Telegram Web Link
ግእዝ ክፍል-፪ ቁጥር

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፫ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 3 🌹
5458235=5*1000000+45*10000+82*100+30+5=፭*፻፼+፵፭*፼+፹፪*፻+፴+፭=፭፻፼፵፭፼፹፪፻፴፭።
አማርኛ፦አምስት ሚልየን አራት መቶ አምሳ ስምንት ሺ ሁለት መቶ ሠላሳ አምስት።
ግእዝ፦ኀምስቱ አእላፋት አርብዓ ወኀምስቱ እልፍ ሰማንያ ወክልኤቱ ምእት ሠላሳ ወኀምስቱ።
English፦Five Million four hundred fifty eight thousand two hundred thirty five.

99999999=99*1000000+99*10000+99*100+90+9=፺፱*፻፼+፺፱*፼+፺፱*፻+፺+፱=፺፱፼፻፺፱፼፺፱፻፺፱
በአማርኛ፦ዘጠና ዘጠኝ ሚልየን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ።
በግእዝ፦ተስዓ ወተስዓቱ አእላፋት ተስዓ ወተስዓቱ እልፍ ተስዓ ወተሰዓቱ ምእት ተስዓ ወተስዓቱ።
English፦Ninety nine million nine hundred ninety nine thousand nine hundred ninety nine.

456346274=4*100000000+56*1000000+34*10000+62*100+70+4=፬*፼፼+፶፮*፻፼+፴፬*፼+፷፪*፻+፸+፬=፬፼፼፶፮፼፻፴፬፼፷፪፻፸፬
በአማርኛ፦አራት መቶ አምሳ ስድስት ሚልየን ሦስት መቶ አርባ ስድስት ሺ ሁለት መቶ ሰባ አራት።
English፦Four hundred fifty six million Three hundred forty six thousand two hundred seventy four.
በግእዝ፦አርባዕቱ ትእልፊታት ኀምሳ ወስድስቱ አእላፋት ሠላሳ ወአርባዕቱ እልፍ ስድሳ ወክልኤቱ ምእት ሰብዓ ወአርባዕቱ።

9218946935=92*100000000+18*1000000+94*10000+69*100+30+5=፺፪፼፼+፲፰፻፼+፺፬፼+፷፱፻+፴+፭=፺፪፼፼፲፰፼፺፺፬፼፷፱፻፴፭
በአማርኛ ዘጠኝ ቢልየን ሁለት መቶ አስራ ስምንት ሚልየን ዘጠኝ መቶ አርባ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ አምስት።
English፦Nine billion two hundred eighteen million nine hundred forty six thousand nine hundred thirty five.
ግእዝ፦ተስዓ ወክልኤቱ ትእልፊታት አሠርቱ ወሰመንቱ አእላፋት ተስዓ ወአርባዕቱ እልፍ ስድሳ ወተስዓቱ ምእት ሠላሳ ወኀምስቱ።

494853921456=49*10000000000+48*100000000+53*1000000+92*10000+14*100+50+6=፱*፼፼፻+፵፰*፼፼+፶፫*፼፻+፺፪*፼+፲፬*፻+፶+፮=፱፼፼፻፵፰፼፼፶፫፼፻፺፪፼፲፬፻፶፮
በአማርኛ፦አራት መቶ ዘጠና አራት ቢልየን ስምንት መቶ አምሳ ሦስት ሚልየን ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ ሺ አራት መቶ አምሳ ስድስት።
English፦four hundred Ninety four billion eight hundred fifty three million nine hundred twenty one thousand four hundred fify six.
በግእዝ፦አርብዓ ወተስዓቱ ምእልፊታት አርብዓ ወሰመንቱ ትእልፊታት ኃምሳ ወሠለስቱ አእላፋት ተስዓ ወክልኤቱ እልፍ አሠርቱ ወአርባዕቱ ምእት ኃምሳ ወስድስቱ።

እንዲህ እንዲህ እያልን እስገፈለገን ድረስ መቁጠር እንችላለን።

ጥያቄ፦
የሚከተሉትን ቁጥሮች ከነንባባቸው ወደ ግእዝ ለውጥ፦
1, 8943289
2, 33678392
3, 892836163949


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 4🌹
ግእዝ ቋንቋን ለመረዳት የሚያገለግሉን 10 መራሕያን አሉ። ዛሬ እነርሱን እንመለከታለን።
ግእዝ አማርኛ English
1 ውእቱ እርሱ He
2 ይእቲ እርሷ She
3 ውእቶሙ እነርሱ They
4 ውእቶን እነርሱ (ሴ) They
5 አንተ አንተ You
6 አንቲ አንቺ You
7 አንትሙ እናንተ You
8 አንትን እናንተ (ሴ) You
9 አነ እኔ I
10 ንሕነ እኛ We

ከዚህ በላይ ያለው ትርጉማቸው እንደ የስም ምትክ ወይም ተውላጠ ስም (Pronoun) ሆነው ሲያገለግሉ ነው።ለምሳሌ ድንግል ማርያምን እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ሲል ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ይላል። መራሕያን የስም ምትክ ሆነው ሲያገለግሉ ከማሰሪያ አንቀጽ (Verb) በፊት መምጣት አለባቸው።ከማሰሪያ አንቀጽ በፊት ከመጡ የሚፈቱት ከላይ ባለው አፈታት ነው።መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ ወይም ረዳት ግስ (Auxilary verb) ያገለግላሉ። ሲያገለግሉም ያላቸው ትርጉም እንደሚከተለው ነው።
ግእዝ አማርኛ English
1 ውእቱ ነው፥አለ፥ነበረ Is, Be, was
2 ይእቲ ናት፥አለች፥ነበረች Is, Be, Was
3 ውእቶሙ ናቸው፥አሉ፥ነበሩ are, be, were
4 ውእቶን ናቸው፥አሉ፥ነበሩ are, be, were
5 አንተ ነህ፥አለህ፥ነበርክ are, be, were
6 አንቲ ነሽ፥አለሽ፥ነበርሽ are, be, were
7 አንትሙ ናችሁ፥አላችሁ፥ነበራችሁ are, be, were
8 አንትን ናችሁ፥አላችሁ፥ነበራችሁ are,be,were
9 አነ ነኝ፥ነበርኩ፥አለሁ am,be,was
10 ንሕነ ነን፥ነበርን፥አለን are,be, were

መራሕያን ነባር አንቀጽ ሆነው ሲያገለግሉ ከስም በኋላ ወይም ከዓረፍተ ነገር በኋላ ይመጣሉ። ለምሳሌ በመጀመሪያ ቃል ነበር የሚለው ቃል በግእዝ ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ይላል። ውእቱ ቃል ከሚለው ስም በኋላ ስለመጣ የሚኖረው ትርጉም "እርሱ" የሚል ሳይሆን "ነው ወይም ነበረ" የሚል ይሆናል። ሌላው መራሕያን እንደ አመልካች ቅጽል "Demonstrative pronoun" ሆነው ያገለግላሉ። ሲያገለግሉም የሚኖራቸው ትርጉም እንደሚከተለው ነው።
ግእዝ አማርኛ
1 ውእቱ ያ
2 ይእቲ ያች
3 ውእቶሙ እነዚያ
4 ውእቶን እነዚያ
5 አንተ አንተ
6 አንቲ አንቺ
7 አንትሙ እናንተ
8 አንትን እናንተ
9 አነ እኔ
10 ንሕነ እኛ
መራሕያን አመልካች ቅጽል ሆነው ሲያገለግሉ ከስም በፊት መምጣት አለባቸው።ለምሳሌ ያ ቃል ሥጋ ሆነ ዮሐ.1፥14 የሚለው በግእዝ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ይላል።አስተውል "ያ" ተብሎ የተተረጎመው "ውእቱ" ነው። ምክንያቱም ቃል ከሚለው ስም በፊት ስለመጣ ነው።ስለዚህ መራሕያን በዓረፍተ ነገር ውስጥ ተጽፈው ስናገኛቸው በየትኛው መተርጎም እንደሚገባቸው ማስተዋል አለብን። በግእዝ ሴቶችን እናንተ ስንልና ወንዶችን እናንተ ስንል የተለያየ ነው።ሴቶችን አንትን ወንዶችን አንትሙ እንላለን። ሴቶች እና ወንዶች ተቀላቅለው ካሉ ደግሞ አንትሙ እንላለን። እነርሱ ስንልም ለሴቶች ውእቶን ስንል ለወንዶች ውእቶሙ እንላለን። ውእቶሙ እና እሙንቱ ትርጓማቸው አንድ ነው። ውእቶንና እማንቱ ትርጉማቸው አንድ ነው።

ሌላው መራሕያን ተከታትለው ሲመጡ የመጀመሪያው የስም ምትክ ሆኖ ያገለግላል። ቀጥሎ ያለው ደግሞ ነባር አንቀጽ ሆኖ ያገለግላል።ለምሳሌ አንትሙ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም ቢል።አንትሙ እና ውእቱ ተከታትለው መጥተዋል ስለዚህ አንትሙ በስም ምትክ እናንተ ተብሎ ይተረጎማል ውእቱ ደግሞ በነባር አንቀጽ "ናችሁ" ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ተብሎ ይተረጎማል። ውእቱ በነባር አንቀጽነቱ እንደ 9ኙም ይተረጎማል። ያ ማለት ናችሁ ነኝ ነን ነሽ ወዘተ እያለ ይተረጎማል።

አነ እና ንሕነ አንደኛ መደብ ይባላሉ። አንተ፣ አንትሙ፣ አንቲ፣ አንትን ደግሞ ሁለተኛ መደቦች ይባላሉ። ውእቱ፣ ውእቶሙ፣ ውእቶን፣ ይእቲ ደግሞ ሦስተኛ መደብ ይባላሉ። በሌላ አከፋፈል አንተ፣ አንትሙ፣ ውእቱ እና ውእቶሙ የወንድ ናቸው። አንቲ፥ ይእቲ፣ ውእቶን እና አንትን የሴት ናቸው።አነ እና ንሕነ ለሴትም ለወንድም ይሆናሉ።በሌላ አገላለጽ ደግሞ አነ፣ ውእቱ፣ ይእቲ፣ አንተ እና አንቲ ነጠላ "Singular" ናቸው። "አንትሙ፣ አንትን፣ ውእቶሙ፣ ንሕነ እና ውእቶን ደግሞ" ብዙ "Plurals" ናቸው።

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ ተርጉም፥የመራሕያኑ አገልፍሎትም ምን እንደሆነ ግለጥ።
1 ይእቲ ማርያም ታፈቅረነ (hint;ታፈቅረነ ያለው ትወደናለች ማለት ነው)
2 እግዚአብሔር ውእቱ ብርሃንኪ (hint;ብርሃንኪ ያለው ብርሃንሽ ማለት ነው)
3 ውእቱ ፈጠረነ (hint;ፈጠረነ ያለው ፈጠረን ማለት ነው)
4 አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም።
5 ሀገርነ በሰማይ ውእቱ።
ግእዝ ክፍል-፬

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፭ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 5 <፭>🌹
ድርብ መራሕያን እና ተሳቢ መራሕያን
ግእዝ አማርኛ English
1 ኪያሁ እርሱን Him
2 ኪያሃ እርሷን Her
3 ኪያሆሙ እነርሱን Them
4 ኪያሆን (ሴ) እነርሱን Them
5 ኪያከ አንተን You
6 ኪያኪ አንቺን You
7 ኪያክሙ እናንተን You
8 ኪያክን(ሴ) እናንተን You
9 ኪያየ እኔን Me
10 ኪያነ እኛን Us

በዓረፍተ ነገር እንደሚከተለው እንጠቀማቸዋለን።
አማርኛ፦እኔ እናንተን እወዳችኋሁ
English; I Love You
ግእዝ፦አነ አፈቅር ኪያክሙ
እንዲህ እንዲህ እያለ ይተረጎማል ማለት ነው። ቀጥለን ደግሞ ድርብ መራሕያንን እንመልከት፦
ግእዝ አማርኛ English
1 ለሊሁ እርሱ ራሱ Himself
2 ሊሊሃ እርሷ ራሷ Herself
3 ለሊሆሙ እነርሱ ራሳቸው Themselves
4 ለሊሆን (ሴ) እነርሱ ራሳቸው Themselves
5 ለሊከ አንተ ራስህ yourself
6 ለሊኪ አንቺ ራስሽ yourself
7 ለሊክሙ እናንተ ራሳችሁ yourselves
8 ለሊክን(ሴ) እናንተ ራሳችሁ yourselves
9 ለልየ እኔ ራሴ myself
10 ለሊነ እኛ ራሳችን ourselves
በዓረፍተ ነገርም እንደሚከተለው ይቀርባሉ።
በአማርኛ፦እኛ ራሳችን እንሞታለን
በግእዝ፦ለሊነ ንመውት
English:We ourselves will die.
እንዲህ እንዲህ እያለ ይተረጎማል ማለት ነው።

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉሙ።
1 ኪያከ እግዚኦ ነአኩት (hint; እግዚኦ፡አቤቱ፤ነአኩት፡እናመሰግናለን)
2 ክርስቶስ አፍቀረ ኪያነ
3 እኛ ራሳችን እናውቃለን (እናውቃለን፡ነአምር)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፮ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
ግእዝ ክፍል-፭

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፮ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 6 [፮]🌹
በኑሯችን አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀማቸውን ቃላት በግእዝ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
ግእዝ አማርኛ English
1 ዝንቱ/ዝ ይህ This
2 ዛቲ/ዛ ይች This
3 ዝኲ/ዝክቱ/ዝስኩ ያ That
4 እልክቱ እኒያ Those
5 እንትኲ/እንታክቲ ያች That
6 እልኲ(ሴ) እኒያ Those
7 እሉ/እሎንቱ እኒህ These
8 እላ/እላንቱ/እሎን(ሴ) እኒህ These
በግእዝ ሴቶችን እኒያ ስንልና ወንዶችን እኒያ ስንል የተለይየ ስለሆነ የሴቶችን "ሴ" ብየ ገልጨዋለሁ።ሌላው በግእዝ ቋንቋ ገንዘብነት የሚገልጹ ቃላት አሉ። እነርሱን ከዚህ ቀጥየ እጽፋቸዋለሁ።
ግእዝ አማርኛ English
1 ዚኣየ የእኔ my/mine
2 ዚኣነ የእኛ our/ours
3 ዚኣከ የአንተ your/yours
4 ዚኣኪ የአንቺ your/yours
5 ዚኣክሙ የእናንተ your/yours
6 ዚኣክን(ሴ) የእናንተ your/yours
7 ዚኣሁ የእርሱ his
8 ዚኣሃ የእርሷ her
9 ዚኣሆሙ የእነርሱ their/theirs
10 ዚኣሆን(ሴ) የእነርሱ their/theirs
እኒህን በምሳሌ እንደሚከተለው እንመልከት።

አማርኛ፦ይህ መጽሐፍ የእኔ ነው።
ግእዝ፦ዝንቱ መጽሐፍ ዚኣየ ውእቱ።
English:This book is mine

አማርኛ፦ኢትዮጵያ የእኛ ናት
ግእዝ፦ዚኣነ ይእቲ ኢትዮጵያ
English: Ethiopia is Ours

አማርኛ፦እነዚያ ሴቶች ቅዱሳት ናቸው።
ግእዝ፦እልኲ አእኑስ ቅዱሳት እማንቱ።
English፦Those women are Saints.

አማርኛ፦የእኛ ወንዝ ዓባይ ነው።
ግእዝ፦ፈለገዚኣነ ውእቱ ግዮን።
English፦Ghion Is our river.

አማርኛ፦የእኔ ንጉሥ እግዚአብሔር ነው።
ግእዝ፦እግዚአብሔር ውእቱ ንጉሠ ዚኣየ።
English፦My king is God

ጥያቄ
የሚከተሉትን የግእዝ ዓረፍተ ነገሮች ወደ አማርኛ አማርኛውን ደግሞ ወደ ግእዝ ተርጉሙ።

1, እነዚያ ሰዎች ዘመዶቻችን ናቸው። (hint:ሰው፦ሰብእ፤ዘመዶቻችን፦አዝማዲነ)
2,ዛቲ አንቀጽ ጸባብ ይእቲ።(አንቀጽ፦በር)
3, ዚኣነ ውእቱ ክርስቶስ

እንደ ዚኣነ የሚተረጎም እንቲኣነ ነው። እንቲኣሁ እንቲኣሃ እንቲኣሆሙ እንቲኣሆን እንቲኣከ እንቲኣክሙ እንቲአኪ እንቲኣክን እንቲኣየ እንቲኣነ ይላል።እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል እንዲል።ረድኤተ እግዚኣብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፯ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
ግእዝ ክፍል-፮

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፯ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 7 (፯)🌹
ሥርዓተ ንባብ
አነባበቡን በቴሌግራም በኦድዮ ስለምለቀው ከዚያ መመልከት ይቻላል።ሕጎቹን ግን ከዚህ ተመልከቱ። የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ አለው።ተነስቶ የሚነበበውን ጥለን ካነበብነው የትርጉም ለውጥ ያመጣል።ለምሳሌ "አእመራ" የሚለውን ቃል አንስተን ስናነበውና በወዳቂ ንባብ ስናነበው የተለያየ ትርጉም አለው። አንስተን ስናነበው እነዚያ ሴቶች አወቁ ማለት ነው። በወዳቂ ንባብ ስናነበው ደግሞ ያ ሰው ያችን ሴት አወቃት ተብሎ ይተረጎማል።ተነሽና ሰያፍ ንባባት ቆጣ ብለው ይነበባሉ። ወዳቂና ተጣይ ንባባት ደግሞ ሰከን ብለው ይነበባሉ። በጠቅላላው በግእዝ ቋንቋ አራት ዓይነት የንባብ ዓይነቶች አሉ።እነዚህም፦
1 ተነሽ ንባብ
2 ወዳቂ ንባብ
3 ሰያፍ ንባብ
4 ተጣይ ንባብ
ናቸው።አንድ ቃል ከአራቱ በየትኛው እንደሚነበብ ለማወቅ የሚረዱን ሁለት መሠረታዊ መለኪያዎች አሉን።እነዚህም፦
1 የቃል ክፍሉ
2 የቃሉ መድረሻ ፊደል
ናቸው።የቃል ክፍሉ ያልነው አንዱ ግሥ (Verb) ሲሆን ሁለተ ኛው ደግሞ ከግሥ ውጭ ያሉ ቃላት ናቸው።ስለዚህ አሁን እያንዳንዱን እንመልከት።
#ተነሽ #ንባብ
ተነሽ ንባብ የሚሆኑ ብዙ ጊዜ ግሦች ሲሆኑ መድረሻ ቃላቸው ከሳድስ እና ከኃምስ ውጭ ሊሆን ይችላል። በኃምስ እና በሳድስ የሚጨርስ ተነሽ ንባብ የለም። ስለዚህ አንድ ቃል መድረሻው ሳድስ ወይም ኃምስ ከሆነ ቀጥታ ተነሽ እንዳልሆነ መረዳት አለብን። ለምሳሌ "ውዳሴ" የሚል ቃል ብናይ መጨረሻ ፊደሉ "ሴ" ኃምስ ስለሆነ በተጨማሪም "ውዳሴ" የሚለው ቃል ከግሥ ውጭ ስለሆነ (ስም ወይም Noun) ስለሆነ ተነሽ አለመሆኑን ያሳየናል።
በግእዝ፦ ቀተለ፣ ወደሰ
በካዕብ፦ቀተሉ፣ቀደሱ
በሣልስ፦ሑሪ ወብልዒ
በራብዕ፦ሑራ
በሳብዕ፦ቀድሶ
ይላል ማለት ነው።በተጨማሪ በሳድስ የሚጨርሱ ስሞች ተሳቢ "Object" ሲሆኑ ተነስተው ይነበባሉ። ለምሳሌ "መንግሥት" የሚለው ቃል መጨረሻ ፊደሉ ሳድስ ስለሆነ ተነሽ አይደለም። ነገር ግን ተሳቢ ሲሆን "መንግሥተ" ስለሚል ተነሽ ይሆናል ማለት ነው።ተነሽ ንባብ በውርድ ንባብ ጊዜ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ መድረሻውን ፊደል ረገጥ አድርጎ ይነበባል። ቅድመ መድረሻው ሳድስ ከሆነ ግን ቅድመ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ ይነበባል።
#ወዳቂ #ንባብ
ወዳቂ ንባብ የሚሆኑት ብዙ ጊዜ ከግሥ ውጭ ያሉ ቃላት ናቸው። መድረሻ ፊደላቸው ከሳድስ ውጭ የሆነ ሲሆን። ሳድስ ሆኖ ወዳቂ የሆነ ቃል "ዝ" የሚለው ብቻ ነው። ሌላ በሳድስ የሚጨርስ ወዳቂ ቃል የለም።ሁልጊዜም በኃምስ የሚጨርሱ ቃላት ንባባቸው ወዳቂ ነው። ምሳሌ ሙሴ፣ ሥላሴ፥ አውሴ ወዘተ ብንል ወዳቂ ንባባት ናቸው።
በግእዝ፦ህየ፥ሠለስተ
በካዕብ፦ክልኤቱ፥መንግሥቱ
በሣልስ፦ሠዓሊ፣ጸሐፊ፥ቀዳሲ
በራብዕ፦መና፥እንዚራ፥ኤርትራ
በኃምስ፦ምናሴ፥ምናኔ
በሳድስ፦ዝ የሚለው ብቻ ነው
በሳብዕ፦ከበሮ፣ሰማዮ
ወዳቂ ንባብ በውርድ ንባብ ጊዜ መድረሻ ቀለሙን ይዞ ይነበባል።
#ሰያፍ #ንባብ
ተሰይፈው የሚነበቡ ቃላት መድረሻቸው ሁልጊዜም "ሳድስ" ሲሆን ግሥ ሆነው በሳድስ የሚጨርሱ ቃላት ተሰይፈው ይነበባሉ። የሰው ስም ሆነው በሳድስ የሚጨርሱ ቃላትም አንዳንዶች ተሰይፈው ይነበባሉ። የሰያፍ ንባብ ምሳሌዎች፦ ወደሰት፥ ይመጽእ፣ ዳንኤል፣ ኢሳይያስ ወዘተ ይላል። ሰያፍ ቃል በውርድ ንባብ ጊዜ ቅድመ ቅድመ መድረሻውን ያዝ አድርጎ መድረሻ ቀለሙን ረገጥ ሳያደርግ ይነበባል።
#ተጣይ #ንባብ
ተጣይ ንባባትም እንደሰያፍ ንባብ የመድረሻ ቀለማቸው ሳድስ ሲሆን ከሰያፍ የሚለዩት ብዙ ጊዜ ተጣይ ንባባት ስሞች ናቸው። ከግሥ ተጣይ ንባብ የሆኑ በትእዛዝ ጊዜ ሁለት ፊደል የሆኑ በሳድስ የሚጨርሱ ግሶች ናቸው። ለምሳሌ፦ሑር፥ ማርያም፥ ስብሀት፥ ኢየሱስ ናቸው። ተጣይ ንባባት በውርድ ንባብ ጊዜ ቅድመ መድረሻቸውን ያዝ አድርገው መድረሻ ፊደላቸውን ረገጥ ሳያደርጉ ይነበባሉ።

ሁለት ፊደል ያለው በሳድስ የጨረሰ ስም ሁልጊዜም ተጣይ ነው።ምሳሌ ኖኅ፣ሴም ወዘተ።በተጨማሪ ፍጹም ሳድስ የሆነ ስምም ንባቡ ተጣይ ነው።ምሳሌ እስክንድር፥ ሌላው ቅድመ መድረሻው ግእዝ ወይም ሣልስ የሆነ ቃልም ንባቡ ተጣይ ነው።ምሳሌ ፋሲለደስ፣ ጊዮርጊስ። በሌላው ግን በልምድ እና መምህራንን በመጠየቅ ይታወቃል እንጂ ሕጉ ብዙ ጊዜ አይጸናም። በቃላት አወቃቀር ማርያም እና ማትያስ ተመሳሳይ ቢሆኑም ማትያስ ሰያፍ ሲሆን ማርያም ግን ተጣይ ንባብ ነው።

ሌላው በሥርዓተ ንባብ ውስጥ ያለው ሕግ ጠብቀው የሚነበቡና ላልተው የሚነበቡ አሉ።በአማርኛ እንኳ "ገና" ስንል በዓሉን ከሆነ "ና" ጠብቆ ይነበባል። ጊዜው አልደረሰም "ገና" ነው ለማለት "ና" ላልቶ ይነበባል። በግእዝም ጠብቆ የሚነበበውን አላልተን ካነበብነው የተለያየ ትርጉም ስለሚያመጣ እርሱን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሁለት ፊደል ሆኖ ሁለቱም ግእዝ ከሆነ በግእዝ ጠብቆ ይነበባል። ምሳሌ ሐመ፣ ነደ፣ ይላል።ለምሳሌ "ሰበከ" ስንል "በ"ን ካጠበቅነው "ጣዖት ሠራ" ተብሎ ይተረጎማል። "በ"ን አላልተን ካነበብነው ደግሞ "አስተማረ" ተብሎ ይተረጎማል።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት ንባባቸውን ለይ
1 ገብርኤል
2 ማኅሌት
3 አንፈርዐፀ
4 እልፍ
5 ስድስቱ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፰ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
ግእዝ ክፍል-፯

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ክፍል ፰ ይቀጥላል ! #ሼር ያድርጉ‼️
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
በቀጣይ የጥያቄዎች መልስ #ግእዝ #ክፍል #1 (፩) እስከ 7 (፯) እንመለከታለን

#ከቻላችሁ የሞከራችሁትን መልስ ላኩልን!!

@learngeezbot @learngeezbot

ካሁን በኋላ የጥያቄዎቹን መልስ ከስር ከስር አስቀምጣለሁ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


#ሼር ያድርጉት
.
.
.
እንቀጥላለን !!

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የጥያቄዎች መልስ
#ግእዝ #ክፍል #1
1...፵፬
2...፷፰
3…፹፫
4…፳፩
5…፴፱
6…83
7...61
8...59
9...78
10...15
። ።
#ግእዝ #ክፍል #2 መልሶች
1 ፹፱፻፴፬
2 ፬፼፵፬፻፵፬
3 ፶፯፼፳፬፻፹፫
። ።
#ግእዝ #ክፍል #3 መልሶች
1 ፰፼፻፺፬፼፴፪፻፹፱
2 ፴፫፼፻፷፯፼፹፫፻፺፪
3 ፹፱፼፼፻፳፰፼፼፴፮፻፼፲፮፼፴፱፻፵፱
። ።
#ግእዝ #ክፍል #4 መልሶች
1 ያች(ይች) ማርያም ትወደናለች። ይእቲ አመልካች ቅጽል ነው።
2 እግዚአብሔር ብርሃንሽ ነው/ብርሃንሽ እግዚአብሔር ነው።ውእቱ ነባር አንቀጽ ነው።
3 እርሱ ፈጠረን። ውእቱ የስም ምትክ ነው።
4 የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ። አንቲ የስም ምትክ ነው። ውእቱ ነባር አንቀጽ ነው።
5 ሀገራችን በሰማይ ነው። ውእቱ የስም ምትክ ነው።


#ግእዝ #ክፍል #5 መልሶች
1 አቤቱ አንተን እናመሰግናለን
2 ክርስቶስ እኛን ወደደ
3 ለሊነ ነአምር


#ግእዝ #ክፍል #6 መልሶች
1 እልክቱ/እልኩ ሰብእ አዝማዲነ እሙንቱ/እማንቱ
2 ይች በር ጠባብ ናት
3 ክርስቶስ የእኛ ነው


#ግእዝ #ክፍል #7
1 ሰያፍ
2 ተጣይ
3 ተነሽ
4 ተጣይ
5 ወዳቂ


ካሁን በኋላ የጥያቄዎቹን መልስ ከስር ከስር እናስቀምጣለን ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
🌻 ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ 🌻
🌸መዝ ፷፬ ፥ ፲፩ 🌸


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐነ እምዘመነ ማቴዎስ ኀበ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ።

🌼 እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።


🌼🌼🌼 ሠናይ ሐዲስ ዓመት 🌼🌼🌼


🌼 መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1 🌼🌻🌼🌻
@learnGeez1 🌼🌻🌼🌻🌼
@learnGeez1 👈🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
🌻🌻🌻🌻2014🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 8🌹
የ "ሰ፣ሠ፣አ፣ዐ፣ጸ፣ፀ፣ሀ፣ኀ፥ሐ" ልዩነት

በግእዝ ቋንቋ በእሳቱ "ሰ" የተጻፈውን በንጉሡ "ሠ" ከተጻፈ እና በዓይኑ "ዐ" መጻፍ ያለበትን በአልፋው "አ" ወዘተ እያልን ከጻፍን የትርጉም ለውጥ ስለሚያመጣ ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልቃል። ለምሳሌ "ሠረቀ" እና "ሰረቀ" ሁሉቱ በጣም የተለያዩ ቃላት ናቸው። "ሠረቀ" ማለት ወጣ ማለት ሲሆን ምሥራቅ የሚለው አቅጣጫ ጠቋሚ የሚወጣበት ነው።"ሰረቀ" ማለት ግን ሰረቀ ማለት ነው። ሥለዚህ ፊደላቱ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።ሌላ ምሳሌ "ሠዐለ" የሚለው እና "ሰአለ" ሲል ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። ሠዐለ ማለት ሥዕል ሣለ ማለት ነው።ሠዓሊ የሚለው ሥዕል የሚስል ማለት ነው። "ሰአለ" የሚለው ግን "ለመነ" ማለት ነው። "ሰኣሊ" ማለት "ለምኚ" ማለት ነው። ሰኣሊ ለነ ቅድስት ስንል ቅድስት ሆይ ለምኚልን ማለት ነው። ስለዚህ ፊደላትን ገና በድምጽ ተመሳሳይ ናቸው ብለን እያደበላለቅን መጻፍ አይገበንም። የፊደላቱ ሥም እንደሚከተለው ነው።

1 አ.....አልፋው አ
2 ዐ.....ዓይኑ አ
3 ሠ.....ንጉሡ ሠ
4 ሰ.....እሳቱ ሰ
5 ፀ.....ፀሐዩ ፀ
6 ጸ......ጸሎቱ ጸ
7 ሀ......ሀሌታው ሀ
8 ሐ.....ሐመሩ ሐ
9 ኀ......ብዙኃኑ ኀ

ይባላሉ ስያሜያቸውን ያገኙት ከዚሁ ከቃሉ ነው። ለምሳሌ "አልፋ" ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ቃል "አ" ስለሆነ ስያሜውን ከዚህ አግኝቷል። ስለዚህ "ዐልፋ" ተብሎ አይጻፍም ማለት ነው።ሌላው ልናውቀው የሚገባን ለቀጣዩ ትምህርትም የሚያገለግለን ከሀ እስከ ሆ ያሉ ፊደላት መጠሪያ አላቸው።ይኽውም እንደሚከተለው ነው።

1 ሀ......ግእዝ
2 ሁ......ካዕብ
3 ሂ.......ሣልስ
4 ሃ........ራብዕ
5 ሄ........ኃምስ
6 ህ........ሳድስ
7 ሆ........ሳብዕ

ናቸው ለምሳሌ "ሀ" እና "ሃ" በድምጽ ተመሳሳይ ስለሆኑ ብለን ደበላልቀን መጻፍ የለብንም። ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ስለሚያመጣ ነው። ለምሳሌ "መርሓ" ብትልና "መርሐ" ብትል መርሓ ማለት ብዙ ሴቶች መሩ ማለት ነው። መርሐ ማለት ግን አንድ ወንድ መራ ማለት ነው። ስለዚህ ይህንን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል።ሌላው ዲቃላ ፊደላት የሚባሉ ቊ፣ኲ፣ኊ፣ጒ ካዕብና ሳብዕ የላቸውም። ስለዚህ በእርባታ ጊዜ ሳብዕ እና ካዕብ ባስፈለገበት ጊዜ በ"ቀ፣ከ፣ኀ፣ገ" ካዕብ እና ሳድስ ይረባሉ።

እያንዳንዱ ቃል በየትኛው ፊደል እንደሚጻፍ ለማወቅ ጥንታዊ መጻሕፍትን አዘውትረን በማንበብ እናውቀዋለን።

ጥያቄ
የሚከተለቱን በየትኛው ፊደል እንደሚጻፉ ለዩ
1) አስተማረ ሲል
ሀ, መሀረ
ለ, መሐረ
ሐ, መኀረ
2) ማረ ይቅር አለ ሲል የትኛው ነው?
ሀ, መሀረ
ለ, መሐረ
ሐ, መኀረ
3) ወደ ሰማይ ወጣ ለማለት ወጣ ሲል
ሀ, ዐርገ
ለ, አርገ
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
2024/10/01 22:27:39
Back to Top
HTML Embed Code: