Telegram Web Link
https://youtu.be/O1y22lCvLRA
ኢትዮጲያዊነት ተሰቅላለች ኸረ እንደውም አሁን ሰንበት ሳይገባ ብለው አጣድፈው ከመቃብር ዘግተው ጠባቂ ሳያኖሩ አይቀርም፡፡ነገር ግን ሰባቱንም ቁልፎች የከፈተው የይሁዳ አንበሳ በተነሣቺው በሴቲቱ ስብእና ውስጥ አለ፡፡ ይመጣል! ከተራራውም ላይ ይወጣል፡፡ ከፍ ብሎ የሚበረው ንስር (የባቢሎን ሥልጣኔ) ላይ ያጋሳበታል፡፡ ብዙ አይናገረውም .. "በቃህ!" ብቻ ይለዋል፡፡ ንስሩም ያውቀዋል፡፡ የዘረጋቸውን ክንፎች ያጥፋል፡፡ ያሾላቸውን ጥፍሮች ይሰበስባል፡፡ ከደመናት በላይ መብረሩንም ያቆማል፡፡ ለእውነተኛው ንስር ቦታውን ይለቃል።
https://youtu.be/tEf9lWXxBt0
መጽሐፈ ሄኖክ ጥንት የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲዩትሮካኖኒካል መጽሓፍ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ዘንድ ይህም በሰዎች ቃላት በግዕዝ በያሮድ ልጅ በሄኖክ ከማየ አይህ አስቀድሞ ተጽፎ ነበር።
በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የትንቢትም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት ኖህ በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ።
በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የመሢህ፣ የሙታን ትንሣኤ እና የዕለተ ደይን ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከአዳም ዘመን ጀምሮ ተገለጹ።
መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በኢትዮጵያ መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በሙት ባሕር ብራናዎች (በቁምራን ዋሾች) መካከል በአረማይስጥ ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የግሪክኛ ወይም የሮማይስጥ ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።
https://youtu.be/tdQ-9rATEr4
ወታደሮቹ የጌታችንን ልብስ ለአራት ክፍል ተከፋፈሉ፡፡ ቀሚሱ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበርና አንቅደደው ተባብለው ዕጣ ተጣጣሉበት፡፡ እነዚህ ወታደሮች ለቀሚሱ ሳስተው ባለመቅደዳቸው ሳያውቁት ትልቅ ምስክርነት መሰከሩ፡፡ ጌታችን ብዙ መንገላታት ሲደርስበት ባደረው በጨለማው ፍርድ ቤት በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከሕግ ውጪ ልብሱን ቀድዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም ሥራው ሊቀ ካህናት ልብሱ ሊቀደድ እንደማይገባውና ልብሱን መቅደዱም ሊቀ ካህናትነቱ ማለፍዋን የሚያመለክት እንደሆነ በሥፍራው ተመልክተን ነበር፡፡ እነዚህ ወታደሮች የጌታችንን ቀሚስ ባለመቅደዳቸው የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ መሆኑንና ልብሱም ፈጽሞ ሊቀደድ እንደማይገባው የሚያሳይ ታላቅ ምሥጢር ተፈጸመ፡፡
https://youtu.be/-D-XyHrYCXk
መጽሐፈ ሄኖክ ጥንት የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ዲዩትሮካኖኒካል መጽሓፍ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ዘንድ ይህም በሰዎች ቃላት በግዕዝ በያሮድ ልጅ በሄኖክ ከማየ አይህ አስቀድሞ ተጽፎ ነበር።
በመጽሓፉ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ብዙ ራዕዮች ሲያይ ይናገራል። ደቂቀ ሴት (ትጉሃን) በአመጻቸው ጽናት ከቃየል ልጆች ጋራ አብረው እንዲዋሀዱ ከደብረ ቅዱስ በወረዱበት ጊዜ ሄኖክ እንደ ገሠጻቸው ይላል። የከለሱት ልጆቻቸውም በቁመት አብልጠው ረጃጅሞች እንደተባሉ እነዚህም አባቶቻቸውንና ምድሪቱን እንደ በደሉ ይላል። በሠሩት እጅግ ክፉ ሥራ ምክንያት የጥፋት ውኃ እንደሚደርሰባቸው ፈጽሞም እንደሚያሰምጣቸው የሚል የትንቢትም መጽሓፍ ነው። ይህም ትንቢት ኖህ በኖረበት ዘመን የተፈጸመ እንደነበረ የሚያምኑ ኣሉ።
በተጨማሪም ሄኖክ ወደ ሰማያት ተወስዶ የሰማይ ቦታዎችን ያሳዩታል። ከዚህ በላይ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብዙ ይነበያል፤ ያኔ ጻድቃን ሺ ልጆችን ይወልዳሉና በሰላም በደስታ እንደሚኖሩ የሚል ትንቢት ነው። በዚህ መሠረት የመሢህ፣ የሙታን ትንሣኤ እና የዕለተ ደይን ትንቢቶች መጀመርያ ከሄኖክ ወይም ከአዳም ዘመን ጀምሮ ተገለጹ።
መጽሐፉ በሙላቱ የታወቀው በግዕዙ ትርጉም ብቻ ሲሆን፣ የተጻፈበት ቋንቋ፡ በተለይም በኢትዮጵያ መምህራን ዘንድ፡ ግዕዝ መሆኑ ይታመናል። ከዚህም ውጭ አንዳንድ ፍርስራሽ ብራና ቅጂዎች በሙት ባሕር ብራናዎች (በቁምራን ዋሾች) መካከል በአረማይስጥ ቋንቋ በ1950ዎቹ በመገኘታቸው፣ በምዕራባውያን ሊቃውንት ዘንድ መጀመርያ የተቀነባበረበት ልሳን ግዕዝ ሳይሆን አረማይስጥ ይሆናል የሚሉ አሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የግሪክኛ ወይም የሮማይስጥ ምንባቦች በከፊል ተርፈዋል።
https://youtu.be/ob6ly044-SQ
የሚስጢር ማሕበራትን መረጃ የሚያወጡ ግለሰቦችም በብዛት የሚያጥራቸው እውቀት ከቴክሎኖጂው ጀርባ ያለው የክፉ መናፍስት ጥልቅ አሠራር ነው፡፡ በዚህም አጥፊዎቹ አሁን የዓለም ሕዝብ ምንም ማድረግ የማይችልበት ነጥብ ላይ እንደቆመ በሚገባ አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ ለሕዝብ እየተለቀቁ ያሉትን የቴክኖሎጂ መረጃዎች በሚስጢራዊ መልክ መጠበቁ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ይፋ እንዲሆን በር መክፈቱ ይጠቅማቸዋል፡፡ ምክንያቱም የዓለም ሕብረተሰብ የተሰበጣጠረ ነገር እየሰማ ግራ ገብቶት መንገድ ሲጠፋው፤ በዚህ ውጥንቅጥ መካከል የሚፈልጉትን አቅጣጫ ቀይሰው ሕዝብ የነርሱን መንገድ ብቻ እንዲያገኝ ያስገድዱታል፡፡
https://youtu.be/ru2PzKs0rLY
ጌታችን ከተገረፈው ግርፋትና ከተንገላታበት የቀራንዮ መንገድ በኋላ ከመስቀሉ ዕንጨት ጋር በረዣዥም ምስማሮች መቸንከሩ እጅግ የማይነገር ሥቃይ የሚያስከትል ነበር፡፡ ሮማውያኑ ይህንን ሥቃይ ጠንቅቀው ስለሚያውቁም የሚሰቀለውን ሰው ከመቸንከራቸው በፊት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ያደርጉት ነበር፡፡ ይህንን የሚያደርጉበት የመጀመሪያው ምክንያት ሊቃውንት በአጭሩ ‹ለቀኖት (ለችንካር) እንዲያዝልላቸው› ብለው እንደሚገልጹት ጠጁ ከከርቤና ሐሞት ጋር ተቀላቅሎ ሲጠጣ የማፍዘዝ የማደንገዝ ኃይል ስላለው የሚቸነከረው ሰው እየተወራጨና እየጮኸ እንዳያስቸግራቸውና እጆቹና እግሮቹ በድካም ዝለው እንዲቸነከሩ ለማድረግ ነው፡፡ ‹ያፈዝዛልና ይጠጣ ዘንድ ወይንን ሰጡት› (ወወሀብዎ ይስተይ ወይነ ዘከመ ያስዖዝዝ) እንዲል፡፡[
https://youtu.be/Z6MoHH1d8XA
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
https://youtu.be/MSVB9tLKb_4
ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት የግብፅ ክርስቲያኖች በአማሌቃውያን ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ ነጻ እንዲወጡ በማድረጋቸው የግብፅ ፓትርያርክ የከበሩ ስጦታዎችን ላኩላቸው:: ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ወርቅ ሳይሆን ጌታ የተሰቀለበትን መስቀሉን እንደሆነ ገለጹላቸው:: በመሆኑም የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግማደ መስቀሉን ከሌሎች ንዋየ ቅድሳት ጋር ለኢትዮጵያ ሰጥታለች:: ይህ ግማደ መስቀል በግሸን ማርያም ገዳም በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ኢትዮጵያን እየባረከ ይገኛል::
https://youtu.be/whzwwSiHF-c
የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለ መስቀል የጠለቀ ዕውቀት እንደነበረው የሚያሳዩ የተለያዩ ኹኔታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ገበሬው ሌላው አካሉ ጥቁር/ዳልቻ/ ኾኖ ግንባሩ ነጭ ያለበት በሬውን መስቀል፣ በተመሳሳይ ላሙን መስቀሌ እያለ ነው የሚጠራቸው፡፡ ይህም ምሳሌያዊ ነው፡፡ ይኸውም አንደኛው ምክንያት የሰው ልጅ ለ5500 ዓመታት በጨለማ ከቆየ በኋላ እውነተኛ ብርሃን ያገኘው ከመስቀል በኋላ መኾኑን ለማሳየት ሲኾን በሌላ አባባል መስቀል የብርሃን ተምሳሌት መኾኑን ለማመልከት ነው፡፡
https://youtu.be/DmWWg_kLJDA
የሰላም ባለቤት የኾነው መስቀሉም በበኩሉ፣ ክብሩና ልዕልናው ለዓመታት እንዲቀበር ያደረጉትን ወገኖች በውጭ ኃይል ሳይኾን በውስጥ ኃይል ድል እንዲነሱና ሰላምን እንዲያጡ አደርጎአቸዋል፡፡ ዛሬም ቢኾን የመስቀሉን ክብርና ልዕልና የሚጋፋና “እኔ ነኝ የበላይ” የሚል አካል ካለ፣ መስቀሉ አኹንም እንደዚያው እንደበፊቱ ኃይሉን የሚያሳይ መኾኑን በጥልቀት ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡
https://youtu.be/TNJ-ugprme8
በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡
https://youtu.be/rVWBM_6R1Ew
እስቲ ሁኔታውን ልብ እንበለው! አብረው ከገነት ሲወጡ አዳም ሚስቱን እንዴት የሚያናግራት ይመስላችኋል? በዚህ ዘመን በሚስቱ ምክንያት እንደ ገነት ካለ ቦታና ክብር የተዋረደ ባል ሚስቱን እንዴት ብሎ የሚያናግራት ይመስላችኋል? እንደቀድሞው ‘አካሌ ሥጋዬ አጥንቴ’ ይላት ይሆን? በፍጹም አያደርገውም! ካልገደልሁ ካላለም ተመስገን ነው! በእርግጠኝነት ይጣላሉ፡፡ ሚስቱን እንኳን በስምዋ ሊጠራት ከተባረረበት ገነት ብዙ ሳይርቅ እዚያው ሲኦል መፍጠሩ አይቀርም፡፡ አዳም ግን ያደረገው ለማመን የሚከብድ ነገር ነበር፡፡
https://youtu.be/CBxn-b_iHUo
‹‹ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ ፤ እኔ የእግዚአብሔርን በትር ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ፡፡ ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ ፤ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ ፤ ሙሴ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ፡፡ እንዲህም ሆነ ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር፡፡
2025/02/23 19:22:00
Back to Top
HTML Embed Code: