Telegram Web Link
ግእዝ-ክፍል ፳፭
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ይህንን ሊንክ ይጫኑት&Share
👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

https://www.tg-me.com/learnGeez1
https://www.tg-me.com/learnGeez1

👆 Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!

@learnGeezbot
👆👆👆
ለአስተያየት ይጠቀሙ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 26🌹
ግእዝ አማርኛ English
ተንበለ ለመነ Beg
ይተነብል ይለምናል Will beg
ይተንብል ይለምን Let him beg
ይተንብል ይለምን ዘንድ
እያለ የሚረባበት መንገድ አለ። እርሱን ዛሬ በደንብ እንመለከታለን። ካልዓይ አንቀጽ ወይም ትንቢት አንቀጽ በግእዝ ቋንቋ ወደፊት የሚሆንን ነገር የምንገልጽበት ነው። ይህም የራሱ ሕግ አለው።ለዚህ የሚያገለግሉም አስራው የሚባሉ አሉ። እኒህም "ት፣ እ፣ ይ፣ ን" ናቸው። ትእዛዝ አንቀጽ ደግሞ ትእዛዝን ይመለከታል ።ይምጣ ይሥራ ያመስግኑ ዓይነት ቃላት ናቸው። ዘንድ አንቀጽ የሚባለው ደግሞ ይመጣ ዘንድ፣ ይሠራ ዘንድ፣ ይሆን ዘንድ ወዘተ እያልን የምንገልጽበት ነው። ተንበለ ኃላፊ ወይም ቀዳማይ አንቀጽ (past tense) ይባላል። ይተነብል ትንቢት ወይም ካልዓይ አንቀጽ ይባላል (Future tense)።

በውእቱ፣ በውእቶሙ፣ በውእቶን ጊዜ ካልዓይ አንቀጽን እና ትእዛዝ አንቀጽን እንዲሁም ዘንድ አንቀጽን ለመፍጠር ከአሥራው ውስጥ የምንጠቀመው "ይ"ን ነው። ይህም በምሳሌ እንደሚከተለው ነው።
ውእቱ ቀደሰ አመሰገነ
ይቄድስ ያመሰግናል
ይቀድስ ያመሰግን ዘንድ
ይቀድስ ያመስግን

ውእቶሙ ቀደሱ አመሰገኑ
ይቄድሱ ያመሰግናሉ
ይቀድሱ ያመሰግኑ ዘንድ
ይቀድሱ ያመስግኑ

ውእቶን ቀደሳ አመሰገኑ
ይቄድሳ ያመሰግናሉ
ይቀድሳ ያመሰግኑ ዘንድ
ይቀድሳ ያመስግኑ
ይላል።አስተውል "ይ" የሚል አስራው ጨምረናል። ሁልጊዜም በውእቱ በውእቶሙ እና በውእቶን ዝርዝር "ይ"ን እንጠቀማለን።

በአንተ፣ በአንቲ፣ በአንትሙ፣ በአንትን፣ በይእቲ ጊዜ ደግሞ ካልዓይ እና ዘንድ አንቀጽን ለመፍጠር ከአስራው ውስጥ "ት"ን እንጠቀማለን። በትእዛዝ አንቀጽ ጊዜ በሁለተኛ መደቦች "ት" አይኖርም። በሦስተኛ መደቦች ይእቲን ጨምሮ ግን በትእዛዝ አንቀጽ ይገኛል።እርሱን እንደሚከተለው እንመልከት።
አንተ ቀደስከ አመሰገንክ
ትቄድስ ታመሰግናለህ
ትቀድስ ታመሰግን ዘንድ
ቀድስ አመስግን
አንትሙ ቀደስክሙ አመሰገናችሁ
ትቄድሱ ታመሰግናላችሁ
ትቀድሱ ታመሰግኑ ዘንድ
ቀድሱ አመስግኑ
አንትን ቀደስክን አመሰገናችሁ
ትቄድሳ ታመሰግናላችሁ
ትቀድሳ ታመሰግኑ ዘንድ
ቀድሳ አመስግኑ
አንቲ ቀደስኪ አመሰገንሽ
ትቄድሲ ታመሰግኛለሽ
ትቀድሲ ታመሰግኚ ዘንድ
ቀድሲ አመስግኚ
ይእቲ ቀደሰት አመሰገነች
ትቄድስ ታመሰግናለች
ትቀድስ ታመሰግን ዘንድ
ትቀድስ ታመስግን
ይላል።አስተውል በትእዛዝ አንቀጽ ጊዜ በሁለተኛ መደቦች "ት" የለም ። ከዚያ ይልቅ ቀጥታ ቀድስ፣ ቀድሱ፣ ቀድሲ፣ ቀድሳ ይላል። በሦስተኛ መደቦች እና ቀጥለን በምንመለከታቸው አንደኛ መደቦች ግን አስራው (ት፣ እ፣ ይ፣ ን) አይጠፉም። ይቀድሱ፣ ይቀድስ፣ ትቀድስ፣ ይቀድሳ ማለቱ አስተውል። በአንደኛ እና በሦስተኛ መደቦች ዘንድ አንቀጽ እና ትእዛዝ አንቀጽ ተመሳሳይ ናቸው። በሁለተኛ መደቦች ግን የተለያዩ ናቸው። ልዩነታቸውን አስተውል።

በአነ ጊዜ "እ"ን በንሕነ ጊዜ ደግሞ "ን"ን እንጠቀማለን።
አነ ቀደስኩ አመሰገንኩ
እቄድስ አመሰግናለሁ
እቀድስ አመሰግን ዘንድ
እቀድስ ላመስግን
ንሕነ ቀደስነ አመሰገንን
ንቄድስ እናመሰግናለን
ንቀድስ እናመሰግን ዘንድ
ንቀድስ እናመስግ
ይላል ማለት ነው።በቀጣይ ክፍል 8ቱ አርእስተ ግሥ የየራሳቸው አረባብ ስላላቸው እነርሱን እንመለከታለን።የሚከብድ አይደለም። ስምንቱ አርእስተ ግሥ አረባባቸው ከታወቀ ሌላው ብዙም አይከብደንም።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፳፮
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 27🌹
የአርእስተ ግሥ እርባታ
1) ጦመረ ጻፈ
ይጦምር ይጽፋል
ይጦምር ይጽፍ ዘንድ
ይጦምር ይጻፍ

2) ዴገነ ተከተለ
ይዴግን ይከተላል
ይዴግን ይከተል ዘንድ
ይዴግን ይከተል

3) ባረከ አመሰገነ
ይባርክ ያመሰግናል
ይባርክ ያመሰግን ዘንድ
ይባርክ ያመስግን

4) ማሕረከ ማረከ
ይማሐርክ ይማርካል
ይማሕርክ ይማርክ ዘንድ
ይማሕርክ ይማርክ

5) ክህለ ቻለ
ይክህል/ይክል ይችላል
ይክሀል ይችል ዘንድ
ይክሀል ይቻል

6) ቀተለ ገደለ
ይቀትል ይገድላል
ይቅትል ይገድል ዘንድ
ይቅትል ይግደል

7) ቀደሰ አመሰገነ
ይቄድስ ያመሰግናል
ይቀድስ ያመሰግን ዘንድ
ይቀድስ ያመስግን

8) ተንበለ ለመነ
ይተነብል ይለምናል
ይተንብል ይለምን ዘንድ
ይተንብል ይለምን

9) ቆመ ቆመ
ይቀውም ይቆማል
ይቁም ይቆም ዘንድ
ይቁም ይቁም

10) ሤመ ሾመ
ይሠይም ይሾማል
ይሢም ይሾም ዘንድ
ይሢም ይሹም

11) ገብረ ሠራ
ይገብር ይሠራል
ይግበር ይሠራ ዘንድ
ይግበር ይሥራ

12) ነደ ነደደ
ይነድድ ይነዳል
ይንድድ ይነድ ዘንድ
ይንድድ ይንደድ

በ12 ቁጥር ያሉት። ሁለት ፊደል ሆነው የመጨረሻው ፊደል ጠብቆ ሲነበብ የሚኖራቸው አረባብ ደጊመ ቃል በማምጣት ነው።ብሎ ይረባል ማለት ነው።የዴገነ ቤቶች ዴገነን መስለው የቀተለ ቤቶች የቀተለን መስለው ሌሎችን መሰሎቻቸውን መስለው ይረባሉ። ለምሳሌ ኖኀ ረዘመ ማለት ነው ። የቆመ ቤት ስለሆነ ይቀውም እንዳለ ይነውኅ ይላል ማለት ነው። የእነዚህን የ8ቱን አረባብ በደምብ መያዝ ያስፈልጋል።
ግእዝ-ክፍል ፳፯
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 28🌹
...........ሣልስ ውስጠ ዘ..............
ይህ በውእቱ ቅድመ መድረሻውን ወደ ራብዕ ቀይሮ መጨረሻውን ሣልስ የሚያደርግ ነው።
1) ቀዳሲ
2) ቀታሊ
3) ተንባሊ
4) ዴጋኒ
5) ባራኪ
6) ጦማሪ
7) ከሃሊ
8) ማሕራኪ
9) ገባሪ
10) ቀዋሚ
11) ሠያሚ
የክህለ ቤቶች በተለየ መነሻቸውን ከሳድስ ወደ ግእዝ ይቀይራሉ። ትርጉሙ ለምሳሌ ቀዳሲ ያመሰገነ፣ አመስጋኝ፣ የሚያመሰግን ተብሎ በሦስት ይተረጎማል።የቆመ ቤቶች መካከል ላይ "ዋ" ፊደልን ይጨምራሉ። የሤመ ቤቶች ደግሞ መካከል ላይ "ያ"ን ይጨምራሉ።

ከላይ ያለው ለአንድ ሰው ለወንድ ነው ለአንድ ሰው ለሴት ሲሆን ደግሞ ልክ እንደላይኛው ሆኖ መጨረሻ ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።
1) ቀዳሲት
2) ቀታሊት
3) ተንባሊት
4) ዴጋኒት
5) ባራኪት
6) ጦማሪት
7) ከሃሊት
8) ማሕራኪት
9) ገባሪት
10) ቀዋሚት
11) ሠያሚት
ይላል።ለብዙ ወንዶች ሲሆን ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል።መጨረሻ ፊደሉን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ያን" ፊደልን መጨመር ነው።
1) ቀዳስያን
2) ቀታልያን
3) ተንባልያን
4) ዴጋንያን
5) ባራክያን
6) ጦማርያን
7) ከሃልያን
8) ማሕራክያን
9) ገባርያን
10) ቀዋምያን
11) ሠያምያን
ይላል ለብዙ ሴቶች ሲሆን ደግሞ ልክ እንደ ብዙ ወንዶች ሆኖ የሚለየው መጨረሻ ላይ "ያት" ፊደልን ይጨምራል።
1) ቀዳስያት
2) ቀታልያት
3) ተንባልያት
4) ዴጋንያት
5) ባራክያት
6) ጦማርያት
7) ከሃልያት
8) ማሕራክያት
9) ገባርያት
10) ቀዋምያት
11) ሠያምያት
ይላል።ማለት ነው።ለብዙ ወንዶች ወይም ለብዙ ሴቶች ሲሆን ትርጉሙ ለምሳሌ ገባርያት/ገባርያን የሠሩ ሠራተኛ የሚሠሩ ተብሎ ይተረጎማል። ለአንዷ ሴት ሲሆን ደግሞ ለምሳሌ ጦማሪት ቢል የምትጽፍ ጸሐፊት የጻፈች ተብሎ ይተረጎማል።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፳፰
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 29🌹
ሳድስ ውስጠ ዘ
1) ቅዱስ
2) ቡሩክ
3) ሥዩም
4) ቅውም
5) ጡሙር
6) ግቡር
7) ዲጉን
8) ክሁል
9) ትንቡል
10) ምሕሩክ
11) ቅቱል
ይህ በውእቱ ጊዜ ነው።በ15 ይተረጎማል። ለምሳሌ ቅቱል የሚለውን ብንመለከት የገደለ፣ ያስገደለ፣ የተገደለ፣ የተገዳደለ፣ ያገዳደለ፣ የሚገድል፣ የሚያስገድል፣ የሚገደል፣ የሚገዳደል፣ የሚያገዳድል፣ ገዳይ፣ አስገዳይ፣ አገዳዳይ፣ ተገዳይ፣ ተገዳዳይ ተብሎ በ15 ይተረጎማል ሌላውንም በዚህ መልኩ መተርጎም ነው። ቅዱስ የሚለው አመስጋኝ ተመስጋኝ አስመስጋኝ... እያልክ ዝለቅ። አስተውል በውእቱ ጊዜ ሁሉንም ሳድስ አድርጎ ቅድመ መድረሻውን ካዕብ ማድረግ ነው። በባረከ እና በጦመረ በተለየ መነሻውን ካዕብ ያደርጋል። ቡሩክ ጡሙር ይላል። እንጂ ብሩክ አይልም። በዴገነ ጊዜ መነሻውን ሣልስ ያደርጋል። ዲጉን ይላል እንጂ ድጉን አይልም።

በይእቲ ጊዜ ሁሉንም ሳድስ አድርጎ መጨረሻ ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።
1) ቅድስት
2) ቡርክት
3) ሥይምት
4) ቅውምት
5) ጡምርት
6) ግብርት
7) ዲግንት
8) ክህልት
9) ትንብልት
10) ምሕርክት
11) ቅትልት
ይላል ።ትርጉሙ ከላይ በውእቱ ጊዜ የቀተለን እንደሠራነው ሆኖ ልዩነቱ ይህንን በሴት ማድረግ ነው። ቅትልት ቢል የተገደለች የገደለች... እያሉ መዝለቅ ማለት ነው።በብዙ ወንዶች (ውእቶሙ) ቅድመ መድረሻውን ወደ ካዕብ ቀይሮ መጨረሻውን ወደ ራብዕ ቀይሮ "ን" ፊደልን መጨመር ነው።
1) ቅዱሳን
2) ቡሩካን
3) ሥዩማን
4) ቅውማን
5) ጡሙራን
6) ግቡራን
7) ዲጉናን
8) ክሁላን
9) ትንቡላን
10) ምሕሩካን
11) ቅቱላን
ይላል።ትርጉሙ ምሳሌ ሥዩማን የሾሙ የተሾሙ ያስሾሙ... እያለ ይዘልቃል።በብዙ ሴቶች ጊዜ ልክ እንደ ውእቶሙ ሆኖ መጨረሻ ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።
1) ቅዱሳት
2) ቡሩካት
3) ሥዩማት
4) ቅውማት
5) ጡሙራት
6) ግቡራት
7) ዲጉናት
8) ክሁላት
9) ትንቡላት
10) ምሕሩካት
11) ቅቱላት
ተብሎ ይዘረዘራል ማለት ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፳፱
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 30🌹
#የ8ቱ #አርእስት #ንዑስ #አንቀጽ
1) ቀድሶ/ቀድሶት ፥ማመስገን
2) ተንብሎ/ተንብሎት፥መለመን
3) ባርኮ/ባርኮት ፥መባረክ
4) ጦምሮ/ጦምሮት ፥መጻፍ
5) ዴግኖ/ዴግኖት ፥መከተል
6) ማሕርኮ/ማሕርኮት፥መማረክ
7) ቀቲል/ቀቲሎት ፥መግደል
8) ሠይም/ሠይሞት ፥መሾም
9) ቀዊም/ቀዊሞት ፣መቆም
10) ክሂል/ክሂሎት ፥መቻል
11) ገቢር/ገቢሮት ፥ መሥራት
ከላይ እንዳየነው ከቁጥር 1 እስከ ቁጥር 6 ያሉት ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ሳድስ ቀይረው መጨረሻቸውን ወደ ሳብዕ ቀይረው ይዘረዘራሉ። ወይም ሁለተኛው አካሄድ እንዲህ አድርጎ መጨረሻ ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።ከቁጥር 7 እስከ 11 ያሉት ደግሞ ቅድመ መድረሻውን ወደ ሣልስ ቀይረው ከዚያ መድረሻውን ሳድስ ማድረግ ነው። በሁለተኛው አካሄድ ደግሞ ቅድመ መድረሻውን ወደ ሣልስ ቀይረው መድረሻቸውን ወደ ሳብዕ ለውጠው ከዚያ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 31🌹
ባዕድ ቅጽል እና ባዕድ ሣልስ ቅጽል
የእነዚህም ትርጉማቸው ከውስጠ ዘ ጋር ተመሳሳይ ነው።መነሻ ላይ "መ"ን ወይም "መስተ'ን ይጨምራሉ።

1) መቀድስ፥ መስተቀድስ፥ መስተቃድስ
2) መባርክ፥ መስተባርክ
3) መቅትል፥ መስተቅትል፣ መስተቃትል
4) መተንብል፣ መስተተንብል፥ መስተተናብል
5) መሴስይ፣ መስተሴስይ፣ መስተሰያስይ፣ መስተሲያስይ፥ መስተስያስይ
6) መጦምር፣ መስተጦምር፣ መስተጠዋምር፣ መስተጡዋምር፣ መስተጦዋምር፣ መስተጥዋምር፣ መስተጦዋምር
7) መማሕርክ፣ መስተማሕርክ
8) መግብር፣ መስተግብር፣ መስተጋብር
9) መቀውም፣ መስተቀውም፣ መስተቃውም
10) መሠይም፣ መስተሠይም፣ መስተሣይም
11) መክህል፣ መስተክህል፣ መስተካህል

ይላል።ትርጉሙ በክፍል 30 እንዳየነው እንደ ሳድስ ውስጠዘ ነው።ይህም ማለት መቀድስ፣ መስተቀድስ፣ መስተቃድስ የሚለው ባዕድ ቅጽል ቅዱስ ከሚለው ሳድስ ቅጽል ተመሳሳይ ትርጉም አለው ማለት ነው።ለአንዲት ሴት ሲሆን ደግሞ እንደሚከተለው ነው።

1) መቀድስት፥ መስተቀድስት፥ መስተቃድስት
2) መባርክት፥ መስተባርክት
3) መቅትልት፥ መስተቅትልት፣ መስተቃትልት
4) መተንብልት፣ መስተተንብልት፥ መስተተናብልት
5) መሴስይት፣ መስተሴስይት፣ መስተሰያስይት፣ መስተሲያስይት፥ መስተስያስይት
6) መጦምርት፣ መስተጦምርት፣ መስተጠዋምርት፣ መስተጡዋምርት፣ መስተጥዋምር፣ መስተጦዋምርት
7) መማሕርክት፣ መስተማሕርክት
8) መግብርት፣ መስተግብርት፣ መስተጋብርት
9) መቀውምት፣ መስተቀውምት፣ መስተቃውምት
10) መሠይምት፣ መስተሠይምት፣ መስተሣይምት
11) መክህልት፣ መስተክህልት፣ መስተካህልት

ይላል ።የብዙ ወንዶች ደግሞ እንደሚከተለው ነው። አስተውል የቀደሰ ቤቶች ቀደሰን መስለው የሌሎችም አርእስታቸውን መስለው ይዘረዘራሉ። ስለዚህ ለምሳሌ የቀደሰን ባዕድ ቅጽል አወቅህ ማለት ቀደሰን የመሰሉ ግሦችንም በራስሕ ማርባት ትችላለህ ማለት ነው።የሌሎችንም እንደዚሁ

1) መቀድሳን፥ መስተቀድሳን፥ መስተቃድሳን
2) መባርካን፥ መስተባርካን
3) መቅትላን፥ መስተቅትላን፣ መስተቃትላን
4) መተንብላን፣ መስተተንብላን፥ መስተተናብላን
5) መሴስያን፣ መስተሴስያን፣ መስተሰያስያን፣ መስተሲያስያን፥ መስተስያስያን
6) መጦምራን፣ መስተጦምራን፣ መስተጡዋምራን፣ መስተጠዋምራን፣ መስተጥዋምራን፣ መስተጦዋምራን
7) መማሕርካን፣ መስተማሕርካን
8) መግብራን፣ መስተግብራን፣ መስተጋብራን
9) መቀውማን፣ መስተቀውማን፣ መስተቃውማን
10) መሠይማን፣ መስተሠይማን፣ መስተሣይማን
11) መክህላን፣ መስተክህላን፣ መስተካህላን

ይላል።የብዙ ሴቶች ደግሞ እንደሚከተለው ይረባል። ልክ እንደ ብዙ ወንዶች ሆኖ ልዩነቱ የብዙ ሴቶች መጨረሻ ላይ "ት"ን ስንጨምር በብዙ ወንዶች ግን ከላይ እንዳየነው "ን"ን መጨመር ነው።

1) መቀድሳት፥ መስተቀድሳት፥ መስተቃድሳት
2) መባርካት፥ መስተባርካት
3) መቅትላት፥ መስተቅትላት፣ መስተቃትላት
4) መተንብላት፣ መስተተንብላት፥ መስተተናብላት
5) መሴስያት፣ መስተሴስያት፣ መስተሰያስያት፣ መስተሲያስያት፥ መስተስያስያት
6) መጦምራት፣ መስተጦምራት መስተጡዋምራት፣ መስተጠዋምራት፣ መስተጥዋምራት፣ መስተጦዋምራት
7) መማሕርካት፣ መስተማሕርካት
8) መግብራት፣ መስተግብራት፣ መስተጋብራት
9) መቀውማት፣ መስተቀውማት፣ መስተቃውማት
10) መሠይማት፣ መስተሠይማት፣ መስተሣይማት
11) መክህላት፣ መስተክህላት፣ መስተካህላት

እያለ ይዘረዘራል ማለት ነው።ባዕድ ሣልስ ቅጽል የሚባለው እንደ ባዕድ ቅጽል መጀመሪያ ላይ "መ"ን ወይም "መስተ"ን የሚጨምር ሆኖ የመጨረሻው ፊደል ሣልስ የሆነ ነው። ለምሳሌ የቀተለን ከዚህ ቀጥለን እንመልከት

ውእቱ መቅተሊ
ውእቶሙ መቅተልያን
ይእቲ መቅተሊት
ውእቶን መቅተልያት

ውእቱ መስተቅተሊ
ውእቶሙ መስተቅተልያን
ይእቲ መስተቅተሊት
ውእቶን መስተቅተልያት

እያለ የሚረባበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ መንፈስ ቅዱስ ማለት "መንጽሒ" ማለት ነው ሲል የነጽሐ ባዕድ ሣልስ ቅጽል ነው። እንደገና መንፈስ ቅዱስ ማለት "መስተፍሥሒ" ማለት ነው ሲል የተፈሥሐ ባዕድ ሣልስ ቅጽል ነው። ትርጉሙ እንደ ሳድስ ውስጠ ዘ ወይም እንደ ባዕድ ቅጽል ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴፩
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 32🌹
መድበል
መድበል የሚባለው መድረሻውን ሳድስ አድርጎ "ት" ፊደልን የሚጨምር ነው።
1) ጸሐፈ ብሎ ጸሐፍት
2) ቀደሰ ብሎ ቀደስት
3) ቀተለ ብሎ ቀተልት
4) ብህለ ብሎ በሀልት
እያለ የሚሄደው ነው።መጨረሻ ፊደሉ "ሀ" ወይም "አ" የሆነ ግሥ መድበሉ ሲወጣ ቅድመ መድረሻውን ራብዕ አድርጎ ይወጣል። ለምሳሌ
1) ፈርሐ ብሎ ፈራሕት
2) በልዐ ብሎ በላዕት
3) ሰምአ ብሎ ሰማእት
ይላል።የባረከ ቤቶችና የጦመረ ቤቶች እንዲሁም የዴገነ ቤቶች መድበላቸው ሲወጣ መነሻቸው አይለወጥም።
1) ዴገነ ብሎ ዴገንት
2) ጦመረ ብሎ ጦመርት
3) ባረከ ብሎ ባረክት
ይላል ማለት ነው።መድበል የሚተረጎመው እንደ ብዙ ወንዶች እና እንደ ብዙ ሴቶች ሳድስ ውስጠ ዘ ነው። ለምሳሌ። ቀደስት የሚለውን ብንተረጉመው እንዲህ ይላል።
1) ያመሰገኑ
2) የተመሰገኑ
3) ያስመሰገኑ
4) ያመሰጋገኑ
5) የተመሰጋገኑ
6) አመስጋኞች
7) ተመስጋኞች
8) አስመስጋኞች
9) አመሰጋጋኞች
10) ተመሰጋጋኞች
11) የሚያመሰግኑ
12) የሚመሰገኑ
13) የሚመሰጋገኑ
14) የማያመሰጋግኑ
15) የሚያስመሰግኑ
ተብሎ በ15 ይተረጎማል። አስተውል ቅዱሳን፣ ቅዱሳት ፣ መቀድሳን፣ መስተቀድሳን፣ መስተቃድሳን፣ መቀድሳት፣ መስተቀድሳት፣ መስተቃድሳት የሚተረጎሙት እንደዚህ በ15 ነው። የእኒህ ሁሉ ትርጉማቸው ከላይ ያሉት 15ቱ ናቸው።

የቆመ ቤቶች ሳቢዘር መነሻቸውን ግእዝ አድርገው መሀል ላይ "ወ"ን ፊደል ጨምረው መድረሻቸውን ሳድስ አድርገው "ት" ፊደልን ይጨምራሉ።የሤመ ቤቶች ደግሞ መነሻቸውን ግእዝ አድርገው "የ" ፊደልን ጨምረው መድረሻቸውን ሳድስ አድርገው "ት" ፊደልን ይጨምራሉ።
1) ቆመ ብሎ ቀወምት
2) ሤመ ብሎ ሠየምት
ይላል።ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴፪
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 33🌹
ሳቢ ዘር
ሳቢዘር የሚባለው መድረሻውን ብቻ ግእዝ አድርጎ ከዚያ "ት" ፊደልን የሚጨምር ነው።ምሳሌ፦
1) ሐይወ ኖረ ብሎ ሕይወት
2) ሰበከ አስተማረ ብሎ ሰብከት
3) ቀጸበ ጠቀሰ ብሎ ቅጽበት
4) ኀዳረ አደረ ብሎ ኅድረት
5) ሠርዐ ሠራ ብሎ ሥርዐት
6) ቀተለ ገደለ ብሎ ቅትለት
7) ፈጠረ ብሎ ፍጥረት
8) ፈርሀ ብሎ ፍርሀት
እያለ የሚወጣ ሲሆን በአድራጊ እና በተደራጊ ይተረጎማል።ለምሳሌ። ቅትለት ብሎ መግደል መገደል አገዳደል ተብሎ ይተረጎማል። ሐይወ ኖረ ብሎ ሕይወት መኖር አኗኗር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። አማርኛው እንዳመቸ ይተረጎማል። ሠርዐ ሠራ ብሎ አሠራር ተብሎ ይተረጎማል። የቆመ ቤቶች ሳቢዘራቸው ሲወጣ መነሻቸውን ካዕብ አድርገው መድረሻቸው ባለበት ግእዝ ሆኖ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።ምሳሌ
1) ቆመ ብሎ ቁመት
2) ሮጸ ብሎ ሩጸት
3) ሖሰ ብሎ ሑሰት
ይላል።የሤመ ቤቶች ደግሞ መነሻቸውን ሣልስ አድርገው መድረሻቸውን ባለበት ግእዝ አድርገው "ት" ፊደልን የሚጨምሩ ናቸው።ምሳሌ
1) ሤመ ብሎ ሢመት
2) ሜጠ ብሎ ሚጠት
3) ቄዐ ብሎ ቂዓት
ይላል። ሌላው መነሻቸው "ወ" የሆኑ ግሦች ሳቢዘራቸው ሲወጣ "ወ"ን ጎርደው ይወጣሉ።ለምሳሌ
1) ወለደ ብሎ ልደት
2) ወረደ ብሎ ርደት
እያለ ይወጣሉ።ምድረሻው ላይ ሁለት ተመሳሳይ ፊደል ያላቸው ግሦች ደግሞ ሳቢዘራቸው በሚወጣበት ጊዜ አንዱን ፊደል ይጎርድና ይወጣል።መነሻው "ወ" ሆኖ መድረሻው "አ" የሆነ ግሥ ደግሞ ሳቢዘሩ ሲወጣ ቅድመ መድረሻውን ግእዝ አድርጎ መድረሻው ባለበት ግእዝ ሆኖ "ት" ፊደልን ይጨምራል። ለምሳሌ፦
1) ሰደደ አባረረ ብሎ ስደት
2) ሠረረ ብሎ ሥረት
3) ወጽአ ብሎ ጸአት
ይላል።የሳቢ ዘር ሕጎን እኒህን ይመስላሉ።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴፫
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 34🌹
ዘመድ ዘር፣ ምእላድ፣ ጥሬዘር፣ ባዕድ ዘር፣ ጉልት ውስጠ ዘ

ዘመድ ዘር የሚባለው ከግሱ ሲወጣ መድረሻውን ሳድስ ያደርጋል። በግሱ ላይ የሚጨመር ምንም ዓይነት ባዕድ ቃል የለም። ነገር ግን ከግሡ ላይ ፊደላት ሊቀንሱም ላይቀንሱም ይችላሉ።
1) ሰብለ ዘረዘረ ብሎ ሰብል
2) ደምጸ ተሰማ ብሎ ድምጽ
3) አፍቀረ ወደደ ብሎ ፍቅር
4) ነገደ ብሎ ንግድ
5) ገብረ ሰራ ብሎ ግብር
6) ፈለከ ፈጠረ ብሎ ፈለክ
7) አንቀልቀለ ብሎ ቃል
8) አከለ በቃ ብሎ አካል
9) ነግሠ ብሎ ንግሥ
10) ሐለበ ብሎ ሐሊብ
ጥሬ ዘር የሚባለው ደግሞ በግሡ ላይ ምንም ዓይነት ባዕድ ቀለም ሳይጨምር ነገር ግን እንዳለ በቃሉ ወይም ቀንሶ መድረሻውን ራብዕ፣ ኃምስ፣ ሳብዕ የሆነ ቃል።
1) ዘመረ ብሎ ዝማሬ
2) መነነ ብሎ ምናኔ
3) ከብረ ብሎ ከበሮ
4) ተሰፈወ ብሎ ተስፋ
5) የበበ ብሎ ይባቤ
6) ጸገየ ብሎ ጽጌ
7) ተንስአ ብሎ ትንሳኤ
8) ወለጠ ብሎ ውላጤ
9) ሐነጸ ብሎ ሕንጻ
10) ፈጠረ ብሎ ፈጠራ
ምዕላድ የሚባለው ደግሞ ከግሡ መጨረሻ ላይ ባዕድ ቃላትን የሚጨምር ነው። እነዚህ ባዕድ ቃላትም "ት፣ን..." ናቸው። ምሳሌ፦
1) ኀበሰ ጋገረ ብሎ ኅብስት
2) በርሀ በራ ብሎ ብርሃን
3) አዕረፈ ብሎ እረፍት
4) ቀደሰ ብሎ ቅድሳት
5) መዐደ ብሎ ምዕዳን
6) ተዋነየ ብሎ ተውኔት
7) ጸለየ ብሎ ጸሎት
8) ተዐገሠ ብሎ ትእግስት
9) ቆረበ ብሎ ቁርባን
10) ባረከ ብሎ በረከት
ባዕድ ዘር የሚባሉት ደግሞ ከግሡ መነሻ ላይ ባዕድ ፊደላት "ም፣ እ፣ ት"ን የሚጨምሩ ናቸው።ምሳሌ፦
1) ቀደሰ ብሎ መቅደስ
2) ለጠነ ብሎ ምልጣን
3) ቆመ ብሎ ተቅዋም
4) በረቀ ብሎ መብረቅ
5) ሰከለ ብሎ አስካል
6) ዘመረ ብሎ መዝሙር
7) ኀተመ ብሎ ማኅተም
8) ሰቀለ ብሎ መስቀል
9) ቤተ ብሎ ታቦት
10) አዕረፈ ብሎ ምእራፍ
ባዕድ ዘር ብዙ ጊዜ በ5 ይተረጎማል። ለምሳሌ መቅደስ ብሎ ማመስገኛ፣ መመስገኛ፣ ማመሰጋገኛ፣ መመሰጋገኛ እያለ ይተረጎማል።አጠቃላይ ግን ከላይ ያየናቸው ዘመድ ዘር፣ ጥሬ ዘር፣ ምእላድ፣ ባዕድ ዘር ባለፈው ያየነው ሳቢዘር በዘርነታቸው ከግሡ ተቀራራቢ በሆነ ስም ይተረጎማሉ። ለምሳሌ መዘረ ጠመቀ ይላል። ምዝር ዘመድ ዘር ነው። ስለዚህ የሚጠመቅ ነገር "ጠላ" አለ። ስለዚህ ምዝርን ጠላ ብለን መተርጎም እንችላለን። ከግሡ ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለው ስም ማውጣት እንችላለን።

ጉልት የሚባሉ ደግሞ መድረሻ ቀለማቸውን ካዕብ የሚያደርጉ ቃላት ናቸው።ለምሳሌ፦
1) አከለ ብሎ ኩሉ
2) አሐደ ብሎ አሐዱ
3) ተልዕለ ብሎ ላእሉ
4) ተትሕተ ብሎ ታሕቱ
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ-ክፍል ፴፬
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
2024/10/01 11:26:16
Back to Top
HTML Embed Code: