Telegram Web Link
#ኅዳር_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ ቀን #የሰማዕት_ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው፣ ሁለተኛው የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_አንያኖስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት

ኅዳር ሃያ በዚህችም ቀን የሠራዊት አለቃ የነበረ የሰማዕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው።

የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።

ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ።

አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ #ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።

ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው።

የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።

ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ አለው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ# ኢየሱስ_ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ ይበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና። ንጉሡም እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ አለው።

በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ የሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በ #እግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ አላቸው። እነርሱም ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን አሉት እርሱም ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ አላቸው።

ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ አሉት።

ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው #ጌታዬ_አምላኬ_ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ_ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን።

ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በ #መስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለ #እግዚአብሔር_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።

አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።

በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው።

ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል #እግዚአብሔርም ይበቀልላታል አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና #ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።

ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው።

ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ #እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል።

በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት።

በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ እነሆ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣ ወይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ።
ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት አንተ ከሀዲ #እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ።

ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ክብር ይግባውና ከ #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከ #ጌታ_ከኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ።

ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በ #ጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም ። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው።

ከዚያ በኋላም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩለት ስብጥ በሚባል በአባቱ አገርም በተሠራች ገዳም ሥጋውን አኖሩ ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ተደረጉ ታላቅ ፈውስም ሆነ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_አንያኖስ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ። እርሱም ለወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ነው።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸው እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስም ወደ እስክንድርያ አገር መጀመሪያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ አታኦስ አለ ትርጓሜውም አንድ #እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የ #እግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት #ክርስቶስን አመሰገነው።

ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው።

ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ #እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት የ #ወልደ_እግዚአብሔርን ሰው መሆን፣ መከራ #መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ፣ ስለ ትንሣኤውና፣ ስለዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ።

የአንያኖስም ልቡ ብሩህ ሆኖለት በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ። የ #መንፈስ_ቅዱስም ጸጋ በላያቸው ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።

ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምዕራብ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።

ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_19_እና_ሐምሌ_20)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቲቶ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
⁶ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።
⁷ ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥
⁸ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤
⁹ ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።
¹⁰ የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤
¹¹ እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
² በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
³ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
⁴ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
⁵ እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
⁶ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
⁷ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
³¹ ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_20_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7።
"በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና። ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል"። መዝ 83፥6-7።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኀዳር_20_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
² በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
³ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
⁴ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
⁵ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
⁶ ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።
⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
¹² እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
¹³ ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
¹⁶ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
¹⁷ ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
¹⁸ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
¹⁹ እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።
²⁰ ከእነርሱም ብዙዎች፦ ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
²¹ ሌሎችም፦ ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
✝️የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አንያኖስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት ቅዱስ መላዕክ ማን ይባላል?
#ኅዳር_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚህች ቀን የእመቤታችን #የቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም የበዓልዋ ነው፣ ከሮሜ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ አረፈ፣ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ቆዝሞስ አረፈ፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ዮሐንስ ዘአስዩጥ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል #ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

#እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። #ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ #መስቀሉንና #ታቦተ_ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ #እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)

በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን #ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።

#በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል #ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘሮሜ

በዚህችም ዕለት ከሮሜ አገር የሆነ ተአምራትን የሚያደርግ ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነቱ ሥራ ይራዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ ።

በበረሀውም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባለገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።

ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከ #እግዚአብሔር የሆነ ነው አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ።

#እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህም ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ ። ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱበት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስበርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፍሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚያች ባሕር #እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች በመካከላቸውም ሰላም ሆነ በእጆቹ ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራት ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም አረፈ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ቆዝሞስ_ሊቀ_ጳጳሳት
በዚህችም ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቆዝሞስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ አራተኛ ነው። ይህም አባት ብዙ መከራና ኀዘን ደረሰበት በዘመኑም በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ላይ መከራና ችግር ደረሰባቸው በእነዚያም ወራት የክርስቲያን ወገኖችና አይሁዳውያን ልብሳቸውን በሰማያዊ ቀለም እንዲያቀልሙት እንጂ ነጭ ልብስ እንዳይለብሱ የእስላሞች ንጉሥ ጋዕፊር አዝዞ ነበርና።

በዚህም አባት ዘመን ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ በአስቄጥስ ገዳም በቅዱስ ሳዊሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል #ማርያም ሥዕል ነበረች ጐኗም ተገልጦ ከእርሷ ብዙ ደም ፈሰሰ በግብጽ አገር ከአሉ ከሌሎች ሥዕሎችም ከዐይኖቻቸው ብዙ ዕንባ ፈሰሰ ይህም የሆነው በሊቀ ጳጳሳቱና በክርስቲያን ወገኖች ላይ ስለ ደረሰው መከራ እንደ ሆነ በመራቀቅ የሚያስተውሉ አወቁ።

ከዚህም በኋላ ስለእነዚያ የከፉ ወራቶች ፈንታ በጎ የሆኑ ወራቶችን #እግዚአብሔር ሰጠው ሁል ጊዜም ምእመናንን የሚያስተምራቸውና የሚያጽናናቸው በቀናች ሃይማኖትም የሚያበረታታቸው ሆነ ። በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይ ሰባት ዓመት ከአምስት ወር ከኖረ በኋላ በአምስት መቶ ሰባ አምስት ዓመተ ሰማዕታት ኅዳር ሃያ አንድ ቀን አረፈ ይንሶር በሚባል ዋሻውም ተቀበረ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘአስዩጥ

በዚችም ቀን ደግሞ የብርሌ የብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ የሆነ ከአስዮጥ አገር ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ ። ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ አሳድገውታል የጥርብ ሥራንም አስተማሩት ከጥቂት ዘመናትም በኋላ አባቱና እናቱ አረፉ። ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ አባ ኤስድሮስና ወደ አባ ባይሞን ዘንድ ሒዶ መነኰሰ በጾምና በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምዶ ተጋደለ ዜናውም በራቁ ገዳማት ሁሉ ተሰማ ።

ከዚህም በኋላ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠለት ወደ ሀገሩ ሒዶ ወገኖቹን የጽድቅን ጎዳና ይመራቸው ዘንድ አዘዘው። ቅዱስ ቊርባንንም ሳይቀበል ከበዓቱ የማይወጣ ሆነ። በአንዲት ዕለትም ሁለት ቅዱሳን አረጋውያን አባ አብዢልና አባ ብሶይ ወደርሱ መጡ ገና ወደርሱ ሳይቀርቡ ከሩቅ ሳሉ ስማቸውን በመጥራት ሳያውቃቸው አባቶቼ ለመምጣታችሁ ሰላምታ ይገባል ብሎ ተናገረ እጅግም አደነቁት አባ ሲኖዳም ከግብጽ አገር እየመጣ ብዙ ጊዜ ይጎበኘው ነበር።

የከዳተኞችም ጠብ በግብጽ አገር ላይ በተነሣ ጊዜ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የላከው የጦር መኰንን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጣ። በጸሎቱም ይራዳው ዘንድ ለመነው ቅዱስ ዮሐንስም #መስቀሉን አንሥቶ መኰንኑን አይዞህ አትዘን አንተ ጠላቶችህን ድል ታደርጋለህና አለው እንደ ቃሉም ሆነ።

ዳግመኛም በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላይ ጠላት በተነሣበት ጊዜ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ላከ እርሱም አትዘን አንተ ጠላትህን ታሸንፋለህ አለው ያን ጊዜም ጠላቶቹን አሸነፈ ።

ከዚህም በኋላ በእነዚያ ወራት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የርኲሰትን ሥራ ስለ ሠሩ የአስዮጥን ሰዎች እንዲገድሏቸው ሀገራቸውንም እንዲአጠፉ አዘዘ። ንጉሡም የላከው መኰንን ሳይደርስ የ #እግዚአብሔር መልአክ ይህን ነገር ለአባ ዮሐንስ አሳወቀው የሀገርም ሰዎች የንጉሡን ትእዛዝ በሰሙ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ገዳም ወጥተው ስለ መጥፋታቸው በፊቱ አለቀሱ አባ ዮሐንስም አትጨነቁ አይዟችሁ #እግዚአብሔር ያድናችኋልና አላቸው።

መኰንኑም በመጣ ጊዜ ከእርሱ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሰ አባ ዮሐንስም ንጉሡ ያዘዘውን ሁሉ ነገረው መኰንኑም ሰምቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዢ ሆነ ለመኰንኑም ርኩስ መንፈስ ያደረበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረው ያድንለት ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስን ለመነው በዚያንም ጊዜ ዘይትን ቀብቶ አዳነው።

ከዚህም በኋላ የአስዩጥ ሰዎችን መገደላቸውን እንዲተው ወደ ንጉሥ ይጽፍለት ዘንድ መኰንኑን አባ ዮሐንስ ለመነው መኰንኑም ጽፎ ለአባ ዮሐንስ ሰጠው አባ ዮሐንስም ተቀብሎ ወደ ዋሻው ገባ ወደ #ጌታችንም ጸለየ ብርህት ደመናም መጣች ተሸክማም ወደ ንጉሡ አደረሰችው ያን ጊዜም ንጉሥ ከማዕድ ላይ ነበረ ያንንም ደብዳቤ ከወደላይ ጣለለት ንጉሡም አንሥቶ በአነበበው ጊዜ ከመኰንኑ የተጻፈ እንደሆነ በመካከላቸው በአለ ምልክት ተጽፎ አገኘው የተጻፈውም ቃል ስለ አባ ዮሐንስ ልመና ሀገሪቱን ማጥፋትን እንዲተው የሚል ነበር ቀና ባለ ጊዜም ደመና አየ ንጉሡም አደነቀ።

ከዚህም በኋላ ሀገሪቱን ማጥፋትን ስለ አባ ዮሐንስ ይተው ዘንድ መልሱን ለመኰንኑ ንጉሡ ጽፎ ደብዳቤዋን ወደ ደመናው ወረወራት የተሰበሰቡትም እያዩ እጅ ተቀበለችውና ወደ ደመናው ገባች ወዲያውኑ አባ ዮሐንስ በዚያች ደመና ወደበዓቱ ተመለሰና በማግሥቱ ያቺን ደብዳቤ ለመኰንኑ ሰጠው በላይዋም የንጉሡ ፊርማውና ማኅተሙ አለ በአያትና በአነበባት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ስለ ሀገሪቱ ድኅነትም #እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደአገሩ ተመለሰ።

የንጉሥ ዘመድ የሆነች የከበረች ሴት ዜናውን በሰማች ጊዜ ከደዌዋ ይፈውሳት ዘንድ ወደርሱ መጣች በጸሎቱም ተፈወሰች። ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በሞተ ጊዜ መናፍቁ መርቅያን ነገሠ ። ቅዱስ አባ ዲዮስቆሮስንም አሠቃየው ። የቀናች ሃይማኖትን ስለመለወጡ አባ ዮሐንስ እየዘለፈና እየረገመው ወደ ርሱ ደብዳቤ ላከ ከጥቂት ወራትም በኋላ #እግዚአብሔር ቀሠፈው።

ለእርሱም ዕድሜው መቶ ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነው ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አወቀ እየጸለየም ግምባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ ነፍሱንም በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር። በቅዱሳኑም ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን!!

((#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_21 እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ))
#ቅዱስ_ዘኬዎስ_ሐጺር

#ቅዱስ_ኤፍሬም ዘኬዎስ #ጌታን ሲቀበል የነበረውን ምናባዊ በሆነ መንገድ እንዲህ ብሎ ጽፎልናል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ ዓይነት ስዕላዊ አጻጻፍ ስልት የሴማዊያን የአጻጻፍ ስልት ነው፡፡

ዘኬዎስ በልቡ“ ይህን ጻድቅ ሰው በእንግድነት በቤቱ የተቀበለ ሰው ብፁዕ ነው” ብሎ በልቡ ጸለየ፡፡ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን የሚያውቅ #ጌታ ደግሞ የልቡን ጸሎት ሰምቶ “ዘኬዎስ ሆይ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ” አለው፡፡ ዘኬዎስም በልቡ ሲያመላልስ የነበረውን #ጌታ እንዳወቀበት ተረድቶ “ይህ ያሰብሁትን ያወቀ የሠራሁትንስ ሁሉ እንዴት አያውቅ? በማለት ለ #ጌታችን መልሶ “ #ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ ብሆን ዐራት እጥፍ እመልሳለሁ” አለ፡፡ #ጌታውም “ፈጥነህ ውረድ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ብሎ መለሰለት፡፡” በኋለኛው የበለስ ተክል ምክንያት በአዳም በለስ ምክንያት የሚታወሰው በለስ ተረሣ፡፡ ዘኬዎስ በበደሉ ምክንያት “ #ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች አሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ ብሆን ዐራት እጥፍ እመልሳለሁ” በማለቱ ለዚህ ቤት መዳን ሆነለት፡፡ ተቃዋሚዎች በዚህ ሰው እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት  ይደነቁ፡፡ አስቀድሞ ሌባ የነበረ አሁን ግን መጽዋቾች ሆነ አስቀድሞ ቀራጭ የነበረ ዛሬ ግን የ #ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ ዘኬዎስ ቅን የሆነውን ሕግ ወደ ኋላ ትቶ ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ላለመስማቱ ምልክት ወደሆነችው ወደማትሰማውና ወደማትለማው ዛፍ ተወጣጣ፡፡

ነገር ግን የእርሱ መዳን በዛፉ ላይ ከመውጣቱ ጋር የተገናኘ ነበረ፡፡ ከታች ከምድር በመለየት ወደ ላይ ከፍ ከፍ በማለት በከፍታ የሚኖረውን መለኮትን ለመረዳት በቃ፡፡ #ጌታም ደንቆሮ ከሆነችው የበለስ ዛፍ ፈጥኖ እንዲወርድ አዘዘው ይህ በምሳሌ ይከተለው ከነበረው የጥፋት መስመር ፈጥኖ እንዲመለስ ስለመጠየቁ የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅን ከሆነች ሕግ ወጥቶ ደንቁሮ ሆኖ ይኖር ዘንድ ስላልፈቀደ ነው፡፡ #ጌታም የቀድሞውን የጥፋት መንገድ እንዲተው ፍቅሩ በእርሱ ላይ እንዲቀጣጠልበት አደረገ ለዚህም ምክንያቱ በፍቅሩ አዲሱን ሰው ሆኖ ዳግም እንዲፈጠር ለማድረግ ነው፡፡ ዘኬዎስም ሌላ አዲስ ልደት እንዳለ ይረዳ ዘንድ #ጌታችን “እርሱ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ በዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” ብሎ የምስራችን ዜና ለዘኬዎስ አበሰረው፡፡ 

#ጌታ_ሆይ መተላለፋችንን ይቅር በል፡፡ ፍቅርህ እኛን ይለውጠን፤ በፍቅርህም ከኃጢአት መንገድ እንድንወጣ አርዳን ፍቅርህን በእኛ ልቡና እንደ ዘኬዎስ አቀጣጥለው ያኔ ከኃጢአት ለፈቃድህ በመትጋት መራቅ ይቻለናል፡፡ #ኅዳር_21 #ቅዱስ_ዘኬዎስ በዓሉ ነው!!!

ጌታ ሆይ እባክህ እርዳን🤲
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በእኛ አልጠበባችሁም በሆዳችሁ ግን ጠቦባችኋል፤
¹³ ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን እላችኋለሁ፥ እናንተ ደግሞ ብድራት መልሳችሁልን ተስፋፉ።
¹⁴ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
¹⁵ ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
¹⁶ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
¹⁷-¹⁸ ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
⁶ በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።
⁷ እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
⁸ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
⁹ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
¹⁰ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁴ እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤
⁴⁵ አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።
⁴⁶ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።
⁴⁷ ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት።
⁴⁸-⁵⁰ ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።
⁵¹ እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
⁵²-⁵³ ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም።
⁵⁴ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት።
⁵⁵ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፦
⁵⁶ እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።
⁵⁷ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥
⁵⁸ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛት ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም"።  መዝ. 131፥13-14።
"እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፣ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ"። መዝ. 131፥13-14።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_21_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴² ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?
⁴³ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።
⁴⁴ በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።
⁴⁵ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤
⁴⁶ ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የ #ማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የጽዮን #ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
     ሥርዓተ ማህሌት ዘኅዳር ጽዮን
   🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር  ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
  👉@EOTCmahlet
   👉@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፤ እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡
👉@EOTCmahlet

ዘጣዕሙ ፦
ሰላም  ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ፤ለወልድኪ አምሳለ  ደሙ ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

👉@EOTCmahlet
ዚቅ
ዘዘካርያስ ተቅዋም  ዘወርቅ፤ዘሕዝቅኤል  ነቢይ ዕፁት  ምሥራቅ ለመሠረትኪ  የኃቱ  ዕንቈ ሰአሊ ለነ ማርያም በአሚን ንጽደቅ፡፡
👉@EOTCmahlet
    ነግስ፦
ነቢያተ እሥራኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤ ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤ ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤ውስተ ኵሃቲሃ እንዚራቲነ ሰቀልነ ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡

👉@EOTCmahlet
ዚቅ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ፤
እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን፤
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ

ወረብ፦
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ  እንተ ረከበተነ/2/
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ/2/
👉@EOTCmahlet
  ማኅሌተ ጽጌ
ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤ ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕጹቁ፤ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤ ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ዉዱቁ፤ለኅበረ ገጽኪ ጽጌ  ሐተወ መብረቁ፡፡
  👉@EOTCmahlet
   ዚቅ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ፤ ወ፯ቱ መሣውር  ዘዲቤሃ፤ ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ ዘኩለንታሃ ወርቅ  ወያክንት፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት
 
👉@EOTCmahlet
ወረብ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ/2/
ዕዝራኒ ርእያ በርእየት ብእሲት/2/
  👉@EOTCmahlet
  👉@EOTCmahlet
ዚቅ(ዘበአታ)
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት፤ ወሶበ ርእያ ኢኮነት  ብእሲት አላ ሀገር ቅድስት ፤ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያክንት
👉@EOTCmahlet
    መልክዓ ማርያም 
ሰላም ሰላም ለዝክረ  ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ  ከልበኒ  ወቍስጥ  ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል  ለባሲተ ዐቢይ ትዕዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ  ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ  ለሠናይ አርዝ፡፡

👉@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሉያ X3 እምነ ጽዮን በሀ፤
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ ሥርጉት በስብሐት፤ ወማኅፈዲሃ  ዘቢረሌ  ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ  ለንጉሥ ዐቢይ ሥርጉት በስብሐት፤
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡

👉@EOTCmahlet
ወረብ
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/2/
ለሰማዕትሥርጉት በስብሐት ሥርጉት በስብሐት/2/

👉@EOTCmahlet
መልክዓ ማርያም፦
👉@EOTCmahlet
ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ፤ ወመራዕየ ቅሩፃት  እለ እምሕፃብ ዐርጋ፤ ማርያም ድንግል  ለደብተራ  ስምዕ  ታቦተ  ሕጋ ፤
አፍቅርኒ  እንበለ  ንትጋ ለብእሴ  ደም ወሥጋ፤ ዘየዐቢ  እምዝ ኢየኃሥሥ ጸጋ፡፡
   
👉@EOTCmahlet
  ዚቅ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት  ሕጽርት፤ ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤ንጉሥኪ  ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር፡፡

👉@EOTCmahlet
   ወረብ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር  በካህናት ሕጽርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/2/
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር/2/

👉 @EOTCmahlet
   መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤እም ታቦተሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ  በአስተብቍዖ፤ ለፀርየ ብእሴ አመጻ ኀይለ  ዚአኪ  ይጽበኦ፤እስከነ  ያሰቆቁ ጥቀድኅሪተ ገቢኦ፡፡

👉 @EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ  ሙሴ ኦሪተ፤ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡
👉 @EOTCmahlet

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

👉 @EOTCmahlet
  መልክዓ ማርያም፦
👉 @EOTCmahlet
ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቃ ዕሥራ፤ ዕጐላት እም ዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤ አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እም ይእዜ ለግሞራ።
👉 @EOTCmahlet

  ዚቅ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ፤አእመርክዋ አፍቀርክዋ፤ከመ እኅትየ  ኀለይኩ፤እም ድኅረ ጉንዱይ መዋዕል፤
ወእምዝ እም ድኅረ ኅዳጥ ዓመታት፤ካዕበ ርኢክዋ ወትትሐፀብ በፈለገ ጤግሮስ ፡፡
👉 @EOTCmahlet

ወረብ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ/2/
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን/2/

👉 @EOTCmahlet
   መልክዓ ማርያም፦
👉 @EOTCmahlet
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤
ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ፡፡

👉 @EOTCmahlet
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ  ጽዮን፤ ዕንቍ ዘጳዝዮን፤
ዘኃረየኪ ሰሎሞን፡፡
👉 @EOTCmahlet

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ጽዮን/2/
ዕንቍ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን ንጉስ/2/
👉 @EOTCmahlet

  ምልጣን 
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርሑቅ፤ ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ፤ ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡
👉 @EOTCmahlet
አመላለስ፦
ዕዝራኒ ተናገራ /2/
ተናገራ ዳዊት  ዘመራ/4/

👉 @EOTCmahlet
ወረብ ዘምልጣን
ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት፤
ዕዝራኒ ተናገራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት

👉 @EOTCmahlet
ቅንዋት
ይቤ ዳዊት በመዝሙር፤ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን፤ነቢይኑ ይቤ እግዚኦ ሰማዕኩ ድምፀከ ወፈራህኩ፤ወአትመረጐዝ በዕጸ መስቀልከ፤ስማዕ ጸሎቶ ለኵሉ ዘስጋ ዘመጽአ ኀቤከ

👉 @EOTCmahlet
👉 @EOTCmahlet
     ሰላም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ገነተ ትፍስሕት መካነ ዕረፍት፤ እንተ ይእቲ ማኅደር ለካህናት፤ ለእለ የኃድሩ በፈሪሃ እግዚአብሔር፤ ይእቲኬ ቤተ ክርስቲያን፤በውስቴታ የዓርጉ ስብሐተ ካህናት በብዙኅ ትፍስሕት ወሰላም፡፡


🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share #
2025/01/07 18:56:20
Back to Top
HTML Embed Code: