Telegram Web Link
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር።
² ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤
³ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤
⁴-⁵ ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።
⁶ ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።
⁷-⁸ የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።
⁹-¹⁰ ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
¹⁴ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
¹⁵ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
¹⁸ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
¹⁹ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።
⁶ ሕዝቡም የፊልጶስን ቃል በሰሙ ጊዜ ያደርጋት የነበረውንም ምልክት ባዩ ጊዜ፥ የተናገረውን በአንድ ልብ አደመጡ።
⁷ ርኵሳን መናፍስት በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ይወጡ ነበርና፤ ብዙም ሽባዎችና አንካሶች ተፈወሱ፤
⁸ በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።
⁹ ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ።
¹⁰ ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።
¹¹ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር።
¹² ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።
¹³ ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ፤ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ።
¹⁴ በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው።
¹⁵ እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን። እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን። ወይትዌክፎሙ ለዕቤራት ወለእጓለ ማውታ"። መዝ 145፥8-9።
"እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድሀ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል፤ የኃጢአተኞችንም መንገድ ያጠፋል። መዝ 145፥8-9።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኀዳር_18_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ዮሐንስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።
⁵ ኢየሱስም ዓይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን፦ እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን? አለው።
⁶ ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።
⁷ ፊልጶስ፦ እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም ብሎ መለሰለት።
⁸ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ፦
⁹ አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።
¹⁰ ኢየሱስም፦ ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር።
¹¹ ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፥ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።
¹² ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው።
¹³ ስለዚህ አከማቹ፥ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ።
¹⁴ ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
¹⁵ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
✝️የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስ የዕረፍት፣ የቅዱሳት ደናግል አጥራስስና ዮና ዕረፍት፣ የቅዱሳን ኤላውትሮስና የእናቱ እንትያ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና)  ጾም ጊዜ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እናት የቅድስት ኤልሳቤጥ እናቷ ማን ትባላለች?
Anonymous Quiz
14%
ቅድስት ማርያም
35%
ቅዱስት ሰሎሜ
32%
ቅድስት ሶፍያ
19%
ቅድስት ዴርዴን
ካህኑ ቅዱስ አሮን በስንት ዓመቱ ነው ያረፈው?
Anonymous Quiz
40%
120
22%
123
22%
125
15%
124
እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነጻ የወጡት በየትኛው ወር ነው?
Anonymous Quiz
32%
በመጋቢት
22%
በመስከረም
32%
በሚያዝያ
14%
በግንቦት
ከ12ቱ ሐዋርያት አብን አሳየንና ይበቃናል ብሎ የክብር ባለቤት ጌታችንን የጠየቀው ሐዋርያ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
12%
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል
13%
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
43%
ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ
33%
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ
ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? ሲለው ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ ያለው ማንን ነው?
Anonymous Quiz
55%
ናትናኤልን
23%
እንድርያስን
17%
ጳውሎስን
5%
ሉቃስን
#ኅዳር_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
#የቅዱስ_ሰርጊስ_ሰማዕት ቤተክርስቲያን የከበረችበት ነው፣ #ቅዱስ_ሐዋርያ_በርተሎሜዎስ የልደቱና በእልዋህ አገር ላደረገው ተአምር መታሰቢያው ነው፣ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ከሚስቱ_ጰጥሪቃ ከአምስት ወር ልጁም #ከደማሊስ ጋር በሰማዕትነት ያረፈበት

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰርጊስ_ሰማዕት

ኅዳር ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ሩጻፋ በሚባል አገር የሰማዕት ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው።

ንጉሥ መክስምያኖስም ወደ ሶርያ አገር ወደ አንጥያኮስ በላካቸው ጊዜ ቅዱስ ባኮስን ከውኃ በማስጠም በጥቅምት ወር በአራተኛ ቀን ገደሉት። ቅዱስ ሰርጊስን ግን አሥሮ በወህኒ ቤት አኖረው።

ከዚህም በኋላ በእግሮቹ ውስጥ ረጃጅም የብረት ችንካሮችን ቸንከረው ከፈረሰኞች ጋር ሩጻፋ ወደሚባል አገር እንዲወስዱት መኰንኑ አዘዘ።

ሲወስዱትም ያስሮጡት ነበር ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር በጐዳናም አንዲት ድንግል ብላቴና አገኘ ከእርሷም ዘንድ ውኃን ጠጣ ሥጋዬን ትወስጂ ዘንድ እስከ ሩጻፋ ተከተይኝ አላት እርሷም ራራችለት ለጒልምስናውም አዘነችለትና ተከተለችው።

አንጥያኮስም እንዲህ ብሎ ጽፏልና ቅዱስ ሰርጊስ ትእዛዜን ተቀብሎ ለአማልክት ካልሠዋ ራሱን በሰይፍ ይቁረጡ። እርሱም ለቅዱስ ሰርጊስ ወዳጅ ነበርና ስለርሱም ይችን ሹመት አግኝቷት ነበርና በዚያንም ጊዜ ወታደሩ በጥቅምት ዐሥር የቅዱስ ሰርጊስን ራስ ቆረጠው ያቺም ብላቴና ቀርባ ከእርሷ ጋር በነበረ የፀጕር ባዘቶ ከአንገቱ የፈሰሰውን ደሙን ተቀበለች። የስደቱም ወራት እስከ አለፈ ድረስ ሥጋውን ጠበቀች።

ከዚህም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን አነፁለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትንም ሰብስበው አከበሩዋት በዚች ቀን ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቅ ተአምር ተገለጠ በእምነት ከእርሱ ለሚወስዱ ሁሉ በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሽታው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከሥጋው የሚፈስ ሁኗልና።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርተሎሜዎስ_ሐዋርያ

በዚህችም ዕለት ጌቶቻችን ከሆኑ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ የቅዱስ ሐዋርያ በርተሎሜዎስ የልደቱ መታሰቢያው ነው፤ ደግሞም እልዋህ በሚባል አገር አስተምሮ ብዙዎችን #እግዚአብሔርን ወደማወቅ ለመለሰበት መታሰቢያው ነው።

ለዚህም ሐዋርያ ሒዶ ያስተምር ዘንድ እልዋህ በሚባል አገር ዕጣው ወጣ። እርሱም ከ ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በአንድነት ሔደ የክብር ባለቤት በሆነ በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም አስተማሩ ልባቸውንም የሚያስደነግጥ ድንቆች ተአምራትን በፊታቸው ከአደረጉ በኋላ #እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሷቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቶ ያስተምር ዘንድ ምክንያት አደረገ ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ ባሪያ ሸጠው። ባለ ጸጋ ለሆነ መኰንንም በወይን አትክልት ውስጥ የሚያገለግል ሆነ ድንቅ ተአምርን በማድረግ የተቆረጡ የወይን ቅርንጫፎች በሠራተኞች እጅ ላይ ሳሉ አፈሩ። የአገረ ገዥውም ልጅ በሞተ ጊዜ ከሞት አሥነሣው የሀገር ሰዎችም ሁሉ አመኑ #እግዚአብሔርንም ወደ ማወቅ ተመለሱ።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በርበር ወደሚባል አገር ሔዶ ያስተምር ዘንድ ሐዋርያ በርተሎሜዎስን አዘዘው እንዲረዳውም ሐዋርያ እንድርያስን ከደቀ መዝሙሩ ጋር ላከለት። የዚያች አገር ሰዎች ግን እጅግ የከፉ ስለሆኑ በፊታቸው ድንቆች ተአምራቶችን እያደረጉላቸው ሐዋርያትን አልተቀበሏቸውም።

#ጌታችንም ሰውን ከሚበሉ አገር አንዱን ገጸ ከልብ ይታዘዝላቸው ዘንድ በሚያዙት ሁሉ ትእዛዛቸውን እንዳይተላለፍ አዘዘው። ሐዋርያትም ወደዚያች አገር ሁለተኛ ይዘውት ገቡ የሀገር ሰዎችም ሐዋርያትን ይበሏቸው ዘንድ ነጣቂዎች የሆኑ አራዊትን አወጡ። ያን ጊዜም ያ ገጸ ከልብ በአራዊቱ ላይ ተነሥቶ እየነጠቀ በላቸው ይህንንም ገጸ ከልብ ከመፍራት የተነሣ ከሰዎች በድንጋጤ የሞቱ ብዙዎች ናቸው።

የሀገር ሰዎች ሁሉም የክብር ባለቤት በሆነ በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ ከሐዋርያትም እግር በታች ሰገዱ የሚሉአቸውን ሁሉ የሚያደርጉ ታዛዦች ሆኑ። ሐዋርያትም ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ካህናትንም ሹመውላቸው ከእነርሱም ዘንድ ወጥተው #እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ሔዱ።

ሐዋርያ ቅዱስ በርቶሎሜዎስም #እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች ወደሚኖሩት በባሕር ዳርቻ ወዳሉ አገሮች ሔዶ የክብር ባለቤት በሆነ በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ሰበከላቸው በፊታቸውም ተአምራትን አደረገ ሁሉም የ #ጌታችን በሆነች በቀናች ሃይማኖት አመኑ።

ሐዋርያ ቅዱስ በርቶሎሜዎስም ከዝሙት ርቀው ንጹሐን እንዲሆኑ ሰዎችን የሚያዝዝ ሆነ። ንጉሥ አግሪጳም ስለርሱ በሰማ ጊዜ በከበረ ሐዋርያ በርቶሎሜዎስ ላይ እጅግ ተቆጣ። በማቅ ከረጢት ውስጥ እንዲአደርጉትና አሸዋ ሞልተው ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ። እንዲሁም ይህን አደረጉበት ምስክርነቱንና ተጋድሎውንም በመስከረም 1ቀን ዕለት ፈጸመ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ በርተለሜዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎፍሎስና_ሚስቱ_ጰጥሪቃ_ደማሊስ (ልጁ)

በዚችም ዕለት ቅዱስ ቴዎፍሎስ ከሚስቱ ጰጥሪቃ ከአምስት ወር ልጁም ከደማሊስ ጋር በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ #እግዚአብሔርን በመፍራትና በአማረ አምልኮ ያደገ ነው ሰዎች ሒደው ቅዱስ ቴዎፍሎስ ክርስቲያን መሆኑን ለመኰንኑ ለአንቲጳጦስ ነገሩት መኰንኑም በዜውስ ጣዖት ቤት ሳለ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ አዘዘ።

ቅዱሱንም በአቀረቡት ጊዜ አንተ ከወዴት ነህ ሃይማኖትህስ ምንድን ነው አለው። እርሱም የክብር ባለቤት #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን የማምን ክርስቲያን ነኝ አለ መኮንኑም በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱሱም ክብር ይግባውና ከ #ጌታዬ_ከኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት አልሠዋም አለው።

መኰንኑም የሆድ ዕቃው እስቲታይ ሰቅለው ይሠነጣጥቁት ዘንድ አዘዘ እርሱ ግን በ #ጌታችን ኃይል ስለተጠበቀ ምንም ምን አልደረሰበትም ሁለተኛም እሳትን አንድደው ከውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ ቅዱሱም በእሳት መካከል በጸለየ ጊዜ እሳቱ ተበተነ ምንም ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ።

መኰንኑም ይህን አይቶ በረኃብ እንዲሞት አሥረው አጽንተው ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ ከስምንት ቀንም በኋላ ሚስቱ ጰጥሪቃ ሕፃኗን ተሸክማ መጣች ምስክርም ሁኖ በ #ክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አጽናናችው።

መኰንኑም ለቅዱስ ቴዎፍሎስ ምግብ የሰጠው እንዳለ ብሎ ሊመረምር ሔደ የእሥር ቤቱንም ደጅ በከፈተ ጊዜ ጣፋጭ የዕጣን መዓዛ ተቀበለው ቅዱስ ቴዎፍሎስንም በተነጠፈ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ሦስት መላእክት ማርና ወተት ሲመግቡት አገኘው በአየውም ጊዜ ደንግጦ ወደኋላው ተመለሰ።

በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎፍሎስን ወደ አደባባይ እንዲአመጡት አዘዘ እርሱም ሚስቱ ተከትላው መጣ መኰንኑም ዲዮስ ለሚባል አምላክ ሠዋ አለው። ቅዱሱም እኔ ዓለምን ሁሉ ለያዘ ለእውነተኛው አምላክ ለ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ለሌላ አልሠዋም አለ።
በዚያንም ጊዜ ለአንበሳ እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ አንበሳውም ሩጦ እግሮቹን ሳመ። ከዚያም በኋላ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አቆሰለው ተጋድሎውን በዚህ ፈጽሞ ነፍሱን ሰጠ። ቅድስት ሚስቱ ጰጥሪቃም ሥጋውን አንሥታ ከሣጥን ጨመረች መኰንኑም እርሷንም ወደ አደባባይ አምጥተው ለአንበሳ እንዲሰጧት አዘዘ። ሕፃኑም አንበሳውን በአየው ጊዜ ሣቀ የአምስት ወርም ልጅ ሲሆን አንድ አምላክ በሚሆን በ #አብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ አምናለሁ ብሎ ተናገረ ይህንንም ብሎ በአንበሳ አፍ ከእናቱ ጋር ተበላ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር እና #የመስከረምና #ጥቅምት ስንክሳር)
"በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

          #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የሥላሴን_መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት_ለልደታቸው በዓል #እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።
                          
#አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።

የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ #እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።

ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።

ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ " #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።

ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው።  ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።

ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት #ድንግል_ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።

ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።

ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ #እግዚአብሔር_አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን #ድንግል_ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።

በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የ #እግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።

ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።

ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት19 ስንክሳር።    
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
²⁹ ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን?
³⁰ ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን?
³¹ ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹-³⁰ አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።
³¹ ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።
³² ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።
³³ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።
³⁴ በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥
³⁵ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_19_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ.18÷7-8
"የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል"። መዝ.18÷7-8
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_19_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።
² የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
³ ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥
⁴ ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
⁵ እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
⁶ ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
⁷ ሄዳችሁም፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ።
⁸ ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።
⁹ ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥
¹⁰ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።
¹¹ በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።
¹² ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤
¹³ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ።
¹⁴ ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።
¹⁵ እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና ጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።   
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2025/01/06 07:13:34
Back to Top
HTML Embed Code: