Telegram Web Link
#ምግብና #መጠጥ ነክ ነገሮች
ግእዝ_አማርኛ
ገይላ____አሞሌ ጨው
ተብሲል___ንፍሮ
ጼተሎ____ጉሽ ጠጅ
ጳኵሲማ____ዳቦ/አንባሻ
ልሔም_ዳቦ
ፕፕሬ____በርበሬ
መዓር_ማር
ሶከር_ስኳር
ሐሊብ____ወተት
ኅብስት____እንጀራ
አረቦናት____ፍትግ ክክ
አያያት_የማር ወለላ
ግብነት_አይብ
ሆሳዕና_መድኃኒት
መና_እንጀራ
ጸደና____የጣዝማ ማር
ዕቋን____ወገሚት
አክራጦን___የወይን ጠጅ
ወይን____ወይን
ጤጉን_ዳቦ ቆሎ
ሐምለ ብሒእ____ስልጆ
ፀቃውዕ_የማር ወለላ
ኮቤዝ_ዳቦ/አንባሻ
ማዕድ____ማዕድ/መሶብ
ቴሮጋ_እርጎ ወተት
ሱራጌ_መረቅ
አንቆቅሖ____እንቁላል

#የአካል ክፍሎች
እራኅ_መሐል እጅ
ድማኅ____መሐል ራስ
ዳሌ__የጀርባ አጥንት
ሰይል_ሽል/ጽንስ
ዐፅም____አጥንት
ተኬሳ_ትክሻ
ሕዋስ_ሰውነት
ሐቌ_ወገብ
ቅርንብ____ቅንድብ
ዘነብ_ጅራት
ደርፍዑ____ሻኛ
ቀርን_ቀንድ
ተላዕ____ፍሪንባ
ጸኵ_ሹልዳ
መስቴካ____ጨጓራ
ገቦ__ጎን
መልታሕት___ፊት/ጉንጭ
ማዑት____አንጀት
መዝራዕት___ክንድ
ሥዕርት____ጸጉር
ኵሊት_ኩላሊት
ሰኮና_ተረከዝ
ሥን_ደም ግባት
እዝን____ጆሮ
ዓይን____ዓይን
ዘባን_ጀርባ
ጕርዔ____ጉረሮ
ሰንቡዕ____ሳንባ
ኵርናዕ_ክንድ
ሐልገዝ____የደም ሥር
መንኮብያ____አውራ ጣት
ክሳድ__አንገት
ከብድ__ሆድ
ቍይጽ__ጭን
መትከፍ_ትከሻ

#የቤት ዕቃዎች & አልባሳት
ቀርጠፋሉ____ቶፋ
ገብላ___ገንዳ/ገበታ
ቤረሌ___ብርሌ/ብርጭቆ
መሐፒል_ሳሙና
መንዲል_ሸማ ልብስ
ሰይቀል_እንዝርት
ጻሕል__ወጪት
ጽንጉል_ፍግ
ፍያል__ፍንጃል
ማዕሎ_አዷማ
ለንጳስ__ግምጃ
ኬጥሮጋውሎስ___የብረት ጋን
ፊላስ_የአልጋ ልብስ
ጌልዳቦሩ____ቡሃቃ
ምዕራ/መታግር_ጉልቻ
ቃሩራ____ጠርሙስ/ብርጭቆ
ንብቲራ_ኩስኩስት
ኮራ____ጋን/ጽዋ
ፓፒራ____ክብሪት
ጶደሬ____ግምጃ
ቢሶስ___አረንጓዴ ዓይነት ልብስ
ከፈር_ቅርጫት/እንቅብ
ጎሞር/ሜላቃ_ቁና
ጻሕር____ብረት ምጣድ
ፀምር____ግምጃ
መባሮ____መቆፈሪያ
መጕድዕ____መዶሻ
መሥነቅ____ስልቻ
መቀቅ_ሙገጫ
ቴውናቅ/ሱጣብ/ሱጣ__ወስከንበያ
ጸርቅ__ድሪቶ
ሶርቃቡ_እርሾ/ሊጥ
ድልጋቡ_አቅማዳ
መኩረቢ_መጥረቢያ
መሶብ_መሶብ
መዝረብ/ሰፌልያ____መዶሻ
መዝገብ_ሳጥን
ግራብ__ገንቦ
ጻሕብ__ማድጋ/ወጭት
ከረቦ__አገልግል
ክእቦ/ክቦ__ኩበት
ልሕኵት__ገንቦ
ሜላት_ሐር ግምጃ
መስብክት____ጋን
መሥነቅት____አቅማዳ
መቅጹት____ድስት/ምንቸት
መንኮክት____እንዝርት
ራግናት__ብቅል
ቀሡት_እንስራ
ዐራት_አልጋ
ወዲፈት____ዳውጃ/ግምጃ ጨርቅ
ጽህርት____ጋን
ጽፍነት____ስልቻ
ቴግኑ_ጉልቻ
ፓና____መብራት
ልጕን____ማሰሮ
ቆጶን____ጫማ
ጤገን____ብረት ምጣድ
ጵርዩን____መጋዝ
ግምዔ____ማሰሮ
ገልዕ____ገል
ፀፍዕ____አዛባ/ፋንድያ
መንካ____ማንኪያ
ማዕከክ_ማሰሮ/ቶፋ/ገንቦ
ማህው__ብርጭቆ/ብርሌ
ጠረጴዛ____ወንበር
ሰፌልያ____ድጅኖ/መዶሻ
አስፈሬዳ____እንቅብ/ቅርጫት
ወሳይድ_ትራስ
ሰንጎጕ_የብረት ዘንግ

#መልክዐ ምድር & ነገረ ሀገር
ሄላ_ምንጭ
ዔላ_የውሃ ጉድጓድ
ቀልቀል___ገደል አፋፍ
ደወል_አውራጃ/ቀበሌ
ዐምዓም___ረግረግ
ገዳም/ሊሳ_ዱር/በረሓ
መጽአሞ____ዋሻ/ግምጃ
ቆሮስ_መስፈሪያ ላዳን
ቀርሜሎስ____ለምለም ዱር
ቃዴስ____በረሓ
አርዮጳጌጤስ____መዝናኛ ቦታ
ባሕር____ባሕር
ወግር_ኮረብታ
ደብር_ተራራ
ሰንሰሪቁ/ኬርቃ____ስርጥ መንገድ
መርቄ____ቆላ
ሐይቅ____ወደብ/ዳር
መርሕብ____ሜዳ
ዐቀብ_ተራራ/ገደል
ግብ__ጉድጓድ
ምኔት_ገዳም
ሰኮት_አውራ መንገድ
ዐዘቅት____ጉድጓድ
ደሴት_የባሕር ጥጋጥግ
ገነት_ጓሮ/የተክል ቦታ
ጾማዕት/ጾላዕት___ዋሻ
ፂዖት____የከብት መሰማሪያ ክልክል
ፍኖት___ጎዳና
መዲና____ከተማ/አደባባይ
ፍና_መንገድ
ጕርን____አውድማ
ደደክ_ደጋ
ሐዝሐዝ____ረግረግ

#የእርሻ እቃዎች
ላሕሎ_ወገል
ሰይራ_ወገል
ሞሰርት_ማረሻ
አርዑት_ቀንበር
አግልዕት____ማነቂያ
ገራህት____እርሻ
ጸጕራፍ____ጅራፍ

#ነገረ #ቤት
ትሄ_____መስኮት
ጽርሕ_አዳራሽ
ኰኵሕ_አለት ደንጊያ
መርኆ_መክፈቻ
ሶልላ__ኩረት፣ አሸዋ፣ አፈር
ጺላ___ጭቃ
ሶቶፍሌ_ምንቸት
መርጡል____አዳራሽ
ሩካም___ዕብነ በረድ
ተንከተም_ድልድይ/መሰላል
ናሕስ___የግንብ ቤት
ኤስኬዴሬ_እልፍኝ
ኆር____መስኮት
ጠፈር____ባጥ
ፍንዱቅ____ሆቴል
ኆኅት_ደጃፍ
ሐይመት____ድንኳን
ልገት_ጎጆ
መሬት_አፈር
ብርት__ብረት
ቤት_ቤት
ኀጺን_ብረት
ሜላንትሮን____ጉልላት
ዕብን_ድንጋይ
ጽንጕን____ጭቃ
ታዕካ____አዳራሽ
ሐኒክ____አፈር
ሰዋስው___መሰላል/ድልድይ
ዴዴ____ደጃፍ በር
ሐመድ____አመድ/ክሰል
ድድ_መሰረት
መምሠጥ____ቁልፍ
አንቀጽ_ደጃፍ/በር
ዕፅ___እንጨት

ለአንድ ቃል ብዙ ተመሳሳይ ትርጉሞች አሉት። ስለዚህ የተደጋገሙ ቃላትን ስናይ በዚህ መልኩ እንደሆነ እናስተውል።
ለልጅዎ የግእዝ ስም ማውጣት ከፈለጉ ክፍል ፪

ግእዝ__አማርኛ
፩) መዓርዒር__ጣፋጭ
፪) አሜር__ፀሐይ
፫) አርያም_ሰማይ
፬) አምኃ_እጅ መንሻ
፭) ብሥራት___የምስራች
፮) ሰሎሜ_ሰላም
፯) አሜን__እውነት/ይሁንልኝ
፰) ሠዊት__እሸት
፱) ጸገየ___አበበ
፲) አስካል____ፍሬ
፲፩) ልዑል____ከፍ ያለ
፲፪) ሣህሉ____ይቅርታው
፲፫) ቀጸላ_አክሊል
፲፬) ሐመልማል___የለመለመ
፲፭) ከሃሊ_የሚችል ቻይ
፲፮) ጸዳሉ_መብራቱ
፲፯) ፈትለ ወርቅ____የወርቅ ፈትል
፲፰) ፊደል_ፊደል
፲፱) ማኅተም____ማተሚያ
፳) ሥዩም__የተሾመ ሹም
፳፩) ስብሐት____ምስጋና
፳፪) ስቡሕ_ምስጉን
፳፫) ተቅዋም_መቅረዝ
፳፬) ንጹሕ_የነጻ
፳፭) ሰላማ__ሰላም
፳፮) አዳም__ያማረ
፳፯) ዳግም_የደገመ
፳፰) ግሩም_ተፈሪ
፳፱) ጥዑም____የሚጣፍጥ
፴) ፍጹም__የተቀባ
፴፩) ይኄይስ____ተሻለ
፴፪) ሐዳስ/ሐዲስ___አዲስ
፴፫) ሕዳሴ__መታደስ
፴፬) ሰንኮሪስ_መምህር
፴፭) መቅደስ_ማመስገኛ
፴፮) ሞገስ__ባለሟል የተወደደ
፴፯) ትዕግሥት_መቻል
፴፰) ንጉሥ__የነገሠ
፴፱) ወራሲ__ወራሽ
፵) ውዳሴ__ምስጋና
፵፩) ጌራወርቅ____የወርቅ ሥራ
፵፪) ማኅደር_ማደሪያ
፵፫) ምሕረት_ይቅርታ
፵፬) መሓሪ__ይቅር ባይ
፵፭) ሠምረ__ወደደ
፵፮) ሥሙር_ተወዳጅ
፵፯) ሥምረት____መወደድ
፵፰) ነጸረ__ተመለከተ
፵፱) ምሥጢሩ____ምሥጢሩ
፶) መራሒ____መሪ
፶፩) ፍሥሓ_ደስታ
፶፪) አእመረ____አወቀ
፶፫) አእምሮ____እውቀት
፶፬) ፍቅር__መውደድ
፶፭) ክቡር__የከበረ
፶፮) ደብሩ__ተራራው
፶፯) ተግባር_ሥራ
፶፰) ረቂቅ__ረቂቅ
፶፱) መብረቁ____መብረቁ
፷) ነጸብራቅ__ነጸብራቅ

፷፩) ይባቤ___እልልታ
፷፪) ጥበቡ___ብልሃቱ
፷፫) መሠረት__መሠረት
፷፬) ብሑት___ስልጡን
፷፭) ትሕትና___ትሕትና
፷፮) ተከሥተ__ተገለጠ
፷፯) ሃይማኖት_ሃይማኖት
፷፰) በየነ__ፈረደ
፷፱) መኰንን____ገዢ
፸) በጽሐ__ደረሰ
፸፩) መስፍን____የሚገዛ
፸፪) ምስፍና____ግዛት
፸፫) ክርስቲያን____ክርስቲያን
፸፬) ወሰን__ድንበር
፸፭) መዋዒ_አሸናፊ
፸፮) ትንሣኤ_መነሳት
፸፯) ነቅዐ ሕይወት_የሕይወት ምንጭ
፸፰) ገዛኢ__ገዢ
፸፱) ምሕርካ ክርስቶስ___የክርስቶስ ምርኮ
፹) ባራኪ____ባራክ
፹፩) መልአክ____አለቃ
፹፪) በረከት____በረከት
፹፫) ህላዌ_መኖር
፹፬) ኂሩት_ቸር የሆነች
፹፭) ልባዌ_ማስተዋል
፹፮) ቤዛዊት_ያዳነች የምታድን
፹፯) ስርጋዌ____ሽልማት
፹፰) ስርጉት____የተሸለመች
፹፱) ተስፋ_ተስፋ
፺) ኬንያ__ብልሃተኛ
፺፩) ኖላዊ__ጠባቂ
፺፪) መርዓዊ____ሙሽራ
፺፫) ማዕዶት____መሻገሪያ
፺፬) ወልታ____መከታ/ጋሻ
፺፭) ሐዋዝ____ያማረ
፺፮) ግእዛን____ነጻነት
፺፯) ሕሊና____ሕሊና
፺፰) ማኅሌት____ምስጋና
፺፱) ኅሩይ__ምርጥ
፻) ሲሳይ__ምግብ
፻፩) ሠናይ____ያማረ
፻፪) ፈታሒ____የሚፈርድ
፻፫) ሐሴት____ደስታ
፻፬) ትርሲት_ሽልማት
፻፭) ተዋናዪ_ተጫዋች
፻፮) ዐቢይ___ከፍ ያለ
፻፯) ትውፊት_ስጦታ
፻፰) ኃያል_የበረታ
፻፱) ጽጌ__አበባ
፻፲) ፍሬሕይወት____የሕይወት ፍሬ
፻፲፩) ምዕዳን_ምክር
፻፲፪) ንኡድ___ያማረ
፻፲፫) ነገደ___ሄደ
፻፲፬) ነጎድጓድ____ነጎድጓድ
፻፲፭) ጸዓዳ_ነጭ
፻፲፮) ሠረጸ_በቀለ
፻፲፯) ደምፀ____ተሰማ
፻፲፰) ሮሐ_ወለወለ/አራገበ/አናፈሰ
፻፲፱) ናርዶስ_ሽቱ
፻፳) እፀ ሕይወት___የሕይወት እንጨት
#ድርሳነ #ቄርሎስ #ወጰላድዮስ #ክፍል 3
በተለያየ ዘመናት በልብ ወለድ እና በመሰለኝ እየተመረኮዙ ከእውነተኛዋ ሃይማኖት ያፈነገጡ ብዙ ናቸው።የሰው መጀመሪያ አዳም ነው።አዳም ደግሞ የሚያመልከው እግዚአብሔርን ነው።አዳም ሃይማኖትን ለልጆቹ እያስተማረ ልጆቹም በቅብብሎሽ (በትውፊት እየተቀበሉ ) ሳይቋረጥ ከአሁኑ ዘመናችን ደርሷል።ይሁንና ከእግዚአብሔር አፈንግጠው በራሳቸው ልቦለዳዊ ሕግ ሠርተው የተገኙ ሰዎች አሉ።እኒህ ሰዎችም ክፉ አመላቸውን ለትውልድ እያስተላለፉ ኖረዋል። ይሁን እንጂ የአዳም እምነት መነሻው የእግዚአብሔር መገለጥ ሲሆን፤የአዳምን ሃይማኖት የያዝን እኛም ከአዳም በቀጥታ የተቀበልነውን እናምናለን ።የመ*na*ፍ-ቃን ፣የአህዛብ ፣የአረማውያን እና የሌሎች እምነት ተከታዮች ግን መነሻቸው ሲመረመር ከአዳም የጀመረ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ የላቸውም ።ወይም በራሳቸው ሰዋዊ (ሰብአዊ )አስተሳሰብ እምነታቸውን የመሠረቱ ወይም ደግሞ በሰይጣን ሽንገላ የተታለሉ ሆነው እናገኛቸዋለን ።የእኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የአረዳዷ መሠረት ከአዳም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ትውፊት ስለሆነ በየዘመናቱ ዶግማዋ (መሠረተ እምነቷ ) አይለወጥም አይሻሻልም ።የአንዳንዶች ግን መነሻ ስለሌላቸው ትውፊታዊ አረዳድ ስለሌላቸው በየዘመናቱ ቋንቋ ፣ባህል፣እና አጠቃላይ የሕዝብ አኗኗር ሂደት በተለወጠ ቁጥር አረዳዳቸውን እየቀየሩ ይኖራሉ ።ይህ ልቦለዳዊ አሠራር ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ።እርሱ በስሜት ህዋሳቱ ስላልተረዳው ፈጣሪ የሚባል የለም ያለ ማኒ የሚባል ሰው ነበረ ፤እርሱን የመሠሉ መ*na*ፍ-ቃን መነናውያን ይባላሉ ።እኛ የማናውቀውን ነገርን ሁሉ የለም ብሎ ማሠብ ሁሉን አውቃለሁ ከሚል ግብዝ አስተሳሰብ የመነጨ ነው። እግዚአብሔርን በባሕርይው ያየው አንድስ እንኳ ባይኖርም ነገር ግን ደግሞ የማናውቀውን ማምለክ ስለማይገባ ለፍጡራኑ እይታ በሚያመች መልኩ በዘፈቀደ (እርሱ በወደደ) ለአብርሃም በሰው አምሳል ለሌሎች ቅዱሳንም በተለያዬ አምሳል ተገልጿል ።አምላክነቱን በተለያዩ ተአምራቶች አሳይቷል እነርሱም አምነው ለኛ ደግሞ በትውፊት አቀብለውናል ማለት ነው።
ሐራ ጥቃ ቃል ከአምላክነት ወደ ሰውነት ተለወጠ ይላሉ።ይኸውም አምላክ ሰው ሆነ ሲል ወደ ሰውነት ተለወጠ ብለው ልክ የሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ሆነች እንደሚለው አድርገው ይተረጉሙታል ።ቄርሎስ 12 ካለመኖር ወደመኖር የተፈጠረ ፍጥረት በእውነት መለወጥ ይስማማዋል ።ለፈጣሪ ግን መለወጥ አይስማማውም መዝ.101፣27 ሰማያት የእጅህ ስራዎች ናቸው።እነርሱ ይለወጣሉ አንተ ግን ያው አንተ ነህ ብሎ እንደተናገረው ። ሐራ ጥቃ ተለወጠ ያሉ ምን የሚለውን ኃይለ ቃል ይዘው ነው
ቢሉ ፤ ቃል ሥጋ ኮነ ያለውን ይዘው ነው።ለመ*na*ፍ-ቃን አንድን ቃል ይዘው መነሳት ልማዳቸው ነው።ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ እኔ ነበርኩ ባለው ቃል ይረታሉ። እኛ ግን ኮነን፣ኀደረን፣መጽአን የመሠለ ግሥ ስናገኝ በምሥጢረ ሥጋዌ ተዋሐደ ብለን እንተረጉማለን። ቅዱሳት መጻህፍትን ሁለንተናቸውን እንቀበላለን እንጅ ግማሹን ተቀብሎ ግማሹን መካድ የመ*na*ፍ-ቃን ጸባይ ነው።ቄርሎስ 13 ውጹእ ውእቱ መለኮት እሚጠት ወእምውላጤ ወፍጥረትሰ ሀሎ ውስተ ሚጠት ወውስተ ውላጤ ። መለኮት ከመመለስ ከመለወጥ የራቀነው።ፍጥረታት ግን ውላጤና ሚጠት ይስማማቸዋል። ሐራ ጥቃ ቃል እግዚአብሔር ተለውጦ ሰው ሆነ ካሉ አንተ ግን ያው አንተ ነህ ያለው የዳዊት ቃል ያሳፍራቸዋል። እና ነገራቸው ፈራሽ በስባሽ ልቦለዳዊ መሆኑን ያሳውቀናል። ፎጢኖስ የተባለ መ*na*ፍ-ቅ ደግሞ የቃል ህልውና ከማርያም ከተወለደ በኋላ ነው።ከማርያም ከመወለዱ በፊት አልነበረም ይላል። ነገር ግን እራሱ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ እኔ ነበርኩ ብሎ በግልጥ ስላስቀመጠልን ነገሩ ውሸት መሆኑን ይነግረናል።ወንጌላዊው ዮሐንስ ዮሐ. 1፣1 ላይ ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ በመጀመሪያ ቃል ነበር። ብሎ ሁሉ በእርሱ ሆነ ብሎ ሲናገርባቸው ፎጢኖሳውያን ያፍራሉ። ቅዱስ ኤፍሬምም በሃይማኖተ አበው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ብሎ ነግሮናል ።ድንግል ማርያም በሥጋ የወለደችው እርሷን አስቀድሞ የፈጠራትን ጌታ ነው። የመ*na*ፍ-ቃን ነገራቸው አንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይዘው ሌላውን በመጣል የተመሠረተ ልቦለዳዊ መሆኑን በዚህ ማወቅ እንችላለን ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
#በነገረ #ሃይማኖት #ዙሪያ #ኦርቶዶክሳዊው #አረዳድ
ለሃይማኖት መኖር መሠረቱ የፈጣሪ መኖር ነው።መቼም እኛ ራሳችንን እስካልፈጠርን ድረስ ፈጣሪ ነን ማለት አንችልም።አዳም እንደኛ ተፈጥሮ የተገኘ ነው።ፈጣሪው እግዚአብሔር መሆኑን ያወቀው ራሱ እግዚአብሔር ተገልጦለት ነው። ቃየልና አቤል እኛ አሁን ከእናት እና አባቶቻችን እንደምንወለደው ተወልደው የተገኙ ናቸው። ለሃይማኖታችን መነሻው በመጀመሪያ የእግዚአብሔር መገለጥ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለአባቶቻችን የተገለጠውን እኛ አምነን በመቀበል (በትውፊት) ነው።ስለዚህ ለሃይማኖታችን መነሻው የራሱ የእግዚአብሔር መገለጥ ነው። ይችን ትክክለኛ ሃይማኖት ለማጥፋት ሰይጣን ያላደረገው ነገር የለም። መጀመሪያ እርሱ ራሱ ፍጡር ሆኖ ሳለ መመለክ ፈልጎ አምላክ ነኝ ያለበት ጊዜ አለ።ነገር ግን ፈጣሪ በፍጥረቱ ስለሚታወቅ ፍጠር ሲሉት እፈጥራለሁ ብሎ እጁን ወደ እሳት ሲከት አቃጠለው።ውሸታምነቱ ታወቀ። ይህ ራሱን አምላክ የማድረግ እሳቤው አልሳካለት ሲል ሌላውን ከትክክለኛው አምላክ እያወጣ ፈጣሪህ ይህ ነው እያለ ፍጡር ፍጡርን እንዲያመልክ ይሰብክ ጀመር። አዳምን እጸ በለስን ብትበላ አምላክ ትሆናለህ ብሎ የውሸት ስብከት ነገረው። አዳምም በሰይጣን ውሸት ተታሎ እጸ በለስን በላ ነገር ግን እንኳን አምላክ ሊሆን የፈጣሪን ትእዛዝ በማፍረሱ ጸጋው ተገፈፈ።ልጅነትን አጣ።አዳም ሰይጣን የነገረው ነገር ውሸት መሆኑን አውቆ ከፈጠረው ፈጣሪ ይቅርታን ለመነ። ፈጣሪም ይቅርታውን ተቀብሎ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ተስፋ ሰጥቶታል።ከዚህ በኋላ አዳም ትክክለኛውን አምላክ ለልጆቹ እያስተማረ ልጆቹ ደግሞ ለልጆቻቸው እያስተማሩ እስካሁን ድረስ ደርሷል።ይህ ነገር እስከ ምጽአትም ይቆያል። በየዘመናቱ ሰይጣን አዳም ለልጆቹ ከነገራቸው ትምህርት ያፈነገጠ ውሸት እያመጣ ከእግዚአብሔር አምልኮ ለማውጣት ጥሯል።በዚህ የሰይጣን ተንኮል ደግሞ በየዘመናቱ የተታለሉ ብዙ ሰዎች ተነስተዋል።እግዚአብሔር ለአዳም አዳም ለልጆቹ እያለ የነገራቸውን ትተው በሰይጣን የማስመሰል ጥበብ እየተሸወዱ ብዙዎች ከትክክለኛዋ ሃይማኖት ወጥተዋል።

ከአዳም ጀምሮ ያለው መነሻዋ የእግዚአብሔር መገለጥ የሆነችው ሃይማኖት እና እስከዛሬ የቀጠለችው ይህች ዓለም እስክታልፍም የምትቆየው ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት።እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃልኪዳን ለመፈጸም አዳምን ወደቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ።ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በሃይማኖተ አበው እንደተናገረው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው።ይሁንና ሰይጣን በየዘመኑ በተንኮሉ ያሳመናቸው ሰዎች በክርስቶስ ላይ የክህደት ሀሳብን አስቡ። እምነታቸውን ከአዳም ጀምሮ በእግዚአብሔር መገለጥ ላይ ያደረጉ ሰዎች ግን "ጊዜው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ" ብለው እነ ቅዱስ ጳውሎስ መሰከሩ። የምን ጊዜ ነው የደረሰ ብለህ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆችን ብትጠይቃቸው አያውቁትም። ምክንያቱም ከአዳም ጀምሮ የመጣ ትውፊታዊ ማስረጃ የላቸውም። መካከል ላይ ሰይጣን አጥፍቷቸው ስለነበር አያውቁትም።የእኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች አረዳዳችንም ትውፊታዊ ነው። እንጂ ቋንቋ፣ ባህል፣ እና አጠቃላይ የሕዝቡ አኗኗር ዘይቤ በተለወጠ ቁጥር የሚለዋወጥ ሃይማኖት የለንም።ምክንያቱም ሃይማኖት የሚሰጥ እንጂ በሰው አእምሮ ተመቻችቶ የሚሰራ አይደለም። ይሁዳ.3 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ስለተሰጠች ሃይማኖት ትጋደሉ ዘንድ ብሎ ነግሮናል።ሃይማኖት አንድ ጊዜ ለአዳም ተሰጥታለች።ከዚያ በኋላ የእኛ ድርሻ እርሷን ተቀብሎ ለሌላው ትውልድ አስተምህሮዋ ሳይባረዝ ማስተላለፍ ነው።

በእርሱ የስሜት ሕዋሳት ስላልተረዳው እግዚአብሔር የሚባል የለም ያለ ማኒ የሚባል ሰው ነበር። እርሱን የመሰሉ ከሃድያን መነናውያን ይባላሉ።አንድን ነገር አንተ ስለማታውቀው የለም ማለት የእውቀት መጨረሻ እኔ ነኝ ከሚል ግብዝነት የመነጨ የትንንሽ ሰዎች እሳቤ ነው።እግዚአብሔርን ያየው አንድስ እንኳ የለም።በባህርይው የማይታይ አምላክ ስለሆነ ማለት ነው።ነገር ግን ደግሞ እኛ የማናውቀውን አናመልክም። እኛ ማየት ባንችልም።እኛ ማየት በምንችለው መጠን በተለያየ ዘመን እግዚአብሔር ተገልጧል።ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል ለሌሎች ነቢያትም በተለያየ አምሳል ተገልጧል።የፈጣሪነት ሥራን ሰርቶም አረጋግጦልናል።አምላክ ሰው ሲሆን ወደ ሰውነት ተለወጠ ያሉ እነ ሐራጥቃ አሉ። ነገር ግን አምላክ የማይለወጥ በመሆኑ መዝ.101፣27 ሰማያት የእጅህ ስራዎች ናቸው እነርሱ ያረጃሉ ይለወጡማል አንተ ግን ያው አንተ ነህ በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይረታሉ።ሌሎች ደግሞ ፎጢኖስን ተከትለው የሚናገሩ ናቸው።ፎጢኖስ የቃል ህልውና ከማርያም ወዲህ ነው።ማርያም ሳትወልደው አልነበረም ብሏል።ነገር ግን ዮሐ.1፣1 በመጀመሪያ ቃል ነበር ሁሉ በእርሱ ሆነ ብሎ ስለሚያመጣው በሌላም ገጸ ንባብ አብርሃም ሳይወለድ በፊት እኔ ነበርኩ ብሎ ጌታችን ስለተናገረ በዚህ ይረታሉ።ድርሳነ ቄርሎስ 11፣ 12፥ 13 በሰፊው የሚናገረው ይህንን ነው።ቀሪውንና የመጨረሻውን ክፍል ነገ አቀርባለሁ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥዑም የሆነው የአጫብር ወረብ።

መዓርዒር
ቤዛ ኩሉ
የሊቃውንቱ ምስጋና ልዩ ነው። ቅዱሳት በዓላት መንፈሳዊ በቁዔት የምናገኝባቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ አንድነታችንን የምናጠነክርባቸው ልዩ ስጦታዎቻችን ናቸው። በዓለ ልደተ ክርስቶስን ደብረ ሮሃ ላስታ ላሊበላ መጥተው ያክብሩ።
Audio
በሙስሊም ወንድማችን በብአል ዋዜማ በመስሪያ ቤቱ ዝግጅት ላይ ያቀረበው ልዪ ዝግጅት!! ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም የቀረበ መነባንብ!!!

#ከአዲስ አበባ
እውነት ትቅደም_
ውኑ ኢትዮጵያ በሕገ ወጥነት በራሷ ፈቃድ ጳጳስ ሾማለችን???? በፍጹም አልሾመችም። ሰይጣንን ለምን ካድክ ቢሉት በውሸት ለአዳም አልሰግድም ብየ ነው አለ እንደሚባለው (ገድለ ጊዮርጊስ)። የግሉ ትእቢትና ከንቱ ውዳሴ ከልዕልናው ጥሎት ሳለ መውደቁን በአዳም ለማላከክ መሮጡ የሰይጣንን ቀላልነት ያሳውቃል። በፍትሐ ነገሥቱ የኢትዮጵያ ሰዎች ከራሳቸው ጳጳስ አይሹሙ የሚል ሥርዋጽ ተቀምጦ ለብዙ ዘመናት ጳጳስ ከግብጽ እየመጣ ኖረናል። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፬፣ ቁጥር ፶-፶፩። በዚህም ምክንያት ቋንቋውን የማያውቅ የማያስተምር ሰው እየመጣ ኖሯል። ኢትዮጵያም በሊቃውንቶቿ ትጋት ወንጌልን ለሕዝቡ እያስተማረች ክርስትናን ጠብቃ ቆየች።  የጵጵስና ዋና ሥራው ሕዝቡን ማስተማር፣ ከሃድያንን ወደ አሚነ ሥላሴ ማምጣት፣ ሕዝቡን ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መመለስ፣ ደጋጉን በመልካም ሥራ ማጽናት ነው። በቋንቋ ምክንያት ግን ከግብጽ ተሹሞልን የሚመጣው ጳጳስ ይህንን ሊያደርግልን አልቻለም ነበር። በኋላ ሊቃውንት ተሰብስበው ይህ ለምን ይሆናል ኢትዮጵያ የራሷ ጳጳስ ይኑራት ብለው መከሩ። ነገር ግን ምንም እነርሱ ቢመክሩ የግብጽ ፓትርያርክ ካልፈቀደ ጉዳዩ እንደማይሆን ስላወቁ ሊቃውንት ተመርጠው ለግብጽ ፓትርያርክ አስረዱ። የግብጽ መንበረ ማርቆስም በጉዳዩ ተስማምቶ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስን ሹመልንና ወደ ኢትዮጵያ ላከልን። የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያ በራሷ እምቢተኝነት ጳጳስ አልሾመችም። ከመንበረ ማርቆስ አስፈቅዳ አደረገችው እንጂ። ክህነት ፲ መዓርግ አላት። እኒህም:-
     ፩) ሊቀ ጳጳሳት (ፓትርያርክ) [ፍት. ነገ. ፬]
     ፪) ጳጳስ (መጥሮጶሊስ)
     ፫) ኤጲስ ቆጶስ [ፍት. ነገ. ፬]
     ፬) ቆሞስ (አብሮጥሮስ) [ፍት. ነገ. ፬፣፷፪-፷፫]
     ፭) ቄስ (ቀስ) [ፍት. ነገ. ፮]
     ፮) ዲያቆን [ፍት. ነገ. ፯]
     ፯) ንፍቀ ዲያቆን [ፍት. ነገ. ፰]
     ፰) አናጉንስጢስ [ፍት. ነገ. ፰]
     ፱) መዘምራን [ፍት. ነገ. ፰]
     ፲) አጻዌ ኆኅት [ፍት. ነገ. ፰]
                            ።
የእነዚህም የየራሳቸው የሥራ ድርሻ አላቸው። ዐጻዌ ኆኅት ዘበኞች ናቸው። በወንዶች መግቢያ ሆነው ወደ ቤተክርስቲያን የሚገባውን ይቆጣጠራሉ። በስሕተትም በድፍረትም የተወገዙ ሰዎች እንዳይገቡ ይጠብቃል። መዘምራን ዳዊት ደጋሚዎች ናቸው። ይጸልያሉ ይዘምራሉ። አናጕንስጢስ አንባቢዎች ናቸው። ቅዱሳት መጻሕፍትን በቤተክርስቲያን የሚያነብ ነው። ንፍቅ ዲያቆንም ከሦስቱ በመዓርግ ከፍ ያለ ነው። ይሁንና እኒህ ሁሉ በአንብሮተ እድ አይሾሙም። እንዲሁ በኤጲስ ቆጶሱ ቃል ይሾማሉ። ንዋየ ቅድሳትን ልብሰ ተክህኖን መንካት መልበስ አይፈቀድላቸውም። ዲያቆናት በአንብሮተ እድ የሚሾሙ ናቸው። ተንሥኡ ለጸሎት እያሉ ምእመናንን የሚያተጉ ናቸው። ቀሳውስት ማቁረብ ማስተማር ይችላሉ። ቄስንም ዲያቄንንም የሚሾማቸው ኤጲስ ቆጶሱ ነው። ቆሞስ መነኵሴ ሆኖ ከቄስ በመዓርግ ከፍ ያለ የኤጲስ ቆጶሱ አማካሪ ነው። ኤጲስ ቆጶስን በፓትርያርኩ ፈቃድ በሲኖዶስ ፈቃድ ሦስት ወይም ከዚያ በላይ ኤጲስ ቆጶሳት አንብሮተ እድ አድርገው ይሾሙታል። ዘመኑ ከፍቶ ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ካልተገኙ ግን በሁለት ኤጲስ ቆጶሳትም ተፈቅዷል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ጳጳሱና ሊቀ ጳጳሳቱ ፈቅደው እንጂ ሳይፈቅዱ መሆን አይችልም።
                             ።
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፬ ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ይናገራል። ፓትርያርክ (ሊቀ ጳጳሳት) ርእሰ ኤጲስ ቆጶሳት ነው። ሊቃነ ጳጳሳትሰ ውእቶሙ ተላውያነ ክርስቶስ። ሊቃነ ጳጳሳትስ እንደምናቸው ብትል ክርስቶስን የመሰሉ የክርስቶስ ተከታዮች ናቸው። የሊቀ ጳጳሳት ሊቅነቱ በምእመናንና በኤጲስ ቆጶሳት ላይ ነው። የኒቅያ ሊቃውንት ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም ላይ አራት ብቻ እንዲሆኑ አዝዘዋል። ፍት. ነገ. ፬፣ ቁጥር ፵። አራቱ የተባሉትም መንበረ ማርቆስ (እስክንድርያ)፣ መንበረ ዮሐንስ ቴዎጎሎስ (ኤፌሶን)፣ መንበረ ጴጥሮስ (ሮምያ)፣ መንበረ ጴጥሮስ ካልእ (አንጾኪያ) ናቸው። በየዘመናቱ የተነሡ አባቶቻችን ደግሞ እንደየዘመኑ ሥርዐትን ማሻሻል ስለሚችሉ አሁን የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ሊቃነ ጳጳሳት ፮ ደርሰዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በሲኖዶስ ፈቃድ እንጂ በጉልበትና በማን አለብኝነት አልሆነም። አንቀጽ ፭ ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ይናገራል። ኤጲስ ቆጶሳትን እንድናከብር እንድንወድ ታዘናል። ፍት ነገ. ፭፣ ፻፵፬ ኤጲስ ቆጶስ ውእቱ አቡክሙ እምታሕተ እግዚአብሔር ዘወለደክሙ ዳግመ እማይ ወእመንፈስቅዱስ። ኤጲስ ቆጶስ ከውሃ ከመንፈስቅዱስ የወለዳችሁ ከእግዚአብሔር በታች ያለ አባታችሁ ነው። ተብሏል። በዚሁ ምዕራፍ ቁጥር ፻፵፮ ወበእንተ ዝንቱ ይደልወክሙ ከመ ታፍቅርዎ ለኤጲስ ቆጶስ በፍቅረ አብ። ስለዚህ ኤጲስ ቆጶስን በአባት ፍቅር ልትወዱት ይገባል ተብሏል። በመሆኑም ያልተረጋገጠ ወሬ ይዞ እንኳንስ ጳጳስን ማንኛውንም ሰው ማማት ትልቅ ነውር ነው። ጳጳስን የምንወደው ግን ከእግዚአብሔር በታች ነው። ምን ማለት ነው?የምንወደው የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዐት ጠብቆ ሲገኝ ብቻ ነው። ካልጠበቀ ግን አናከብረውም አንወደውም። ረስጣ ፶፪ "እመቦ ኤጲስ ቆጶስ ዘፈቀደ በሕጸተ አእምሮቱ በቀለ ኢኮነ ውእቱ ኤጲስ ቆጶስ። ዳእሙ ስም ሕስው ሀሎ ላዕሌሁ። አኮ ውእቱ እምኀበ እግዚአብሔር ዳእሙ እምኀበ ሰብእ" እንዲል በቀለኛ የሆነ ነውር ያለበት ከሆነ ቆብ ብቻ አደረገ እንጂ ኤጲስ ቆጶስ ሊባል አይገባውም አይደለም ተብሏል። የተሾመውም ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰው ነው ተብሏል። በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳይ ችግር አለ ብሎ ያሰበ ሰውም በሕገ ወጥነት ጳጳስ መሾም ሳይሆን በሲኖዶስ ስብሰባ ጉዳዩን ማቅረብ ነው። ፍት. ነገ. ፭፣ቁጥር ፻፷፭  "ኤጲስ ቆጳሳት ከጳጳሳቸው ወይም ከሊቀ ጳጳሳታቸው በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰብሰቡ። በዘ ያሰስሉ እከየ ወቍጥዐ። ቂም በቀልን ያርቁ ዘንድ" ተብሎ እንደተጻፈው።በዚህ ጉባኤ አጀንዳ አስይዞ ተነጋግሮ ችግርን መፍታት ነው።
                               ።
መውጫ
ፍት. ነገ. ፭፣፻፸ "ኢይሠየሙ ክልዔቱ ኤጲስ ቆጶሳት ላዕለ አሐቲ ሀገር" ይላል። የሎዶቅያ ሊቃውንትም በ፶፯ኛው አንቀጽ ይህንኑ ብለዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከተመደቡት ጳጳሳት ውጭ ሌላ በእነ አባ ሳዊሮስ በወሊሶ ያለ ሥርዐት የተሾመ ኤጲስ ቆጶስን ምእመናን ሊቀበሉት አይገባም። እንዲያውም በዚሁ አንቀጽ ይህን ያደረገ ቢኖር ይወገዝ ተብሏል። ስለዚህ ከሥርዐተ ቤተክርስቲያን ወጥታችሁ በሕገ ወጥነት የተሾሙትን ግለሰቦች እንዳትቀበሉ። ብትቀበሉ ግን ጠባችሁ ከሥርዐተ ቤተክርስቲያን ባለቤት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኑን ከወዲሁ እወቁት። ጵጵስና በጉቦ፣ በጉልበት፣ በተንኮል ኤጲስ ቆጶስነትን የተቀበለ ይሻር። የሾመው ጳጳስም ይሻር። ተብሎ ፍት. ነገ. ፭፣ ቁጥር ፻፸፫-፻፸፬። ተገልጿል። ቤተክርስቲያን ባለቤቷ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ባለቤት ያላትን ቤተክርስቲያንን ባለቤት እንደሌላት በጉልበት የሚሿሿሙባት አይደለችም።
                               ።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
ባሕረ ሐሳብ.pdf
389.7 KB
ባሕረ ሐሳብ ከነ የአባባል ሥርዓቱ

https://www.tg-me.com/learnGeez1
2024/10/01 09:25:48
Back to Top
HTML Embed Code: