Telegram Web Link
የሰው ዘር መጀመሪያ የሆኑት #አደም

ልዩ የክብር ቦታ የተሰጣቸው #እንድሪስ

950 ዓመታት በማስተማ ር የቆዩት #ኑህ

ወደዓድ ህዝቦች የተላኩት #ሑድ

ድንጋይ ተፈልቅቆ ግመል የወጣችላቸው #የሰሙዱ ሳሊህ።

የኑምሩድን እሳት ድል በማድረግ የወጡት #ኢብራሒም

መላእክት በእንግድነት ወደቤቱ የገቡት #ሉጥ

በካዕባ ግንባታ የተሳተፉት #ኢስማኢል

የአባታቸው የኢብርሂም ልድ #ኢስሐቅ

የ12 ወንድ ልጆች አባት የሆኑት #ያዕቆብ

እጅግ ታጋሹና ጥበበኛው #ዩሡፍ

መከራን ቻዩና ጸሎተኛው #አዩብ

የሁለት ሴቶች አባት የሆኑት የመደኑ #ሹዓይብ

ባህር የተሰነጠቀላቸው የኢምራን ልጅ #ሙሳና ወንድማቸው #ሐሩን

በዓሣ ሆድ ውስጥ ዚክር ያደረጉት የነይነዋው #ዩኑስ

ብረት እንደጭቃ የሚለዝብላቸው ድምጻዊው #ዳውድ

ንፋስን እንደፈለጉ የሚያዙት ንጉሱ #ሱለይማን

ቁርኣን ስማቸውን እንጅ ያላስዋወቀን አልየሰእ፤ #ኢሊያስና #ዙልኪፍል

አናጺውና የመሪየም አሳዳጊ #ዘከርያ

በልጅነታቸው ነብይነትን የተሰጡት #ያህያ

ያለአባት የተወለዱት ተአምረኛው የመሪየም ልጅ #ዒሣ

ለተልእኳቸው የቦታና የዘመን ግርጾሽ የተነሳላቸው #ሙሐመድ ናቸው።

እንግዲህ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል በተላኩት ነቢያት በሙሉ ያለምንም ልዩነት ማመን ይኖርብናል።
#Share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
#የደሴቷ_ብቸኛ_ነዋሪ....ደስ የሚል ታሪክ

በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል። ይህም ሰው በውሃው እየተገፋ አንዲት ደሴት ላይ ራሱን ያገኘዋል።

እርዳታ ለመጠየቅ በደሴቷ እየተዘዋወረ ሰው ለማፈላለግ ቢሞክርም ምንም ዓይነት የሰው ዘር ማግኘት አልቻለም። በአካባቢው ማዕብሉ ከሚያናውጠው ባህርና ከወፎች ድምፅ በስተቀር የሚሰማ ነገርም የለም። በዚህን ግዜ በትንሽየዋ #ደሴት ውስጥ የሚኖረው ብቸኛው ሰው እርሱ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጣም ተጨነቀ። ፍርሃትም አደረበት። ከዚህ አስፈሪ ችግር ያወጣውም ዘንድ አላህን ለመነ።

አንዳች የአላህ ተዓምር መጥቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ግን በደሴቷ ውስጥ መቆየቱ እንደማይቀር በማሰብም የሚጠለልበት ትንሽ ግዜያዊ ጎጆ ቤት ሰራ። አንገቱ ላይ ባንጠለጠለው ቦርሳ መሰል ይዞት የነበረውንም እቃ ጎጆዋ ቤት ውስጥ አስቀመጠ።

ወደ ጫካው በመግባትም የተለያዩ የሚበሉ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላ ቅጠሎችን ማግኘት ቻለ። በዚሁ ሁኔታ በደሴቷ መኖር ጀመረ.....

ከዕለታት አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወደ #ጫካው ሄዶ ሲመለስ ትንሿ ጎጆ ቤቱ በእሳት እየተቀጣጠለች ደረሰ። በተመለከተው አጋጣሚ በጣም አዘነ። የበለጠ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት።

"አላህ ሆይ! ለምንድን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የምትፈፅምብኝ!?" በማለትም በጣም አለቀሰ።

በተከታዬ ቀን የሆነ ድምፅ ከእንቅልፋ ቀሰቀሰው። ወደ ደሴቷ እየቀረበች የነበረች አንዲት መርከብ ናት ከእንቅልፋ የቀሰቀሰችው። መርከቧ እሱን ለመውሰድ ነበር ወደ ደሴቱ የመጣችው።

ሁኔታውን ማመን ያቃተው ሰውዬው "በዚህ አካባቢ እኔ መኖሬን ማን ነገራችሁ?" በማለት መርከቧ ላይ የነበሩትን ሰዎች ጠየቀ። እነርሱም "ትናንት ከዚህ አካባቢ የሚወጣ #ጭስ አይተን ነው የመጣነው" ሲሉ መለሱለት።


#አስተምህሮት.....
እኛ ሰዎች አጋጣሚዎች ሁሉ መጥፎ ሲሆኑብን በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን። እንዲህ በቀላሉ መሸነፍ የለብንም። ምክንያቱም አልህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኛን በተመለከተ ሁል ጊዜ ስራ ላይ መሆኑን መዝምንጋት የለብንም። በመከራችንና በህመማችን ወቅትም እንኳ ቢሆን እርሱ አይረሳንም።

ኢንሻአላህ 🙏🙏🙏

ሼር ሼር ሼር ሼር

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_4

ብቻዋን መሄድም አልፈለገችም::የሩሲያ የአየር መንገድ አውሮፕላን የሆነውን ተሳፈሩ፡፡ከነ ኒቃቧ ነበር የተሳፈረችው፡፡ ከባሏ ጎን ኩራት እየተሰማት ተቀመጠች፡፡ ኻሊድ "በሂጃብሽ የተነሳ ችግር እንዳይገጥመን እፈራለሁ፡፡" አላት፡፡ እሷም "ሱብሀን አላህ! እነዚን ኢ-አማንያን እንድታዘዝና በአላህ እንድክድ ትፈልጋለህን? ወላሂ ፈፅሞ አይሆንም፡፡ አላደርገውም፡፡ ያሉትን ይበሉ፡፡" አለችው፡፡

ሰዎች በግርምት ወደሷ ይመለከታሉ ፡፡አስተናጋጆች ምግብ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ከምግቡ ጋር መጠጥ ይቀርብ ነበር፡፡ የጠጡት ሞቅ እያላቸው ሲሄድ መናገርና እሷን በነገር መውጋት ጀመሩ፡፡ ከዚህም ከዚያም ያሾፉባት ጀመር፡፡ አንዱ ይሳለቃል ፣ሌላው ይስቃል ፣ ሌላው ያላግጣል፡፡አጠገቧ ቆመው ስለሷ ያወራሉ ፣ያጣጥላሉ፡፡ ኻሊድ ይመለከታቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በራሳቸው ቋንቋ ያወሩ ስለነበር የሚሉት አይገባውም ፡፡ እሷ ግን እየሰማች እና፡እየሳቀች የሚሉትን ትተረጉምለታለች፡፡
በዚህን ጊዜ ኻሊድ ተቆጣ፡፡

እሷ ግን እንዲረጋጋ መከረችው፡፡"አይዞህ አትዘን ፤ አትጨናነቅ፡፡ሶሐቦችን ካገኛቸው ችግር አንፃር ሲታይ ይሄ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡" አለችው፡፡ እሷም ባሏም ትዕግስትን መረጡ፡፡ በመጨረሻም የተሳፈሩበት አውሮፕላን አረፈ፡፡
ኻሊድ እንዲህ ይላል፡- ሩሲያ ስንደርስ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በመሄድ እነርሱ ዘንድ ቀናትን ቆይተን ጉዳያችንን ጨርሰን የምንመለስ ነበር የመሰለኝ፡፡የሚስቴ ሀሳብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነበር፡፡ እንዲህ አለችኝ፡- "ቤተሰቦቼ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ሀይማኖታቸውን በጣም ያጠብቃሉ ፡፡አሁን እነሱ ዘንድ መሄድ የለብንም፡፡ማረፊያ ቤት እንከራይ፡፡እዚያው ቆይተንም የፖስፖርቱን ጉዳይ እናስጨርስ፡፡ከጨረስን በኃላ ሄደን ቤተሰቦቼን እንገናኛለን፡፡"

በሐሳቧ ተስማማሁ፡፡ማረፊያ ተከራየንና እዚያው ቆየን ፡፡በነጋታው ወደ ፓስፓርት ማደሻ ማዕከል ሄድን፡ወደ ቢሮው ዘለቅን፡፡ አስተናጋጃችን የቀድሞውን ፓስፓርትና ሌላ ፎቶ ጠየቀን፡፡ በጥቁርና ነጭ የተነሳችውን ፎቶ አቀበለችው፡፡ የፊቷ ቅርፅ ብቻ ነበር የሚታየው፡፡
አስተናጋጁ "ይህ ፎቶ ለፓስፓርት አይሆንም ፡፡ባለቀለም ፎቶ ነው የምንፈልገው ፡፡ፀጉርና ተከሻሽ መታየት አለበት፡፡" አላት፡፡ ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ እንደማትሰጥ አስረግጣ ነገረችው...

#ክፍል_5_ይቀጥላል...

@Halali_tube
@Halali_tube
ኢንሻአላህ ራመዳን 31 ቀናቶች ብቻ ነው የቀሩት። አንድ ሰው ለሌላ ሰው የረመዳንን ቀን ቀድሞ ካሳወቀ እሳት በሱ ላይ ሀራም ትሆንበታለች።
ኢንሻአላህ ሼር በማድረግ አስተላልፉ
#Share 🙏🙏🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
ነፍሳችንን በሀጢአት በድለን ከሱ ትዕዛዝ ርቀን ቆይተን ወደሱ ትክክለኛ መመለስን ተፀፅተን ስንመለስ ወንጀላችንንም ምሮ ውዴታውንም የሚሰጠን ከአላህ በቀር ማን አለን? ያአላህ እኛ ነፍሳችንን በዳይ ባሮችህ ነንና ወንጀላችንን ማርልን ትክክለኛ መመለስን ከተመለሱ ከተፀፀቱ ባሮችህም አድርገን አሚን🤲
Share 🙏🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_5

በሱ በኩል የማይሳካ መሆኑን ስታውቅ ሌላ የቦታው ሰራተኛ ዘንድ ሄድን፡፡ ቀጥሎም ሌላ ሀላፊ ዘንድ፡፡ ሁሉም ፀጉሯ ተገልጦ የተነሳችው ፎቶ ካልሆነ በስተቀር አንቀበልም አሉ፡፡ ባለቤቴ በእንቢታዋ ፀናች፡፡ እነርሱም በዚ ፎቶ እንደማያስተናግዷት ገለፁላት፡፡ፎቶውን እንዳያፀድቁላት ብለን ዋና ሀላፊ ዘንድ ሄድን፡፡

ብዙ ጣረች ብዙ አስረዳች፣ ተከራከረች ፣ሞገተቻቸው፡፡"የሚፈለገው ፊት ነው፡፡ ምንድነው ልዮነቱ ?ስትፈልጉ ፎቶዎቹን አነጻጽሯቸው፡፡" አለቻቸው፡፡
ሀላፊዋም አሰራራቸው ይህን የማይፈቅድ መሆኑን አስረዳቻት፡፡ በመሆኑም እንደማትቀበላት ገለፀች፡፡ባለቤቴም ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ በፍፁም አላመጣም ፡፡

ባይሆን ማድረግ ያለብኝን ሌላ መፍትሔ ንገሪኝ አለቻት፡፡ በመጨረሻም ሀላፊዋ "ይህን ችግር ሊፈታ የሚችለው ሞስኮ የሚገኘው ዋና ቢሮ ብቻ ነው፡፡"አለችን፡፡ የፓስፓርት ጣቢያውን ትተን ወጣን፡፡ወደ እኔ በመዞር "ኻሊድ ሞስኮ እንሂድ" አለችኝ፡፡ ተበሳጨሁ "እነርሱ የሚሉትን ፎቶ ስጪአቸው በቃ" አልኳት፡፡
"አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም ፤የቻላችሁትን ያሀል አላህን ፍሩ፡፡

"ነው የተባለው፡፡የግድ ስለሆነብሽ ነው የተጠየቅሽውን እያደረግሽ ያለሽው፡፡ፓስፓርትሽን ሊያዩ የሚችሉት ደግሞ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ይህም ግድ ስለሆነ ነው፡፡ ከዚያ ጊዜው እስኪያልቅ ድረስ ቤትሽ ነው ምታስቀምጪው
ስለዚህ እባክሽ እራስሽን አታጨናንቂ ፡፡ሞስኮ ድረስ ለምን እንሄዳለን?አልኳት፡፡
"አይሆንም፡፡"አለች፡፡

ተገላልጬማ ፈፅሞ ፎቶ ተነስቼ አልሰጣቸውም፡፡የአላህን ዲን ካወኩ በኃላማ ይህ ሊሆን አይችልም፡፡በማለት ተከራከረችኝ፡፡ካልሄድን በሚል አቋም በመፅናቷ ወደ ሞስኮ መሄዳችን ግድ ሆነ፡፡ማረፍያ ክፍል ተከራየንና በነጋታው ወደ ፓስፓርት ጣቢያው ሄድን፡፡የተለያዩ ሀላፊዎች ዘንድ ገባን፡፡ በመጨረሻም ዋናው ሀላፊ ዘንድ ቀረብን፡፡ሲበዛ መጥፎ ሰው ነው፡፡ ፓስፓርቱን እያየ ፎቶውን ማገላበጥ ጀመረ፡፡

#ክፍል_6_ይቀጥላል.......
#share
@Halali_tube
@Halali_tube
ምናልባት የሆነ ቀን ላይ ከራሴ ጋር ወይም ከመንጋ ጋር ሁኜ ፤ ሆን ብዬ ወይም ሳላስበው አምቼሽ/ቼክ ይሆናል። (እስከኖርን ድረስ) የምላስ ወለምታ አይቀርም። አምቼሽ /ክ ከሆነ ይቅር ትዪኝ/ለኝ ዘንድ እመኛለሁ። በእርግጥ አላህ በሀሜት የተዘፈቀን ሰው የሚምረው የታማው አካል በይቅርታ ሲያልፈው እንደሆነ አውቂያለሁ። ይህንን መልዕክት በመዝገብ ዝርዝር ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ልክያለሁ። ከኔ ለማስታወሻነት የተሰጠ ስጦታ ሳይሆን የሰማያትና የምድር መለኮት በእጁ የሆነውን ፈጣሪ በመፍራት ያደረግሁት ነው። ይቅር ካልከኝ /ሽኝ መልዕክቱን ደግመክ/ሽ ላክልኝ/ላኪልኝ ። የይቅርታ ጥሪ ነውና ነፍሳችንን ንፁህ እናድርገው። ይቅር በሉኝ። ድንገተኛ ሞት እጅግ በዝቷ። ለአላህ ስል ይቅር ብዬሻለሁ/ካለው። ለዚህም አላህ ምስክሬ ነው። ከረመዷን በፊት የይቅርታና የንፁህነት ጥሪ አድርጉት። ዳግም እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ።
ኢንሻአላህ ሼር አድርጉት 🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_6

ከዚያም ወደ ባለቤቴ ቀና በማለት የዚህ ፓስፓርት ፎቶው የሷ መሆኑን በምን ላውቅ እችላለሁ? አለ ለማመሳከር ፈልጎ ፊቷን ገልጣ እንድታሳየው ያሰበ ይመሰላል፡፡"ላንተ ፊቴን አልገልጥም፡፡ሴት ሰራተኞቾ ካሉ ሊያዩኝ ይችላሉ፡፡ አለችው ባለቤቴ፡፡በዚህን ጊዜ ሰውዬው ክፍኛ ተቆጣ፡፡

የድሮውን ፓስፓርት ፣ፎቶዎቹንና ሌሎቹን ሰነዶች ጨምሮ ወደ ራሱ የማስቀመጫ ቦታ ወረወራቸው፡፡ ትክክለኛውን የፓስፓርት ፎቶ ይዘሽ ካልመጣሽ በስተቀር ከአሁን በኃላ የበፊቱንም ሆነ አዲስ ፓስፓርት አይኖርሽም፡፡ አላት፡፡
ባለቤቴ ከሱ ጋር በማውራት ልታሳምነው ጣረች ፡፡በሩሲያኛ ነበር የሚያወሩት ፡፡ባለቤቴ ተናዳለች፡፡ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል፡፡

ሀላፊው ከያዘው አቋሙ የሚመለስ አይመስልም ፡፡ በፍፁም አይሆንም አለ ፡፡እሷም ተስፋ ሳትቆርጥ ተከራከረች፡፡ ጠብ ያለላት ነገር የለም፡፡ ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ቆመች፡፡ ወደሷ ጠጋ አልኩኝ፡፡ አላህ ነፍስን ከምትችለው በላይ አያስገድዳትም ፤ችግር ላይ መሆናችንን ልብ በይ፡፡ በዚህ መልኩ የምንጉላላው እስከ መቼ ነው? አልኳት፡፡

"አላህ እሱን ለሚፈራ ሰው መውጫ ያበጅለታል ፤ባላሰበውም በኩል ሲሳዮን ይለግሰዋል፡፡" አለች፡፡

እዚያው ሆነን ከኔ ጋር ብዙ ተከራከርን፡፡የጣቢያው ሀላፊ በሁኔታችን ተቆጣና እንድንወጣለት አስገደደን፡፡ወጣን፡፡ደክሞናል፡፡ በአንድ በኩል ስታሳዝነኝ በሌላ በኩል አናዳኛለች፡፡ተቀምጠን በሰፊው እንድናወራ በማሰብ ወደተከራየነው ክፍላችን አመራን፡፡እኔ ላሳምናት እጥራለሁ፡፡ እሷም ልታሳምነኝ ትሞክራለች፡፡ዕለቱ መሸ ፡፡ዒሻ ሰገድን ፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ በሀሳብ ተወጥሬያለሁ፡፡ርቦን ስለነበር ያገኘነውን በላን፡፡ለመተኛት ብዬ ራሴን ከትራስ ጋር አገናኘው፡፡

ለመተኛት ማሰቤን ስታይ ፊቷ ላይ ቁጣ አነበብኩኝ፡፡ወደኔ ዞረችና "ኻሊድ ትተኛለህ?የ አለችኝ፡፡"አዎን ደክሞኛል እኮ "አልኳት፡፡"ሑብሀን አላህ የምትገርም ነህ ፡፡በዚ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለን መተኛት ታስባለህ?በዚህ ሁኔታ ውስጥ እኮ መተኛት ሳይሆን ወደ አላህ (ሱ.ወ) መጠጋት፤ ወደሱ ፊታችንን ማዞር ነው ያለብን፡፡በል ተነስና አላህን እንለምን እሱ ነው የሚሻለን፡፡"አለችኝ፡፡

#ክፍል_7_ይቀጥላል...

@Halali_tube
@Halali_tube
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ በኒ መስጅድ ከ ዙሁር ሰላት ቡሀላ ሸህ መንሱር የተናገሩት ነገር አለ እሱም አንድ የ ፊልስጤን ሸህ ረሱል ሰ.ዐ.ወ በህልማቸው ያያሉ እንዲህ ስልም ጠየኳቸው ይላሉ "ይህ በሽታ እንዳይደርስብን ምን ማድረግ አለብን?" ረሱልም ሰ.ዐ.ወ " 1ኛ 313 ጊዜ ሀስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል 2ኛ 3 ጊዜ ቁል ሁወላሁ አሀድ 3ኛ 3 ጊዜ ቁል አዑዙቢረቢል ፈለቅ 3 ጊዜ ቁል አዑዙቢረቢል ናስ 4ኛ 3 ጊዜ ፋቲሀን ቅሩ ከበሽታው ትጠበቃላቹ "ብለዋል እኚህ ሼህ አዲስ አበባ ላሉት ሼህ በመደወል ያዩትን ህልም ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲጠቀም ብለዉ ተናግረዋል ስለዚህ በየቀኑ ይሄንን ማለት አንርሳ ተወኩላችንን በአላህ እናድርግ ለቻላቹት ሰው በሙሉ አስተላልፉ! አላህ ነጃ ከሚወጡት ያድርገን።🙏
#share 🙏🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_7

ተነሳሁና የቻልኩትን ያህል ሰገድኩ፡፡ተመልሼ ተኛሁ፡፡እሷ ግን በሰላቷ ቀጠለች፡፡በነቃው ቁጥር ሩኩዕ ላይ፣ ሱጁድ ወርዳ ፣ቆማ ዱአ ስታረግ ፣ስታለቅስና ስትማፀን አያታለሁ፡፡ፈጅር እስኪወጣ እስኪወጣ ድረስ በዚሁ ሁኔታ ቆየች፡፡ ከዚያ ቀሰቀሰችኝ፡፡"በል ተነስ ሱብሒ ደርሷል፡፡አብረን እንስገድ ፡፡" አለችኝ፡፡ ሰገድን ጥቂት ተኛች፡፡

ፀሀይ ስትወጣ በል ወደ ፓስፓርት ጣቢያው እንሂድ ከ አለችኝ፡፡ "እንዴ ....ወዴት ?ምን ልናረግ?በምን መረጃ ..የታለ ፎቶው? አልኳት፡፡
"ሄደን እንሞክር" አለችኝ ።ከአላህ እዝነት ተስፋ ለምን እንቁረጥ አለችኝ፡፡ ሄድን፡፡ወላሂ ጣቢያው ግቢ እንደገባን በለበሰችው ኒቃብ እሷ መሆኗን እንዳዐ
ወቁ አንደኛው ሰራተኛ "አንቺ እገሌ ነሽ አይደል? አላት፡፡"አዎን" አለችው፡፡ "በይ ፓስፖርትሽን ውሰጂ ተሰርቶልሻል አላት፡፡

ስታየው ከነ ሒጃቧ በሰጠችው ፎቶ ተሰርቶላታል፡፡ ደስ አላት፡፡"አላህን ለሚፈራ ሰው እሱ መውጫ ያበጅለታል፡፡ አላልኩህም ወይ !"አለችኝ፡፡
ለመውጣት ስንንደረደር አንደኛው ሰራተኛ "ወደ መጣችሁበት ሀገር ሄዳቹ ምህተም ማስመታት አለባቹ " በማለት አሳሰበን፡፡
ወደ ትውልድ ከተማዋ ተመለስን፡፡እኔም በውስጤ ቤተሰቧን ለመጠየቅ ይህ የመጨረሻ እድሏ ነው ፡፡አልኩኝ፡፡ከትንሿ ከተማ ደረስን፡፡

ማረፍያ ቤት ተከራይተን አረፍን፡፡ማህተም አስመታን ፡፡ ከዚያም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ብለን ተንቀሳቀስን ፡፡ደርሰን በሩን አንኳኳን፡፡ቤታቸው ያረጀና እዚ ግባ የማይባል ነው፡፡ድህነት በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ታላቅ ወንድሟ በሩን ከፈተልን ፡፡ወጣትና ፈርጠም ያለ ጎረምሳ ነው፡፡ስታገኘው እጅግ ደስ አላት፡፡በፈገግታ ፊቷን ገልጣ መደሱ ሄደች፡፡ሰላምታ አቀረበችለት ፡፡እሱ ግን ገና እንዳያት ፊቱ ተቀያየረ...


#ክፍል_8_ይቀጥላል...

@Halali_tube
@Halali_tube
እስላሙ አለይኩም
ምናልባት ይሄ በለዐ😷 የመጣው በኔ ወንጀል ሊሆን ይችላል...ስለዚ ቢያንስ ትንሽ እንኳን ወንጀሌ እንዲቀንስ በማወቅም ይሁን ባለ ማወቅ ያስቀየምኳቹ ከልባቹ አውፍ በሉኝ 🙏 ወላሂ እኔ ሁላቹንም አውፍ ብያቿለው.....ከአላህ ምህረትን አገኝ ዘንድ እናንተም ዱዐ አርጉልኝ.....ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ ምናልባትም እኮ በአንዳችን ምክኒያት ይሆናል ይሄ ሁሉ በለዐ....

ኢንሻአላህ ሼር ይደረግ🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_8

በሰላም መመለሷ ያስደሰተው ቢመስልም ሙሉ አካሏን በሚሸፍነው ልብሷ ግን ሳይገረም አልቀረም፡፡በፈገግታ ተሞልታ ወንድሟን አቅፋ ወደ ቤቱ ዘለቀች፡፡ከኃላዋ ተከትዬ በመግባት ብቻዬን ሳሎን ውስጥ ተቀመጥኩኝ፡፡

እሷ ወደ ውስጥ ዘለቀች፡፡በሩሲያ ቋንቋ ታወራቸዋለች፡፡ሚያወሩትን ማወቅ አልቻልኩም፡፡በሂደት ግን ድምፃቸው ከፍ እያለ መጯጯህ ጀመሩ፡፡ሁሉም በዚህ እና በዚያ እየጮሁ ያዋክቧት ጀመር፡፡ሁኔታው አላማረኝም፡፡የሚሉትን በርግጠኝነት አላወኩም ምንም ማረግ አልቻልኩም ፡፡

በሂደት ድምፁ እኔ ወዳለሁበት ክፍልእየቀረበ መጣ፡፡አንድ ጎረምሳ ሰው ከፊት ሆኖ ሶስት ወጣቶች ወደኔ እየጦቀሙ መጡ፡፡ መጀመርያ አስቤ የነበረው ያቀረብኩትን የጋብቻ ጥያቄ ይቀበሉኛል ብዬ ነበር፡፡ሆኖም ግን ወድያው እንደ አውሬ ሰፈሩብኝ፡፡በቅፅበት ቡጢ ፣ ጥፊ ፣ እርግጫ ....አከታትለው አሳረፉብኝ፡፡ለመከላከል ሞከርኩኝ ፡፡ሰዎች እንዲደርሱም ጮውኩ ፡፡ማንም የደረሰልኝ አልነበረም፡፡ በመጨረሻም ደክሞኝ ወደኩኝ፡፡ይህ ቤት ለህይወት ዘመኔ የመጨረሻዬ ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ዱላው በዛብኝ፡፡

ለመሸሽ አሰብኩና በአይና የገባሁበትን በር ማፈላለግ ጀመርኩ፡፡በሩን እንዳስተዋልኩ ወድያው ሩጨ ወጥቼ ማምለጥ ቻልኩ፡፡ተከትለው አሳደዱኝ፡፡በአከባቢው ብዙ ሰው ስለነበር በሰዎች መሀል ገብቼ ተሰወርኩባቸው፡፡ከዚያም ትንሽ አርፌ ወደነበርኩበት ማረፊያ ሄድኩኝ፡፡ከቤቱ ብዙ አይርቅም፡፡ክፍሌ ገብቼ የደረሰብኝን ማየት ጀመርኩ፡፡ጥርሴና ከንፈሬ ደምቷል፡፡ፊቴ በደም ተለውሷል፤ልብሴ ተበጣጥሷል፡፡

ታጠብኩኝ፡፡ከነዛ አውሬዎች ያስመለጠኝን ከላህ አመሰገንኩ ፡፡ ወድያው ደግም የባለቤቴ ጉዳይ በሀሳቤ መጣብኝ፡፡እንዴት አድርገዋት ይሆን ፊቷ ድቅን አለብኝ፡፡እኔን በደበደቡበት ሁኔታ ይደበድቧት ይሆን!እኔ መቋቋም ያልቻልኩትን ዱላ እሷ በሴት አቅሟ እንዴት ትችላለች፡፡ሚስኪን ባለቤቴ፡፡ በዱላ ብዛት እጅ እንዳትሰጥ እና አቋሟን እንዳትለውጥ ሰጋሁ፡፡ ከሷ ከተለየሁበት ጊዜ ጀምሮ ሸይጧን ስራውን መስራት ጀመረ፡..


#ክፍል_9_ይቀጥላል....

@Halali_tube
@Halali_tube
ለሀዘናችን "ሶላት ከሰገድን"

ለህመማችን - "ቁርዐን ከያዝን"።

ለልብ ጭንቀት እና መጥበብ
‹እስቲግፋር ምህረት መጠየቅ ከቻልን›

~ ለወደፊቱ ምኞቶቻችን “በዱዐ ከታገዝን ”
በዱኒያ ላይ ላጣናቸው everything ማንኛውም ነገሮች ‹ጀነት እንዳለ ካሰብን › ፡፡

ይህ ካረግን ሀዘናችሁ ፈተናችሁ
ምንም ቢከብድ በሰላም እና በደስታ
ተረጋግታችሁ ትኖራላችሁ!
#Share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_9

"በቃ ወደ ሀይማኖቷ ወደ ክርስትና መመለሷ አይቀርም፡፡አንተም ብቻህን ወደ ሀገርህ ትሄዳለህ" እያለ ሹክ ይለኛል ፡፡ግራ ገባኝ ፡፡ ምን ማድረግ እችላለሁ ?...በዚ ሰው በማላቅበት ሀገር ውስጥ የት ልሂድ ምንስ ልስራ?በዚ ሀገር ነፍስ ምንም ዋጋ ያላት አትመስልም ፡፡ በጥቂት ገንዘብ ከንዱን ነፍሰበሊታ ቀጥረህ የምትፈልገውን ሰው ማስገደል ትችላለህ፡፡ ፈራሁኝ፡፡

አሰቃይተዋት ያለሁበትን ማረፍያ ብትጠቁማቸውስ? አድብተውና ተከታትለው በጨለማ ቢደፉኝስ?በሬን ከውስጥ ዘጋሁ፡፡ክስከ ጠዋት ድረስ በፍርሀት ተውጨ እዚያው ነጋብኝ፡፡ጠዋት ላይልብሴን ቀይሬ ወጣሁ፡፡ በሩቅ ሁኜ የቤታቸውን አከባቢ መቃኘት ጀመርኩ ፡፡ ነገር ግን በሩ ዝግ ነው፡፡ ቆሜ መጠባበቅ ያዝኩኝ ፡፡ብዙም ሳልቆይ በሩ ሲከፈት አየሁ፡፡

ሶስት ወጣቶችና አንድ ጎረምሳ ሰው ሲወጡ ተመለከትኩ፡፡ የደበደቡኝ ሰዎች ናቸው፡፡ከሁኔታው ወደ ስራ የሚሄዱ ይመስላሉ ፡፡እንደገና በሩን ዘጉና ቆለፉት፡፡ እዚያው ጠበኩኝ....ጠበኩኝ፡፡የባለቤቴ ፊት ናፈቀኝ፡፡ሆኖም ግን አልተሳካልኝም፡፡ላያት ላገኛት አልቻልኩም፡፡በዚሁ ሁኔታ ላይ ሰዎች ከስራ እስኪመለሱ ድረስ ለሰዓታት ቆየሁኝ፡፡

በመጨረሻም ደከመኝና ወደ ማረፍያ ክፍሌ አመራሁ ፡፡ ከተለየኀት በሶስተኛ ቀኔ በህይወት መኖሯንም ተጠራጠርኩ፡፡ምናልባት ገድለዋት ከሆነም በአከባቢው ላይ የሆነ እንቅስቃሴ ይኖር ነበር፡፡ምንም ነገር ባለማየቴ በህይወት ትኖራለች የሚል ተስፋ አደረብኝ፡፡ በቅርቡ አገኛታለሁ ብዬም አሰብኩ፡፡ተፅናናሁ በአራተኛው ቀን በማረፍያ ክፋሌ ታግሼ መቀመጥ አልሆነልኝም፡፡

በሩቅ ሆኜ የቤቱን ሁኔታ መከታተል ጀመርኩኝ፡፡እንደተለመደው ወጣቶቹ ከአባታቸው ጋር በመሆን ለስራ ሲሄዱ ተመለከትኩ፡፡የተመኘሁት ነበር፡፡ ወድያዉ በሩ ተከፈተ...

#ክፍል_10_ይቀጥላል............

@Halali_tube
@Halali_tube
``ምርጥ ታሪክ ከሰሃቦች አምድ``

ሸዳድ ኢብኑ አል-ሀድ ስለ አንድ ሙስሊም ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የተናገሩትን ይነግሩናል። አንድ ወደ ኢስላም የገባ ዐረብ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ ይመጣና ከሳቸው ጋር መውጣት እንደሚፈልግ ነገራቸው። ነብዩም ከሰሃቦች ጋር እንዲወዳጅ አደረጉት።

በኃላ በተካሄደ ጦርነት ከጦርነቱ የተገኙውን ምርኮ ለተከታዩቻቸው ሲያከፋፍሉ፤ ለዚህ ተከታይም ድርሻውን ባልደረቦቹ ዘንድ አስቀመጡለት። ባልደረቦቹ የተቀመጠለትን ምርኮ ሲሰጡት "ይህ ምንድነው?" ሲላቸው እነርሱም "ይህ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ላንተ ያስቀመጡልህ የምርኮ ድርሻ ነው" አሉት።

ሰውየው ምንም ሳይናገር ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወዳሉበት በመሄድ እሳቸውንም "ይህ ምንድነው?", አላቸው። እሳቸውም "ይህ እኔ የመደብኩልህ ድርሻህ ነው" አሉት። እሱ ግን "እኔ የተከተልክዎት ለዚህ (ምርኮ ለማግኘት) ሳይሆን እዚህ ጎሮሮዬ ላይ በቀስት ተወግቼ ሸሂድ በመሆን ጀነት ለመግባት ነበር" አላቸው። እሳቸውም "አንተ ለአላህ ሐቀኛ ከሆንክ አላህ ቃልህን ያሟላልሃል" አሉት።

በኃላ ሰሃቦች ጉሮሮው ላይ ተወግቶ የተገደለ ሰው ከውጊያ ቦታ ተሸክመው አመጡ። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ተከታዩቻቸውን"ይህ እሱ ነው?" በማለት ጠይቀው እሱ መሎኑ ሲነገራቸው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም "እሱ ለአላህ እውነተኛ ነበር፤ አላህም ለሱ እውነተኛ ሆነ" አሉ።

ሸሂድ ስለሆነ ለብሶት ከነበረው ልብስም ጋር ቀበሩት። በኃላም እንዲህ ማለታቸው ተሰምቷል:- "አላህ ሆይ! ይህ ያንተ ባሪያ ነው፤ በአንተ መንገድ ላይ ሂጅራ አድርጓል። ሸሂድ ሆኖም ሞቷል። ለዚህ ደግሞ እኔ ምስክር ነኝ።"

አላህን የሆነን ንግር ስንጠይቀው ከልባችን መሆን አለበት። ያኔ ፍላጎታችን ይሳካል.....

#ኢንሻአላህ_share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_10

አሻግሬ የባለቤቴን ፊት አየሁኝ ፡፡ ወደግራና ቀኝ ትመለከታለች፡፡ ፊቷ ቀልቷል፣ ቆዳዋ በልዟል፡፡ልብሷ በደም ተጨማልቋል፡፡ በጣም ጎድተዋታል፡፡ሁኔታዋ አስደነገጠኝ፡፡አሳዘነችኝ ፡፡ ፈጠን ብዬ ወደ በሩ ቀረብኩኝ፡፡በቅርበት ሁኜ ለረጅም ጊዜ ተመለከትኳት፡፡ፊቷ ቆሳስሏል፡፡ከእጅና እግሯ ደም ይፈሳል፡፡
ልብሷም ተበጣጥሷል፣ እራፊ ጨርቅ ብቻ ነው የሚታይባት፡፡

እጅ ና እግሯ በሰንሰለት ታስሯል፡፡ሳያት አለቀስኩ ፡፡ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ድምፄን ከፍ አርጌ ጠራዋት፡፡ ስጠራት ወደኔ ዞረች ስቃይዋን እየቻለች ኻሊድ ሆይ !!ስማኝ አለችኝ፡፡"ኻሊድ ስለኔ አታስብ ፡፡እኔ በቃሌ እንደፀናው ነኝ፡፡ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን መሰክራለሁ ::አሁን እኔን የሚያገኘኝ ስቃይ ነቢያችንን የአላህ መልዕክተኛ ፣ሰሀቦችን ፣ ታቢኢዮችን ካገኘው አንፃር ምንም ማለት አይደለም፡፡

ኻሊድ ሆይ! "ኻሊድ ሆይ በኔና በቤተሰቦቼ መሀል አትግባ፡፡አሁን ቶሎ ሂድ፡፡እዚያው ክፍልህ ጠብቀኝ ፡፡ኢንሻአላህ እመጣለሁ፡፡ነገር ግን በደንብ ዱአ አብዛ ፣ ሰላት ,የሌሊት ሰላት አብዛ አደራ" አለችኝ :: ውስጤ በቁጭት እየነደደ ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ፡፡ቀኑን ሙሉ ጠበኩአት ፡፡መምጣቷን እየናፈኩ ቆየሁ ተጨማሪ ቀን አለፈ፡፡

ሶስተኛ ቀንም እንዲሁ አለፈ፡፡ መሸ፡፡በዚ ሁኔታ ላይ እያለሁ ድንገት የክፍሌ በር ተንኳኳ፡፡ደነገጥኩ፡፡ማን ይሆን?ያረፍኩበትን አውቀው ሊገሉኝ መተው ይሆን?በሰኮንዶች ቅፅበት ብዙ ነገር ውስጤ ተመላለሰ፡፡የሞት ፍርሀት ፈራሁ፡፡በመሀከላችን ያለው ርቀትም የጠበበ መሰለኝ፡፡ የሞት ሞቴን "ማነው?" አልኩኝ፡፡ "እኔ እገሌ ነኝ ክፈትልኝ"ረጋ ያለው የባለቤቴ ድምፅ ነው፡፡ክፍሌ ፣ ተስፋዬ በብርሃን ተሞላ፡፡

በሩን ከፈትኩላት፡፡ቆሳስላለች ፡፡ተጎሳቁላለች፡፡ ቁና ቁና እየተነፈሰች ወደ ውስጥ እንደገባች "በል ቶሎ እንሂድ እንውጣ!" አለችኝ፡፡በዚህ ሁኔታሽ ላይ ሆነሽ ወዴት አልኳት ፡፡ዝም አለችኝ...

#ክፍል_11_ይቀጥላል..

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_11

ልብሴን መሰብሰብ ጀመርኩ፡፡ እሷም ወደ ልብስ ሻንጣዋ ዞረች፡፡ልብሷን ቀየረች፡፡ሂጃቧን እና አባያዋን ለበሰች፡፡ወጣንና ታክሲ ተከራየን፡፡የዛለ ሰውነቷን መሸከም
አቅቷት የታክሲው ወንበር ወንበር ላይ ጣለች፡፡ሚስኪን....ቀድሜ ተሳፈርኩ ፡፡ለሹፌሩም "ወደ አየር ማረፍያ ውሰደን፡፡"አልኩት፡፡

የተወሰኑ የራሺያ ቋንቋ ስለለመድኩ እንደምንም ገጣጥሜ ነገርኩት፡፡ ባለቤቴ ግን "አይሆንም አየር ማረፍያ መሄድ የለብንም" ብላ ተቃወመችኝ፡፡ወደዚያ መንደር እንሄዳለን ብላ ስም ጠራች፡፡ "ማምለጥ አለብን ልክ ነህ ግን አየር ማረፍያ ከሄድን ያጠያይቁና ይደርሱብናል አለች፡፡ያ እንዳይሆን ወዳልኩህ ከተማ እንሄዳለን "አለች፡፡

ወዳለችው ትንሽ ከተማ ደረስን፡፡እዚያ ወረድን፡፡ከዚያ ደግሞ ሌላ መኪና ይዘን ወደ ሌላ ከተማ፡፡ቀጥሎም ወደ ሌላ ትንሽ ከተማ፡፡በመጨረሻም አንዲት ኤርፓርት ያላት ከተማ ደረስን፡፡ወደ ሀገራችን ለመመለስ ትኬት ቆረጥን፡፡የበረራ ቀኑ ይዘገይ ስለነበር ክፍል ተከራይተን ቆየን፡፡

በቤቱ ውስጥ የመረጋጋት ስሜት ሲሰማን ባለቤቴ አባያዋን አወለቀች፡፡ሰውነቷን ተመለከትኩ፡፡ያ አላህ!! እንዴት ያለ ጭካኔ ነው፡፡ሴት ልጅን እንዴት በዚ መልኩ ያሰቃያሉ ፡፡ፍርሀትና ድንጋጤ ወረረኝ፡፡ደም ያልነካው ሰውነት የለም፡፡ቆሳስላለች፡፡ደም ቋጥሯል፡፡ከንፈሯ በልዟል፡፡

እነሆ ታሪኳ!
"እስቲ ምን እንደተፈጠረ አውጊኝ አልኳት ፡፡ገጠመኟን ማውጋት ጀመረች፡፡
ቤት እንደገባን ከቤተሰቦቼ ጋር ማውራት ጀመርን ፡፡
"ይህ ልብስ ምንድነው ?አሉኝ፡፡
"የሙስሊም ልብስ ነው ሰልሜያለሁ፡፡"አልኳቸው፡፡
"አብሮሽ ያለውስ?"
"ባለቤቴ ነው፡፡"አልኳቸው፡፡"ከዚህ ሰውዬ ጋርም ተጋብቻለሁ፡፡"ብዬ እቅጩን ነገርኳቸው...

#ክፍል_12_ይቀጥላል......

@Halali_tube
@Halali_tube
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_12

"ይህማ አይሆንም፡፡መሆንም የለበትም አሉኝ። "ታገሱኝ የሆነውን ልንገራቹ" አልኳቸው::ታሪኬን ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገርኳቸው፡፡ከዚህ ይዞኝ የሄደው ሰውዬ መጥፎ ስራ ሊያሰማራኝ እንደነበር አጫወትኳቸው ፡፡የውስጣቸውን ነገሩኝ፡፡"ሙስሊም ከምትሆኚ ሴተኛ አዳሪ ሆነሽ ብትቀሪ እንመርጣለን፡፡ "አሉኝ፡፡

አክለውም አስጠነቀቁኝ፡፡"ከዚ ቡሀላ ከዚ ከክርስትያን ቤት ሚወጣው ሬሳሽ ብቻ ነው" አሉኝ፡፡ከዚያም ይዘው አሰሩኝ ቀጥሎ አንተን ለመደብደብ ወጡ፡፡ሲደበድቡህ እሰማ ነበር፡፡እኔ ታስሬያለሁ፡፡አንተ ስታመልጥ ተመልሰው መሳደብና እኔን ማነወር ጀመሩ፡፡ ከዚያም ወጡና ሰንሰለት ሰንሰለት ገዝተው፡፡ተመልሰው አሰሩኝ፡፡በአለንጋም ይገርፋኝ ጀመር ፡፡በየቀኑ ከአስር ጀምረው ይገርፉኛል፡፡ ያሰቃዩኛል፡፡

ጠዋት ወደ ስራ ይሄዳሉ፡፡እናቴ በቤት ውስጥ ስራ ትጠመዳለች፡፡ቤት የምትቀረው ትንሿ እህቴ ብቻ ናት፡፡ 15 አመት ይሆናታል፡፡ትመጣና ትስቅብኛለች፡፡ለኔ የዕረፍት ጊዜ የሚባለው ይሄው ነው፡፡ እንቅልፍ እንኳ የምተኛው ራሴን በሳትኩበት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ራሴን እስክስት ድረስ ይገርፉኛል፡፡ በዚያው እንቅልፋ ይወስደኛል፡፡ከኔ የሚፈልጉት ክርስትያን እንድሆን ብቻ ነው፡፡

ሊያሳምኑኝ እና ሊመልሱኝ አልቻሉም ፡፡ ከዚያ በኃላ ትንሻ እህቴ ትጠይቀኝ ጀመር፡፡ለምን የእናት የአባት የአያቴን ሀይማኖት እንደተውኩ...
ሁኔታዎችን ዘርዝሬ አጫወትኳት፡፡በተደጋጋሚ ሞከርኩ፡፡ስለ አላህ አንድነት ፣ስለ እስልምና እምነትምንነትና ስለ ሌላም፡፡በርግጥ እያመነች መጣች ፡፡ አሳዘንኳትም፡፡

በአላህ ፍቃድ ቀጥሎም ሳልቆርጥ ባደረኩት ጥረት ስለ እስልምናም ግልፅ እየሆኘላት መጣ፡፡"አሁን ተረድቼሻለሁ አንቺ እውነት ላይ ነሽ!የያዝሽው እኔም ልይዘው ሚገባኝ እውነተኛ ሃይማኖት ነው፡፡

እንደውም ረዳሻለሁ!አለችኝ
እሺ ከባለቤቴ ጋር አገናኚኝ አልኳት፡፡
ከጣርያው ላይ ወታ አከባቢው ላይ አንተን ተመለከተች አየችህ፡፡የአካላዊ ገለፃ አረገችልኝ እሱ እራሱ ነው አልኳት..

#የመጨረሻው_ክፍል_ይቀጥላል...

@Halali_tube
@Halali_tube
🔻||እስካሁን ስለዚህ በሽታ ምንም ለማለት አልፈለኩም እንዲያውም ላለማሰብና ለመርሳት እየሞከርኩኝ ነበር ጭንቀት በራሱ ከበሽታው በላይ እንደሚጎዳም አውቃለው ግን እዩት እስኪ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ምን እንዳለ አዎ ሀያል አገር ነኝ ነበር የምትለው ግን ከዚህ ወረርሽኝ እራሱዋን ማዳን አልቻለችም።

" ከሁሉም አገሮች በላይ ጣሊያን በ24 ሰአት ውስጥ ብቻ ሪከርድ በሆነ አሳዛኝ ቁጥር 793 ሰዎችን በኮሮና አጥታለች ጠቅላላ የሟቾቿ ቁጥር ደግሞ 4,825 ደርሷል።

"ልጅ ሲያጠፋ እናቱ ልትገርፈው ትችላለች ግን እያለቀሰ ተመልሶ እሷ ጋር ነው የሚጠጋው እኛም የሰው ልጆች አጥፊዎች ነን ይሄ ደግሞ ትንሹ ቅጣታችን ነው ልክ ጠቅላያቸው እንዳለው በራሳችን ልናደርግ የቻልነው አንዳች ነገር የለንም እያለቀስን አምላካችንን ከመጠጋት ውጪ ይቅር እንዲለን ከመለመን ውጪ እኛ ኢትዮጵያውያን እነሱ ያልቻሉትን እኛ ብለን በማሰብ እንጠንቀቅ።

" አትርሱ እነሱጋም ከ 1 ነው የጀመረው 9 ትንሽ ነው ብለን አንዘናጋ ስለ ጉዋደኛየ ስለ ቤተሰቤ እኔ ከተጠነቀኩኝ እኔም ሀገሬም እንድናለን ስለዚህ እራሳችንን እንጠብቅ ከኛ በላይ ለኛ የሚያስበው አላህ በቃ ይበለን ከምድርም ያንሳልን!!!

@Halali_tube
@Halali_tube
#የኮቪድ19_በሽታ_የየቀኑ_ምልክቶች
*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
፨ ከ1-3 ቀን
. በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ።
. የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ ሊኖራቸው ይችላል ።

፨ በ 4 ኛው ቀን
. የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም የድምፅ መወፈር ይኖራል ።
. ብዙ ጊዜ ትኩሳት አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል
. ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ሊስተገዋጎል ይችላል ።

፨ በ 5 ኛው ቀን
. ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ ይጎረንናል ።
. በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት ድካም ይኖራል ።

፨ በ 6 ኛው ቀን
. ትኩሳት ይጀምራል
. ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል
. ምግብ በመመገብ ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ ህመም ይኖራል ።
ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ።

፨ በ 7 ኛው ቀን
. ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል
. ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል
. የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ።

፨ በ 8 ኛው ቀን
. መተንፈስ መቸገር
. የደረት መክበድና ህመም
. ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም
. የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም በጣም ይጨምራል ።
. ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል

፨ በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት
. ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ።

ማንኛው ስው የሚከተሉት አደገኛ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቁአም መሄድ ያስፈልጋል ።
፧ የተራዘመ ድረቅ ሳል
፧ የትንፋሽ ማጠር
፧ የደረት ህመም
፧ ከፍተኛ ትኩሳት


ሀላልን ይቀላቀሉ!
👇👇👇
@Halali_tube
@Halali_tube

#Share 🙏🙏🙏
2025/02/06 04:51:44
Back to Top
HTML Embed Code: