Telegram Web Link
ክለባችን ሀዋሳ በጋና ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እጩ የሆነውን ተጫዋች አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ መሪነት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች እስከ አሁን በስብሰባቸው ውስጥ የሀገር ውስጥ አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና ነባሮችን በመያዝ ልምምዳቸውን ቀጥለዋል። አሁን ደግሞ የመጀመሪያ የውጪ ዜጋ ፈራሚያቸው በማድረግ በጋና ሊግ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ የተካተተውን ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ስሚካኤል ኦቶውን አስፈረመ።

አብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ህይወቱን በሀገሩ ክለቦች ዩኒ ስታር ፣ ኢንተር አላይንስ እና ግሬት ኦሎምፒክስ ከተጫወተ በኋላ በመቀጠል ወደ ፓርቹጋል አምርቶ ለፖርትሞኔንሴ ተጫውቷል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ወደ ሀገሩ ጋና በመመለስ ለሊጎን ሲቲስ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን በክለቡ ውስጥ ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ በመቻሉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ስድስቱ ውስጥ የተካተተ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ ወደ ሀገራችን በመምጣት ሀዋሳን ተቀላቅሏል። Soccer Ethiopia
ኢትዮጵያ 1 - 1 ቡሩንዲ

ረድኤት አስረሳኸኝ

የክለባችን ተጫዋች ለሀገሯ ግብ አስቆጥራለች
ለሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሸኛኘት ተደረገለት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ውድድሩን ለማከናወን ዝግጅቱን ሲሰራ የነበረው ሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ እና በተለያዩ የወዳጅነት ጨዋታዎች አዳዲስ ፣ ነባር እንዲሁም ታዳጊ ተጫዋቾችን በመያዝ ልምምዱን ሲሰራ እና ሲወዳደር ቆይቶ ለዋናው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ራሱን አዘጋጅቶ ወደ አዳማ ከማምራቱ በፊት ዛሬ ምሽት በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል አሸኛኘት ተደርጎለታል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የክለቡ የበላይ ጠባቂ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ፣ የክለቡ ከፍተኛ የቦርድ አመራሮች ፣ ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ የመምሪያ ሀላፊዎች ፣ የክለቡ አመራር ፣ የደጋፊ ማህበሩ ተወካዮች ፣ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች በተገኙበት ነው በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ሽኝቱ የተደረገው።

የከተማው ከንቲባ እና የክለቡ የበላይ ጠባቂ አቶ መኩሪያ በንግግራቸው የስራ መመሪያ ለክለቡ አባላት ያቀረቡ ሲሆን የዘንድሮው አመት የተሻለ ውጤት እንዲመጣ ከተማ አስተዳደሩም ሆነ እርሳቸው በልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚከታተሉ ገልፀዋል። በመቀጠል የክለቡ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እና አምበሉ ሙጂብ ቃሲም ክለቡ ያደረገላቸው ትኩረት እንዳስደሰታቸው ጠቁመው። ከክለቡ የተላለፈውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳስበዋል። በመጨረሻም የኬክ መቁረስ እና የእራት ግብዣ ተከናውኖ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከፋሲል ከነማ ጋር በጥሩ እንቅስቃሴ 3ለ3 አጠናቆ የነበረው ክለባቸን ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት በ2ኛ ሳምንት ጨዋታው ከጥሩ እንቅስቃሴ ጋር ሻሸመኔ ከተማን በእዮብ አለማየሁ ጎል 1ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።

እንኳን ደስ አላችሁ 🙏
2025/02/06 13:40:49
Back to Top
HTML Embed Code: