Telegram Web Link
https://youtu.be/jt6FyrkN3vE
​‹‹ክርስቶስ በራስ ቅል ሥፍራ ተሰቀለ ማለት ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ በሚነሡ ክርስቲያኖች ጭንቅላት ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእኔና በእናንተ ጭንቅላት ውስጥ ተሰቅሎ መኖር አለበት ማለት ነው፡፡ ፍቅሩ ፣ መከራውና የመስቀሉ ነገር በጭንቅላታችን ተቋጥሮ እንዲኖር ፣ እንዳንረሳው ፣ ምንጊዜም ተቀርጾብን እንዲኖር ነው፡፡ አሁንም በጭንቅላታችን ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎ ይኖራል! አይወርድም! አይወርድም! ዛሬ የመስቀሉ ሥፍራ ቀራንዮ አይደለም ፣ የእኛ ጭንቅላት ነው፡፡ ቀራንዮ ዛሬ ይተረካል እንጂ ዛሬ መስቀሉ የለም፡፡ መስቀሉ ያለው በምእመናን ጭንቅላት ውስጥ ነው››
https://youtu.be/b7R5EHSL5II
ጲላጦስ የጌታችንን የክሱን ጽሕፈት ያረቀቀው ሲያስጨንቁት ያረፈዱትን የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ለመበቀል ነበር፡፡ ‹የአይሁድ ንጉሥ ነኝ በማለቱ የተሰቀለው ኢየሱስ› ብሎ ሊጽፍ ሲገባው ‹ኢየሱስ ናዝራዊው የአይሁድ ንጉሥ› በማለቱ የክስ ጽሕፈት ሳይሆን የአንድን ንጉሥ ማንነት የሚያስረዳ መግለጫ አደረገው፡፡[191] ይህንን ጽሑፍ የሚያነቡት አይሁድ ብቻ እንዲሆኑ አላደረገም ፤ ከሌላ ሀገር የሚመጡ ሰዎችም በግሪክና በላቲን ቋንቋዎች የተጻፈውን መግለጫ ሲያነቡ ‹አይሁድ ነጻ የሚያወጣቸውን የገዛ ንጉሣቸውን ሰቀሉ› ብለው እንዲሳለቁባቸው ፈልጓል፡፡
https://youtu.be/SPG1n3SovEY
አስተውሉ! ለወንጀለኛ መቼም ፍርድ እንደሚገባው ማንም የሚያምንበት ጉዳይ ነው፡፡ወንጀለኛም ከወንጀል እስካልጸዳ ድረስ ፍርድ ከእርሱ ጋር እንደ ጥላ ትከተለዋለች፡፡ቅጣትንም እንደ አክሊል በራሱ ላይ ደፍቶ ይመላለሳል፡፡ለኃጢአተኛም እንዲሁ ነው፡፡ራሱን በንስሓ መርምሮ ፣ወድቆ ተነሥቶ ፣በሥጋው በደሙ(ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል) አምላኩን እስካልታረቀው ድረስ ሁል ጊዜም ኃጢአተኛ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ኃዘኑን እጥፍ የሚያደርገው ያሃ ኃጢአተኛ በዚህ አቋሙ እያለ በሞት ከተወሰደ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው የሚድንበትን መንፈሳዊ ተግባር ማከናወን የሚችለው በምድር በሕይወተ ሥጋ እስካለ ድረስ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
https://youtu.be/UvltonFO9Cs
የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?!
https://youtu.be/bVnICgqqBr8
አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም:: በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ:: ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ::
https://youtu.be/MMv0BWmvIdo
በጸጋ እግዚአብሔር ደስ እንሰኝ ዘንድ ጸጋ ማግኛውን መንገድ አንሰቀቀው። አንዳንዴ እኒህ ሁሉ ነገሮች ተሰጥተውንም እንጨነቃለን። ‹‹ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦አንድ ባለጠጋ ሰው እርሻው እጅግ ፍሬያማ ሆነችለት። እርሱም፦ፍሬዬን የማከማችበት ሥፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ ዐሰበ። እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጎተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለኹ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ። ነፍሴንም፦አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። እግዚአብሔር ግን፦አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዷት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው። ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።››
https://youtu.be/KHd7uQasTI0
ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)
https://youtu.be/BmJEN-8kSFY
ከጠፈር በላይ ርቀቱ፣ ከባሕር በታች ጥልቀቱ፣ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ የማይታወቅ፣  ነፋሳት ሳይነፍሱ፣ አፍላጋት ሳይፈሱ፣ ብርሃናት ሳይመላለሱ፣ የመባርቅት ብልጭታ ሳይታይ፣ የነጎድጓድ ድምጽ ሳይሰማ፣ መላእክት ለቅዳሴ ከመፈጠራቸው አስቀድሞ፣ በአንድነቱ ሁለትነት፣ በሦስትነቱ አራትነት ሳይኖርበት፣ ለቀዳማዊነቱ ጥንት፣ ለማዕከላዊነቱ ዛሬ፣ ለደኃራዊነቱ ተፍጻሜት የሌለበት፣ በባሕርዩ ሞት፣ በሥልጣኑ ሽረት፣ በስጦታው ንፍገት የማይስማማው፣ የማይሾሙት ንጉሥ፣ የማይጨበጥ እሳት፣ የማይነጥፍ የፍቅር ጅረት፣ የነበረ ያለና የሚኖር፣ እንደ አምላካችን እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፡፡
https://youtu.be/_DP4POHRQ_M
ቤተ ክርስቲያን የመላእክትን ብዛት በምሳሌ አራቃ ስታስተምር አንዳንዶች ‹አሁን የእነርሱን ብዛት ማወቅ ለእኔ መዳን ምን ይረባኛል?› የሚል ጥያቄን ያቀርባሉ፡፡ አበው መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ስለመላእክት ብዛት መናገራቸውንም እንደ ቅንጦት እና አጉል ፍልስፍና አድርገው የሚወስዱ ወገኖች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ለመሆኑ የመላእክት ብዛታቸውን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
https://youtu.be/HKqSuq5LweE
ሰው በምላሱ ከሚወድቅ ከፍ ካለ ቦታ ቢወድቅ ይሻላል። ሃይማኖታችን በከንቱ እንዳይሆን በአንደበታችን ከልብ ከመነጨ ሐሳብ እውነትን ልንናገር ያስፈልጋል፡፡ አምልኮትን ለመፈጸም የምናደርጋቸው ነገሮች እውነትና የእውነት መሆን አለባቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን መሄዳችን የልማድና የታይታ ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችንንና ድኅነትን ፈልገን ሊሆን ይገባል፡፡
https://youtu.be/Ry1kZ0GLj2E
የጌታህ ፊት ከፀሐይ አብርቶ ይታይህና ሌላ ፀሐይ መሞቅ ያስጠላሃል፡፡ በሙሴ ሕግጋት ውስጥ እየተመላለስህ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ልብህን ይሰውረዋል ፤ እንደ ኤልያስ ያሉትን መናኞች ቅዱሳንን ታሪክ እያነበብህ ልብህ ይመንናል፡፡ ማቋረጥ የማትፈልገው የነፍስ እርካታ ታገኛለህ ፤ ሰማያዊ ሕልም እያየህ ነውና እንዳትነቃ ትሰጋለህ፡፡ ከዚያ ተራራ ፣ ከዚያ ከፍታ መውረድ ያስፈራሃል፡፡ ስለዚህ ጌታን ትማጸናለህ ፤ ጌታ ሆይ በእዚህ መሆን ለእኔ መልካም ነው፡፡ እባክህ አልውረድ ትለዋለህ፡፡ ከዚህ ተራራ ከወረድሁ ምን እንደምሆን ምን እንደምሠራ አውቀዋለሁና ጌታ ሆይ እባክህ እዚሁ ብቀር ይሻለኛል፡፡ ወርጄ ሦስቴ ከምክድህ እዚህ ሦስት ዳስ ሠርቼ አንተን ባገለግል እመርጣለሁ፡፡ ወርጄ አላውቅህም ከምልህ እዚሁ ፊትህን እያየሁ ልቆይ! እባክህን ከዚህ ከፍታ አልውረድ፡፡
https://youtu.be/eCV0uGHzw2E
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ። 36 ስለዚህ አይሁድ። እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ አሉ። 37 ከእነርሱ ግን አንዳንዶቹ። ይህ የዕውሩን ዓይኖች የከፈተ ይህን ደግሞ እንዳይሞት ያደርግ ዘንድ ባልቻለም ነበርን? አሉ። 38 ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እርሱም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።
https://youtu.be/gF9EOdpjLuU
መጽሐፈ ሄኖክ ጥንት የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲዩትሮካኒካል
 መጽሓፍ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እምነት ዘንድ ይህም በሰዎች ቃላት በግዕዝ በያሮድ ልጅ በሄኖክ ከማየ አይህ አስቀድሞ ተጽፎ ነበር።
በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የትንቢትም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት ኖህ በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ።
በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የመሢህ፣ የሙታን ትንሳኤ እና የዕለተ ደይን ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከአዳም ዘመን ጀምሮ ተገለጹ።
መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በኢትዮጵያ መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በሙት ባህር ብራናዎች (በቁምራን ዋሾች) መካከል በአረማይስጥ ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የግሪክኛ ወይም የሮማይስጥ ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።
https://youtu.be/XmhmnDvJt60
"የሚመራኝ ኮከብ የለም" ትል ይሆናል:: ምንም ቢሆን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብህም:: ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል:: የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎህ የተወለደውን ንጉሥ እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ:: እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልሃል:: እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠህ ከመንገድ አትቅር:: "የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው" ብለህ ጠይቅ::
https://youtu.be/RCn8Q3iacHk
ትሕትና በጎ ሥራዎች ሁሉ የሚጠበቁባት አጥር ቅጥር ነች፡፡ ከእግዚአብሔር የምናገኛቸው ጸጋዎችም ያለ ትሕትና ሊጸኑ ፣ ሊሰነብቱ አይችሉም፡፡ ቅዱሳን በጽኑዕ ተጋድሎ እና በፈጣሪ ቸርነት የገነቡትን የጸጋ ግንብ ሰይጣን እንዳያፈርስባቸው ፈጣሪያቸው የሚከላከልላቸው ትሑታን የሚሆኑበትን ደዌ ወይም አንዳች ነገር በእነርሱ ላይ በማምጣት ነው፡፡ ባለ ብዙ ጸጋ የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን የእግዚአብሔር አሠራር ሲያስረዳን ‹በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ…ተሰጠኝ ይኸውም እንዳልታበይ ነው› በማለት ግልጽ አድርጎ ይናገራል፡፡(2ኛ ቆሮ 12፡7)
https://youtu.be/-9nRxkanHz4
ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ ይገልጻቸዋል፦ ‘ፖለቲካዊ ሥልጣን የነበራቸው ሰዎች የትኞቹ ናቸው? ወደር ያልተገኘላቸው አንደበተ ርቱዐን ተናጋሪዎችስ ወዴት አሉ? የጦር መሪዎች ፣ ሀገረ ገዢዎችና ፣ አምባገነኖች ወዴት ናቸው? ሁሉም ወደ ትቢያ ተለወጡ አይደለምን? የሕይወት ዘመናቸው ማስታወሻ የአጥንቶቻቸው ቅሪተ አካል አይደለምን? ጎንበስ በሉና መቃብሮችን ፈትሹ ፣ ማን ጌታ ማን ባሪያ ፣ ማን ደሃ ማን ሀብታም ፣ እንደሆነ ለመለየት ሞክሩ፡፡ ከቻላችሁ ምርኮኛና እስረኛውን ከንጉሡ ፣ ኃያሉን ከደካማው ፣ ውቡን ከመልከ ጥፉው ለይታችሁ አውጡ፡፡ የሁላችንም ተፈጥሮ መጨረሻ አንድ መሆኑን ስታስቡ ያን ጊዜ መመካትና መታበያችሁ ይቆማል’
2025/02/23 15:40:54
Back to Top
HTML Embed Code: