Telegram Web Link
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 35🌹
ባዕድ ከምዕላድ፣ ጥሬ ምዕላድ፣ ባዕድ ጥሬ ዘር፣

ባዕድ ከምእለድ የሚባለው ከግሡ መጀመሪያ እና መጨረሻ ባዕድ የሚጨምር ነው።
1) ቀሠፈ ብሎ መቅሠፍት
2) ጠብሐ ብሎ መጥባሕት
3) መሀረ ብሎ ትምህርት
4) አመረ ብሎ ትእምርት
5) ገረመ ብሎ ትግርምት
6) ወዐለ ብሎ መዓልት
7) ሰፈረ ብሎ መስፈርት
8) አንጦልዐ ብሎ መንጦላዕት
9) ዐደወ ብሎ ማዕዶት
10) አወፈየ ብሎ ትውፊት
ጥሬ ምእላድ የሚባለው ደግሞ መጨረሻ ላይ ባዕድ የሚጨምር እና ያ ባዕድ ቃል "ራብዕ፣ ኃም ስ፣ ሳብዕ" ሲሆን ነው።
1) ተትሕተ ብሎ ትሕትና
2) ተልእለ ብሎ ልእልና
3) ቀደሰ ብሎ ቅድስና
4) ነጽሐ ብሎ ንጽሕና
5) ሀለወ ኖረ ብሎ ህልውና
6) ለበወ ብሎ ልቡና
7) ተደንገለ ብሎ ድንግልና
8) ተባሕተወ ብሎ ብሕትውና
9) ተበኲረ ብሎ ብኲርና
10) ተሰብአ ብሎ ሰብእና
ባዕድ ጥሬ ዘር የሚባለው ደግሞ መነሻው ላይ ባእድ ጨምሮ የመጨረሻው ፊደል "ራብ ዕ፣ ኃምስ፣ ሳብዕ" የሚያደርግ ነው።
1) ርእየ ብሎ አርአያ
2) ሰንቀወ ብሎ መሰንቆ
3) ረግዐ ብሎ ቴሮጋ
4) መከለ ብሎ አሜከላ
እንዲህ እንዲህ እያሉ ይወጣሉ። የሰው ስምነት ካላቸው ወይም ቅጽልነት ካላቸው ባ እ ድ ውስጠ ዘ፣ ምእላድ ውስጠዘ ጥሬ ውስጠ ዘ ይባላሉ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴፭
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 36🌹
አዕማድ
አዕማድ የሚባሉ 5 ናቸው።
አድራጊ ቀተለ ገደለ
አስደራጊ አቅተለ አስገደለ
ተደራጊ ተቀትለ ተገደለ
ተደራራጊ ተቃተለ ተገዳደለ
አደራራጊ አስተቃተለ አገዳደለ
እኒህ ደግሞ ለየብቻቸው እስከ ንዑስ አንቀጽ ይረባሉ።
ቀተለ
ይቀትል
ይቅትል
ይቅትል
ቀቲል/ሎት
አቅታሊ
አቅታልያን
አቅታሊት
አቅታልያት

አቅተለ
ያቀትል
ያቅትል
ያቅትል
አቅትሎ/ሎት
አቅታሊ
አቅታልያን
አቅታሊት
አቅታልያት

ተቃተለ
ይትቃተል
ይትቃተል
ይትቃተል
ተቃትሎ/ሎት
ተቃታሊ
ተቃታልያን
ተቃታሊት
ተቃታልያት

ተቀትለ
ይትቀተል
ይትቀተል
ይትቀተል
ተቀትሎ /ሎት
ተቀታሊ
ተቀታልያን
ተቀታሊት
ተቀታልያት

አስተቃተለ
ያስተቃትል
ያስተቃትል
ያስተቃትል
አስተቃትሎ/ሎት
አስተቃታሊ
አስተቃታልያን
አስተቃታሊት
አስተቃታልያት

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 37🌹
ቦዝ አንቀጽ
ቦዝ አንቀጽ የሚባሉት በልቶ፣ ሠርቶ፣ ኖሮ ወዘተ ለማለት የምንጠቀመው ሲሆን በ10ሩ መራሕያን እንደሚከተለው ነው።
1) ቀዲሶ አመስግኖ
2) ቀዲሶሙ አመስግነው
3) ቀዲሳ አመስግና
4) ቀዲሶን አመስግነው
5) ቀዲሰከ አመስግነህ
6) ቀዲሰክሙ አመስግናችሁ
7) ቀዲሰክን አመስግናችሁ
8) ቀዲሰኪ አመስግነሽ
9) ቀዲስየ አመስግኜ
10) ቀዲሰነ አመስግነን
ይላል ማለት ነው።ለምሳሌ አመስግነን መጣን ለማለት ቀዲሰነ መጻእነ እንላለን ማለት ነው።የቀደሰ ቤት ሆነው መጨረሻ ፊደላቸው "የ" የሆኑ ግሦች ቅድመ መድረሻቸውን ሳድስ አድርገው ይዘረዘራሉ።
1) ሀልዮ አስቦ
2) ሀልዮሙ አስበው
3) ሀልያ አስባ
4) ሀልዮን አስበው
5) ሀልየከ አስበህ
6) ሀልየክሙ አስባችሁ
7) ሀልየክን አስባችሁ
8) ሀልየኪ አስበሽ
9) ሀልይየ አስቤ
10) ሀልየነ አስበን
ይላል ማለት ነው። አስተውል በአነ ብቻ መድረሻውን ሳድስ ሲያደርግ በሌላው ግን ግእዝ አድርጎ ይዘረዘራል።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 38🌹
የ "በ፣ለ፣ነ" ዝርዝር
ውእቱ ነዋ፣ናሁ....እነሆ
ውእቶሙ ነዮሙ......እነኋቸው
ውእቶን ነዮን.......እነኋቸው
ይእቲ ነያ......እነኋት
አንተ ነየከ..... እነሆህ
አንትሙ ነየክሙ...እነኋችሁ
አንቲ ነየኪ......እነሆሽ
አንትን ነየክን.....እነኋችሁ
አነ ነየኩ....... እነሆኝ
ንሕነ ነየነ........እነሆን
ይላል።ይህም በምሳሌ ለምሳሌ ጌታችን በመስቀል ሳከ ለዮሐንስ እነኋት እናትህ እነሆ ልጅሽ ብሏታል። ይህ በግእዝ ቋንቋ "ነያ እምከ ወነዋ ወልድኪ" ይላል። ቀጥሎ የቦን እና የሎን ዝርዝር እንመልከት።
ውእቱ ቦቱ፣ሎቱ
ውእቶሙ ቦቶሙ፣ሎቶሙ
ይእቲ ባቲ፣ላቲ
ውእቶን ቦቶን፣ሎቶን
አንተ ብከ፣ለከ
አንትሙ ብክሙ፣ለክሙ
አንቲ ብኪ፣ለኪ
አንትን ብክን፣ለክን
አነ ብየ፣ልየ/ሊተ
ንሕነ ብነ፣ለነ
ይላል።እኒህ አንቀጽ ተቀባይ ሲሆኑ የቦ እና የሎ ዝርዝሮች ከላይ ወደታች በቅደም ተከተል በት/ለት፣ ባቸው/ላቸው፣ ብሽ/ልሽ፣ ባቸው/ላቸው፣ ብህ/ልህ፣ ባችሁ/ላችሁ፣ ብሽ/ልሽ፣ ባችሁ/ላችሁ፣ ብኝ/ልኝ፣ ብን/ልን ተብለው ይተረጎማሉ። በምሳሌ ለማየት ያህል፦
መጽአ ብክሙ...መጣባችሁ
ሰአሊ ለነ.......ለምኝልን
መጽአ ለኪ......መጣልሽ
ንዒ ሊተ..........ነይልኝ
ሠርዐ ለነ........ሠራልን
እያለ ይዘረዘራል ማለት ነው።በተረፈ የቦ እና የሎ ሌላ ሰፊ ዝርዝር ስላለው ከዚህ ቀደም ከግእዝ ክፍል በጻፍኩ https://www.tg-me.com/learnGeez1/902 አካባቢ ታገኙታላችሁ። ያንን ማየት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
.......... #ቅዱስ #ገብርኤል.........
በመላእክት ዓለም ዲያብሎስ አምላክ ነኝ ብሎ በውሸት በተናገረ ጊዜና ሁከት በጸና ጊዜ በያለንበት እንቁም ብሎ መላእክትን ያረጋጋ ቅዱስ መልአክ ነው። ንቁም በበህላዌነ በያለንበት እንቁም አለ። በዚህም ምክንያት ለድንግል ማርያም የምሥራች ዜና/ብሥራት እንዲናገር የተገባ ሆነ። አዳምን ያረጋጋው የነበረ መልአክም ቅዱስ ገብርኤል ነው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ሠለስቱ ደቂቅን ንጉሥ ናበከደነጾር ወደ እሳት በወረወራቸው ጊዜ እሳቱ እንዳያቃጥላቸው ያደረገና በመካከላቸው የተገ ኘ ቅዱስ ገብርኤል ነው። ታኅሣሥ 19 የምናከብረው በዓል ይህንን በተመለከተ ነው። እግዚአብሔር ሰውን ወዳጅ ስለሆነ ለሚያመልኩት እንዲረዷቸው መላእክትን ይልካል።

በሐዲስ ኪዳን ለድንግል ማርያም የምሥራችን የተናገረ እርሱ ነው። በላይ ቤት የመጻሕፍት ትርጓሜ ስልት ለድንግል ማርያም የምሥራች እንዲናገር ለምን ገብርኤል ተላከ? ለሚለው ጥያቄ ሲያብራራ ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ ገብርኤል ማለት የ ስሙ ትርጓሜ ሰውም አምላክም ማለት ነው። ስለዚህ አምላክ ሰው እንደሚሆን ሰውም አምላክ እንደሚሆን በዚህም ለሰው ልጅ ታላቅ ደ ስታ እንደሚሆን የስሙ ትርጓሜ ከተላከበት ጉዳይ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ነው ይላል።

በዘመነ ሰማእታት ሰማእታትን በገድል እንዲጸኑ የተራዳቸው እርሱ ነው። ቅድስት ኢየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከፈላ ውሃ ያዳናቸው እርሱ ነው። መላእክት እኛን እንዲጠብቁን እና እንዲረዱን የሰጠን ፈጣሪያችን ነው። ስለዚህም የጸጋ ምሥጋና እናመሰግናቸዋለን። የጸጋ ክብር እናከብራቸዋለን።

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ከዛሬ ወረቦች የተወሰኑትን በድምጽ
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
።።።።#የተቀደደው_ደብዳቤ።።።።
።።።።።#የተሰረዘው_እዳ።።።።።።
ሰዓቱ፦ ከሌሊቱ10:00
ዕለቱ፦ማክሰኞ
ቀኑ፦ 11
ወሩ፦ጥር
ወንጌላዊው፦ ሉቃስ
ዓመተ ምህረቱ፦ 31 ነው።
ቦታውን፦ በእስራኤል ሀገር በዮርዳኖስ ወንዝ
ወቅቱ፦ከቅዝቃዜው አልፎ ውርጫማ
በቦታው_የነበሩ፦ ህዝብ፣አህዛብ፣ ዮሐንስ፣ ስላሴ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በተለየ አካሉ መንፈስ ቅዱስ፣ በተለየ አካሉ አብ በደመና ውስጥ
ተአምር፦ የዮርዳኖስ ወንዝ ተናወጠ ወደ ኋላው ሸሸ

ኦሪት ዘፍጥረት 3፥23 " እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከዔድን ገነት አስወጣው።"

#አዳምና ሔዋን #ዕፀ_በለስን በልተው ከገነት ተባረው ወደዚህ ምድር ከመጡ በኋላ በጠላት ዲያብሎስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።
#ዲያብሎስም ዋና ዓላማው በእባብ ተሰውሮ መግባት ወደማይገባው ገነት የገባው አዳምን ከገነት አስወጥቶ እንደፈለገ ሊጫወትበት ወደሚችል ገላጣና ለመጣል ምቹ ቦታን ይፈልግ ነበርና እንደተመኘውም እንግልት፣ ድካም፣ ሞት ባለባት እሾክና አሜከላም በምታበቅለው በዚህች ምድር አገኘው።
#ዲያብሎስም አዳምና ሔዋንን ብዙ አንገላታቸው አሰቃያቸው።
ሁሌ ሲያማርሩት የሰማው ሰይጣን ከእለታት አንድ ቀን ከእነሱ ፊት ቀረበና #ቀንበር_ላቀልላችሁና የእኔ ለመሆናችሁ #ደብዳቤ_እንጻጻፍ አላቸው።
እነሱም መከራው በዝቶባቸው ነበርና #ፈቃደኛ ሆኑ።
ደብዳቤውም በማይሰበርና በማይጠፋ የዐለት #ድንጋይ ላይ እንዲህ ተብሎ ተጻፈ
1.አዳም የዲያብሎስ #ባሪያ አገልጋይ ነው
2.ሔዋን የዲያብሎስ #ገረድ አገልጋይ ናት
ይህንን ደብዳቤ ተፈራርመው
አንዱ #በሲዖል
አንዱ #በዮርዳኖስ ወንዝ ተጣለ
ጠላት ዲያብሎስ ግን ምን ጊዜም ሀሰትና #የሀሰትም_አባት ነውና አቀልላችኋለሁ ያላቸውን ቀንበር እጥፍ አድርጎ አከበደባቸው።
አዳምና ሔዋን እሾህና አሜከላ እየወጋቸው መከራም በዝቶባቸው እያለቀሱ << በቃ ይህ ነው የእኛ የዘለዓለም እጣ ፈንታ ድካምና ሞት፣ አትሞቱም ያለን የእግዚአብሔር ቃል ናፈቀን አሉና>> ምርር ብለው #አለቀሱ
እያለቀሱ እየተከዙ እያለ #እግዚአብሔር_ወደ_እነሱ_ቀረበና አዎ የማይታበል ቃሌ ነው። ዕፀ በለስን ባትበሉ ኖሮ ዘለዓለማዊና #ህያው ነበራችሁ። ነገር ግን ዕፀ በለሥን በላችሁና የሞት ሞትን ሞታችህ አላቸው።
በሉ አዳምና ሔዋን ሆይ ፍጠረን ሳትሉኝ ፈጠርኳች አሁን ግን በራሳችሁ ፍላጎት ተሰቃያችሁ ሞታችሁ። ቢሆንም እኔ ከልጅ ልጃችሁ ተወልጄ #አድናችኋለሁ
ቀንበር ያጸናባችሁንም የእዳ ደብዳቤ እቀድድላችኋለሁ
ባርነትን ሰርዠ ያጣችሁትን ልጅነት እመልስላችኋለሁ
አባታችን ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት ፀጋን አድላችኋለሁ
እኔም ልጆቸ ብዬ እጠራችኋለሁ
እስከዚያ ድረስ እናንተ ያመጣችሁትን እዳ ልጆቻችሁም መቅመስ አለባቸውና (ጥንተ አብሶ) 5500 ዓመት የቀኖና ጊዜ ሰጥቻችኋለሁ አለና እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገብቶላቸው ሄደ።
እነሱም በጉጉት ሲጠባበቁ ሲኖሩ ሳለ ዘመኑ ሲደርስ ተወለደና በ30 ዘመኑ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ
እንደሰውነቱ ረግጦ
እንደ አምላክነቱ አቅልጦ #የእዳ_ደብዳቤውን_ቀደደው
በምትኩ የልጅነትን ደብዳቤ ጽፎ በአዳምና በልጆቹ ልብ ውስጥ አተመው።
ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም አዳምና ሔዋን በ40 እና በ80 ቀናቸው ገብተው ያጧትን ገነት ለማውረስ።
በአንጻሩ በ40 እና በ80 ቀን ወደ ዮርዳኖስ(ቤተ ክርስቲያን) ወስዳ
1.በጥምቀት የስላሴ የልጅነት ደብዳቤ ጽፋ
2.በሜሮን ለተጻፈው ደብዳቤ ህጋዊነት ማህተም አትማ
3. በቅዱስ ስጋውና በክቡር ደሙ የዘለዓለም ህይወት አሰጥታ በክብርና በሞገስ የምታሳድገው የምታኖረው ለዚህ ነው።

።።።። #ጥምቀት_የነጻነት_ቀን_ነው።።።።
።።#አዳም_ከጥምቀት_በፊት
ባሪያ አገልጋይ ነበር
የፈለገውን ማድረግ አይችልም
ከገነት ርቆ ርስቱን ተነጥቆ በሲዖል ይኖር ነበር
የተረገመና የልጅ ልጆቹም ርጉማን ነበሩ
ተቅበዝባዝ ነበር
ሟቾ ነበር

።።።።#አዳም_ከጥምቀት_በኋላ።።።
የእግዚአብሔር ልጅ ሆነ
የፈለገውን ማድረግ ይችላል
ከሲዖል ወጥቶ ወደነበረበት ወደርስቱ ገነት ተመለሰ
እርግማን ተወገደለት
የተረጋጋ ሆነ
~~ህያው ሆነ ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋገረ

#የትናንትናው_አዳም እንዲህ ከብዙ ድካም በኋላ
ቀንበሩ ከላዩ ላይ ተነሳለትና ሠላሙ ታወጀ
በዚህም ሰላሙን የመለሰለት ጌታ እንዲህ ተብሎ ተዘመረለት
የሠላሙ መሪ የሠላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ

ይህ መልካሙ አባታችን ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም
የማቴወስ ወንጌል 11፥28-30
እናንተ ደካሞች #ሸክማችሁ_የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
#ቀንበሬ_ልዝብ ሸክሜም #ቀሊል ነውና።

።።።።።#ጌታን_ሆይ።።።።።
~እኛም ልጆችህ ዛሬ በጠነከረ የሐጢአት ህይወት ውስጥ ነን
~በመለያየትና በአድማ መንፈስ ተወስደናል
~ወንድም ወንድሙን እየገደለ ነው
~ዐየሩ ተበክሎ ጤናችን አጥተናል
~አንጀራው ጠፍቶ ተርበናል
~አልጋችን በእንባ ርሷል
~መሬቱ አኬልዳማ(የደም መሬት) ሆኗል
~የፍርድ ወንበሮች ሁሉ ተጣመዋል
~በፊታችንም በሀዘን ጠውልጓል
~ሠላም ከእኛ ከራቀ ቆይተናል
~በልዩ ልዩ መከራና ሲቃይ ውስጥ ነንና በቶሎ ና ምህረትህን ላክልን #ከመከራችንም_አድነን

+++++#እንኳን_ለብርሃነ_ጥመቀቀቱ_አደረሰን+++++

መምህር አሸናፊ መልካሙ ዘዋግ ኽምራ
ጥር10/2014
ጾመ ድጓ.pdf
21.4 MB
#ጾመ_ድጓ

ከቅዱስ ያሬድ መጽሐፎች አንዱ ነው
የግእዝ ትምህርትን

ሰኞ

ረዕቡ

እና

አርብ

ከኰኲሐ ሃይማኖት ጋር በመተባበር እናቀርብላችኋለን!!!

ይከታተሉን!!
#ነነዌ_እና_የአጽዋማትና_በዓላት_አወጣጥ

❖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዐት መግቢያቸውና መውጪያቸው የሚዘዋወር የሐዲስ ኪዳን አጽዋማትና በዓላት 11 ናቸው፡፡ እነዚህም ጾመ ነነዌ ፣ በአተ ጾም(ዐቢይ ጾም) ፣ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ስቅለት ፣ ትንሣኤ ፣ ርክበ ካህናት ፣ ዕርገት ፣ ጰራቅሊጦስ ፣ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ድኅነት ናቸው፡፡ ሁሉም የሚገቡበትን ለማወቅ መሠረታቸው ነነዌ ነው፡፡

→ ዐቢይ ጾም ነነዌ በገባ በ14ኛው ቀን ይገባል፤
→ ደብረ ዘይት ነነዌ በገባ በ41ኛው ቀን ይውላል፤
→ ሆሣዕና ነነዌ በገባ በ62ኛው ቀን ይውላል፤
→ ስቅለት ነነዌ በገባ በ67ኛው ቀን ይውላል፤
→ ትንሣኤ ነነዌ በገባ በ69ኛው ቀን ይውላል፤
→ ርክበ ካህናት ነነዌ በገባ በ93ኛው ቀን ይውላል፤
→ ዕርገት ነነዌ በገባ በ108ኛው ቀን ይውላል፤
→ በዓለ ኀምሳ ነነዌ በገባ በ118ኛው ቀን ይውላል፤
→ ጾመ ሐዋርያት ነነዌ በገባ በበ119ኛው ቀን ይገባል፤
→ ጾመ ድኅነት ነነዌ በገባ በ121ኛው ቀን ይገባል፡፡
ስለዚህ አንድ ጊዜ የነነዌ መግቢያ ከታወቀ ሌሎቹን ማግኘት ቀላል ነው፡፡

❖ ነነዌን ለማግኘት ደግሞ ጥልቅ ከሆነው የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ ግድ ነው፡፡ ከብዙ መንገዶች ውስጥ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡

❖ ነነዌን ለማግኘት ዓመተ ዓለም፣ መጥቅዕ፣ ወንበር፣ መደብ፣ የዕለታት ተውሳክ፣ መባጃ ሐመር፣ ዐቢይ ቀመር፣ ማእከላዊ ቀመር፣ ንኡስ ቀመር የተባሉትን የስሌት ጽንሰ ሐሳቦችን መረዳት ተገቢ ነውና በቅድሚያ እነርሱን እያብራራን እናስላ፡፡

✥ ዓመተ ዓለም፦
የዘመነ ብሉይና የዘመነ ሐዲስ ድምር ነው፡፡ በመሆኑም የዘንድሮው ዓመተ ዓለም 5500 + 2014 = 7514 ይሆናል፤

✥ ዐቢይ ቀመር፦
በባሕረ ሐሳብ ትምህርት በየ502 ዓመቱ የሚመጣውን ዑደት (ሳይክል) ዐቢይ ቀመር እንለዋለን፡፡ (ወንጌላውያን በየዐራት ዓመቱ የሚመጡ መሆናቸውን ዐውደ ወንጌላውያን በሚለው ቃል፣ ዓመት የ365/6 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ዓመት በሚለው ቃል፣ ወር የ30 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ወርኅ በሚለው ቃል፣ ሳምንት የ7 ቀናት ዑደት መሆኑን ዐውደ ሳምንት በሚለው ቃል እንደምንገልፀው በየ502 ዓመቱ የሚከሰቱ ክስተቶችን በዐውደ ቀመር እንጠራቸዋለን፡፡ ቁጥሩንም ዐቢይ ቀመር እንለዋለን፡፡) ብዙ ማብራሪያ ያለው ቢሆንም ለጊዜው ዐቢይ ቀመር 502 ዓመት መሆኑን መያዝ በቂ ነው፤

✥ ማእከላዊ ቀመር፦ ይህ 76 ዓመት ነው፤

✥ ንኡስ ቀመር፦ ይህ 19 ዓመት ነው፤

✥ መደብ፦ ማለት ዓመተ ዓለም ለዐቢይ ቀመር ተካፍሎ፣ ቀሪው እንደገና ለማእከላዊ ቀመር ተካፍሎ፣ የዚህም ቀሪ እንደገና ለንኡስ ቀመር ተካፍሎ ከውጤቱ ባሻገር የሚገኘው ትርፍ/ቀሪ ነው፡፡

★ የ2014 ዓ.ም መደብ
→ ዓመተ ዓለም / ዐቢይ ቀመር = 7514/ 502 = 14 ደርሶ 486 ይቀራል፤

→ ቀሪው/ ለማእከላዊ ቀመር = 486/76 = 6 ጊዜ ደርሶ 30 ይቀራል፤

→ ቀሪው / ለንኡስ ቀመር = 30/19 = 1 ደርሶ 11 ይቀራል፤

★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መደብ 10 ነው፡፡

✥ ወንበር፦ ማለት ደግሞ ዓመተ ዓለም ለንኡስ ቀመር ተካፍሎ ከውጤቱ ባሻገር ከሚገኘው ቀሪ ላይ 1 ሲቀነስ የሚገኘው ውጤት ነው፡፡

★ የ2014 ዓ.ም.ወንበር
→ 7514 / 19 = 395 ደርሶ 9 ይቀራል

→ 9 – 1 = 8

★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም ወንበር 8 ነው፡፡

✥ መጥቅዕ፦ ማለት ነጋሪት ማለት ነው፡፡ ነጋሪት ሲመታ ሕዝብ አንደሚሰበስብ በመጥቅዕ የተሰየመው ዕለት ደግሞ አጽዋማትንና በዓላትን ስለሚሰበስብ መጥቅዕ ይባላል፡፡ መጥቅዕን ለማግኘት የዘመኑን ወንበር በ19 በማባዛት ውጤቱ ከ30 ቢበልጥ ለ30 ከተካፈለ በኋላ የሚገኘው ትርፍ የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል፡፡ ከ30 ባይበልጥ ግን የተገኘው ውጤት የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል፡፡

★ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ = የ2014 ዓ.ም ወንበር X 19 = 8 X 19 = 152

→ 152 ከ30 ስለሚበልጥ ለ30 እናካፍለዋለን።
→ 152 / 30 = 5 ደርሶ 2 ይቀራል፤

★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነው።

✥ መጥቅዕ ከ14 ከበለጠ በመስከረም፣ ከ14 ካነሰ በጥቅምት ይውላል፡፡

❖ የዘንድሮው መጥቅዕ 2 በመሆኑና ከ14 በማነሱ የሚውለው በጥቅምት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው፡፡ የ2014 ዓ.ም ጥቅምት 2 የዋለው ማክሰኞ ዕለት ነበር፡፡

✥ የዕለታት ተውሳክ፦ ማለት ምን እንደሆነና ከየት እንደተገኘ ለማወቅ አንባቢን ከመጻሕፍት እንዲያነብ በመጋበዝ የዕለታት ተውሳክን እንጠቁም።

√ የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው፤
√ የእሑድ ተውሳክ 7 ነው፤
√ የሰኞ ተውሳክ 6 ነው፤
√ የማክሰኞ ተውሳክ 5 ነው፤
√ የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው፤
√ የሐሙስ ተውሳክ 3 ነው፤
√ የዓርብ ተውሳክ 2 ነው፡፡

✥ መባጃ ሐመር፦ በዓለ መጥቅዕና የበዓለ መጥቅዑ ዕለተ ተውሳክ ተደምረው የሚገኘው ውጤት ከ30 ባይበልጥ መባጃ ሐመር ይባላል፡፡ የበዓለ መጥቅዑና የዕለቱ ተውሳክ ተደምረው ድምሩ ከ30 ቢበልጥ ከድምሩ ላይ 30 ተቀንሶለት ተራፊው መባጃ ሐመር ይባላል፡፡ መባጃ ሐመር ጾመ ነነዌን ለማግኘት የሚያገለግል ቁጥር ነው፡፡

★ የ2014 ዓ.ም መባጃ ሐመር
→ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ + የመጥቅዑ ዕለተ ተውሳክ
(የመጥቅዑ ተውሳክ 5 ነው ምክንያቱም ጥቅምት 2 ማክሰኞ ስለዋለና የማክሰኞ ተውሳክ ደግሞ 5 ስለሆነ ነው፡፡)

→ 2 + 5 = 7
★ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መባጃ ሐመር 7 ነው፡፡

✥ በመሆኑም የ2014 ዓ.ም ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 ይገባል ማለት ነው፡፡ በዚህ መንገድ ነነዌ አንዴ ከተገኘ ሌሎቹን አጽዋማትና በዓላት በመደመር ብቻ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡

✥ የ2014 ዓ.ም ዐቢይ ጾም የሚገባው መች እንደሆነ ለማወቅ ቀደም ሲል «ዐቢይ ጾም ነነዌ በገባ በ14ኛው ቀን ይገባል» ስላልን ከነነዌ ተነሥተን በመቁጠር ማወቅ እንችላለን።

• የ2014 ዓ.ም ዐቢይ ጾም መግቢያ = የካቲት 7 + 14 = የካቲት 21

• የ2014 ዓ.ም ደብረዘይት = የካቲት 7 + 41 = መጋቢት 18
• የ2014 ዓ.ም ሆሣዕና = የካቲት 7 + 62 = ሚያዝያ 9
• የ2014 ዓ.ም ስቅለት = የካቲት 7 + 67 = ሚያዝያ 14
• የ2014 ዓ.ም ትንሣኤ = የካቲት 7 + 69 = ሚያዝያ 16
• የ2014 ዓ.ም ርክበ ካህናት = የካቲት 7 + 93 = ግንቦት 10
• የ2014 ዓ.ም ዕርገት = የካቲት 7 + 108 = ግንቦት 25
• የ2014 ዓ.ም በዓለ ኀምሳ (ጰራቅሊጦስ) = የካቲት 7 + 118 = ሰኔ 5
• የ2014 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት = የካቲት 7 + 119 = ሰኔ 6
• የ2014 ዓ.ም ጾመ ድኅነት = የካቲት 7 + 121 = ሰኔ 8
አጽዋማቱንና በዓላቱን የበረከትና የረድዔት ያድርግልን፡፡


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
2024/10/01 09:33:14
Back to Top
HTML Embed Code: