Telegram Web Link
https://youtu.be/EHVrD19h6E8
ቅድስት ቤተክርስትያን ደሆች ከመቀነታቸው ፈተው ከመጸወቱት ምጽዋት ቀንሳ ለሚያገለግሏት ካህናት ትከፍላለች ሁሉም ባይሆኑም አንዳንዶች ካህናት ደግሞ በግላቸው ይህንንም ያንንም በመሸጥ ኑሮ ለመለወጥ ሲሯሯጡ ይታያሉ ቤተክርስትያንን ግን ያገልግሎት ቤት ሳይሆን የመሸቀጫ ቤት ማድረግ ልክ አይደለም ያየነውንና የሰማነውን እንመሰክራለን እከሌ ቄስ ነው ዝም በሉ የሚባልበት አሮጌው ዘመን አልፏል ይህ የእውቀትና የእውነት ዘመን ነው።
https://youtu.be/VRcHKmM9hYo
ጠላት ዲያብሎስ ንስሐ ገብተን መንግሥተ ሰማይትን እንዳንወርስ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊ ኑሯችንም ቢሆን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ ተምረን ተገቢውን እውቀት ይዘን ሥራችንን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ እንዳንሠራ በማድረግ፤ ሠርተንም እንዳንጠቀም ዕንቅፋት በመፍጠር (በስንፍናና በውሸት፤ በዝሙትና በስካር፤ በቃሚነትና በአጫሽነት፤ በጨፋሪነትና በዳንሰኛነት፤ በስርቆትና በአጭበርባሪነት፤ …. በተለያዩ የኃጢአት አሸክላዎች ተብትቦ ይይዘናል፤
https://youtu.be/pEFtyPvFDX8
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን "እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን" ብላ በቅዳሴዋ የምትጸልየው በሞት የምወሰድበት ወቅት ምናልባትም ክፉ የምንሠራበትና ፈጣሪን የምንክድበት ጊዜ እንዳይሆን ነው:: "ሽሽታችሁ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" እንዲል እንደ ክረምትና ሰንበት ሥራ አቁመን ከበጎ ምግባር በራቅንበትና በሰነፍንበት ሰዓት እንዳንሞት እንጸልያለን::
https://youtu.be/4Rs7ad_heJM
የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ያስፈልገዋል ብሎ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ለሙሴ «በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ» ዘጸ 25፥7 ብሎ ባዘዘው መሰረት ተንቀሳቃሽ መቅደስ ከድንኳን ሰርተው ነበር። ይቺም ድንኳን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝባት ስለነበረች የመገናኛ ድንኳን የሚል ሰያሜ ተሰጥቷት ነበር። «እግዚአብሔርን የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበረ።»ዘጸ 33፥7
https://youtu.be/-m0m7bxUn4s
ሴቶችም ወንዶችም ከሚስቶቻቸውና ከባሎቻቸው ከልጆቻቸው ጭምር ተሰብስበው በየወሩ ወደ ጭፈራ ቤት የመግባት ክፉ ልማድ ነበራቸው፡፡
ቅዱስና ንጹሕ፥ ጻድቅና መስተጋድል፥ መነኰስና ካህን አባ ጳውሊ ከዚህች አገር ደርሶ፤ የዚያችን ሃገር ሰዎች ወደ ጭፈራ ቤት ሲሄዱ ባደረበት ጸጋ እግዚአብሔር የሰዎቹን የኀጢአት ሥራ አውቆ ፈጽሞ አዘነ፤ ወደ ዳንስ ቤቱ ተጠግቶም ከበር ቆመ ሰዎቹም መብራት አጥፍተው፥ ራቁታቸውን ሆነው በዱር እንዳሉና እንደጠገቡ ፈረሶች ሲጮሁ ሰማቸው፡፡
https://youtu.be/P2u-Z0GWxdg
በቤተ ክርስቲያኒቱ ለረዥም ዓመታት ደክመው ፣ ወጥተው ወርደው ያገለገሉ ፣ በዓለምም ቤተ ክርስቲያንዋን ወክለው የሚሠሩ ልጆች አሉአት፡፡ እነዚህ አባቶችና ወንድሞች ያሉበት ለመድረስ ረዥም የምንኩስና ዳገት ፣ ረዥም የትምህርት ሒደት ፣ ረዥም የአገልግሎት አቀበት ወጥተዋል፡፡ ወደድንም ጠላንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅተሞች ናቸው፡፡ በግላቸው ብዙ ድክመቶች ሊኖሩባቸው ይችላል፡፡ ሆኖም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትእምርት ሆነው በምእመናንም በሌሎችም ልቡና ታስበዋል፡፡ እነዚህን ሰዎች በማጥቃት የምናጠቃው የፈረደባትን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡
"እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፡—

በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" ኢሳ ፶፮ ፡ ፬-፭።

በእግዚአብሔር ዘንድ ቅዱሳን የተሰጣቸው ክብር ይህን ያኽል ከፍታ አለው። ከዚህ ከፍታ ደርሶ ዝቅ ሊያደርጋቸው የሚችል አንዳችም ፍጡር የለምና ክርስቲያኖች ሆይ ዝም ብላችሁ ከበረከታቸው ስብ ጥገቡ።

እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!!!
https://youtu.be/VOFABNcNcuM
በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ኃይሌን እስከሚያደክመው ድረስ አላወቅሁም ነበር፡፡ መላእክት ሲያመሰግኑት፥ ሙታን ሲነሡ፥ ምድር ሲነዋወጥ፥ ፀሐይ ሲጨልም አየሁ፤ ያን ጊዜ የዓለም ብርሃን፥ የፍጥረታት ፈጣሪ እርሱ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ አወቅሁ
https://youtu.be/dxCv8wkiNhQ
‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ!’’ አለ፡፡ ወደ እኔ ጥምቀት ሲመጣ እርሱ በደል ያለበት እንዳይመስላችሁ! እርሱ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው ብሎ በሕዝቡ ፊት መሰከረ፡፡ ይህ አዋጅ በዙሪያው ካሉት በላይ ለሁላችን የሚሠዋውን በግ ተስፋ ላደረግን ለሁላችን ታላቅ ብሥራት ነበር፡፡ አባቱን ‘የመሥዋዕቱ በግ ወዴት አለ?’’ እያለ በጥያቄ ሲያስጨንቅ እንደነበረው እንደ ይስሐቅ በጉን ልናይ ለናፈቅን ለሁላችን ደስ የተሰኘንበት መልስ ይህ የመጥምቁ ዮሐንስ ‘የእግዚአብሔር በግ እነሆ’ የሚል አዋጅ ነበር፡፡
https://youtu.be/T0AnroAGMU0
ከቸርነቱ ያርቃቸው ዘንድ አምላካቸውን ሐሰተኛ አድርገው እስኪያዩትና ፣ እስኪነቅፉት እስኪሰድቡትም ድረስ ሐሰትን እናስተምራቸዋለን፡፡ ዳግመኛም የማስተዋል አእምሮን በመንሳት የነቀፋና የስድብ መንፈስ ከልባቸውና ከአፋቸው እንዳይጠፋ እናደርጋለን አለው፡፡
ዝምተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እንኳን ለ32ኛ ዓመት በዓለ ሲመትዎ አደረሰዎት…
https://youtu.be/we6SYp7idv8
ስለ ጌታችን ሕማም እያሰበ መከራን ታግሦ ፣ በጾም ፣ በጸሎትና በስግደት ይኖር የነበረው ታላቁ መነኩሴ አባ ጳኩሚስ በአንድ ወቅት እየጸለየና እየሰገደ ሳለ ጌታችን ተገልጦለት ነበር፡፡ አባ ጳኩሚስ ከመድኃኔ ዓለም ፊት በግንባሩ ተደፍቶ እየሰገደ ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተን ብዬ የምሆነውን አየህልኝን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹እኔ አንተን ብዬ የሆንሁትን ብታውቅ ኖሮ ይህንን ባላልህ ነበር›› ብሎ መልሶለታል፡፡
https://youtu.be/WDXsVT4TtdQ
ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን በሚያስተምርበት ጊዜ ከሕዝብ ጋር ሆኖ ለመማር የአይሁድ አዋጅ ቢያስፈራውም፣ ባለጸጋና ምሁረ ኦሪት ከመሆኑ የተነሳ ከሕዝብ ጋር እንዳላዋቂ ሆኖ ለመማር ፈተና ቢሆንበትም በሌሊት ማንም ሳያየው ወደ ጌታ እየሄደ እርሱ ማንም ሊሰራ የማይችለውን ሥራ የሚሰራ መሲህ መሆኑን ተረዳ። የተማረ ሊቅ ቢሆንም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን አላዋቂነቱን ተረዳ። በትህናም ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን ብሎ ለመማር ራሱን ዝቅ አድርጎ ቀርቧል።
https://youtu.be/jvrVF8U6bSc
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እንደ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትምህርታቸውና በስብከታቸው ፣በድርሰታቸውና በሌላውም ሥራቸው ሁሉ " ከሳቴ ብርሃን" ነበሩ።ልዩ የንግግርና፣የስብከትና የማስተማር ስጦታ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ታላቅ አባት ነበሩ።
Forwarded from Biniam
2025/02/24 19:16:48
Back to Top
HTML Embed Code: