Telegram Web Link
ግእዝ ክፍል 55
©ቅኔ 3©
ወደ ቅኔ ከመግባታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገባን የቅኔ መሠረታውያን።
1 የቅኔው ቤት
ይህ ማለት ቅኔው ቤቱ ሲገጥም የመጨረሻው ፊደል ቤት ይባላል።ግልጽ እንዲሆን በምሳሌ እንየው።የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ቅኔ

አኃውየ ሕቱ ርእሰክሙ ወልበክሙ አንጽሁ።
ጉባኤቃና መሥዋእት ማሕየዊ እስመተፈተተ ናሁ።

የዚህ ቅኔ ቤቱ "ሁ" ነው።ይህም ማለት ይህ ቅኔ በ"ሁ" ገጠመ ይባላል።ስለዚህ በቅኔ ጊዜ በ"ለ" ከጀመርን በ"ለ" በሌላም ስንጀምር በጀመርንበት እንጨርሳለን እንጂ ቤት አናቀያይርም።
2 የቅኔው ዓይነት
ለምሳሌ ከላይ ያለው ቅኔ "ጉባኤ ቃና" ይባላል። ጉባኤ ቃና የሚባለው 2 ቤት ያለው ቅኔ ነው። ዘአምላኪየ 3 ቤት አለው።ሚበዝኁ 3 ቤት አለው።ሚበዝኁና ዘአምላኪየ የሚለዩት በዜማ ልክ ነው።ዜማ ልክን ለብቻው እናየዋለን።ዋዜማ 5 ቤት አለው።ሥላሴ 6 ቤት አለው።ዘይእዜ 6 ቤት አለው።መወድስ 8 ቤት አለው።
3 የቅኔው ክፍሎች
ከላይ ያለው ቅኔ እንደምታዩት በቃላት የተደረደረ ነው።የቃሉ አደራደር የራሱ የሆነ ስያሜ አለው።መጀመሪያ የምናገኘው ቃል ከላይኛው ቅኔ "አኀውየ" መደብ ይባላል።መደብ ከተባለው ቃል ቀጥሎ ያለው ቃል ደግሞ የመደብ ተቀባይ ይባላል።ከላይኛው ቅኔ "ሕቱ" የመደብ ተቀባይ ይባላል።ከዚያ ቀጥሎ መካከል ላይ ያለው ሐረግ ይባላል።ከላይኛው ቅኔ "ርእሰክሙ" የሚለው ነው።ቀጥሎ ያለው የቤት መምቻ መደብ ይባላል።ከላይኛው ቅኔ "ወልበክሙ" የሚለው ነው።የመጨረሻው የቤት መምቻ መደብ ተቀባይ ይባላል።ይኽውም "አንጽሑ" የሚለው ነው።ከ2ኛው ቤት ያለውም ስያሜው እንደመጀመሪያው ነው።ሐረግ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል።የቅኔን ዜማ ልክ ለማወቅ እነዚህን ስያሜዎች በትክክል ማወቅ አለብን።

4 ትረካ... ቅኔ ከማድረጋችን በፊት ቅኔ ስለሚደረግለት ቅዱስ ታሪክ ይተረካል።የተተረከውን ታሪክ ለወርቅ መነሻ አድርጎ ሰም አድርገን ቅኔ እናደርጋለን።ቅኔ ስናደርግ ቅኔ ስለምናደርግለት አካል ማወቅ ያስፈልጋል።ምሳሌ ነገ ጊዮርጊስ ቢሆን የጊዮርጊስ ታሪክ ስቃዩ መቆረጡ ሁሉ ታሪኩ ይነገራል።ይህን ይዘን ነው ቅኔ የምናደርገው ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 56
©ዜማ ልክ©
ዜማ ልክን ለመረዳት 4ቱን ሥርዓተ ንባባት ከዚህ ቀደም ከክፍል 1 እስከ ክፍል 55 ያለውን በደንብ እይ።ተጣይ፥ሰያፍ፥ተነሽ፥ወዳቂ ናቸው
የጉባኤ ቃና ዜማ ልክ
©መደቡ.....ተጣይ ከሆነ ከ2 እስከ 7 5ትን ሳይነካ።ተነሽ ከሆነም እንዲሁ ከ2 እስከ 7 ሆኖ 5ትን ሳይነካ።ወዳቂ ከሆነ ከ1 እስከ 6 ሆኖ 4ትን ሳይነካ።ሰያፍ ከሆነ ከ3 እስከ 8 ሆኖ 6ትን ሳይነካ ነው።እኒህ ቁጥሮ ቀለም ናቸው።ቀለም ማለት እያንዳንዱ ተነባቢ ፊደል ማለት ነው።ምሳሌ ቀተለ ቢል 3 ቀለም አለው ይባላል።ፍቅር ቢል 2 ቀለም አለው ይባላል ከዚህ ላይ "ቅ" ስለተዋጠ ነው። መካከል ላይ ሳድስ ሲመጣ ረገጥ ተደርጎ ካልተነበበ አይቆጠርም።
© ተቀባይ......ለተጣይ መደብ 3 ወይም 4 ሰያፍ፥2 ወይም 3 ተነሽና ተጣይ ነው። ለወዳቂ መደብ 4 ሰያፍ፥3 ተነሽ ወይም ተጣይ ነው።ለተነሽ መደብ 3 ሰያፍ፥2 ተነሽና ተጣይ ነው።ለሰያፍ መደብ 3 ሰያፍ፥2 ተጣይና ተነሽ ነው።ወዳቂ ተቀባይ አይሆንም።
© ሐረግ..... ተጣይ ተነሽ ሰያፍ ከ4 እስከ5።ወዳቂ ከ3 እስከ 5 ነው።
© የቤት መምቻ መደብ....ተነሽ ከ5 እስከ 7።ወዳቂ 5 እና 6።ተጣይ 6 እና 7።ሰያፍ ከ6 እስከ 8 ነው።
© የቤት መምቻ መደብ ተቀባይ... ለ5 ተነሽ 3 ተጣይ ወዳቂ ወይም ተነሽ።ለ6 እና ለ7 ተነሽ 2 ተጣይ ወዳቂ ወይም ተነሽ።ለወዳቂ 3 ተጣይ ወዳቂ እና ተነሽ።ለተጣይ 2 ወይም 3 ወዳቂ ተነሽ ተጣይ ነው።ለ6 ሰያፍ 3 ተጣይ ወዳቂ ወይም ተነሽ።ለ7 እና ለ8 ሰያፍ 2 ተጣይ ወይም ወዳቂ ወይም ተነሽ ይሆናል።ሰያፍ የቤት መምቻ መደብ ተቀባይ አይሆንም።
© በሁለተኛው ቤትም እንደመጀመሪያው ቤት ማድረግ ነው።ሐረጉ ግን ይለያል።ይኽውም በ2ኛው ቤት ሐረግ ካለ ወዳቂ ብቻ ያውም 3 ቀለም ያለው ነው እንጂ ሌላ አይሆንም።

ምሳሌ ቅኔ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ቅኔ።

አኃውየ ሕቱ ርእሰክሙ ወልበክሙ አንጽሑ።
ጉባኤቃና መሥዋዕት ማሕየዊ እስመ ተፈተተ ናሁ።

ሲል ዜማ ልኩን እንየው
አኀውየ 4 ተነሽ ነው ይቻላል።ተቀባዩ ሕቱ 2 ተነሽ ነው።ሐረጉ 4 ተነሽ ነው ርእሰክሙ/እ ሳድስ ስለሆነች ተውጣለች።የቤት መምቻው መደብ ወልበክሙ 5 ተነሽ ነው።ተቀባዩ 3 ተነሽ ነው።2ኛው ቤት ጉባኤቃና 5 ወዳቂ ነው።ተቀባዩ መሥዋእት 3 ተጣይ ነው። ሥ እና ዕ ሳድስ ስለሆኑ ስለተዋጡ ነው 3 የሆነው።ማሕየዊ ሐረግ ነው 3 ወዳቂ ነው።እስመተፈተተ 6 ተነሽ ነው።"ስ" ተውጣለች።ተቀባዩ ናሁ 2 ወዳቂ ነው።

ስለዚህ ከላይ የጻፍነውን ሕግ ሙሉ በሙሉ ያሟላ ስለሆነ ዜማ ልክ አልሰበረም ይባላል።ግን አኀውየ አንፈርዐፁ ብል ዜማ ልክ ሰበረ ያሰኛል መደቡ ልክ ነው።ተቀባዩ ግን ለተነሽ ተነሽ ሲሆን 2 ነው።አንፈርዐፁ ደግሞ 4 ስለሆነ አይቻልም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 57
©ዜማ ልክ ክፍል 2©
በክፍል 56 የጉባኤ ቃናን ዜማ ልክ አይተናል።በዚህ ክፍል ደግሞ የዘአምላኪየና የሚበዝኁን ዜማ ልክ እንመለከታለን።
የዘአምላኪየ ዜማ ልክ
ዘአምላኪየ 3 ቤት ነው ያለው።የመጀመሪያው ቤት ክፍል 56 ላይ እንዳየነው እንደመጀመሪያው ቤት ጉባኤ ቃና ሆኖ ግን ሐረግ የሌለው ነው።ሁለተኛው ቤት ማንደረደሪያ ይባላል።
© የማንደርደሪያው ዜማ ልክ
መደቡ ተነሽ ከሆነ ከ2 እስከ 4 ነው።ተጣይም እንዲሁ ከ2 እስከ 4 ነው።ሰያፍ ከ3 እስከ 5 ነው።የእነዚህ ሁሉ ተቀባያቸው ሰያፍ ያልሆነ 6 ቀለም ያለው ተጣይ ወይም ተነሽ ወይም ወዳቂ ነው።ከዚያ የቤት መምቻው መደብ ወዳቂ 3 ብቻ ተጣይ 4 ብቻ ተነሽ 3 እና 4 ሰያፍ 4 እና 5 ናቸው።የቤት መምቻው መደብ ተቀባይ ለተጣዩ 2 ወይም 3 ተነሽ ተጣይ ወይም ወዳቂ ነው።ለተነሹ ለ3ቱ ተነሽ 3 ተጣይ ወዳቂ ወይም ተነሽ ሲሆን ለ4ቱ 2 ተጣይ ወይም ወዳቂ ወይም ተነሽ ነው።ለሰያፉ ለ4ቱ ሰያፍ 3 ወዳቂ ተጣይ ወይም ተነሽ ሲሆን ለ5ቱ ሰያፍ 2 ተጣይ ወይም ወዳቂ ወይም ተነሽ ነው።
© ሦስተኛው የዘአምላኪየ ቤት እንደ ሁለተኛው የጉባኤ ቃና ቤት ነው።
ሚ በዝኁ
እንደ ዘአምላኪየ 3 ቤት ቢኖረውም በዜማ ልክ ግን ከዘአምላኪየ ይለያል።
© የመጀመሪያው ቤት...
መደብ+ተቀባይ+መደብ+ተቀባይ+የቤት መምቻ መደብ+የቤት መምቻ ተቀባይ ነው።ከዚህ ላይ መደብ እና ተቀባዩ ጉባኤ ቃና ላይ እንዳለው ነው።
© ሁለተኛው ቤት
መደብ+ተቀባይ+የቤት መምቻ መደብ+የቤት መምቻ ተቀባይ ነው
© ሦስተኛው ቤት
ልክ እንደመጀመሪያው ቤት ያለ ነው።

ምሳሌ ከሊቀ ሊቃውንት ያሬድ
ዘአምላኪየ

አንተ ዝኅር ሰንኮሪሰከዊን ዐማፄ።
ኢየዐርግ ለኀበፈጣሪ ማሕሌትከ ዕፄ።
እስመአንተ አንተ አሐዱ እምዐበይተዘረዐብ ሕንጼ።

ሚበዝኁ

ኢየሩሳሌም ሳሌም ኢየሩሳሌም ሳሌም ዲዎስቆራሰናኦር ዲዎስቆራ።
በአፍኣ ለወርቅ ብእሲተኤላውጦን አአምራ።
ይቤ ይቤሉ ይቤ ይቤሉ ሐራ ዐማኑኤል ሐራ።

ሚበዝኁ 2 መንገድ ነው ያለው።አንደኛውን መንገድ ከላይ ያየነው ነዋ።ሌላኛው ግን ከላይ ካለው ቅኔ ዓይነት ነው።ልውጥ ሚበዝኁ ይባላል። መደቡ ጉባኤ ቃና ላይ እንዳየነው ሆኖ ተቀባዩ ግን ለተነሹ እና ለሰያፉ 4 ተጣይ ወዳቂ ሰያፍ ተነሽ ሲሆን።ለወዳቂ 5 ተጣይ ተነሽ ወዳቂ ሰያፍ ነው።ለተጣይ 4ም 5ም ተጣይ ተነሽ ወዳቂ ተጣይ ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 58
©ቅኔ እና ሙያ®
በነገራችን ላይ ዜማ ልኩን እስከ ሚበዝኁ ብቻ ነው የጻፍኩት።ከዚያ በላይ ያለውን ልጻፈው ብል አሰልቺ ስለሚሆን ትቼዋለሁ።አሁን የቅኔ ሙያዎችን እንይ።
አገባቦች ፍቻቸውና የቅኔ ሙያቸው።
አገባቦች......ፍቻቸው.....የቅኔ ሙያቸው
በ...............በ.............ማደረጊያ
ምስለ.......ጋር(with)...........አፈቃቃሪ
እምነ...........ከ(from).............መነሻ
ኀበ.............ወደ(to)..........መገስገሻ
እስከ..........እስከ...............መድረሻ
እስመ.........ና....................አስረጅ
ለ.............ለ............ምስጢር አቀባይ
አመ/ሶበ.....ጊዜ.........ማንጸሪያ
እንዘ...........ሲ/ሳ.........ማንጸሪያ
እንበለ........ያለ............አቃላይ

እኒህን አስቀድሞ ማወቅ ይገባል።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 59
©የቅኔ ሙያ ክፍል 2©
በቅኔ ሙያ ሲሰጥ እያንዳንዱ ቃል እና አገባብ በቅኔው ላይ ያለው ጥቅም ይገለጻል።ግዴታ ማንኛውም ቅኔ ባለቤት እና ማሰሪያ ሊኖረው ይገባል።ይህ minimum requirement ነው።
© ባለቤት..... .....ባለቤት የሚባለው ቅኔው የሚናገርለት ወይም የሚነገርለት አካል ነው።
© ማሰሪያ አንቀጽ........ይህ ደግሞ የባለቤቱን ድርጊት ገላጭ ነው።
© ቅጽል..... ቅጽል ደግሞ ባለቤቱን የሚያጎላምስ ስለባለቤቱ ተጨማሪ መታወቂያ የሚገልጽ ነው።
© አንቀጽ አጎላማሽ..... ይህ ደግሞ የአንቀጹ አደራረግ አኳኋን የሚያሳይ አንቀጹን የሚያጎላምስ ነው።
© ተሳቢ....... ይህ ደግሞ አንቀጹ የሚስበው ነው።"ን"ን ያመጣል በትርጉም ጊዜ።

ለምሳሌ
ማርያም ቅድስት ታፈቅር ጥቀ ክርስቶስሀ ቢል።ማርያም ባለቤት ናት።ቅድስት የማርያም ቅጽል ይባላል።ታፈቅር ማሰሪያ አንቀጽ ይባላል።ጥቀ ትርጉሙ እጅግ ማለት ነው።ታፈቅርን ስለሚያጎላምስ ጥቀ አንቀጽ አጎላማሽ ይባላል።ክርስቶስሃ ሲተረጎም ክርስቶስን ማለት ስለሆነ ተሳቢ ይባላል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 60
ቅኔ ፩
ጉባኤ ቃና
አርምሚ ባሕር በስመአጋእዝት ሥላሴ።
እስመ ኢተውኅጠ ለኪ ነገረዚአኪ ሙሴ።

ይህን ቅኔ ታላቁ ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ከጻፉት መጽሐፈ ቅኔ ያገኘሁት ነው።

ትርጉም
ባሕር ሆይ ነገርሽ ሙሴ አልተዋጠልሽምና በሥላሴ ስም ዝም በይ።

ሰም
አንዳንድ ሴቶች ነገር አልዋጥላቸው ስሉ ተናገሩ ተናገሩ ያሰኛቸዋል እና እስኪ ዝም በሉ ይባላሉ።

ወርቅ
ባሕረ ኤርትራ ሙሴን አልዋጠችውም ማለት አላሰጠመችውም።

ሙያ
አርምሚ..... ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጅ አይሳብም።
ባሕር....... የአርምሚ ባለቤት
በ.......ፍቹ በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ
ስም.....የማድረጊያ ባለቤት
አጋእዝት.....የሥላሴ ቅጽል
ሥላሴ......የስም ዘርፍ
እስመ....ፍችው ና ሙያው አስረጅ
ኢ........አሉታ
ተውኅጠ..እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል
ሙሴ ነገር ምሳሌ....ነገር ሰም ሙሴ ወርቅ ተመስለው የኢተውኅጠ ባለቤት።
ዚአኪ....የነገር ዘርፍ (ሌላ ሙያ አሰጣጥም አለው)

እንዲህ እንዲህ እያለ እያንዳንዷ ቅንጣት ሙያ ይሰጣታል ማለት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 61
©ቅኔ 9©
የታላቁ ሊቅ የመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ሥላሴ ቅኔ።የሚገርም ቅኔ ስማማ።
አእዱገ ዘአጥረዩ በኀሢሠ መስነቅት ይጻምው
ወዘአጥረዩ መስነቅተ ለአጥርዮተ አድግ ተግሁ።
እስመ ባዕድ እም ረባሐ አድግ ለመስነቅት ረባሑ።
በቁዔቱሰ ለቶማስ በቋዒ ለእመ አኮ ከማሁ።
እለ አጥረይዎ ይትፌሥሑ።
እስመ መስነቅተ ጽድቅ ይከውን ማዕሰ ሥጋሁ።
ወመሥነቅተ ይጼዓን ለሊሁ።

ትርጉም

አህያ የገዙ ስልቻ በመፈለግ ይደክማሉ። ስልቻ የገዙ ደግሞ አህያ ለመግዛት ይተጋሉ።
የስልቻ ጥቅም ከአህያ ጥቅም ልዩ ነውና።
ጠቃሚ የሆነ ቶማስ የቶማስ ጥቅሙ ግን እንደሱ ባይሆን።
የገዙት ይደሰታሉ።
የሥጋው ቆዳ የእውነት ሥልቻ ይሆናልና።ስልቻውንም እርሱ ራሱ ይሸከማልና።

ሰም

በገጠሩ የሀገራችን ክፍል አንዳንድ ጊዜ ስልቻ ኖሮት አህያ አልኖረው ይላል።አህያ ኖሮት ደግሞ ስልቻ አልኖረው ይላል። አህያ ከእነ ስልቻ ያላቸው ጥቂት ናቸው።

ወርቅ

የቶማስን ቆዳ ዓላውያን ገፈው አድርቀው ሥልቻ አስደርገው ራሱን ቶማስን አሸከሙት ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
አእዱገ......የአጥረዩ ተሳቢ
ዘ..........በቂ
አጥረዩ......እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
በ............ማድረጊያ
ኀሢሥ........የማድረጊያ ባለቤት
መስነቅት.......የኀሢሥ ዘርፍ
ይጻምው......ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም
ወ..........ደጋሚ
ዘ...........በቂ
አጥረዩ......እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
መስነቅት.......የአጥረዩ ተሳቢ
ለ.............ምስጢር አቀባይ
አጥርዮት......የአቀባይ ባለቤት
አድግ........የአጥርዮት ዘርፍ
እስመ......ፍችው ና ሙያው አስረጅ
ባዕድ.....ውእቱን መርምሮ እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
እም........መነሻ
ረባሕ......የመነሻ ባለቤት
አድግ....የረባሕ ዘርፍ
ለ.........ዘርፍ ደፊ ዘርፍ ደፊነቱም ረባሐ መስነቅት የሚያሰኝ ነው።
ረባሕ.....የውእቱ ባለቤት
መስነቅት......የረባሕ ዘርፍ
በቁዔት........
ለ......ዘርፍ አያያዥ አያያዥነቷም በቁዔተ ቶማስ የምታሰኝ ናት።
ቶማስ.....የበቁዔት ዘርፍ
በቋዒ.....ቅጽል
ለ...........አዳማቂ
እመ.......ማንፀሪያ
አኮ.......እንዳያስር ማንጸሪያ ይጠብቀዋል።
ከማሁ........
እለ.........በቂ
አጥረይዎ.....እንዳያስር እለ ይጠብቀዋል።
ይትፌሥሑ.....ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
እስመ.....አስረጅ
መስነቅት....የይከውንት ተሳቢ
ጽድቅ.......የመስነቅት ዘርፍ
ይከውን......እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
ማዕሥ.......የይከውን ባለቤት
ሥጋሁ........የማዕሥ ዘርፍ
ወ.............አውራጅ
መስነቅት......የይጼዓን ተሳቢ
ይጼዓን.........እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
ለሊሁ........የይጼዓን ባለቤት።

እንዲህ እያለ እያለ ይተረጎማል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 62
©ቅኔ 10©
ጉባኤ ቃና ዘአቶ ላቀው

ኃያል ጾም ለእመ አንስአ በትሮ።
አያውስአ ቃለ ፈራሀልቡና ከበሮ።

ትርጉም
ኃያል ሰውየ ጾም በትሩን ቢያነሳ
የልብ ፈሪ ከበሮ ቃልን አልመለሰም

ሰም
አንዳንድ ኃያል ሰዎች በችግር ጊዜ በትር ሲያነሱ ፈሪ ሰው እየተናገረ ከነበረም ፈርቶ ጸጥ ይላል።

ወርቅ
በዓቢይ ጾም ጊዜ ከበሮ አይመታም።በትር ማለት መቋሚያ ግን ለዝማሜ ይውላል ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
ኃያል......የጾም ቅጽል
ጾም.......የአንስአ ባለቤት
ለ.........አዳማቂ/በር ከፋች?
እመ......ማንጸሪያ
አንስአ.....እንዳያስር እመ ይጠብቀዋል
በትር......የአንስአ ተሳቢ
ኢያውስአ....ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
ቃል......የኢያውስአ ተሳቢ
ፈራህ ከበሮ.....ምሳሌ ፈራህ ሰም ከበሮ ወርቅ ተመስለው የኢያውስአ ባለቤት
ልቡና......የፈራህ ዘርፍ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 63
©ቅኔ 11©
ጉባኤ ቃና ዘቄሰ ገበዝ እንግዳ ዲማ

ጊዮርጊስ ካህን መፍቀሬ ማኅሌት ተመትሮ።
ርእሶ አጽነነ ለጸዊረ መጥባሕት ከበሮ።

ትርጉም
ማህሌት መቆረጥን የሚወድ ካህን ጊዮርጊስ።ከበሮ ቢላዋ/ካራ/ሰይፍን ለመሸከም/ለማዘል ራሱን አዘነበለ።

ሰም
ማህሌት የሚወዱ ካህናት በማህሌት ጊዜ ከበሮ ለመያዝ አንገታቸውን ዘንበል አድርገው ይዘው ይመታሉ።

ወርቅ
ቅዱስ ጊዮርጊስ አንገቱን በሰይፍ ተቆረጠ ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
ጊዮርጊስ ካህን.....ምሳሌ ካህን ሰም ጊዮርጊስ ወርቅ ተመስለው የአጽነነ ባለቤት።
መፍቀሪ....የጊዮርጊስ ካህን ቅጽል
ማህሌት ተመትሮ......ምሳሌ ማህሌት ሰም ተመትሮ ወርቅ ተመስለው የመፍቀሬ ዘርፍ።
ርእስ.......የአጽነነ ተሳቢ
አጽነነ.......ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
ለ..........ምስጢር አቀባይ
ጸዊር........የአቀባይ ባለቤት
መጥባሕት ከበሮ......ምሳሌ ከበሮ ሰም መጥባሕት ወርቅ ተመስለው የጸዊር ዘርፍ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 64
©ቅኔ 12©
ቅኔ ሲደረግ መሪው ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ነው።ይኽውም
©ጉባኤ ቃና ሲደረግ©
ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራሕየ፥ይሄይስ ተአምኖ በእግዚአብሔር፥ ለከ ይደሉ እግዚአብሔር ስብሐት በጽዮን ወለከ ይትፌኖ ጸሎት በኢየሩሳሌም ተብሎ ነው።ትርጉሙ አቤቱ ቃሌን ስማ ጩኽቴንም አስተውል፥በእግዚአብሔር መታመን ይበልጣል፥አቤቱ ለአንተ በጽዮን ምስጋና ይገባል።ማለት ነው
©ዘአምላኪየ©
ሲደረግ ደግሞ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ..አምላኬ አምላኬ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ የሚለው ተብሎ ነው።
©ሚበዝኁ©
እግዚኦ ሚ በዝኁ እለ ይሣቅዩኒ....አቤቱ የሚያሰቃዩኝ ምንኛ በዙ ብሎ ይጀምራል።
©ዋዜማ/ዋይ ዜማ©
እግዚአብሔር ነግሠ ስብሐቲሁ ለብሰ ለብሰ እግዚአብሔር ኃይሎ ወቀነተ ብሎ ይጀምራል።እግዚአብሔር ነገሠ ምስጋናውን ለበሠ እንደማለት ነው።
©ሥላሴ©
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልኡልኒ ውእቱ ለዓለም ብሎ ይጀምራል።ትርጉሙ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።ለዘላለም ምስጉን ልዑክ ነው ማለት ነው።
©ዘይእዜ©
ይእዜ ትስእሮ ለገብርከ እግዚኦ በከመ አዘዝከ ብሎ ይጀምራል።ትርጉሙ አቤታ እንዳዘዝከው ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ማለት ነው።
©መወድስ©
ፍታሕ ሊተ እግዚኦ ወተበቀል በቀልየ ብሎ ይጀምራል።አቤቱ ፍረድልኝ በቀሌንም ተበቀልልኝ እንደማለት ነው።
©ኩልክሙ©
ኩልክሙ አህዛብ ጥፍሑ እደዊክሙ... ብሎ ይጀምራል።

ቅኔ ትምህርት ጥልቅ ነው።አገባቡን ጠንቅቆ መማር ያስፈልጋል።ቅኔ ከ300 በላይ መንገዶች አሉት።መጻሕፍትን በማንበብ መምህራንን በመጠየቅ እና በመማር የቅኔ የግእዝ እውቀታችንን አሳድገን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስጢር አውቀን በሕይወት እንድንኖረው እግዚአብሔር ይርዳን።

አነሳስቶ ለአስጀመረን
አስጀምሮ ለአስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው አሜን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 1
ጉባኤ ቃና
ተመየጥ ልብ ኖላዊ እምነ ሐተታ ፍኖት።
እስመ ኢትትረከብ ምንተ ባሕርየ ሥላሴ በግዕት።

©ትርጉም©
ባሕርየ ሥላሴ በግ ምንም አትገኝምና እረኛ ልብ ሆይ ከምርምር መንገድ ተመለስ ማለት ነው።

©ሰም©
አንዳንድ እረኛ በግ ፍለጋ ሲሄድ።ጓደኛው ከዚህ ቦታ በጊትን ስለማታገኛት ተመለስ ብሎ ከመንገድ ይመልሰዋል።

©ወርቅ©
የሰው ልብ ሆይ የሥላሴ ባሕርይ አይመረመርምና እጹብ እጹብ ብለህ ወደ አለማወቅህ ተመለስ ማለት ነው።

©የቅኔው ሙያ©
ተመየጥ.....ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
ልብ ኖላዊ.....ምሳሌ ኖላዊ ሰም ልብ ወርቅ ተመስለው የተመየጥ ባለቤት።
እምነ.......ፍችው "ከ" ሙያው መነሻ
ሐተታ ፍኖት....ምሳሌ ፍኖት ሰም ሐተታ ወርቅ ተመስለው የመነሻ ባለቤት
እስመ......ፍችው "ና" ሙያው አስረጅ
ኢትትረከብ....እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
ምንት..... የኢትትረከብ ተሳቢ/ ቦ ዘይቤ አንቀጽ አጎላማሽ
ባሕርይ በግዕት.....ምሳሌ በግዕት ሰም ባሕርይ ወርቅ ተመስለው የኢትትረከብ ባለቤት።
ሥላሴ.......የባሕርይ ዘርፍ

አስተውል ቅኔ የሚታሰረው በሰም ነው።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 2
ጉባኤ ቃና ዘመምህር ይኄይስ ወርቄ

ረኀብ ስቅለት በኢየሩሳሌም ጸንዐ።
አሐዱ ኅብስት እስመ ለኀምሥቱ ተሠርዐ።

ትርጉም
ረኀብ ስቅለት በኢየሩሳሌም ጸንቷል።ለአምስት ሰው አንድ እንጀራ ይቀርባልና።

ሰም
ረኀብ ሲፀና ለ5 ሰው አንድ እንጀራ ሊቀርብ ይችላል።

ወርቅ
በስቅለት ጊዜ ኀብስት የተባለ ጌታ ለ5 ሰዎች ቀረበ ማለት በ5 ቅንዋት ተቸነከረ ማለት ነው።እንዲህ ዓይነት ቅኔ ሕብር ቅኔ ይባላል።ኅብስት ጌታ ተብሎ ይተረጎማል አነ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ብሎ አስተምሯልና።

የቅኔው ሙያ
ረኀብ ስቅለት......ምሳሌ ረኀብ ሰም ስቅለት ወርቅ ተመስለው የጸንዐ ባለቤት።
በ...................ማድረጊያ
ኢየሩሳሌም......የማድረጊያ ባለቤት
ጸንዐ...........ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
አሐዱ.........የኅብስት አኀዝ ቅጽል
ኅብስት.......የተሠርዐ ባለቤት
እስመ.......አስረጅ
ለ............ምስጢር አቀባይ
ኀምስቱ......የአቀባይ ባለቤት
ተሠርዐ.......እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 3
ጉባኤ ቃና

መርዓት ጾም ኢያፈቅሩኪ ሰብእ።
አምጣነ አልብኪ ደም ወኢሀለወኪ ቅብእ።

ትርጉም
ወዝ እና ደም ግባት የለሽምና ሙሽራይት ጾም ሆይ ሰዎች አይወዱሽም።

ሰም
እንግድህ ያው አንድ ሙሽራ ደም ግባት ከሌላት ሰው ይነቅፋታል እንጂ አይወዳትም ነው።

ወርቅ
በጾም ወቅት ደም ማለት ሥጋ እና ቅቤ አይበላም ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
መርዓት ጾም.......ምሳሌ መርዓት ሰም ጾም ወርቅ ተመስለው የኢያፈቅሩኪ ባለቤት።
ኢያፈቅሩኪ......ያለው ማሰሪያ ያስራል እንጂ አይሳብም።
ሰብእ........የኢያፈቅሩኪ ተሳቢ
አምጣነ......ፍችው ና ሙያው አስረጅ
አልብኪ......እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
ደም........የአልብኪ ተሳቢ/ተለዋጭ
ወ.........አውራጅ
ኢሀለወኪ.......እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል።
ቅብእ.......የኢሀለወኪ ተሳቢ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 5
ከክፍል 1 እስከ ክፍል 5 ጉባኤ ቃና ነው ያደረግነው።ከክፍል 6 እስከ ክፍል 10 ዘአምላኪየ።ከክፍል 11 እስከ 15 ሚበዝኁ እያልን እስከመጨረሻው እንቀጥላለን።አሁን ወደ ጉባኤ ቃና
ጉባኤ ቃና ዘመምህር አክሊሉ ወርቅነህ

ተከለ አብራም ሥላሴ ዕፀወገነት በዓውዱ።
ለእመሎቱ ይለምድ እምነ ሠለስቱ አሐዱ።

ትርጉም
ከሦስቱ አንዱ ቢለምድልኝ(ቢበቅልልኝ) ብሎ አብርሃም በጓሮው የገነት እጽዋት ሥላሴን ተከለ።

ሰም
እንግዲህ አንድንድ ሰው 3 አትክልት ይይዝና እንዳው ከሦስቱ አንዱ ለምዶ ቢጸድቅልኝ ብሎ ይተክላል።

ወርቅ
በአብርሃም ቤት ሥላሴ መጥተው ነበር።ከሦስቱ አካላት ደግሞ ወልድ በተለየ አካሉ ቢለምድልኝ ማለት ሰው ሆኖ አዳነው እንደማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
ተከለ.......ማሰሪያ አንቀጽ
አብራም.....የተከለ ባለቤት
ሥላሴ ዕፀው.....ምሳሌ ዕፀው ሰም ሥላሴ ወርቅ ተመስለው የተከለ ተሳቢ።
ገነት........የዕፀው ዘርፍ
በ............ማድረጊያ
ዓውድ.......የማድረጊያ ባለቤት
ለ.........አዳማቂ/በር ከፋች?
እመ......ማንጸሪያ
ሎቱ.....ለ አቀባይ ቱ ዝርዝር
ይለምድ....እንዳያስር እመ ይጠብቀዋል
እምነ.......መነሻ
ሠለስቱ....የመነሻ ባለቤት
አሐዱ.......የይለምድ ባለቤት

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 6
ዘአምላኪየ
አመ ሞተ ቀርን ብእሴ ላእሉ ወታሕቱ።
ኀቢረነ ትቤ ጸናጽል መርዓቱ።
እንዘ እንግድዓሃ ትጸፍዕ በአጻብዒሃ ኀምስቱ።

ትርጉም
የላይና የታች ሰውየ ከበሮ በሞተ ጊዜ ሚስቱ ጸናጽል በአምስት ጣቶቿ ደረቷን እየደቃችን አብረን እንሙት አብረን እንሙት አለች ማለት ነው።

ሰም
እንግዲህ አንዳንድ ሚስቶች ባሎቻቸው ሲሞቱባቸው ከኀዘናቸው ጽናት የተነሳ አብረን በሞትን አብረን በሞትን ይላሉ።

ወርቅ
በዓብይ ጾም ከበሮም ጸናጽልም አይመቱም ማለት ነው።የጸናጽል አምስት ጣቶቿ ያላቸው።በጸናጽል ውስጥ ያሉ ቅጠሎች ብዛት 5 ስለሆኑ ነው።አጻብዒሃ እና እንግድዓሃ ስለዘረዘሩ ወርቅ ያመጣሉ።ሰም ሲዘረዘር ወርቅ ያመጣል።ወርቅ ግን አይዘረዝርም።

የቅኔው ሙያ
አመ.........ማንጸሪያ
ሞተ..........እንዳያስር አመ ይጠብቀዋል
ቀርን ብእሲ.....ምሳሌ ብእሲ ሰም ቀርን ወርቅ ተመስለው የሞተ ባለቤት
ላእሉ ታሕቱ.....በወ ተጫፍረው የብእሲ ዘርፍ
ኀቢረነ..........የትቤ ተለዋጭ/ተሳቢ
ትቤ.............ማሰሪያ አንቀጽ
ጸናጽል መርዓት....ምሳሌ መርዓት ሰም ጸናጽል ወርቅ ተመስለው የትቤ ባለቤት
እንዘ...........ማንጸርያ
እንግድዓሃ.......የትጸፍዕ ተሳቢ
ትጸፍዕ......እንዳያስር እንዘ ይጠብቀዋል
በ.........ማድረጊያ
አጻብዒሃ.....የማድረጊያ ባለቤት
ኀምስቱ.......የአጻብዒሃ አኀዝ ቅጽል

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 7
ሚበዝኁ ዘመምህር ገብረ ሥላሴ

አመ ሰማእክሙ ቀርነ ውስተ ቤተ ጸሎት ኬብሮን ባሕታውያን ዘገዳም።
በሉ ነግሠ መብልዕ አቤሴሎም።
እስመ አሜሃ ይሰደድ እንተ ልማዱ ብካይ ንጉሠ እስራኤል ጾም።

ትርጉም
የገዳም ባሕታውያን (እስራኤል) በጸሎት ቤት ኬብሮን ውስጥ ነጋሪትን በሰማችሁ ጊዜ አቤሴሎም መብል ነገሠ በሉ።ልማዱ ልቅሶ የሆነ የእስራኤል ንጉሥ ጾም ያን ጊዜ ይሰደዳልና ማለት ነው።

ሰም
በመሰረቱ ይህ ዓይነት ቅኔ የታሪክ ቅኔ ይባላል።ሰሙ አቤሴሎም በእስራኤል በነገሠ ጊዜ ንጉሠ እስራኤል ዳዊት መሰደዱን ይገልጻል።

ወርቅ
ወርቁ በዓቢይ ጾም ከበሮ አይመታም።ከበሮ መመታት የሚጀምረው በትንሳኤ ነው።እና ከበሮ መመታት ሲጀምር ጾም ንጉሠ እስራኤል ይሰደዳል ማለት።ጾሙ አልቆ 50 ቀን ምግብ ስለሚበላ ነው።

የቅኔው ሙያ
አመ.......ማንጸርያ
ሰማእክሙ....እንዳያስር አመ ይጠብቀዋል
ቀርን.....የሰማእክሙ ተሳቢ
ውስተ.....አስፈች
ቤት ኬብሮን....ምሳሌ ኬብሮን ሰም ቤት ወርቅ ተመስለው የአስፈች ባለቤት
ጸሎት.....የቤት ዘርፍ
ባሕታውያን....የሰማእክሙ ባለቤት
ዘ.........ዘርፍ አያያዥ
ገዳም.....የባሕታውያን ዘርፍ
በሉ.......ማሰሪያ አንቀጽ
ነግሠ......የበሉ ተለዋጭ/ተሳቢ
መብልዕ አቤሴሎም....ምሳሌ አቤሴሎም ሰም መብልእ ወርቅ ተመስለው የነግሠ ባለቤት
እስመ.......አስረጅ
አሜሃ......አንቀጽ አጎላማሽ
ይሰደድ....እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል
እንተ.....የንጉሥ ጾም ቅጽል
ልማድ....ውእቱን መርምሮ እንዳያስር እንተ ይጠብቀዋል
ብካይ.....የውእቱ ባለቤት
ንጉሥ ጾም....ምሳሌ ንጉሥ ሰም ጾም ወርቅ ተመስሎ የይሰደድ ባለቤት
እስራኤል.....የንጉሥ ዘርፍ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 8
ዋዜማ ዘመርጌታ ያሬድ

መነነቶ ወኀደገቶ
ለተክለሃይማኖት አብ ጽኑዐ ሃይማኖት መሐላ።
ብእሲት እግሩ ዘዓቢይ ኃይላ።
ወኢፈቀደት ነቢረ ውሳጤ ቀዊም መርጡላ።
ስድስተ አክናፈ ደቂቀ ተድላ።
በላእሌየ ወለደ ብሂላ።

ትርጉም
ኀይሏ ታላቅ የሆነች እግር ሚስቱ በመሐላ ሃይማኖት የጸና ተክለ ሃይማኖት አባትን ፈጽማ ናቀችው።በመቆም አዳራሿ ውስጥም መቀመጥን አልወደደችም።ስድስት የደስታ ልጆች ክንፎችን በላዬ ላይ ወልዷልና ብላ መቀመጥን አልወደደችም ነው።

ሰም
እንግዲህ አንዳንድ ሴቶች ባላቸው ከሌላ ሴት በላያቸው ላይ ሲወልድባቸው እምቢ ብለው ቤታቸውን ትተው ይወጣሉ ነው።

ወርቅ
የተክለ ሃይማኖት እግር በጸሎት ብዛት በተቆረጠች ጊዜ ስድስት የጸጋ ክንፍ እግዚአብሔር ሰጣቸው ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
መነነቶ ኀደገቶ.....በወ ተጃምለው ማሰሪያ አንቀጽ
ወ......ፍችው ፈጽሞ ሙያው ጀምላይ
ለ......ፍችው "ን" ሙያው ተጠቃሽ
ተክለ ሃይማኖት አብ....ምሳሌ አብ ሰም ተክለሃይማኖት ወርቅ ተመስለው የተጠቃሽ ባለቤት
ጽኑዕ....የተክለ ሃይማኖት አብ ቅጽል
ሃይማኖት መሐላ....ምሳሌ መሐላ ሰም ሃይማኖት ወርቅ ተመስለው የጽኑዕ ዘርፍ
ብእሲት እግር.....ምሳሌ ብእሲት ሰም እግር ወርቅ ተመስለው የመነነቶ ባለቤት
ዘ.........ቅጽል
ዐቢይ....ውእቱን መርምሮ እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
ኃይላ....የውእቱ ባለቤት
ወ........ፍችው ም ሙያው ደጋሚ
ኢፈቀደት....በወ የተደገመ ማሰሪያ አንቀጽ
ነቢር.........የኢፈቀደት ተሳቢ
ውሳጤ......አስፈች
ቀዊም መርጡል....ምሳሌ መርጡል ሰም ቀዊም ወርቅ ተመስለው የአስፈች ባለቤት
ስድስቱ......የአክናፍ ደቂቅ ቅጽል
አክናፍ ደቂቅ.....ምሳሌ ደቂቅ ሰም አክናፍ ወርቅ ተመስለው የወለደ ተሳቢ
ተድላ.......የደቂቅ ዘርፍ
በ......ማድረጊያ
ላዕል.....የማድረጊያ ባለቤት
ወለደ.....የብሂላ ተለዋጭ
ብሂላ......ቦዝ አንቀጽ ይስባል እንጂ አይሳብም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ቅኔ ክፍል 9
ሥላሴ ዘመምህር ገብረ ሥላሴ
አእላፍ የኀምይዎ
ለኪሩብ ካህን እንዘ ንጹሕ
ከመ እምኔሁ ተወልደ በሥጋ ተክለሃይማኖት መድኅን።
ለውእቱ እስመይመስሎ በመልክእ ወስን።
ወትእምርተ ዝንቱ ተረክበ በኀበ ተክለአብ ሕጻን።
እመንገለ ጸጋም ወየማን።
ወከመ ኪሩብ ቀሲስ በሊሐ ልሳን።
ወመጠኑ ዘኪሩብ መጠን።

ትርጉም
አዳኝ ተክለ ሃይማኖት በሥጋ ከእርሱ እንደተወለደ ንጹሕ ሲሆን ካህን ኪሩብን ወገኖች ያሙታል።በመልክና በደም ግባት እርሱን ይመስለዋልና።የዚህ ምልክትም በስተግራና በስተቀኝ በኩል በተክለ ሃይማኖት ሕጻን ዘንድ ተገኝቷልና።እንደ ኪሩብ ቄስም አንደበተ ርቱእ ነውና።ልኩም የኪሩብ ልክ ነውና።

ሰም
አንዳንድ ካህን ንጹሕ ሆኖ ሳለ ወገኖቹ ካህናት የእገሌ ልጅ የእርሱ ዲቃላ ነው በመልኩም በደም ግባቱም እርሱን ይመስላል ይሉታል።

ወርቅ
ተክለ ሃይማኖትም ስድስት የጸጋ ክንፍ ስለነበረው የኪሩብ ልጅ ነው ይሉታል ማለት ኪሩቤልን ይመስላል እያሉ ጻድቃን ያደንቁታል ማለት ነው።

የቅኔው ሙያ
አእላፍ....የየኀምይዎ ባለቤት
የኀምይዎ....ማሰሪያ አንቀጽ
ለ.........ተጠቃሽ
ኪሩብ ካህን....ምሳሌ ካህን ሰም ኪሩብ ወርቅ ተመስለው የተጠቃሽ ባለቤት
እንዘ......ማንጸሪያ
ንጹሕ....ውእቱን መርምሮ እንዳያስር እንዘ ይጠብቀዋል።
ከመ እምኔሁ.....
ተወልደ......እንዳያስር ከመ ይጠብቀዋል
በ.........ማድረጊያ
ሥጋ.......የማድረጊያ ባለቤት
ተክለ ሃይማኖት መድኅን.....ምሳሌ መድኅን ሰም ተክለ ሃይማኖት ወርቅ ተመስለው የተወልደ ባለቤት።
ለ........ተጠቃሽ
ውእቱ.....የተጠቃሽ ባለቤት
እስመ......አስረጅ
ይመስሎ....እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል
በ.....ማድረጊያ
ወ......አጫፋሪ
መልክእ ስን.........በወ ተጫፍረው የማድረጊያ ባለቤት
ወ......ደጋሚ
ትእምርት......የተረክበ ባለቤት
ዝንቱ.....የትእምርት ዘርፍ
ተረክበ....በወ የተደገመ ማሰሪያ
በ.........ማድረጊያ
ኀበ.......በር ከፋች
ተክለ አብ ሕጻን....ምሳሌ ሕጻን ሰም ተክለ አብ ወርቅ ተመስለው የማድረጊያ ባለቤት
እም.......
መንገለ....
ጸጋም የማን.....በወ ተጫፍረው...
ወ.......አውራጅ
ከመ......አስፈች
ኪሩብ ቀሲስ....ምሳሌ ቀሲስ ሰም ኪረብ ወርቅ ተመስለው የአስፈች ባለቤት።
በሊሕ....የኪሩብ ቀሲስ ቅጽል
ልሳን......የበሊሕ ዘርፍ
ወ.........አውራጅ
መጠን.....የውእቱ ባለቤት
ዘ..........ዘርፍ ደፊ ዘርፍ ደፊነቱም መጠነ ኪሩብ የሚያሰኝ
ኪሩብ የመጠን ዘርፍ።
መጠን.....

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 65
የውእቱ ትርጉም
ውእቱ ብእሲ ዘመዱ ውእቱ ለውእቱ ብእሲ ከሚለው ቃል ዘመዱ ውእቱ ያለው በ33 ይተረጎማል።በ10ሩ መራሕያን ሲዘልቅ ደግሞ 2640 ትርጉም እናገኝለታለን።ስለዚህ የውእቱ ብቻ 2640 ትርጉም አለው ማለት ነው። ለጊዜው 33ቱን ብቻ እንተረጉመዋለን። ውእቱ ብእሲ ዘመዱ ውእቱ ለውእቱ ብእሲ ያ ሰውየ ለዚያ ሰውየ ዘመዱ፦
ነው፥አለው፥ሆነው፥ኖረው፥ነበረው፥ተባለው፥አለለት፥ሆነለት፥ኖረለት፥ነበረለት፥ተባለለት፥አለበት፥ሆነበት፥ኖረበት፥ነበረበት፥ተባለበት፥ይሆነዋል፥ይኖረዋል፥ይባለዋል፥ይሆንለታል፥ይኖርለታል፥ይባልለታል፥ይሆንበታል፥ይኖርበታል፥ይባልበታል፥ይሁነው፥ይኑረው፥ይባለው፥ይኑርለት፥ይሁንለት፥ይባልለት፥ይሁንበት፥ይኑርበት፥ይባልበት።
ተብሎ ይተረጎማል እንግዲህ ውእቱ ውእቱን ሲስብ እንዲህ እንዲህ ከተተረጎመ ውእቱ አንተን ሲስብ ደግሞ ነህ፥አለኽው፥ሆንከው፥ኖርከው፥ተባልከው.... እያለ በላይኛው መሰረት ይሄዳል። እንደገና ይእቲ ውእቱን ስትስብ ደግሞ ውእቱ ብእሲ ዘመዳ ውእቱ ለይእቲ ብእሲት ይልና ያ ሰውየ ለዚያች ሴትዮ ዘመዷ ነው፥አላት፥ሆናት፥ኖራት፥ነበራት.... እያለ ይዘልቃል።

ሳይዘረዝር ደግሞ
ውእቱ ውእቱ ብሎ እርሱ ነው ሆነ ኖረ ነበረ ተባለ ይሆናል ይኖራል ይባላል ይሁን ይኑር ይባል ተብሎ ይተረጎማል።
አንተ ውእቱ ብሎ ደግሞ አንተ ነህ ኖርክ ተባልክ.... እያለ ይዘልቃል። አንተ አንተ ቢልም ከዝህ ጋር ይመሳሰላል።ውእቱ በነባር አንቀጽነቱ በ9ኙም መራሕያን ያገለግላል ያልነው ይህንን ነው።

የውእቱ አሉታ (negative) አኮ ነው። ውእቱ ነው አለ የሚል ከሆነ አኮ ውእቱ ካለ ግን አይደለም የለም እያለ አፍራሽ ያደርጋል።አለበት የሚለው የለበትም እያልክ በ33ቱም ይዘልቃል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 66
የቦ፥ሎ እና ሀሎ ዝርዝር
ቦ፥ሎ፥ሀሎ ብሎ አለ፥ኖረ፥ነበረ፥ይኖራል፥ ይኖር ነበር፥ይኑር ተብሎ ይተረጎማል።እንደገና
ቦ፥ሎ፥ሀሎ ብሎ አለህ፥ኖርክ፥ነበርክ፥ትኖራለህ ትኖር ነበር፥ኑር እያለ ይሄዳል።ስለዚህ እንድህ እንድህ እያልክ በ10ሩ መራሕያን ዝለቅ።

በዋናነት በ15 የሚያስተረጉመው በዝርዝር እርባታ ጊዜ ነው።ይኽውም
ቦ፥ቦቱ፥ሎ፥ሎቱ ብሎ አለው ኖረው ነበረው አለለት ኖረለት ነበረለት አለበት ኖረበት ነበረበት ይኖረዋል ይኖርለታል ይኖርበታል ይኑረው ይኑርለት ይኑርበት ይላል።
ቦ፥ብከ፥ሎ፥ለከ ብሎ አለህ ኖረህ ነበረህ አለልህ ኖረልህ ነበረልህ አለብህ ኖረብህ ነበረብህ ይኖርሀል ይኖርልሀል ይኖርብሀል እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል።

የቦ አሉታ አል ነው። ቦ አለ ካለ አልቦ ደግሞ የለም ይላል ማለት ነው። ባቲ አላት ካለ አልባቲ የላትም እያለ አሉታ ያደርጋል።

የሎ አሉታ ደግሞ ሐሰ ነው። ላቲ ይገባታል ተብሎ ከተተረጎመ ሐሰ ላቲ አይገባትም ይላል። ስለዝህ የሎ አሉታ ሐሰ ነው።

የሀሎ አሉታ ደግሞ ኢ ነው። ሀሎ አለ ካለ ኢሀሎ የለም ተብሎ ይተረጎማል።

በነገራችን ላይ ቦቱ በተለየ በእርሱ ይላል ባቲ በእርሷ እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል። ከአንቀጽ በኋላ እየመጣ ደግሞ ባት ባችሁ ብህ እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል።መጽአ ብየ ብሎ መጣብኝ መጽአ ብክሙ መጣባችሁ እያለ ይዘልቃል።

በተመሳሳይ የሎ ዝርዝርም ይገባዋል ይገባታል እያለ ይተረጎማል። ሎቱ ስብሐት ሲል ለምሳሌ ምስጋና ይገባዋል ማለት ነው።ለከ ይገባሀል ለኪ ይገባሻል እያለ ይሄዳል።ሰላም ለኪ ሲል ምስጋና ይገባሻል ማለት ነው።በተጨማሪ ከአንቀጽ በኋላ እየመጣ ልህ ልሽ ላችሁ እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል።መጽአ ለከ ብሎ መጣልህ ይላል። እሙት ለኪ ብሎ ልሙትልሽ እያለ ይዘልቃል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
2024/10/01 22:27:08
Back to Top
HTML Embed Code: