Telegram Web Link
https://youtu.be/_mNSMdLLhNM
የዘመን መለወጫ ሲደርስ በኢትዮጵያ ተራሮችና ሸንተረሮች የፈኩ አበቦችን ማሳየት ይጀምራሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት መስከረም አንድ ቀን “ዕንቁጣጣሽ” ትባላለች፡፡ የዚህ ቃል ምንጩ ምንም ያልተቀላቀለበት አማርኛ ቋንቋ ነው፡፡ ተንቆጠቆጠ የሚለውን የአማርኛ ግሥ ወስዶ ተዋበ፣ ተሸለመ፣ አሸበረቀ ማለት ይቻላል፡፡ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ሰማዩም ምድሩም ብሩሕ ሆኖ ይታያል፡፡ ምድርም ከልምላሜው በተጨማሪ የአበቦች ውበት ይሸፍናታል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ወርኃ መስከረምን ልዩ ያደርጓታል፡፡
https://youtu.be/lemNd-bSsvE
የመጀመሪያ ትምህርቱ የንስሐ ጥሪ ነው። ህዝቡ እንዲመለሱ ይሰብካል ደንዳና ልብ የነበራቸውን እንደ ሄሮድስና የአይሁድ መምህራን ያሉትን ይገስጻል ይህ ትምህርቱ ዘመኑን እየዋጀ በየዘመናቱ የሚነሱ ምእመናንን ህይወት ለማነጽ ይጠቅማል። ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ለመጡ ለህዝቡ ቸርነትን ስለማድረግ ለቀራጮች ስለእውነት ሚዛን ለጭፍሮች ስለ ፍትህ ያስተማራቸው ትምህርቶች ዘመናትን እየተሻገሩ የሚመክሩ ሁለት አፍ ያለው ሰይፍ ናቸው።
https://youtu.be/Bi6D45hlq74
በዚያን ጊዜ እንድርያስ ጌታችንን ‹‹በመርከብህ አሳፍረን፤ ነገር ግን የምንከፍልህ የመርከብ ዋጋ የለንም›› አለው፡፡ በሊቀ ሐመር የተመሰለ ጌታችንም ‹‹ስለምን የላችሁም›› ብሎ ጠየቀው፡፡ እንድርያስም ‹‹በከረጢታችን ወርቅን ብርን እንዳንያዝ ስለአዘዘን›› ነው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ከሆነ መርከቤ ወጥታችሁ ተሳፈሩ›› አላቸው፡፡ ያንጊዜም ወደ መርከቡ ወጥተው ተሳፈሩ፡፡
https://youtu.be/-Cfz0-vzFhw
ማርያም ግን የማይቀሟትን በጎ ዕድል መረጠች፡፡ ከራሱ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብሎ ከመማር በላይ ምን ዕድል አለ? ፈጣሪ ሲናገር መስማትስ እንዴት መታደል ነው? እርሱ የሚናገረው ቃል እኮ መለኮታዊ ቃል ነው! ከጌታ የሚወጣው ቃል የሚሠራና ሕያው የሆነው የራሱ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ
https://youtu.be/fbHgEz0CVUg
ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን በመንቀፍ ንሥሐ እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋው የተወሰነ ኃጥያትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃሎ " ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። " ራዕ 2÷14 በማለት ነው
https://youtu.be/kfDlCUtwCvM
እግዚአብሔርን ስታስብ መከራህ ሁሉ ትንሽ ይሆናል፡፡ ጳውሎስን በቀዝቃዛው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ደስታ ያሰጠመው ፈጣሪውን አስቦ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር ውጪ ላሉት ክርስቲያኖች ‘በደስታ እጸልያለሁ’ አለ ፣ እሱ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ወንጌል የሚሰብኩ ሰባኪያን በመብዛታቸው ‘ክርስቶስ ይሰበካልና ደስ ብሎኛል’ አለ፡፡ እስር ቤት መጥተው ላልጠየቁት ሰዎችም ‘አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ ጊዜ አጣችሁ እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር’ እያለ በደብዳቤው አጽናንቶአቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ደስታ ምንጩ ግን ከመከራው በላይ እግዚአብሔርን ማየቱ ነበር፡፡
https://youtu.be/iOKiGkMOVXc
ከዓለም ክርስቲያኖች በበለጠ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የተለየ እምነትና አክብሮት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ምእመናን ጌታችን ሰውን ለማዳን ሲል ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለበትንና ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ ያገኘንበት መስቀልን ለአፍታም ያህል የማያስታዉሱበት ቅፅበት ባይኖራቸውም በዓመት ለአምስት ጊዜያት ያህል በቤተ ክርስቲያንና በዐደባባይ ያከብሩታል፡፡
https://youtu.be/4ZHCmxLUHr0
አባ ስምዖንና አባ አዝቂርም ስምህ ማነው ብለው ጠየቁት፣ መባዓ ጽዮን ነው አላቸው፡፡ ከመምህራን ሁሉ እንዲህ ያለ ስምስ አይገባም ስምህ ተክለ ማርያም ይባል እንጂ አንተ ሕፃን ነህና አሉት፡፡ በዚህም የተነሣ ባለ ሁለት ስም ሆነ፡፡ ቅኔንና የጥበብ መጻሕፍት፣ተግሳጽንም ጾምና ጸሎትን ሥዕል መሳልን መጽሐፍ መጻፍን ሁሉ ተማረ፣ በመንፈሳዊ ሥራ ሁሉ ፍጹም ሆነ፡፡
https://youtu.be/DZpnfkiFD9k
ብዙዎቻችን በመናፍስት ውጊያ ውስጥ ከምንይዛቸው የተሳሳቱ አመለካከቶች ውስጥ አንደኛው፤ መናፍስት ተሸነፉ ማለት የሚመስለን ተዳክመው ከሕይወታችን ተለይተው ሲወጡ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሄ ዲያቢሎስን ተዋግቶ የማሸነፍ መግለጫ እንጂ ማሸነፍ አይደለም፡፡
https://youtu.be/c9zrjvyvFZU
የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡
https://youtu.be/a0A5chrxeSI
ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን::
የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም::
የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም::
በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::
https://youtu.be/E08TnF59zDY
የተቀጠቀጠ ሸንበቆ የማትሰብረው የሚጤስ ጧፍ የማታጠፋው ትሑት አምላካችን ሆይ ክፉ ንግግሮቻችን የሚፈልቁት ከክፉ አኗኗራችን ነውና እባክህን እኛንም ታገሰን፡፡ ኢትዮጰያውያን ተሳዳቢዎች ፣ ዘረኞች ፣ ነውረኞች ያደረገን የተበላሸ ሕይወታችን ነውና ይቅር በለን፡፡ በመጥፎ ንግግሮቻችን የምናሳዝንህ ፣ በእርስ በእርስ መበላላት የምናስከፋህ ሳምራዊትዋ ሴት ባሎች እንደተፈራረቁባት ብዙ ፖለቲከኞች ተፈራርቀውብን ፣ ትዳር አልሳካ ብሎን ነውና እርስዋን እንደታግስህ ታገሰን፡፡
https://youtu.be/1SiiTcTU530
ሠራተኛ የሚሠራው ለደሞዝ ብሎ ነው:: አንዳንድ ሰዎች ሁልጊዜም ገነት ለመግባት ሲሉ በጎ ሊሠሩ ይችላሉ:: "የነፍስ ዋጋ አድርግልኝ" እያሉ የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ አድርገው ለተሻለው ሲሉ አሁን ዋጋ ይከፍላሉ:: "ከሩቅ አይተው ተሳለሙት ሀገራቸው እንደሆነችም አወቁ" እንዲል የተስፋይቱን ሀገር ብለው በጎ ይሠራሉ:: ከበጎነታቸው ጋር ደሞዝ ፍለጋ አለበትና ቅዱስ ባስልዮስ ሠራተኞች አላቸው::
https://youtu.be/EZWm2A7tb9c
እኛ 'አንተ ከእኔ ጋር ነህና' የምንልበት የሥጋና ደሙ አንድነት ላይ መንፈሳዊ ግንዛቤና የእምነት ትርጉም በሚገባ ሰጥተን ስለማናውቅ፤ ችግራችን በተቃዋሚ መናፍስት በኩል እየበለጸገና ሌሎች ችግሮችን ወደ ሕይወታችን እየጠራ ዕድሜያችንን አስቸገረው፡፡
https://youtu.be/pywpD0IVfEA
እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
https://youtu.be/AvyK0FeIxWk
ጌታችን ስለ ይሁዳ ‹በመንፈሱ ታወከ› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ዮሐ. ፲፫፥፳፩) ከዚያ በፊት በመንፈሱ የታወከው የሚወደው አልዓዛር በሞተበት ወቅት ነበር፡፡ (ዮሐ. ፲፩፥፴፫) ስለዚህ ጌታ በሥጋ ለሞተው ለሚወደው አልዓዛር በመንፈሱ ታውኮ እንዳለቀሰ ሁሉ አሳልፎ ለሰጠውና ራሱን በነፍስ ጭምር ለገደለው ለሚወደው ይሁዳም አልቅሶለት ነበር፡፡
https://youtu.be/ZzJ2QShJzmo
የእግዚአብሔር መንፈስ ራሱን በሥጋ እስከሚገልጥበት ጥግ ድረስ ሔዋንን እንደወደደ ልብ በሉ፡፡ ለዘመናት ስሟ ሲጠፋ፣ ስለ ሰው ልጆች መጥፋት ስትወቀስ፣ ሞትን በልታ በማብላቷ ስትነቀፍ የኖረቺውን ሴት እግዚአብሔር አሰባት፡፡ ስለዚህም ከልጅ ልጇ ተወልዶ አዳም ይሆን ዘንድ ቃሉን ወደ ሔዋን ላከ፡፡ እመቤታችንን የባሕሪያችን መመኪያ የምንልበት ምክንያት ይሄ ነው፡፡
2025/02/24 16:39:27
Back to Top
HTML Embed Code: