Telegram Web Link
``ሩሲያዊቷ ሱመያ``
««ሙሉ በሙሉ #እውነተኛ»»


#ክፍል_13(የመጨረሻው ክፍል)

"ካየሽው ዝም ብለሽ በሩን ብቻ ከፍተሽልኝ ተይ፡፡እኔ አወራዋለሁ ፡፡"አልኳት፡፡ በርግጥም በሩን ከፈተችውና ላናግርህ ቻልኩኝ፡፡በሁለት ሰንሰለት ታስሬ ስለነበር ወጥቼ ላናግርህአልቻልኩም፡፡ቁልፎቹ ደግሞ ወንድሜ እጅ ነው ያሉት፡፡የሶስተኛው ቁልፍ ከቤቱ ምሶሶ ጋር የታሰረ ነው፡፡የዚህኛው ቁልፍ እህቴ እጅ ላይ ይገኛል፡፡ሽንትቤት ስሄድ የምትፈታኝ እሷ ናት፡፡

ይህ ሁሉ እንዳላመልጥ ነው፡፡ያኔ ሳገኝህም ታስሬ ነበር፡፡እህቴን ለማሳመን ብዙ ጣርኩኝ ፡፡በመጨረሻም ሰለመች፡፡ ከኔ በላይም መሰዋእት ለመክፈል ወሰነችና ከቤቱ እንዳመልጥ ረዳችኝ፡፡
የሰንሰለቶቹ ቁልፍ ወንድሜ እጅ ነበር የሚገኘው፡፡ሳመልጥ እለት ከበድ ያለ አስካሪ መጠጥ ለወንድሞቼ እህቴ አዘጋጀችላቸው፡፡እስከ እኩለ ሌሊት ሲጠጡና ሲደጋግሙ አመሹ ::

ሰክረው ተኙ ከዛም የሰንሰለቱን ቁልፍ ወስዳ ፈታችኝ፡፡በጨለማ የመጣሁትም በዛ ምክንያት ነበር፡፡ አለችኝ፡፡
"የእህትሽ ነገር ይበልጥ አሳሰበኝ፡፡እሷስ እንዴት ሆና ይሁን?"አልኳት፡፡
"ዋናው ነገር መስለሟ ነው፡፡በሂደት እናስተካክላለን፡፡መስለሟን እንዳታሳውቅ ነግሬያታለሁ" አለችኝ፡፡
ለሊቱን ተኝተን አደርን፡፡በነጋታው ወደ ሀገራችን ተመለስን፡፡

እንደደረስን ባለቤቴን ወደ ሆስፒታል ወሰድኳት፡፡ለቀናት ቁስሉ እስኪያገግም ሆስፒታል አብሬአት ቆየን፡፡አሁን ደግሞ አላህ በዲኗ እንዲያፀናት ለእህቷ ዱአ እያረግን ነው ፨

ውዷ እህሀቴ !!ይህን ታራክ የምነገርሽ ከንፈር መጠጣሽን ፈልጌ አይደለም፡፡ነገር ግን አንድ ነገር እንድታውቂ ነው፡፡ዛሬም ይህ ዲን የሚጠብቁትና የሚከላከሉት ፣ መሰዋእት የሚሆኑለት ፣ ወድ ነገራቸውን ሁሉ የሚከፍሉለት ፣ደማቸውን የሚያፈሱለት ስጋቸውን የሚቆርሱለት ብዙ ጀግኖች አሉት፡፡የትላንቶቹ የኢስላም ጠላቶች እና አቡ ጀህል ኡመያ ሱመያንና ቢላልን አሰቃይተው ከሆነ የዛሬዎቹም የሙስሊም ጠላቶች ሙስሊሞችን በማሰቃየትና ለስደት በማብቃት እስልምናን ለማጥፋት ብዙ እየሰሩና እያሴሩ ነው፡፡

ታድያ በነሱ ወጥመድ ከሚገቡትና ከሚታደኑት እንዳትሆኚ አደራ፡፡ክብርሽ ምን ያህል ከፍ ያለ እንደሆነ ታውቂ ዘንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በተቀደሰው የመካ ምድር የኖረችው ሴት መሆኗን ልብ በይ።

°ተ•ፈ•ፀ•መ°

@Halali_tube
@Halali_tube
የ ውቃቢ እና የዛር ጉዳይ ዳሰሳ
ጠቅላላ ግንዛቤ ለሁሉም
⭕️ #የዛር እና የውቃቢ ጉዳይ በኢስላም ሚዛን ላይ
🔰 #ጠቅላላ_እውቀት_ለሁም
በኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ
#Share 🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
🏠ከቤት ሲወጡ የሚደረግ ዱዓእ🏡

ኡሙ ሰለመህ ረ.ዐ. እንደዘገቡት ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ከቤታቸው ሲወጡ
‹ቢስሚልላህ ተወከልቱ ዐለልላህ፣ አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ አን አዲልለ አው ኡዶልለ፣ አው አዚልለ አው ኡዘልለ፣ አው አዝሊመ አው ኡዝለመ፣ አው አጅሀለ አው ዩጅሀሉ ዐለይየ፡፡› ይላሉ፡፡ (አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል፡፡)
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ትርጉሙ -/በአላህ ሥም፡፡ በአላህ ተመክቻለሁ፡፡ አላህ ሆይ! እንዳልጠም እንዳላጠም፤ እንዳልሣሣት እንዳላሣሥት፣ እንዳልበድል እንዳልበደል፤ እንዳላጠፋ ሌሎች እንዳያጠፉብኝ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡/
😊 እንተዋወስ😊

#Share_share_your_friend
🙏🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
ከረመዷን ቀዷእ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች
---------------
1. የረመዷንን ቀዷእ ወዲያው ማውጣት ግዴታ ነው ወይስ ቀስ ብሎ ማውጣት ይቻላል?
2. የቀዷእ ፆምን ለያይቶ መፆም ይቻላል ወይስ አከታትሎ መፆም ግዴታ ነው?
3. በአሳማኝ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበት ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
4. ያለ ተጨባጭ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበትስ ሰው ምን አለበት?
አራቱንም ነጥቦች በቅደም-ተከተል እንመልከት።
ጥያቄ አንድ፡-
የረመዷንን ቀዷእ ረመዷን እንዳለቀ ወይም ያቆምንበት ዑዝር እንደተነሳ ወዲያው ማውጣት ግዴታ እንደሆነ የሚያመላክት ቀጥተኛና ግልፅ (ሶሪሕ) ማስረጃ የለም። ስለሆነም ቀጣዩ ረመዷን እስካልገባ ድረስ እስከ ሸዕባን ድረስ ባለው ረጅም ጊዜ ቀዷእ ማውጣት ይቻላል። ይህ አቋም እንደ ኢብኑ ዐብዲል በር እና መጅድ ኢብኑ ተይሚያ ያሉ ዑለማዎች ኢጅማዕ ያለበት ነው ይላሉ። በርግጥ ኢጅማዑ አጠያያቂ ነው። ምክንያቱም የዟሂሪያው መዝሃብ ኢማም ዳውድ ረመዷን እንደተጠናቀቀ፣ ከዒድ በኋላ ከሸዋል ሁለት ቀጥሎ ቀዷእ ማውጣት ግዴታ ነው። ሳይፆመው ከሞተ ግን ወንጀለኛ ነው ብለዋልና። ሌሎችም ተመሳሳይ አቋም ያንፀባረቁ ዑለማዎች አሉ።
የብዙሃኑ የኢስላም ምሁራን ዐቋም ግን ቀጣዩ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ቀዷእ ቢዘገይም ችግር የለውም የሚል ነው። ሼር🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
ኢንሻአላህ ራመዳን 15 ቀናቶች ብቻ ነው የቀሩት። አንድ ሰው ለሌላ ሰው የረመዳንን ቀን ቀድሞ ካሳወቀ እሳት በሱ ላይ ሀራም ትሆንበታለች።
ኢንሻአላህ ሼር በማድረግ አስተላልፉ
#Share 🙏🙏🙏🙏
@Halali_tube
@Halali_tube
{የተውሒድ ጀግና ሁን}

➪የሰው ልጅ የተለያዩ ስሞችን እያወጣልህ
በራሱ ሚዛን መዝኖ ዝቅ ያደርግሃልና
በሰዎች ሚዛን እራስህን አታጨናንቅ
➪ዋነው አላህ ዘንድ ከፍ ማለቱ ነው

➪ነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ)
ሰዎች ዘንድ እንዲህ ተብሎ ነበር

(قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ۝)
«ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል» ተባባሉ ፡፡
[)አንቢያእ 60(]

➪አላህ (ﷻ) ዘንድ ደግሞ
እንዲህ ተባለ…

(إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ۝)
“ ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር ከአጋሪዎቹም አልነበረም ፡፡"
[)ነህል 120(

ኢንሻአላህ ሼር🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ጠ ብ ቀ ን
`````````


ጌታችን ሲታመፅ ወንጀሉ ሲጠና፡
ተግሣፅ ይሆነን ዘንድ ላከብን ኮሮና፡
እኛ ግን አሁንም ከአመፅ አልቦዘንም፡
ወስነን ወደ አሏህ አወ አልተመለስንም፡

አድባር ቆሌ ጂኒ እየተመለከ፡
በወልይ በራሒሎ ሰው እየታከከ፡

ለፈጠረን ጌታ ሱጂድን ስንተወው፡
ያው ኮቪድ ናይንቲን ሀገሩን ወረረው፡
ገና በቲወሪ ህዝቡን አሰከረው፡

ሽርክ እየፈፀምን እያሰርን አትርሽኝ፡
ወሰነብን ጌታ ኮሮና ወረርሽኝ፡
መች ተመለስንና መች አሏህ ታረቀን፡
በጤና መታወክ ጌታ እያሣቀቀን፡
በኮቪድ 19 እባክህ ጠብቀን፡

Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
በአላህ ላይ ማጋራት እና ሞትን መፍራት
ኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን
👆👆👆
🔈 #በአላህ ላይ ማጋራት እና ሞትን መፍራት
ኢንሻአላህ ሼር ይደረግ 🙏🙏🙏
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
• ስለ «ኑሽራ» ሸሪዐችን ምን ይላል?

~ ኑሽራ ማለት በአጭሩ:- ድግምትን ከተደገመበት ሰው ላይ ማስፈታት ነው።

በአሁን ዘመን ዑመተል ኢስላም ተውሒድን አበጥረን ካለማወቃችን በተጨማሪ በብዙ አንግል የተውሒድ ድክመቶች ይስተዋሉብናል። ከነዚህ ድክመቶች ውስጥ ይህ ነጥብ «ኑሽራ» አንዱ መገለጫ ነው።

በየመንደሩ ብንፈትሽ አብዘሀኛው ሰው በመስጂድ በሮች መገፋፋት ሲኖርበት ይልቁንስ በዚህ ተቃራኒ የሰውም የጂኒም ሸይጧን ከሆኑት የደጋሚዎችን፣ የጠንቋዮችን፣የነገን አዋቂ ነን ባዮችን በሮቻቸው ላይ እርስ በእርስ ሲገፋፉ እናገኛቸዋለን።

እነዚህን ሰዎች አቁመህ እያንዳንዳቸውን የመጡበትን ምክንያት ብትጠይቃቸው መልሳቸውን ስትሰማ በጣም ያስገርምሀል።

• ከፊሉ ድግምትን እንዲፈታልን ይሉሀል
• ከፊሉ ድግምት እንዲሰራልን ይሉሀል
• ከፊሉ ሀብታም የሚያደርገኝን ስራ እንዲሰጠኝ ይልሀል
• ከፊሉ ደግሞ የወደፊት የሂይወታቸውን እጣ ፈንታ እንዲነግረኝ ይሉሀል
«ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ»

ይህ ግባቸው እንዲሳካ በሚችሉት ያክል ስፍር ቁጥር የሌለውን ገንዘብ ወጪ ያደርጋሉ። ይህ ሁሉ ሊቀረፍ የሚችለው አሏህ እውቀት የሰጣቸው ሰዎች በተሰጣቸው እውቀት የቻሉትን ያክል ሌት ተቀን ሲተጉ፣ሲለፉ ነው።

ድግምትን መማሩም ሆነ ማስተማሩ በሸሪዐችን የተከለከለ፣የተወገዘ ተግባር ከመሆኑምጋ ዑለሞችም በአጠቃላይ የተስማሙበት ጉዳይ ነው።ድግምት አጥፊ ከተባሉት ሰባት ወንጀሎች አንዱና ወደ ኩፍር፣ሽርክ የሚወስድ መንገድ ነው።

~ ኑሽራ በሁለት ይከፈላል:-

① በቁርዐን ና በሀዲስ ላይ እንደመጠበቂያ ተደርገው በተቀመጡ አዝካሮች ና በሸሪዐችን በተፈቀዱ መድሐኒቶች በመጠቀም ቅድመ መስፈርቶች በተሟላ መልኩ ድግምትን መፍታት ሲሆን ይህ ዐይነቱ የተፈቀደ ለመሆኑ ከቁርዐን፣ከሀዲስ እንዲሁም [ኢጅማዑል ዑማ] ያለበት ነው።

② በዚህ ፁሁፍ ለመዳሰስ የምንሞክረው የሆነው ድግምትን በድግምት ማስፈታት ነው።

ይህ እንዴት ነው? የሚሆነው ካልን በብዙ ዐይነት መንገድ የሚፈፀም ነው። ከዚህም ውስጥ:-

① ድግምት የተደገመበት ግለሰብ ወደ ጠንቋይ ዘንድ በመምጣት ጠንቋዩ ድግምቱ የት ቦታ እንደተሰራ፣በምን እንደተሰራ፣ማን እንዳሰራው ለተደጋሚው ይነግረውና የተደገመበት አካልም ወደ ቦታው በመሄድ ድግምቱን በማውጣት ድግምቱን ያፈርሰዋል።

② ጠንቋዩ በሸይጧን በመታገዝ ድግምቱን ከተደበቀበት ቦታ በማስወጣት ለተደጋሚው አካል ፊት ለፊቱ ያስቀምጥለታል።

• በነዚህ በሁለቱም መንገድ ጠንቋዩ ተደጋሚው ላይ እውነታውን ለማለባበስ ሲል የተወሰኑ የቁርዐን ሱራዎችን በመቅራት ቱፍታውን ይተፋበታል።

③ ጠንቋዩ ለተደገመበት አካል የተለያዩ ተግባሮችን እንዲፈፅም ያዘዋል።በግ ወይም የተለያዩ እንስሳዎችን በጠንቋዩ ስም ወይም በጂን[ጋኔን] ስም በመጥራት ወደ ጂኑ ወይ ወደ ጠንቋዩ በመቃረብ እሳቤ እንዲያርድ በማዘዝ ድግምቱ ይፈታልሀል ይለዋል።

④ ጠንቋዩ ለተደጋሚው ግለሰብ የተለያዩ ሰይጣናዊ መጠበቂያዎችን በወረቀት ላይ በመፃፍ ተደጋሚው በአካሉ ላይ፣በእንስሳቱ ላይ፣ እንዲያንጠለጥለው እንዲሁም ሲተኛ ከትራሱ ስር እንዲያስቀምጠው ያዘዋል።

• በእነዚህ አራቱ መንገዶች ተደጋሚው ሊፈወስም ላይፈወስም ይችላል።ምክንያቱም ፈውስ በአንዱ አሏህ እጅ ነውና ነገር ግን ጥቅም የተገኘበት ነገር ሁሉ የተፈቀደ ነው ማለት አይደለም።

• በእነዚህ አራቱ መንገዶች ላይ ብዙ አደጋዎች አሉ ከእነርሱም ውስጥ:-

~ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የከለከሉት የሆነው ጠንቋዮች ዘንድ መምጣት

~ ጠንቋዩች ያሉበትን መንገድ ፅድቅ ተግባር እንደሆነ ማረጋገጥ

~ ጠንቋዩ በሰይጣን በመታገዙና ተደጋሚው ደግሞ ጠንቋዩን በመታዘዙ ሁለቱም ወደ ሸይጧን መቃረብን ፈፅመዋል።

~ አሏህ ሐራም ባደረገው ነገር መታከም አለበት ምክንያቱም ጠንቋዮች ዘንድ በመምጣት እነርሱን እገዛ መጠየቅ በሸሪዐ የተወገዘ ነው።

~ ከጃሂሊያዎች ጋር መመሳሰል በውስጡ አለበት

~ ሸሪዐዊ ባላዘዘበት መንገድ ገንዘብን ማባከን አለበት

• ከጃቢር [ረዲየሏሁዐንሁ] እንደተዘገበው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ኑሽራ (ድግምትን በድግምት ስለማስፈታት) ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል:-

[[ እርሷ ከሸይጧን ተግባር አንዷ ነች]] ኢማም አህመድ ዘግበውታል

• ይህ ማለት ወደ ሸይጧን በመቃረብ ቢሆን እንጂ በሌላ መንገድ አትፈፀምም ማለት ነው።

~ በስተመጨረሻም

• ከዚህ አፀያፊ ተግባር ራሳችንን ልንጠብቅ ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል።መጥፎን በመጥፎ መመለስ የለብንም ሰው ሽርክ ላይ ስለወደቀ እኛም መውደቅ የለብንም ይልቁንስ እነርሱን ከሽርክ ለማውጣት ልንለፋ ይገባል።

Share plz🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
😔😔 ይቅርታ😔😔

እኔ ረመዳን ከመድረሱ በፊት ይቅርታ ለመጠየቅ 1ኛ መሆን እፈልጋለሁ


ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያስቀየምኩአችሁ
ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያማሁአችሁ
ይቅርታ በኔ ምክንያት ትንሽም ብቶን ያናደድኩአቹ

የምታቁኝንም የማታቁኝንም ሁላችሁንም ይሄን ፅሁፋ ያነበባችሁ በሙሉ ከዚ በፊት ያረኩትን ደግሜ ላላደርገዉ ከልቤ ይቅር Awfu እንድትሉኝ እጠይቃችሁአለሁ ሁላችሁንም 🙏🙏🙏😢😢በልባቹ ይቅር ሳትሉ እንዳታልፉ pleass

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
Remedan Talaqu Were
Sadat Kemal
ረመዳን ታላቁ ወር
Share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
ﻛﻮﺭﻭﻧﺎ/ ኮሮና

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAE-9wOC4EOwIkB7fPg

የሚለውን የዓረብኛ ምህፃረ ቃል የዚክር ባለቤቶች በዚህ መልኩ ሸርሕ
አድርገውታል ! ህዕ
‏(ﻙ ‏) ፦
ﻛُﻞُّ ﻧَﻔْﺲٍ ﺫَﺍﺋِﻘَﺔُ ﺍﻟْﻤَﻮْﺕِ ۗ
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡
【አል_ዒምራን 【

‏(ﻭ ‏) ፦
ﻭَﻣَﺎ ﺍﻟْﺤَﻴَﺎﺓُ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﺘَﺎﻉُ ﺍﻟْﻐُﺮُﻭﺭِ
ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
【አል_ዒምራን 【
‏( ﺭ ‏) ፦
ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺤَﻤِّﻠْﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻟَﺎ ﻃَﺎﻗَﺔَ ﻟَﻨَﺎ ﺑِﻪِ ۖ
ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡
【አል_በቀራህ 【
‏(ﻭ ‏) ፦
ﻭَﺍﺻْﺒِﺮْ ﻟِﺤُﻜْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﻓَﺈِﻧَّﻚَ ﺑِﺄَﻋْﻴُﻨِﻨَﺎ ۖ
ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡
【አጥ_ጡር 【
‏(ﻥ ‏) ፦
ﻧَﺤْﻦُ ﻗَﺪَّﺭْﻧَﺎ ﺑَﻴْﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟْﻤَﻮْﺕَ
እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች
አይደለንም፡፡
【አል_ዋቂዓህ 【
‏( ﺍ ‏) ፦
ﺇِﻧَّﺎ ﻟِﻠَّﻪِ ﻭَﺇِﻧَّﺎ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﺭَﺍﺟِﻌُﻮﻥَ
‏« እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን
【አል_በቀራህ 【

አጃኢብ በሉ እንመከርበት ተዘከሩ እስኪ!!

ሼር 🙏


@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ከኮሮና ይልቅ በፈጣሪ አምልኮ ላይ ማጋራትን፣ በነብዩ ሱና ላይ ቢድዓን፣ እንከላከል

ከኮሮና ይልቅ ኢየሱስ ፈጣሪ ነው እያላችሁ ፈጣሪን በፍጡር የመሰላችሁ የኣዳም ልጆች ይህን አባባላችሁን በመከላከል ወደ ተፈጠራችሁበት እስልምና በመመለስ ፈጣሪን በብቸኝነቱ ተገዙ

ከኮሮና ይልቅ በደልን ክህደትን፣ ወለድን፣ ዝሙትን፣ አስካሪ መጠጥን፣ የወላጅ መብት መርገጥን፣ የሙት ( የየቲም ) ገንዘብ መብላትን፣በሃሰት መመስከርን፣ ነፍስን ያለ አግባብ መግደልን ወ,ዘ,ተ አጠቃላይ ወንጀሎችን እንከላከል

ኮሮናን ከመጣም በሞት መገላገል ይቻላል
የአላህን መብት ጥሶ በሱ ላይ አጋርቶ ግን በገሀነም እሳት እንጂ በሞት መገላገል የለም

ታዲያ ከኮሮና ቫይረስና ከዘለዓለም የገሀነም የእሳት ቅጣት የቱ እንደሚብስ ሁላችንም ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል!!!
share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
የረመዷን ፆም ከአጥቢና ነፍሰ–ጡር አኳያ
----------------------------------
አጥቢ እናት እና ነፍሰ-ጡር ሴት በመፆማቸው ልጆቻቸው እንዳይጎዱ የሚሰጉ ወይም መፆም የሚከብዳቸው ከሆነ ማፍጠር ይችላሉ፡፡ “ካፈጠሩ ምን አለባቸው?” በሚለው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡ ለማሳጠር ያክል በዚህ ጉዳይ በዑለማዎች ከተሰነዘሩ ሃሳቦች ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ ያመንኩበትን ብቻ ላስፍር፡-
አጥቢ እናት እና ነፍሰ-ጡር ሴት ካፈጠሩ ያለባቸው ግዴታ በሚችሉ ጊዜ ቀዷእ ማውጣት ብቻ ነው፡፡ ይሄ አቋም የሐሰኑል በስሪይ፣ የዐጧእ፣ የዶሓክ፣ የኢብራሂም አንነኸኢይ፣ የአውዛዒይ፣ የዙህሪይ፣ የረቢዐህ፣ የአቡ ዑበይድ፣ የአቡ ሠውር፣ የኢብኑል ሙንዚርና የሌሎችም ምርጫ ነው፡፡ ዐብደላህ ኢብን ዐባስም ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ማለታቸው ተረጋግጧል፡-
«تُفْطِرُ الْحَامِلُ وَالْمُرْضِعُ فِي رَمَضَانَ، وَتَقْضِيَانِ صِيَامًا، وَلَا تُطْعِمَانِ»
“ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ በረመዷን ያፈጥሩና ፆምን ቀዷእ ያወጣሉ፡፡ እንጂ አያበሉም፡፡” [ሙሶነፍ ዐብዱረዛቅ አስሶንዓኒይ፡ ቁጥር7564]
ከኢብኑ ዐባስና ከኢብኑ ዑመር ከዚህ የተለየ ቢዘገብም ቀጥሎ ለሚመጣው ሐዲሥ የሚገጥመው ግን ይሄኛው ንግግራቸው ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
ይህንን አቋም የመረጡ ዑለማዎች ማስረጃቸው ቀጣዩ ሐዲሥ ነው፡፡
إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى وَضَعَ عَنِ الْمُسَافِرِ الصَّوْمَ، وَشَطْرَ الصَّلاَةِ، وَعَنِ الحَامِلِ أَوِ الْمُرْضِعِ الصَّوْمَ أَوِ الصِّيَامَ
“ከፍ ያለው አላህ ከመንገደኛ ፆምንና ከሶላትም ግማሹን አንስቶለታል፡፡ ከነፍሰ-ጡርና ከአጥቢም እንዲሁ ፆምን፡፡” [አቡ ዳውድ፡ 2408] [ቲርሚዚ፡ 715] [ነሳኢይ፡ 2274፣ 2275፣ 2277] [ኢብኑ ማጀህ፡ 1667] ሸይኹል አልባኒ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
ከመንገደኛ ሰው ፆም ተነስቶለታል ማለት ማፍጠር ይችላል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ግን በጉዞ መልስ ምንም የለበትም ማለት እንዳልሆነ ለማንም የሚታወቅ ነው፡፡ ይልቁንም በጉዞው ላይ ካፈጠረ ኋላ ቀዷእ ያወጣል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
فَمن كَانَ مِنْكُم مَرِيضا أَو على سفر فَعدَّة من أَيَّام أخر
“ከናንተ ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች (ተመሳሳይ) ቁጥሮችን መፆም አለበት፡፡” [አልበቀራህ፡ 184]
ልክ እንዲሁ ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ እናትም ፆም ተነስቶላቸዋል ማለት በዚህ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ ማፍጠር ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ልክ በጉዞ ሰበብ ያፈጠረ ሰው ቀዷእ እንደሚያወጣው ቀዷእ ያወጣሉ፡፡ ልክ በጉዞ ሰበብ ያፈጠረ ሰው ምስኪን ማብላት እንደማይጠበቅበት እነሱም ምስኪን ማብላት አይጠበቅባቸውም፡፡ ማፍጠር የተፈቀደው ለዑዝር ነው፡፡ በዑዝር ሰበብ (ለምሳሌ በመንገድ፣ በህመም) ያፈጠረ ሰው የሚጠበቅበት ዑዝሩ ሲነሳ ቀዷእ ማውጣት እንደሆነው ሁሉ ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ እናትም (ለራሳቸውም ይሁን ለልጃቸው ሲሉ ያፈጠሩበት) ዑዝራቸው ሲነሳ የሚጠበቅባቸው ያለፈውን ቀዷእ ማውጣት ብቻ ነው፡፡
ይሄ ቀዷ ብቻ ነው ያለባት የሚለው አቋም ከዘመናችን ዑለማዎች ውስጥ የኢብኑ ባዝ፣ የኢብኑ ዑሠይሚን፣ የሙቅቢል አቋም ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ማብላት ሳይሆን ቀዷእ ብቻ ነው የሚመለከታት የሚለውን “እኔ ዘንድ ሚዛን የሚደፋው አቋም ነው” ብለውታል፡፡ [አሽሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/347]
ወላሁ አዕለም

Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ለመሞት አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ነበር የምትሰራው!?👇

ለኢብኑ ሙባረክ ረሂመሁሏህ ተጠየቀ?
«ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ታደርግ ነበር ተባሉ ?
ሰዎችን አስተምር ነበር አሉ»።
📚ምንጭ፦
‏رواه البيهقي في المدخل [٢/٤٥]
@Halali_tube
@Halali_tube
በኮሮና ቫይረስ ላለመያዝ የፈራነውን፣ ያስነጠሰ እና ያሳለ ሰው ስጋት ውስጥ የከተተንን ያክል ዘለላም አለም ጀሀነም ውስጥ የሚያከርመውን ታላቁ በደል ሺርክ እና ባለቤቶቹን፣ የኢስላም እና ሱና ፀር የሆነውን ቢድአ እና ባለቤቶቹን በተጠነቀቅን ኖሮ በ2 ሀገር ምንኛ እድለኞች በሆንን ነበር።
አላህ እኛንም ዝርያዎቻችንም ከታላቁ በደል ሺርክ፣ ከቢድአ፣ ከዘረኝነት እና እሱ ከጠላው ሁሉ ይጠብቀን።

@Halali_tube
@Halali_tube
ይሄ ቆሻሻ ቅጠል ወገናችን ላይ ያደረሰው ግፍ አንድና ሁለት አይደለም።

① የስንቶችን ዐቂዳ አፈር ድሜ አብልቷል።
② ስንቱን ባለትዳር አባልቷል።
③ የስንቱን ጤና አናግቷል።
④ የስንቱን ኢኮኖሚ አድቅቋል።
⑤ የስንቱን ወጣት ህይወት አጥፍቷል።
⑥ በዐረብ ሃገር በሰው ቤት የሚዳክሩ የስንቱን ወገኖቻችንን ላብ ከንቱ አስቀርቷል።
⑦ ስንት መስራት፣ ስንት መድረስ የሚችሉ ጀግኖቻችንን ወኔያቸውን አፍስሷል።

ጫት:–
* ወኔው የላሸቀ፣
* አእምሮው የዛገ፣
* ነገን ቀርቶ ዛሬን የማያስብ፣
* ይሉኝታ ቢስ፣
* አጉል ጀብደኛ፣
* "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" የሚል አህያዊ መርህ የሚያራምድ፣
* ለቤተሰብም፣ ለወገንም፣ ለሃገርም ሸክም የሆነ ከንቱ ፍጡር ነው የሚያፈራው።
ጫት የስንቶችን አእምሮ ነክቷል። አማኑኤል ሆስፒታል ለዚህ ምስክር ነው። በየሰፈሩ ግማሽ እብድ ግማሽ ጤነኛ የሆነውን ወፈፌ ቤቱ ይቁጠረው። ስንቶች አሉ በዐረብ ሃገር ያሉ ልጆቻቸው፣ ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው ብር እንዲልኩላቸው እየወተወቱ ተዘፍዝፈው ቅጠል የሚያኝኩ። በስንት መከራ የተገኘን ገንዘብ፣ ሽንት ቤት ጠርገው፣ በእሳት ተለምጥጠው፣ ክፉ ደጉን አይተው፣ ነጭ ላብ አፍስሰው፣ ህይወታቸውን ቤዛ አድርገው የሚያገኟትን ገንዘብ ስጋነት ይዟቸው፣ የቤተሰብ ህይወት አስጨንቋቸው ሲልኩ በማመስገን፣ ለቁም ነገር በማዋል ፋንታ እንደ ዋዛ ቁጭ ብለው ይህን ቆሻሻ ቅጠል በውድ ገዝተው ሲያደቁበት ስታዩ ጫት ምን ያክል ለልጅ፣ ለእህት፣ ለወንድም፣… መቆርቆርን፣ ርህራሄን እንደሚገድል ታያላችሁ። ምን ያክል ይሉኝታ ቢስ ፍጡር እንደሚያደርግ ትረዳላችሁ። ምን ያክል የወገንን ላብ ቀርቶ ደም ለመጠጣት የማይመለስ አውሬ ፍጡር እንደሚያፈራ ትመለከታላችሁ።
ጌታዬ ሆይ! ይህንን መርዝ ከአገሬ አጥፋው። ወገናችንን ልብ ስጠው። ኣሚን።
#share_share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
በጫት ቤተሰብ የሚያስተዳድሩስ እንዴት ይሁኑ?
~~~~~~~~~
ጫት ትውልድ ገዳይ ነው። የኢኮኖሚ ፀር ነው። ሃገር አምካኝ ነው። የጤና ጠንቅ ነው። አሁን ደግሞ ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሰበብ የመሆን እድሉ ሰፊ ስለሆነ በቸልታ ሊታይ አይገባውም። አንድ የጫት አከፋፋይ በቫይረሱ ቢያዝ እስከ ታችኛው ተጠቃሚ፣ እስከ ቀርጥ (ገራባ) ሰብሳቢው ድረስ በቀላሉ ሊሰራጭ ይችላል። በጎን በወረርሽኙ ላይ በቂ ስራ እንዲሰራ እየጠየቅን፣ በሌላ በኩል ጫት ላይ እርምጃ ሲወሰድ የምናለቃቅስ ከሆነ ቀዳዳ በርሜል ላይ ውሃ መቅዳት ነው የሚሆነው። "ጫት ቸርችሮ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ሰው እንዴት ይሁን?" የሚሉ ሰዎች አሉ። ይህንን ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች የሚዘሉት ነጥብ ግን ጫት ስጋት ነው አይደለም? "አዎ" ካሉ እና የህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ ይውደቅ ነው የምትሉት?! ለምንድነው ነው ይህኛውን ነጥብ እንደዋዛ የምናልፈው?እንዲያውም የእውነት ለህዝብና ለሃገር የሚቆረቆር አካል ቢኖር ኖሮ እስከዛሬም በቸልታ አይታይም ነበር።
Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
👉 ከኮሮና ጥቅሞች
አላህ ጥራት የተገባው ጌታ በዚህ ፍጥረተ ዓለም ላይ በሁሉም መልኩ ሸር ብቻ የሆነ ነገር አልፈጠረም በታቃራኒው ኸይር ብቻ የሆነን ነገር ግን ፈጥሯል
ላዩ ሸር ብቻ የሆነ ነገር ውስጡ ኸይር ይኖረዋል በከፊሎች ላይ ቢደበቅም
ታዲያ ከፊሎቻችሁ በኮሮና ደግሞ ምን ኸይር አለ እንደምትሉኝ አውቃለሁ ከኸይሮቹ ጥቂቶቹ
- መጠጥ ቤቶች መዘጋታቸው
- ጭፈራ ቤቶችም እንደዚሁ
- መጥቀናል ብለው ወንድ ለወንድ አልፈው ከእንሰሳ ጋር መጋባት የጀመሩ የነበሩ ወንዱ ለወንዱ አጅ ነብይ መሆኑ
- የኒቃብ ክብር በኢአማኒዮች መመስከሩ
- ኢኽቲላጥ ወንድና ሴት መቀላቀል መጥፋቱ
- ማን አለብኝ ባይ ልኩን ማወቁ
- ፈጣሪ አለ ወደሚለው ሀሳብ ቁሳዊያኖች መመለሳቸው
- አላህ ቁርአን አውዶ መልእክተኛ ልኮ የልተፈፀሙ ህጎቹ የማይታይ ሰራዊቱን ልኮ እንዲፈፀም ማድረጉ
እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ናቸው

Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አሜሪካ ለመሄድ ስንት ጉጉት የነበራቸው፣ ከአሜሪካ የመጣ/ች ወንድ/ሴት አግብቶ ለመሄድ፣ አሜሪካ ለመሄድ ዲቪ በየአመቱ የሚሞሉ ሰዎች ሰሞኑን ምን ተሰማቸው?
ምድር ሁሉ የአላህ ናት። ደስተኛ ህይወት ለመኖር ሲሰጠን አላህን ማመስገን እና እኛም ለሌሎች መስጠት፣ ስናጣ መታገስ፣ ስንሳሳት ወዲያው አላህን ምህረት መለመን።
ሀገራችን ተቀምጠን ለረጅም አመት አሜሪካ ካልሄድን እያልን በምኞት የምንሰቃይ ሰዎች ከዚህ ተግባራችን እንቆጠብ። ባለንበት ሀገር አላህ ባዘዘው መንገድ ከኖርን ስልጡኖች፣ ደስተኞች እንሆናለን። የትም ሀገር ላይ አላህን ከመፍራት የበለጠ መልካም ህይወት የለም።
Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
2025/02/06 07:47:28
Back to Top
HTML Embed Code: