https://youtu.be/2j9ogfsBvlI
በሁኔታዎች መለዋወጥ አብሮ የሚለዋወጠው ደስታ ሁሌም ሊያገኘን አይችልም። በምድር እንደመኖራችን ሰዎች ተምረው ሲመረቁ፣ ትዳር ሲመሠርቱ፣ ልጆች ሲወለዱ ደስ ይለናል፤ ሰዎች ሲሞቱ ግን እናዝናለን። ሀገር ሰላም ሲሆን ደስ ይለናል። በአንጻሩ ሰላም ሲደፈርስና ሕዝብ ሲራብ እናዝናለን።
በጌታ የሆነ ደስታ ኀዘንን አይሽርም (አይቃወምም)። ‹‹የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና!›› እንዲል፤ ሞተ ወልደ እግዚአብሔርንና በሰማዕታት ላይ የተፈጸመውን ግፍ እያሰቡ ማዘን ማልቀስ የተወደደና መዓዛው ያማረ ድንቅ መሥዋዕት ነው።

YouTube
ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ....በዲያቆን ያሬድ በጋሻው
በሁኔታዎች መለዋወጥ አብሮ የሚለዋወጠው ደስታ ሁሌም ሊያገኘን አይችልም። በምድር እንደመኖራችን ሰዎች ተምረው ሲመረቁ፣ ትዳር ሲመሠርቱ፣ ልጆች ሲወለዱ ደስ ይለናል፤ ሰዎች ሲሞቱ ግን እናዝናለን። ሀገር ሰላም ሲሆን ደስ ይለናል። በአንጻሩ ሰላም ሲደፈርስና ሕዝብ ሲራብ እናዝናለን።
በጌታ የሆነ ደስታ ኀዘንን አይሽርም (አይቃወምም)። ‹‹የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና!›› እንዲል፤ ሞተ ወልደ…

https://youtu.be/yai4eOHnE8w
ኤልሳቤጥ ልጅ ካለመውለድዋ ይልቅ ትልቅ ስቃይ የሆነባት የሰዎች ነቀፌታ ነበር፡፡ በዚህ መሰቃየቷን የምንረዳው ከጸነሰች በኋላ እንኳን ጸነስኩ ብላ ለመናገር ተሳቅቃ አምስት ወራት ያህል ጽንሱን መሰወርዋ ነው፡፡ በእርግጥም ብዙዎች ከመካንነት በላይ ስቃይ የሚሆንባቸው የሰዎች ክፉ ንግግር ነው፡፡‹መቼ ነው የምትወልዱት?› ‹ትዳር ያለ ልጅ እንዴት ይሆናል?› ‹እስካሁን አልወለድሽም?› እየተባሉ በጥያቄ የሚቆስሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ አልፎ ተርፎም በአሽሙር የሚሰደቡ ፣ በነገር ጅራፍ የሚገረፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን ጣውንትዋ ፍናና ታስቆጣትና ታበሳጫት የነበረችው ሃና ናት፡፡ ሃና ባለመውለድዋ በሚደርስባት ነቀፋ ምክንያት እህል እንኳን አስጠልቷት አትቀምስም ነበር፡፡ ደግነቱ ባልዋ ሕልቃና አለመውለድዋን አይቶ አልናቃትም ይልቁንም ‹‹ለምን ታዝኚአለሽ? ለምንስ እህል አትቀምሺም? ከአሥር ልጆች እኔ አልሻልሽም?›› ብሎ የሚያጽናና መልካም ባል ነበረ፡፡ (1ሳሙ. 1፡4-8)

እግዚአብሔር ያስታውሳል (ያልወለዱትን የሚያጽናና ግሩም መልዕክት) በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኤልሳቤጥ ልጅ ካለመውለድዋ ይልቅ ትልቅ ስቃይ የሆነባት የሰዎች ነቀፌታ ነበር፡፡ በዚህ መሰቃየቷን የምንረዳው ከጸነሰች በኋላ እንኳን ጸነስኩ ብላ ለመናገር ተሳቅቃ አምስት ወራት ያህል ጽንሱን መሰወርዋ ነው፡፡ በእርግጥም ብዙዎች ከመካንነት በላይ ስቃይ የሚሆንባቸው የሰዎች ክፉ ንግግር ነው፡፡‹መቼ ነው የምትወልዱት?› ‹ትዳር ያለ ልጅ እንዴት ይሆናል?› ‹እስካሁን አልወለድሽም?› እየተባሉ በጥያቄ የሚቆስሉ…
https://youtu.be/M8lPE153O4w
ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።

የህይወት ጥያቄዎችና መካሪ መልዕክቶች---- ከዲያቆን አቤል ካሳሁን ብዕር
ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ…
ጋሽ ግርማ ከበደ ልክ የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ያረፈ ታላቅ መምህር ነበረ:: ሲያስተምር እኔ ባልደርስበትም በእርሱ የተማሩ መምህራን ግን እኔን አስተምረውኝ ነበርና ስለዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሰው ብዙ ሰምቼአለሁ::
ከሁሉም ከልቤ የቀረው ግን ጋብቻውን ሊፈጽም ሲል ያደረገው ነው:: የሰርጉን ወረቀት ለታዳሚዎቹ ሲበትን ለአቶ እገሌ እገሌ ብሎ ይጽፍና ከ ጋር ብሎ እንደሚጽፍ የታወቀ ነው:: እርሱ ግን ለመጀመሪያ የጻፈለት ተጠሪ ልዩ ነበር::
ለጌታዬ ለአምላኬ ለመድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ
ከእናትህ ከድንግል ማርያም ጋር እና ከመላእክትህ ጋር በሰርጋችን ላይ እንድትገኝልን በማክበር ጠርተንሃል የሚል ነበር:: ይህንን ጥሪም በመንበሩ ፊት እንዲያስቀምጡለት ለካህናት ሠጣቸው::
ይህንን የመምህሩን ነገር የሰማ አንድ ወንድም ሃሳቡን ወደ መዝሙር ቀይሮ እንዲህ ብሎ ግጥም አደረገው::
በሰርጋችን ዕለት እንድትባርከን
ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋራ ከእመቤታችን
ከመላእክትህ ጋር ና በሰርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሰርጋችን
በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ስንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተ ነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
በነገው ዕለት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባሳደገችኝ ደብር በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጋብቻችንን እንፈጽማለን:: እኔ የጋሽ ግርማ ከበደ ዓይነት ሕይወት ቅድስና ባይኖረኝም እሱ ያገለገላት ቤተ ክርስቲያን ልጅ እንደመሆኔ እርሱ የጠራውን መሐሪ አምላክ ጠርቼአለሁ:: አምላክና ሰው በሆድዋ ውስጥ የተሞሸሩባት ወላዲተ አምላክ ወደ እኔ ብትመጣ ከቃና በላይ ብዙ የጎደለ ነገር ታገኛለችና እርስዋም አደራ ብያለሁ::