+፯=፼፯፻፶፯
በአማርኛ፦አሥር ሺ ሰባት መቶ አምሳ ሰባት
በግእዝ፦እልፍ ወሰብዓቱ ምእት ኃምሳ ወሰብዓቱ።
English፦ten thousand seven hundred fifty seven.

92983=9*10000+29*100+80+3=፱*፼+፳፱*፻+፹+፫=፱፼፳፱፻፹፫
በአማርኛ፦ዘጠና ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሦስት
በግእዝ፦ተስዓቱ እልፍ እሥራ ወተስዓቱ ምእት ሰማንያ ወሠለስቱ
English፦Ninety T
two thousand nine hundred eighty three.

874937=87*10000+49*100+30+7=፹፯*፼+፵፱*፻+፴+፯=፹፯፼፵፱፴፯
በአማርኛ፦ስምንት መቶ ሰባ አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ሰባት
በግእዝ፦ሰማንያ ወሰብዓቱ እልፍ አርብዓ ወተስዓቱ ምእት ሠላሳ ወሰብዓቱ።
English፦Eight hundred seventy three thousand nine hundred thirty seven.

.
ጥያቄ
የሚከተሉትን ቁጥሮች ከነንባባቸው ወደ ግእዝ ለውጥ።
1, 8934
2, 44444
3. 572483


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፫ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
2024/10/01 19:24:57
Back to Top
HTML Embed Code: