Telegram Web Link
📌 #ኢፍጧርን_ማፈጠን_የተወደደ ሲሆን ከተገኘ በቴምር ካልተገኘ በዉሃ ማፍጠር #የተወደደ ነዉ፡፡
📌 #አንድፆመኛ_ሲያፈጥር
እንድህ ማለቱ ይወደዳል፦
اللهُمَّ لَكَ صُمتُ وَعَلَى رِزقِكَ أَفطَرتُ
📌 #አላሁመ_ለከ_ሱምቱ_ወዓላ
ሪዝቂከ_አፍጦርቱ (አሏህ ሆይ!ላንተ ብዬ ጾሜያለሁ #በሲሳይህም አፍጠሬያለሁ)
#ذهب_الظمأ_وابتلت_العروق_وثبت
_الأجر_إن_شاء_الله

📌 #ዘሃበ ዞመኡ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢን ሻ አሏህ

📌 #ውሃ ጥም ተወገደ የደም ስሮችም ለዘቡ በአሏህ ፍቃድም ምንዳው ጸደቀ

@Halali_tube
@Halali_tube
"""""""ረመዷን """""""""
ነብያችን (ሰ ዐ ወ) በ3 ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው ብለዋል!!!
1 "ረመዷን መቶ ራሱን ወደ ኸይር ስራ ያልመለሰ ሰው::
2 "የኔ ስም ሲነሳ ሶለዋት የማያወርድ ሰው::
3 "እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀመባቸው ሰው ናቸው ብለዋል:: ሰለዚህ ይህ ታላቅ እንግዳ ብዙ ኸይሮችን ይዞልን እየመጣ ነው አኛስ በዚህ በተባረከ ወር አጅር ለመሰብሰብ ምን ያክል ዝግጁ ነን?? ""በዚህ ተላቅ እንግዳ መምጣት ምክንያት,,,,,
1 ሾይጧን ይታሰራል
2 የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ
3 የጀነት በሮች ይከፉፈታሉ:: ይሉናል ረሱል )ሰዐወ( ::
በዘህ በረመዷን ወር:,
1 "በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት አላህ ለባሮቹ ራህመት
የሚያወርድበት ነው::
2 "በመካከለኛዎቹ 10 "ቀናት አላህ ባሮቹን የሚምርበት ነው::
3 "በመጨረሻዎቹ 10 ቀናት ደግሞ አላህ ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚያወጣበት ነው:: ይሉናል ነብይና ሙሀመድ (ሰዐወ) ያ አላህ እውነትም በዘህ ወር
ያልተጠቀመ ከአላህ እዝነት የወጣ ነወ አላህ ይጠብቀን
እና:: እናም እህት ወንድሞቸ የ11 ወር ወንጀል ተጠራርጎ
ገደል በሚገባበት በዘህ ታላቅ ወር ሁላችንም ለዒባዳ
መነሳሳት ለኸይር ስራ መሽቀዳደም ይኖርብናል በዘህ ወር አላህ ጋ ያለንን ግንኙነት ካላስተካከልን መቸም አናስተካክልም:: አላህ በዚህ ታላቅ ወር ከሚጠቀሙት ያድርገን:: አሚን
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5 ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።
እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ ተጠቃሚ ይሁኑ።
*እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል።
*ሲከፍቱት ይወድቃል።
*እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል።
*ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ ይሞክራል።
እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ።
5. እባክዎን ሸይጣንን ያሸንፉና ይህንን መልዕክት ሼር ያድርጉት መልካም እረመዳን ይሁንላችሁ

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አሰላሙ አለይኩም

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፆም እንዴት ነው ኢባዋው፣ ኢሽቁ ፣ ቂራቱ፣ የኢፍጣር ላይ ያለው ድባቡ፣ የተራዊህ ስግደቱ፣ የ ስሁሩስ ነገር ? ባጠቃላይ ኢባዳዎች እንዴት ይዝዋችሃል??? አይዞን በርቱ አላህ ፃማችን ኢባዳችንና ቂራታችን ሁሉ ይቀበለን፤

...ታድያ ወንድም እህቶቼ አላህ የፆመኛን ዱዓ ተቀባይ ነውና በዱዓ እንበርታ ቀልባችንን ከአላህ ጋር እናገናኝ ጀነተል ፊርዶውስን ደጋግመን እንለም እንዲሁም ይህ ከ አላህ ቁጣ የሆነው (ወረርሽኙም) እንዲጠፋ በዱዓ እንበርታ,,

...ከቤተሰቦቻቹ በተሰበሰባቹ ጊዜም ስለ ዲን አውሩ አንዳንድ ሸሪያዊ ብይኖች ( እግጋቶችን) ተጠያየቁ ረሱልን አውሱ ስለ አላህ ትልቅነት ፍፁም ፍጡራንን እንደማይመስል ተነጋገሩ ምን አልባት መስጂዶቻችን የተዘጉት ከቤተሰቦቻችን ጋር ሆነን ስለ ሰላት አሰጋገድ ባጠቃላይ ስለ ዲናችን እንድንማማር ይሆናልና ይሄንን ጊዜ እንጠቀምበት,,,,,,

ላስታውሳቹ ብዬ ነው

ወላሁ አእለም

#ሼር ማድረጋችንን አንርሳ


@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
♡ የቂያም ቀን 3 ስራዎች ከትልቅነታቸው የተነሳ
ሚዛን ላይ አይገቡም ...
① ሰብር
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል ...
" ታጋሾች ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው "
{ ዙመር : 10 }
☞ ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆን ወሰን አልሰጠውም

② ለሰዎች ይቅር ማለት
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል ...
" ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው
በአላህ ላይ ነው ... "
{ ሹራ : 40 }
☞ የዚህም ምንዳ ወሰን አልተሰጠውም

③ ፆም
ከአቡ ሁረይራ እንደተዘገበው
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
" አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ
ሁሉም የአደም ልጅ ስራ የርሱ ነው
ከፆም በስተቀር
ፆም የኔ ነው እኔም ነኝ ምንዳውን የምመነዳው "
{ ቡኻሪና ሙስሊም }
☞ የዚህም ምንዳ ምን ያህል እንደሆነ
ወሰን አልሰጠውም ።
የቂያም ቀን ተጣሪው የታሉ ምንዳቸው በአላህ ላይ የሆነው ሲል ይጣራል ...
⇨ ፆመኞች
⇨ ታገሾችና
⇨ ይቅር ባዮች
ለበይክ ለበይክ እያሉ ይመጣሉ ...
#የኔ_ውዶች ፁሙ ታገሱ ይቅርም በሉ
አላህ ከነሱ አድርጎን ጀነት ውስጥ ያገናኘን
ኢንሻ አላህ ።
 SHARE ⇒

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
መዲነቱል ሙነወራ ውስጥ ጀናዛ በማጠብ ሥራ ላይ የተሠማራን አንድ ግለሠብ በሬሳ አጠባ ወቅት ከገጠሙት እንግዳ ነገሮች መካከል አንዱን እንዲህ ሲል ተረከልኝ:-
《 ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሬሳ መጥቶልኝ አጥቤው ከጨረስኩ በኋላ ከተኛበት ተነስቶ ውኃ የምጠጣበትን ኮዳ እንድሰጠው አመላከተኝ። እኔም በድንጋጤ ተሸብሬ እየተንቀጠቀጥኩ የውኃውን ኮዳ አቀበልኩት ። ውኃን ጠጥቶ ከጨረሰ በኋላ ወደመተኛው ተመልሶ ተጋደመ ። እኔም ከመሸበሬ የተነሳ ከመቅጽበት አምቡላንስ ባፋጣኝ እንዲመጣልኝ አዘዝኩ ። የአምቡላንስ ሠራተኞችም መጥተው የተሸፈነበትን ከፈን በመግለጥ በሕይወት መኖር አለመኖሩን አረጋገጡ ሩሑ ወጥታለች። እኔም የአላህ ነገር ደንቆኝ ይህ ሰው ከዚህች ዓለም ሪዝቁ ያቺ የጠጣት ውኃ ቀርታው ነበር ። እርሷንም ጠጥቶ ይህችን ዓለም ተሰናበታት ። የሰው ልጅ ሪዝቁን ሳይጨርስ ከዚህች ዓለም እንደማይወጣ በዚህ ግለሠብ አረጋገጥኩኝ ።
ሪዝቅህንም ሆነ ሪዝቅሽን ሳትጨርሺ ዱንያን ለቀህም ሆነ ለቀሽ አትወጪምና በሰው ሀቅ ላይ አላህን መፍራትን አትዘንጋ.

Share ⇒

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
በረመዷን ወር ውስጥ የሸይጧኖች መታሰርና አንዳንድ ኃጢያቶች መሰራትን በተመለከተ።
.................
🔻 ለታላቁ ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሓዲል ዋዲዒ (ረሂመሁላህ) የሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው:–

ጥያቄ:– ጂኒዎች በረመዷን ወር የሚታሰሩ ከሆነ ለምንድነው ሰዎች ርስበርሳቸው በረመዷን ወር ውስጥ ድንበር ሲተላለፉ የሚታዩት? ወይስ ጂኒዎች ሰዎች እስኪያፈጥሩ ታስረው ሲያፈጥሩ ይፈታሉ?

መልስ:– ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሶሂህ ሀዲስ:– "ረመዷን በገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሸይጧኖች ይታሰራሉ።" ብለዋል። በሶሂህ ኢብኑ ኹዘይማ "አመፀኛ ሸይጧኖች ይታሰራሉ።" የሚል ዘገባ አለ።

ይህ ማለት ትላልቅ አላህ ላይ አመፀኛ የሆኖ ሸይጧኖች ይታሰራሉ ማለት ነው።

በመሆኑም ከሸይጧን በሰዎች መካከል ፈሳድ የሚያሰራጩ ጥላቻንና መጠላላትን የሚያሰራጩ የሉም ማለት አይደለም።

ከዚህ በተጨማሪም የነፍሲያ ስሜት አለ፣ አንዳንድ ነፍሶች ሸረኛና እንደ ሸይጧን ወደ ፊትና የምትጣራ ናት።

በተለይ በተለይ የጫት ባለቤቶች (ጫት ቃሚዎች)፣ ወደ ዐስር ጊዜ ሲቃረብ መሰዳደቡ፣ መተቻቸቱ… እነሱ ጋር ነው። ዋነው ነገር ጫት ቃሚዎችን ተጠንቀቁ ራቁ፣ እነሱ ከዐስር በኋላ ልባቸው ይጣበባል። [አስኢለት አል ኢዛዓት ቢል ሀዲድ፣ ከሚለው ካሴታቸው፣ የተወሰደ]

የሌሎችም ወንጀሎች (ኃጢያቶች) ውጤት ነፍሲያና ሳይታሰሩ የቀሩት ሸይጧኖች ውጤት ነውና በረመዷን ወርም ነፍሲያን እና ያልታሰሩ ሸይጧኖችን እየታገልን ዒባዳችን ላይ መበርታት ይጠበቅብናል!!።


#share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
@Halali_tube
ቁርአን ጁዝ 9 በአቡበክር አል ሻጥሪ
www.tg-me.com/Mahdi_Quran_Recitation
🌙ቁርአን ጁዝ ዘጠኝ (9)🌙

📚አል አእራፍ 88_ አል አንፋል 40🌙

🌙ቃሪእ:- አቡበክር አል ሻጥሪ 🌙

➣የማይጠገብ ፣ የማያቋርጥ !

አብረን እናክትም እንደጋግመው !!!

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
╔══════ ❁✿❁ ══════╗
@HALALI_TUBE
╚══════ ❁✿❁ ══════╝
#ቁርአን እቀራለሁ ብለህ ትወስንና
ስልክ ተደውሎልህ ትተወዋለህ
- ሰላት ለመስገድ ትፈልግና
የምትላላካቸው ሚሴጆች ይዙሃል
- አንድ ነገር ለማንበብ ፈልገህ
አንዱ ወንድምህ በሆነ ምክኒያት ያናግርሃል
- ጥሩ ስራ ለመስራት ፈልገህ
የሆነ ያን ስራ እንዳትሰራ የሚያደርግህ
ነገር ይመጣብሃል‥
๏ ታግለህ ታግሰህ ፀንተህ እንቅፋቶቹን
ካለፍካቸው ‥ ቀጥተኛውን መንገድ
ትመራለህ ‥ አላህም ካንተ ጋር ይሆናል ።
 
 
( وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ)
" እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን ፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው ፡፡"
[ዐንከቡት 69]
Share

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
📌 #አንድ_ሰው ማታ ከ ነየተ ለሊት ተነስቶ ሱህር ላይ ባይነይትም
.... ሱሁር ባይበላም ችግር የለውም ፆሙም ይበቃለታል _

= እና ሱሁር ላይ ውሃም ቢሆን እንኳን ተነስቶ መቅመስ የተውደደ ነው 🌙

📌 #ሱሁር_ሰውችን ቀስቅሶ ያበላ መንዳ { አጅር } አለው

📌 #እንድ_ሴት_ሀይድ ላይ እያለች መግብ በብዛት ብትበላ ሀራም አይደለም ።

❗️#አንድ_ሴት_ከ_ወር_አበባ ነፀው ብላ ማታ ላይ ታጥባ 2⃣ ቀን ከ ፆመች ቡሃላ ተመልሶ ቢመጣባት
#የፆመቹ ፆም ተቀባይነት የለውም መክኛቱም የመጀመሪያው የወር አበባ ሙሉ ለሙሉ አልጠፍም ማለት ነው
....................

📌 እንድ ሰው ፆመኛ ሁኖ ጧት
#ጥርሱን_የፋቀ ድዱ ቢደማ ፆሙ አይጠፍም ደሙን ካልዋጠው እንጂ .........

💯 #ያለስሜት_እና_ያለፍላጎት ያለምንም ድርጊት የ ዘር ፈሳሽ ያውጣ ሰው ፆሙ አይበላሽም
SHARE YOUR FRIENDS
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ረመዳን ቀን 15
Sadat
ረመዳን ቀን 15
ድግምት እና ጥንቆላ
ሁለት ዱአዎች

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አሏሁመ ተቀበል ሢያመና
አሏሁመ ተቀበል ዱአና
አሏሁመ ተቀበል ሣላተና
አሏሁመ ተቀበል ሩኩአና
አሏሁመ ተቀበል ሡጁደና
አሏሁመ አህዲ ቀልበና
አሏሁመ አግፊር ዙኑበና
አሏሁመ አሪዚቅና እርዚቀን ከሢራ
አሏሁመ አግፊሪለና
አሏሁመ እሂዲና
አሏሁመ ወረህመና
አሏሁመ ወአፊና
አሏሁመ ወርዙቀና
አሏሁመ ወረፋእና
ቢረህመትክ ያርህማርሂሚን አሚን !!


@HALALI_TUBE
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
ነብዩ ሙሃመድ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ … ☞‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ
ሲጣራ ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ ከሪም!’... አሉ።

ዓእራብዩም አቅጣጫ በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው …’ያ ከሪም!’… አሉ።

ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:- “አንተ ባለግርማ እና
በሻሻ ፊት ሆይ!... ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?...
በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:-
☞ “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ!
ነብይህን አታውቀውም ማለት ነው?” አሉት

ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው።



“ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት

ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው ግን አላውቅም፣
ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ! አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል መለሰላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ! የዱንያው ነብይህ እና
የአሄራ አማላጅህ እኔ መሆኔን እወቅ!” አሉት።

ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት መሳም ያዘ ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ህዝቦች
ንጉሶቻቸውን እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ) ኩራተኛ
እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤ ይልቁንም አብሳሪ እና
አስጠንቃቂ አድርጎ በእውነት ልኮኛል።” አሉት።

በዚህን ጊዜ ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ ሆይ አላህ
(ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል! በክብር እና ልቅናም ከሌሎች
አስበልጦሀል፤ ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣ በልምጩ ይሁን
በቅሉ እንደሚተሳሰበው ንገረው”… አላቸው።

ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ
ይተሳሰበኛል ማለት ነው?” ብሎ ጠየቃቸው

“አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት

“እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ
ከሆነ እኔም እተሳሰበዋለሁ!” አለ።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ጌታህን በምን
ትተሳሰበዋለህ?” አሉት።

“ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ እተሳሰበዋለሁ፣
በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣
በስስታምነቴ ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”… አለ።



ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ አለቀሱ።

ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:-
☞ “ሙሐመድ ሆይ! አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን
ተስቢህ ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሀል። ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን ንገረው! እኛም
አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው።

‘አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመድ ወ አላ አሊ ሙሐመድ’ …ጌታዬ

ሼር ማድረጎን አይዘንጉ
አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል ብለዋልና ረሱሌ ሰ.ዐ.ወ

⬇️⬇️

@HALAI_TUBE
@HALAI_TUBE
as wr wb ለመላው ሙስሊም የነብያችንን መስጅድ ጠባቂ የሆኑት ሽክ አህመድ ናቸው ይህንን ደብዳቤ የፃፋት እና 1 ቀን ጁምአ ቀን ቁርአን ቀርቸ ተኛሁ በህልሜ ነብያችን መጡና እድህ አሉኘ በዛሬው እለት 6000 ሠወች ሙተዋል ግን አዱም ጀነት አልገባም እኒህ ሰወች የባላቸውን ፤የሚስታቸወን ሀቅ ያልጠበቁ ዘካ ያልሰጡ ሀብታሞች ህጅን በአግባቡ ያልሀጀጁ ሶላትን በወቅቱ የማይሰግዱ ናቸው አሉ ውሸቴን ከሆነ የነብያችንን ሽፈአ አላግኝ ነው ያሉት ሽህ አህመድ ይህንን ለመላው ሙስሊም ሽር አርጉ ወላሂ አይቶ ዝም ያለ እርዛኢል ይመጣና ይወስደዋል ነው ያሉት ሞት ማለት ነው እሳቸው ደግሞ ሽር ያረገ የነብያችንን ሸፈአ ያገኛል አላህ ጀዛውን ይከፍለዋል ነው ያሉት ቢየንስ ለ20 ሰው ወድሞቸ እህቶቸ አደራ as wr wb

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
Audio
ረመዷን 20 ጁዝ (20)

Al'Naml 56 – Al'Ankabut 45
Sheikh Maher 43 Min

ቀናቶቹ እየነጎዱ ነው እንጠቀምባቸው
መልካም ግዜ ከንግግሮች ሁሉ በላጭ
ከሆነው የአላህ ቃል (ቁርኣን) ጋር💕


ⒿⓄⒾⓃ ⇊
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
✿┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
عيد مبارك🍥
ዒድ ሙባረክ!
عيد مبارك

እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ውድ ቤተሰቦቻችን በዓሉን ስናከብር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምንወስዳቸውን አስፈላጊ #የጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰድን እንዲሆን
2025/02/05 20:30:58
Back to Top
HTML Embed Code: