Telegram Web Link
በመርቆርዮስ ቀን መርቆርዮስ ሄዱ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አራተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
በረከታቸው ይደርብን::
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 4ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም. ሲኾን፣ በፖሊቲካዊ ግፊትና ጫና መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን፣ ይታወቃል፡፡
ልደት

በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በአለታ ወረዳ አረጊት ኪዳነ ምሕረት በተባለችው ገዳም ሰበካ፣ ልዩ ስሙ ማር ምድር በ1930 ዓ.ም.፣ ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከወ/ሮ ለምለም ገሰሰ ተወለዱ፡፡

መንፈሳዊ ትምህርት

ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ፣ በተወለዱበት ገዳም መሪጌታ ላቀው ከሚባሉ መምህር፣ ንባብና ዳዊት ተማሩ፡፡ ከዚያም በኋላ አጭታን ኪዳነ ምሕረት በምትባለው ደብር ምዕራፍና ጾመ ድጓ ተምረዋል፡፡

ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ሔደው ጎንጅ ቴዎድሮስ በተባለው ገዳም ለኹለት ዓመት ከመሪጌታ ወርቁ፣ ወደ ዋሸራ በመዛወር በቅኔ ዝነኛ ከነበሩት ከመሪጌታ ማዕበል ፈንቴ ለኹለት ዓመት በጠቅላላ በአራት ዓመት የቅኔ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰው፣ በደብረ ታቦር አውራጃ እስቴ ወረዳ አጋጥ ደብረ ጽዮን፥ የምዕራፍ፣ ጾመ ድጓና ድጓ ትምህርታቸውን ከመሪጌታ ሙጩ አጠናቀዋል፡፡

ወደ አቋቋም ቤት በመግባት፣ መነጒዘር በሚባለው ደብር፣ ከመሪጌታ ሚናስ ለኹለት ዓመት የአቋቋም ትምህርት ተምረዋል፡፡ ከዚያም ቁት አቡነ አረጋዊ ደብር፣ ከመሪጌታ ውብ አገኝ ለአንድ ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት ተምረዋል፡፡ ወደ ደብረ ታቦር አውራጃ ተመልሰው፣ ከጥንቱ መምህራቸው ከመሪጌታ ሙጩ ላቀ ዘንድ የድጓ ትምህርታቸውን በመቀጠል ጽፈውና አመልክተው ከጨረሱ በኋላ፣ በነፋስ መውጫ አውራጃ በታች ጋይንት ወረዳ በምትገኘው በስመ ጥሩዋ በቤተ ልሔም አራት ዓመት ቆይተው ድጓ አስመስክረው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡

የድጓ ትምህርታቸውን ካስመሰከሩ በኋላ ወደተወለዱበት ገዳም ሔደው፣ በአረጊት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ለሰባት ዓመታት ያህል ድጓ አስተምረዋል፡፡

ሥርዐተ ምንኵስናና መንፈሳዊ አገልግሎት

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ሥርዐተ ምንኵስናን ከመምህርነት ጋራ አጣምሮ ለመያዝ ያላቸው ፍላጎት ከፍ ያለ ስለኾነ በጣና ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ በመግባት ማዕርገ ምንኵስናን ከመምህር ኃይለ ማርያም(በኋላ የባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ መልአከ ገነት) በ1961 ዓ.ም. ከተቀበሉ በኋላ፣ በዚሁ ዓመት ማዕርገ ቅስናን፣ ከጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል፡፡

የገዳምን ሥነ ሥርዐት ይበልጥ ማጥናት ስለፈለጉ፣ በባሕር ዳር አውራጃ ልዩ ስሙ ጋሾላ በተባለ ገዳም ገብተው የገዳሙን ሥነ ሥርዐት እያጠኑና ለገዳማውያን እየታዘዙ ለኹለት ዓመት ገዳሙን ረድተዋል፡፡ በገዳሙ በነበሩበት ጊዜ፣ በጸሎተ ማኅበር፣ የልማት ሥራ በመሥራትና አቅመ ደካሞችን በመርዳት ገዳሙን አገልግለዋል፡፡

ከዚያ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በቅዳሴና በማሕሌት እያገለገሉ ትርጓሜ ሐዲሳትንና አቡሻኽርን ተምረዋል፡፡ ዘመናዊ ትምህርታቸውንም በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት እስከ ኹለተኛ ደረጃ ተከታትለዋል፡፡ በተጨማሪም ለመምህራን፣ የተደረገውን የስብከት ዘዴ ኮርስ ለኹለት ዓመታት ተምረው የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ኾነው በመሾም በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረውን ችግር ተገንዝበው ለአገልጋዮች መኖሪያ ቤት አሠርተውላቸዋል፡፡ የእሑድ(የሰንበት) ት/ቤት ወጣቶችም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስላልነበራቸው አንድ አዳራሽ ከነሙሉ ድርጅቱ አሠርተው በመስጠት ችግራቸውን አቃለውላቸዋል፡፡ ተጀምሮ የነበረው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንዲጠናቀቅና በአካባቢው የነበሩ ምእመናንም በሰበካ ጉባኤ እንዲደራጁ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡

ሢመተ ጵጰስና

ባላቸው በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ባሳዩትም የመንፈሳዊ አገልግሎትና የሥራ ወዳድነት፣ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ባደረገችው የ13 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠው የኦጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ተሾመዋል፡፡

በዚህ አውራጃ፣ በጠላት ፈርሶ የነበረውን ቤተ ክርስቲያን በማሠራትና በማሳደስ፤ በጦርነት ምክንያት የተሸበረውንና የተደናገጠውን ሕዝብ በማጽናናት ስለ ኢትዮጵያ አገሩ ፍቅር በማስተማርና በማስረዳት ሐዋርያዊ ተልእኳቸውን ፈጽመዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በ1971 ዓ.ም. ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተዛውረዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በጎንደር ሀገረ ስብከት የፈጸሙአቸው ሥራዎች፡-

በወቅቱ በነበረው አለመረጋጋት፣ በጭልጋና በደባርቅ አውራጃዎች እየተዘዋወሩ ሕዝቡን በማስተማር ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በየጊዜው በሚያሳዩት መልካም የሥራ ውጤት፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሊቀ ጵጵስና ማዕርግ ተቀብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷን እንድትችል ለማድረግ ቀዳሚ ተግባር የሚኾነው ምእመናንን በሰበካ ጉባኤ ማደራጀትና ማጠናከር ስለኾነ፣ በሀገረ ስብከት በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የሰበካ ጉባኤን በማቋቋምና በማጠናከር፣ የሰንበት ት/ቤቶችንም በማስፋፋት ቅርሳቅርሶች በክብካቤ እንዲያዙ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች ለሕዝበ ክርስቲያን እንዲደርሱ፣ የቤተ ክርስቲያን መመሪያና ደንብ ቃለ ዐዋዲ በተግባር እንዲተረጎም አድርገዋል፡፡

በጎንደር ክፍለ ሀገር የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታደሱና በርከት ያሉ አዲስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ አድርገዋል፡፡ በተለይም በደብረ ታቦር አውራጃ በእስቴ ወረዳ፡-

የአረጊት ኪዳነ ምሕረትን ቤተ ክርስቲያን በግል ገንዘባቸው ቆርቆሮ እንድትለብስ አድርገዋል፡፡
በዚሁ ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን፣ ከግል ገንዘባቸው ብር 9ሺሕ በማውጣት ቆርቆሮ እንድትለብስ አድርገዋል፡፡
መንፈሳዊ አዳሪ ት/ቤቶች እንዲከፈቱ፣ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲቋቋምና ካህናት በተግባረ እድ የሚሠለጥኑበት ት/ቤት እንዲከፈት አድርገዋል፡፡
ምንም መተዳደሪያ ያልነበራቸው የአብነት መምህራንና ሊቃውንት፣ ለክህነት ከሚከፈለው ገንዘብ ደመወዝ እንዲቆረጥላቸው በማመቻቸት ሳይሰለቹና ሳይቸገሩ ሞያቸውን ለትውልድ እንዲያስተላልፉና የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችም በትምህርት አቅማቸውን እንዲያሻሽሉበት አድርገዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ለአንድ የዜማ መምህር፣ ለአንድ የቅዳሴ መምህር፣ ለአንድ ዕቃ ቤት ጠባቂ በድምሩ ለሦስት ሰዎች ከራሳቸው ደመወዝ በመክፈል ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ አድርገዋል፡፡ በብፁዕነታቸው ሊቀ ጵጵስና፣ 43 አብያተ ክርስቲያናት ተተክለዋል፤185 አብያተ ክርስቲያናት ተሠርተዋል፡፡
የልማት ሥራዎች፤
ሀ/ በጋይንት አውራጃ በታች ጋይንት ወረዳ በምትገኘው በታላቋ ደብር ቤተ ልሔም ከአንድ በጎ አድራጊ ርዳታ በመጠየቅ በናፍጣ የሚሠራ አንድ የሞተር ወፍጮ አቋቁመው ለካህናቱና ድጓ ለሚያደርሱ ተማሪዎች ደመወዛቸውን እንዲችሉ ጥረዋል፡፡

ለ/ በደብረ ታቦር አውራጃ በእስቴ ወረዳ ሊጋባ ቅዱስ ሚካኤል በተባለው ቤተ ክርስቲያን አካባቢ አንድ የሞተር ወፍጮ በጎ አድራጊዎችን በመጠየቅ እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ አገልጋይ ካህናትም የወር ደመወዝተኛ እንዲኾኑ አድርገዋል፡፡

ሐ/ ጥንታውያን መጻሕፍት ለትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ ባደረጉት ጥረት፡- ጠቢበ ጠቢባን፣ ሙሉ ሲኖዶስ፣ የቅዳሴ አንድምታ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰናቸውን ውሳኔዎች በሙሉ በብራና እንዲጻፉ አድርገዋል፡፡ በጭልጋ፣ በሊቦ፣ በደብረ ታቦር፣ በጋይንት አውራጃዎችና በእስቴ ወረዳ የችግኝ ጣቢያዎች አቋቁመው በየዓመቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ችግኞች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሰበካና ለሕዝባውያን ድርጅቶች እንዲከፋፈሉ በማድረጋቸው የተራቆቱ መሬቶች በዛፎች እንዲዋቡ ጥረዋል፡፡

መ/ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በማስፈቀድ በማኅደረ ማርያም የሐዲሳት፣ የድጓና የቅዳሴ ት/ቤት አሠርተው ለመምህራኑ ከ50 እስከ 200 ብር ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣ ለደቀ መዛሙርቱ ድጎማ እንዲሰጣቸው አድርገዋል፡፡

ሠ/ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ቂርቆስ ገዳም በብር 8ሺሕ835 እንዲታደስ አድርገዋል፡፡ በጣና ለሬማ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ብር 4ሺሕ ረድተዋል፡፡ የደረሞ ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን ብር 21ሺሕ 114 በማውጣት አሳድሰዋል፡፡ እንዲሁም ጥንታዊውን የግርቢ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብር 8ሺሕ860 ብር እንዲታደስ አድርገዋል፡፡ በአዘዞ በሰሚ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ካህናቱ ማሠልጠኛ የሚወስደው መንገድ በምግብ ለሥራ መርሐ ግብር እንዲሠራ አድርገዋል፡፡

በጎንደር መንበረ መንግሥት ጥበበ እድና የአዳሪ ቤቱ ዙሪያ ርዳታ በመጠየቅ ከ9ሺሕ በላይ በማወጣት እንዲሠራ አድርገዋል፡፡ በጎንደር ጉባኤ ቤትና የዶክተር አየለ ዓለሙ የመቃብር ቤት የአራቱ ጉባኤያት ሥዕል እንዲሠራበት አድርገዋል፡፡ በሊቦ አውራጃ በቆላ እብናት ለአምራቾች የኅብረት ሥራ ማኅበር ብር 15 ሺሕ ረድተዋል፡፡ በጎንደር ከተማ በአዘዞ አባ ሳሙኤል በመጠለያ ለሚረዱ ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ጋራ በመተባበር የኤልክትሪክ ምጣድ ርዳታ አድርገዋል፡፡ በዳባት ወረዳ የሚገኘውን የደፍቂ ቅዱስ ሚካኤልን በብር 5ሺሕ፣ ቆማ ፋሲለደስን በብር 5ሺሕ አሳድሰዋል፡፡ ለአምስትያ ገዳም ብር 4ሺሕ፣ ለጣርክ ማርያም ብር 7ሺሕ ረድተዋል፡፡

ዐደባባይ ኢየሱስም በብር 40ሺሕ እንዲታደስ አድርገዋል፤ የድምፅ ማጉያም አስገብተውለታል፡፡ በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ለቸንከር ተክለ ሃይማኖት ርዳታ በመጠየቅ ብር 764ሺሕ አበርክተዋል፡፡ በዚያው በጎንደር ዙሪያ ከማክሰኝት እስከ አርባያ ለመንገድ ሥራ ብር 30ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ አድርገዋል፡፡ ከእብናት እስከ ጎሐላ ለመንገድ ሥራ የብር 6ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ አድርገዋል፡፡

በስሜን አውራጃ ለሚገኙ ጥንታውያን ገዳማት፤ ለቤተ ሚናስ ዋልድባ ከብር 10ሺሕ በላይ፤ ለጣዕመ ክርስቶስ ብር 10ሺሕ፣ ለሰቋር ዋልድባ ብር 4ሺሕ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ(የዓይነት) ርዳታ አድርገዋል፡፡

በጎርጎራ ገዳም በደሴተ ጣና ለሚገኙ ገዳማት፤ ለማን እንዳባ ገዳም ብር 1ሺሕ880፤ ለብርጊዳ ማርያም ገዳም ብር 1ሺሕ ለበሬ መግዣ እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡

ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ርዳታ ሰጪ ድርጀቶች በመጠየቅ አቅም በፈቀደ መጠን በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት የቆዳ፣ የሽመና፣ የሹራብ ሥራ፣ የልብስ ስፌት፣ የወፍጮ ቤትና የዳቦ ቤት እንዲቋቋምና አገልግሎት እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም ለስብከተ ወንጌል፣ ለሰንበት ት/ቤትና ለሕዝብም መሰብሰቢያ የሚያገለግሉ አዳራሾች በየአብያተ ክርስቲያናቱ አካባቢ አሠርተዋል፡፡ ሕዝቡ ንጹሕ ውኃ ማግኘት እንዲችል የውኃ ጉድጓድ በማስቆፈር ለዚሁ የሚያገለግል ሞተርና ቧምቧ እንዲያገኙ የበኩላቸውን ጥረዋል፡፡

ለሀገረ ስብከቱ ያስገኟቸው ሽልማቶች፤

የሰበካ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ደንብ በትክክል እንዲፈጸም በማድረጋቸውና ሰበካ ጉባኤን በሚገባ በማደራጀታቸው፣በየዓመቱ በሚደረገው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ የሥራ ግምገማ በተደረሰበት ውጤት የጎንደር ሀገረ ስብከት ቅድሚያ ቦታ እንዲይዝ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት፡- ከ16ቱ አህጉረ ስብከት፣ ከ1975 እስከ 1977 ዓ.ም. በተከታታይ እንዲሁም በ1979 ዓ.ም. አንደኛ፤ በ1978 ዓ.ም. ኹለተኛ በመኾን በውጤታማነት እንዲሸለም አድርገዋል፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ከዚህ በላይ ጠቅለል ባለ መልክ በተዘረዘረው ዓይነት ተልእኳቸውን በትክክል የተወጡ አባት ከመኾናቸውም በላይ በ1979 ዓ.ም. በተደረገው የብሔራዊ ሸንጎ አባላት ምርጫ በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ምርጫ ጣቢያ ደንቢያ ከመረጠው 26ሺሕ127 ሕዝብ መካከል 17ሺሕ249 ድምፅ በማግኘት ተመርጠው ሕዝብን አገልግለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ የበላዮቻቸውን መካሪ፣ የበታቾቻቸውን አክባሪ፣ በሥራ ታታሪ፣ መንፈሳዊ አባትነታቸውና ትሑት ሰብእናቸው አርኣያነት ያለው ቁጥብ አባት ናቸው፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም አረፉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ እሁድ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት አሳውቋል።
አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን
✝️ እንቋዕ አብጽሐክሙ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና። ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ ሕዝበ ክርስቲያን!

"ኢሀሎ ፡ ዝየ ፡ ተንሥአ ፡ በከመ ፡ ይቤ ፤ እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም"
ማቴ ፳፰ ፥ ፮

"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ።"
✝️ ለሁሉም የክርስቲያን ሕዝብ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁን


○▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭○

🔆 የቃሎች ትክክለኛ አጻጻፍ

በዓል - የሚከበር ቀን
በአል - የጣዖት ስም

ዓመት - ዘመን
አመት - አገልጋይ

ትንሣኤ - መነሣት
ትንሳኤ

ሰላም - ሰላም
ሠላም

ዓመተ ምሕረት - የይቅርታ ዘመን
መሀረ - አስተማረ
መሐረ - (ምሕረት) ➜ ይቅር አለ (ይቅርታ)


🌸 መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
attachment.pdf
21.4 MB
ጾመ ድጓ

ዘቅዱስ ያሬድ
#የቅኔ #ጉባኤ #ቤት
ባህር ዳር የሚገኘው ታላቁ የቅኔ ጉባኤ ቤት ሊሠራ የሚከተለውን ዓይነት ዲዛይን ወጥቶለታል፡፡ የጉባኤ ቤት ቤት አሠራር ትውፊትን የያዘ ድንቅ ዲዛይን ነው፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለትርጓሜም ለሌሎች ትምህርቶችም ዋናው ቁልፍ ቅኔ ነው፡፡ የግእዝ ትምህርት በጥልቀት የሚሰጠው ቅኔ ቤት ነው፡፡ ግእዝ ደግሞ ብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት የተጻፉበት ቋንቋ ነው፡፡ ሊቃውንቱ በቅኔያቸው የእግዚአብሔርን ቸርነቱን፣ መግቦቱን፣ ሁሉን ቻይነቱን፣ ፈታሒነቱን፣ ይቅር ባይነቱን፣ አንድነቱን፣ ሦስትነቱን፣ ጌትነቱን፣ ዘለዓለማዊነቱን በአማረ የቋንቋ አሰካክ በሰምና ወርቅ ይገልጡበታል፡፡ የቅዱሳንን አማላጅነት የሰማዕታትን መንፈሳዊ ቆራጥነት የመላእክትን ተራዳኢነት በቅኔያቸው ይገልጹታል፡፡ በቅኔያቸው ክፉዎችን ይገሥጹበታል፡፡ ምእመናንን ይመክሩበታል፡፡
፡፡
በአጭሩ ለመግለጽ ቅኔ መንፈሳዊ ፍልስፍና ነው፡፡ ቀድሞማ መሳፍንቱ መኳንንቱ ወይዛዝርቱ ሁሉ ባለቅኔ ነበሩ፡፡ የዚችን ዓለም ከንቱነት በቅኔያቸው ይገልጡት ነበር፡፡ የእነ ተዋነይ መንፈሳዊ ፍልስፍናኮ ቅኔ ነው፡፡ የቅኔ ትምህርት በአሁኑ ሰዓት በስፋት የሚሰጥበት ጉባኤ ደግሞ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ልጅ የሆኑት የየኔታ ቅዱስ ያሬድ ጉባኤ ቤት ነው፡፡ ይህን ጉባኤ ቤት ለመሠራት ወደ 200 ሚልየን ብር ይፈጃል ተብሏል፡፡ ስለዚህ ሁሉም በችሎታው ማገዝ አለበት፡፡ ለማገዝ የምትፈልጉ ከስር በተገለጡት የአካውንት ቁጥሮች መርዳት ትችላላችሁ፡፡
፡፡
አምላከ ሊቃውንት እግዚአብሔር ቤተጉባኤን ይጠብቅልን፡፡
audioclip-1568144296000-694501.mp4
2.7 MB
ምርጡ ጓደኛየ መምህር ልሳነወርቅ ናቸው። ጥዑም ዜማ ያድምጡ።
#እንኳን #ለቅድስት #ሥላሴ #ዓመታዊ #በዓል #በሰላም #አደረሳችሁ
ዓለምን ካለመኖር የፈጠሩ፣ ፈጥረውም የሚያስተዳድሩ ሥላሴ በአካል ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ አንድ ናቸው።

√ በአካላዊ ግብር ሦስት ናቸው። በአካላዊ ግብር ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም ወላዲ አሥራጺ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ መባል ነው።

√ በሥልጣናዊ (በባሕርያዊ) ግብር አንድ ናቸው። በባሕርያዊ ግብር ሥምም አንድ ናቸው። ይህም አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ወዘተ የመሳሰለው ነው።

√ በከዊን ሦስት ናቸው። እኒህም ቃል መሆን፣ ልብ መሆን፣ እስትንፋስ መሆን ናቸው። በዚህም ሥላሴ ነባብያን፣ ሕያዋን፣ ለባውያን መሆናቸውን እናውቃለን

√ በባሕርይ አንድ ናቸው። ይህም ማለት የሦስቱ ኩነታት ተገናዝቦ አንድ ሕይወተ አንድ ባሕርይ ይባላል።

√ በአካል ሦስት ናቸው። በአካል ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ መባል ነው።
+++++++++
+++++++++
እንኳን አደረሳችሁ።አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ። አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዐ። ዛሬ በማኅሌት የሚባሉ ወረቦችን የባሕርዳር ብዙኃን ማርያም የአቋቋም መምህር የሆኑት መምህር ልሳነ ወርቅ በዩቲይብ ቻናላቸው ለቀውልናል። #ልሳኑ #ዘያሬድ በሚለው የዩቲይብ ቻናል ገብተው ይመልከቱ።

ከዚህ ቀጥሎ ከዛሬ ወረቦች የተወሰኑትን ስሟቸው ። እነሆ
#ዕፀዋት #በግእዝ #ቋንቋ
ግእዝ__አማርኛ
ሰናፔ__ሰናፍጭ
ሐረፍ__ጎመንዘር/ቅባኑግ
መናሂ__ነጭ ጤፍ
ዳሂ____ጓያ
ሡራሕ_ድንች
ቤዴላህ____እንጉዳይ
በጢሕ_ዱባ
ሄላ____የወይን ዘለላ
ደንጎላ__ሱፍ
ስንዳሌ_ስንዴ
ሐምል__ጎመን
በድል/ፋል___ባቄላ
በጸል/ቱማ___ነጭ ሽንኩርት
እክል___እህል
ዚፋል___ሽንብራ
ቢጸልቱማ___ቀይ ሽንኩርት
ሕጥሜ_ጎመንዘር
ኅጥጥሜ___ጥጥ
ሐምሐም____ቅል
ሰገም___ገብስ
ሊጦስ/አስፈሊጦስ__ሰሊጥ
መለንስ_ኑግ
ሲላስ__አብሽ
ቆንደራጢስ/ዱሓን__ዳጉሳ
ተርሙስ____አተር
አለንስ__አጃ
ሕምር/ጥምዐት____እንሶስላ
ትለቤ/ከሙን__ተልባ
ሶመት_ነጭ ሽንኩርት
እንጎት_ትርንጎ
መርሳኒ_ቀጋ
መልጰጶን____ጎመን
ከሜን__ፌጦ
ከርካዕ_ሎሚ
ፔርካ__ሽንብራ
ጓልኬ_ሰናፍጭ
ሴዋ__ጌሾ
ቃሕዋ_ቡና
ሥርናይ___ስንዴ
ተቅዳ_ድንብላል
ስጕርንድ___ሽንኩርት
ሑስጱ_አሽክት
ክርዳድ_እንክርዳድ
ኵሓ____ከያ ዛፍ
ኤርጋሄ__አክርማ
ሰግላ___ሾላ
አሜከላ_እሾህ
ኩላ___ሙጫ
ሕንጽዋል___አረማሞ(የእፅዋት በሽታ)
ከርሜል__ችፍርግ
ቢሶም___ምሳና
በርሴም__ጽድ
በራቄኒም_ኮሸሽላ
ዖም_____ዛፍ
ተቢሳ___ሸንበቆ
ሜርሴንስ____ቀጋ
ቄድሮስ__ዋንዛ
ባሕሩስ_መቃ ሸንበቆ
ብሕውስ____መጭ/አብሾ/አስተናግር
ኤልያስ__ወይራ
ጠርቤንቶስ____ዋርካ
መዓረግራ_ሙጫ/አዶሮማር
ፐፒራ/አዛብ____እንዶድ
መምሬ_ወይራ
ተምር__ተምር
ዕጕስታር_ሬት
አጽፋር__አደይ አበባ
ሳቤቅ_ያረግ ሬሳ
ዘግባ_ዝግባ
ቀረብ_እንቧይ
ዐቃብ____ኮሸሽላ ሾኽ
ስት___ቄጤማ
አርቦት_ችባሓ
አቃኒ_ችፍርግ
ጳውቄና____ጽድ
ልብኔ_ልምጭ
ሰቂኖን_ኮክ
ሰኪኖን_እንዶድ
ሰውሳን_ሱፍ
ሰጥረጲሎን____ዋንዛ/ሽነት
ራምኖን_ዶግ
ቄድሮን__ዋንዛ
ተርሜን_ድድሆ/ክትክታ
ከርሜን_ድድሆ
ጢጤን_ዶቅማ
ጎሜዕ__ሸንበቆ/ቅርቅሀ
ሮዛ____ጽጌረዳ
አርዝ___ዛፍ
ፒርልዩ__ቀንጠፋ
ምግራይ____ግራር
መጽርይ_ቀጋ
ፐፒረለይ____እንዶድ
መድዮ___ጨፌ
ቀለምጤዳ____ቅንጭብ
ቀለምጼዳ_ቁልቋል
ተሐግ_____ሰርዶ
እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፋት በግእዝ
ግእዝ_አማርኛ
ቶራ_አጋዘ
ሐንዘር___አነር
ር____ነብር
ድግ____አህያ
ካሂ_ጥገት (አራ ላም)
ካሂ__ጊደር
ተክሉ____የበግ አውራ
ናጦሊ__የግመል ጊደር
____ፍየል
ዳቤላ___የፍየል አውራ
ቅል___በቅሎ
ዕዋል___የአህያ ውርንጭ
ዕጕል__ግልገል
ገመል__መል
ላሕም__ላ/በሬ
ሰቄዘሩ__አራስ ውሻ
ሦር____በሬ/ወይፈን
ልብ___ውሻ
ሔሴሜት____ድመት
ቴፈን__ወይፈን
መሐስዕ_ቦት
በግዕ___በ
በሐኵ__ጠት/አውራ
ጣዕ__ጥጃ
ሐርጌ__ጊደ/ሙክት
ሐርፅ__አዞ
ተስጴዳ_ጥን
ቀርዱ__ዝጀሮ
ከማንዮ__ግስላ
ከራግልዮ_ሳማ
ሐለስትዮ__
ሆባይ _ዝንጀሮ
ርዌ___አውሬ
ግሔ____እሽኮኮ
ቢሕ____ጉማሬ
ዔሊ___ድንጋይ ልብሱ
ኵላ__ተኵላ
መንተሌ_ጥቸል
ሐራድል_ጅ
ኀየል____ዋ
ቀይዘል_ሚዳቋ
ቍንጽል_ቀበ
ወይጠል____ፌቆ
አንበሳ____አንበሳ
ሐሪስ_አውራሪስ
ዋኖስ___ዋሊያ
ገሙስ__
ጋስ____የዳ አህያ
ቃንስ__ጉሬዛ
ራኩብ____የግመል ወሳብሬ
ዝእብ_ጅብ
ላጽቂት____ንጣ/እንሽላሊት
ሥርዐት____ድርጪት
ብሄሞት____ጉማሬ/ጎሽ
ተረቅት/ጽግነት_የሌት ወፍ
ጼዴነት____ድንጋይ ልብሱ/ዔሊ
ጻጹት___ጫጭት
ጽርኒ____አይጥ
ኦርና____ሚዳቋ
ማዖን____ድኩላ
ሰርኖን____ሰገኖ
ሰራግልዮን___ዐሳማ
ቅጥራቅጥሬን____ድንቢጥ
ተመን_ዘንዶ
ደስከን_ጎሽ
ደራጎን_ዘንዶ
ቀቀኖ_ርኩም
ደስከኖ_ጎሽ
እልልድኩ_አነ ድመት
ሐርማ_ጎሽ
ቅንፉዝ_ጃርት
ነጌ__ዝሆን

ጸያጴ____እንሽላሊት
መንጢጥ____ድምቢጥ ወፍ
አዲማ/ቶብኒ____ትኋን
ቃሕም____ገብረ ጉንዳን
ቆጶሮጢስ___የንብ አውራ
ንብሌስ_ፌንጣ
አክሳስ____ሺህ እግር/ቅንቡርስ/የእበት ትል
ዘንቢር____ተቆናጣጭ ዝንብ
ሐንቄ/ቆብኒ_ቅማል
ንህብ____
አቅራብ_ንጥ
ሣሬት__ሸረ
ሰኳዕት____ጉንዳን
ጸንጾላዕት___የእሳት ራት
ጽንጽንት____ነቀዝ/ብል
ቁንቁኔ___ነቀዝ
ሐሴን____አሸን
ቀርነናዕ____ትል
ቈርነናዕ____እንቁራሪት
ኮራኪ_ምስጥ/ጉንዳን
አንዋ____አይጥ
ከመዝ____የውሃ እናት
ትንንያ____ትንኝ
ጽንጽንያ____ዝንብ
ጕጋ__ቁንጫ
ዕፄ_ትል
ፄ__ብል/ነ
አንባ____አንበጣ
ኤርጌት____አውራ ዶሮ
ፍኅርት_ጫጭት
ዖፍ__ወፍ
ርሆ_ዶሮ
ርቤዶ_ዥግራ
ቆቅሕ___ቆ
ገምሉ___ለቅት
ኔስታሊ__የመስክ እባብ
ሊ__የእሳት ራት
ከይ_እባብ
ዓሣ__ዓሣ
ርሣ_አንባ
ሬክትም/ፊትም_የውሃ እናት
ሰጳላስስ/ገላሜዎስ____እስስት
አንበሪ/ዐንበር__ታላቅ ዓሣ
ጳልቃ_ርኩም
ሰገኖ_ሰጎን
ንስር_አሞራ
ዐንቄ____ጭላት
ርግብ___ርግብ
ማዕነቅ____ሽመላ
ቋዕ____ቁራ
ሶቤቃካ____ጅግራ
ኬሌሜዎን____እስስት
ዙዝዮን_አለቅት

ማስታዎሻ:-ለአንዱ የአማርኛ ቃል ብዙ የተለያዩ የግእዝ ቃላት ሊኖሩት ይችላሉ። ለምሳሌ ርኩም ለሚለው የአማርኛ ቃል በግእዝ "ጳልቃን" ወይም "ቀቀኖ" ይሆናሉ። ስለዚህ ከጽሑፉ የተደጋገመ ነገር ብታዩ ተሳስቶ ሳይሆን ለአንዱ ቃል ብዙ አቻ ትርጓሜ ስላለው መሆኑን እንድትገነዘቡ።
2024/10/01 11:23:31
Back to Top
HTML Embed Code: