Forwarded from  አትሮንሰ ተዋህዶ ( Atronise Tewahdo )  (𓃬 𝔏𝔢𝔬 𓃬)
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ
#ይቀላቀሉ

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
"ማንነትህን ማወቅ"

ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።
ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10

(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ ይመክራል፦"ደስታና ሰላምን የሚነጥቁ ሦስት የሰይጣን ወጥመዶች አሉ፦
➛ ስላለፈው መጸጸት፣
➛ ስለሚመጣው መጨነቅ እና
➛ ስለ ዛሬው አለማመስገን ናቸው"

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
#የፍቅሩ_ምክንያት

እግዚአብሔር ሰውን ያፈቅራል ስንባል ሰምተናል። ልክ ነው በተግባርም አይተነዋል። ይሁን እንጂ በምን ምክንያት ነው ያፈቀረን? ምን ምክንያት ሆኖ ነው የወደደን? እስኪ ወንድሜ ለተወሰነ ሰከንድ ይህን ጥያቄ እራስህን ጠይቅ አንቺም እህቴ እራስሽን ጠይቂ። ...... ለምን ወደድከኝ...በምን ምክንያት ነው ያፈቀርከኝ

እናንተ በእግዚአብሔር ስለመወደዳችሁ ምክንያት ሊሆን የሚችል ከእናንተ ምን በጎ ነገር አገኛችሁ። እግዚአብሔርማ ከዚህ ነገሬ የተነሳ ሊወደኝ ይገባል የምትሉት አንዳች ምክንያት አገኛችሁን? አዎ አገኝቻለሁ ካላችሁ ዋሳችሁ።

እግዚአብሔር እኛን የወደደን በእኛ ዘንድ ለእርሱ ባህሪ ተስማሚ የሆነ ነገር ተገኝቶብን ሳይሆን እንዲሁ ነው። የወደደን እንዲሁ ነው።  “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን #እንዲሁ ወዶአልና።”(ዮሐንስ 3፥16)

እግዚአብሔር እኔን በመውደዱ ውስጥ እኔ ያዋጣሁት ነገር የለም ማለት እጅግ አስተዋይነት ነው። ለእርሱ ፍቅር እኛ የምናዋጣው ነገር ቢኖር ኖሮ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ መዋጮ ልክ ከፍ እና ዝቅ ይል ነበር። እናም እግዚአብሔር ከራሱ በሆነ መውደድ የሚወደን አምላካችን ነው።

አንዳንዴ ስራዎቻችን መጥፎ ሲሆኑ እግዚአብሔር የጠላን ይመስለናል። ወይም ድርጊታችን ልክ ሳይሆን ሲቀር የእግዚአብሔር ፍቅሩ የሚቀዘቅዝ ይመስለናል። አልያም በጎ ስንሰራ፣ ሰው ስንረዳ፣ ሰው ስናገዝ፣ እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ስናደርግ፣ መንፈሳዊ ህይወታችን ያመረ ሲሆን የእግዚአብሔርን የፍቅሩ ግለት የሚጨመርን ይመስለናል።

የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ምክንያት ስላልመጣ በእኛ ምከንያት አይጸናም የሚጸናው እርሱ እግዚአብሔር እራሱ ጽኑ ስለሆነ ነው። አትሳሳቱ እግዚአብሔር የሚወደኝ እንዲህ ሳደርግ ነው አትበሉ። እግዚአብሔር እኛ ጠላቶቹ ሆነን ሳለ የፍቅሩን ሃያልነት ገለጠልን እንጂ ወዳጁ ስለነበርን አይደለም። “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”( ሮሜ 5፥8)

የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ሰዎች ፍቅር መልክ እና ሁኔታ እያየ አይጎርፍም ይልቁንም ጠላት የሆነውን ያቀርባል እንጂ። እግዚአብሔር በደለኞቹን እኛን ማዳኑ የመውደዱ ማብራሪያ ነው ይህም ከእኛ በሆነ በጎ ምግባር ላይ የተመሰረተ አይደለም። “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9)

ፍቅር ምክነያት ይፈልጋል የምንለው ፍቅሩ ሰዋዊ ሲሆን ነው ምከንያቱም የሰው ልጅ ስለቀረብነው የሚያፈቅር ስለራቅነው ደግሞ የሚረሳ ወረተኛ ስለሆነ ነው።  እግዚአብሔራዊ ፍቅር ግን ከእራሱ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ የፍቅር ውሃ ነውና ሁሉን ያረሰርሳል። የእግዚአብሔር ፍቅር ምክንያት አልባነት ከተሰወረበት ሰው ይልቅ አላዋቂ ሰው አይኖርም።

ስናለማም ስናጠፋም
ፍቅሩ ግን ከቶ አይጠፋም
ስናበጅም ሳናበጅም
ፍቅሩ ጭራሽ አያረጀም
ስናደርግም ሳናደርግም
ፍቅሩ ግን አይዋዥቅም
ሰንቀርብም ስንርቅም
ፍቅሩ ግን ፈቅ አይልም
ስንጨልምም ስንበራ
የእርሱ ፍቅር ያው ጠንካራ
ስንሰጥም ሳንሰጥም
የእርሱ ፍቅር ሰው አይመርጥም
ስንሄድም ስንመጣም
ፍቅሩ ላይ ለውጥ አይመጣም
ስንስቅም ስንከፋም
ድርጊታችን የሱን ፍቅር አያፋፋም
በሁኔታችን ከፍ አይልም
ወይም ደግሞ ዝቅ አይልም
ሁሌም ጽኑ የእርሱ ፍቅር
ለዘላለም ለዘወትር

ያለ ምክንያት ስለሚፈሰው ፍቅርህ አማኑኤል ሆይ ተመስገን።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሚያዝያ 21  2015 ዓ.ም ተጻፈ

♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
[ የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሕዝቅኤል ፦ "ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በምሥራቅ አየሁ፡፡ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም፡፡" አለ፡፡ [ሕዝ.፵፬፥፩] ይህ የተዘጋ በር የድንግልናዋ ዜና ነው፡፡ " እግዚአብሔርም ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል። " [ሕዝ.፵፬፥፩]

ሰሎሞንም ፦ "የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ [ ያንቺ መንገዶች ናቸው ] አለ፡፡ " እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት ፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።" [ መኃ.፬፥፲፪ ]

በገነት አካባቢ ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ፍሬ አይደለምን ? የሚጣፍጠው ፍሬ ምንድን ነው ? የእናቱ የድንግል ማርያም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን ? የተዘጋች ገነት ማለትስ በድንግልና ቁልፍ በተዘጋች በአንቀጸ ሥጋዋ ይተረጎማል፡፡ ዳግመኛ ከጉድጓድ ከሚጣፍጥ ውሃ በስተቀር ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ውሃ ምንድን ነው ? በወንጌል ፦ " ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። " [ዮሐ.፯፥፴፯] ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የታተመች ጉድጓድ የተባለው የንጽሕይት እናቱ የድንግልናዋ ኃይል ነው፡፡ ሁሉም ነቢያት ስለ ሥጋዋ በር ፦ " የተዘጋች ፥ በድንግልና የታተመች" ብለዋታልና፡፡

ለቀደሳትና ላነጻት [ በንጽሕና ለጠበቃት ] ለእግዚአብሔር ለዘላለም ምስጋና ይሁን፡፡ ❞

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

†                       †                         †

@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
"እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
"ወደ አንተ እመጣለሁ"

በቅዱሳን ኹሉ አንደበት ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ከሰማያት እንደወረደ (ማለት ሰው እንደሆነ) እንዲሁ የማዳኑን ሥራ ፈጽሞ (ፍጹም አድርጎ) ወደ ሰማያት በምስጋና ዐረገ፡፡ ሰው ሲሆን ረቂቁ ገዝፎ፤ የማይታየው ታይቶ ነው፡፡ ሲያርግ ነሥቶ የተዋሐደውን ሥጋ ሳይለቅ ነው፡፡ መድኅን ክርስቶስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ተዋሐደውን ሥጋ በምድር ላይ አልተወውም፡፡ አስቀድሞ በወንጌለ ዮሐንስ “ወደ አንተ እመጣለሁ” (ዮሐ 17፡ 11) ብሎ የተናገረው በዕርገቱ እውን ሆነ፡፡ ዳግመኛም “ወደ አንተ እመጣለሁ” ብሎ የተናገረው፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምትሠዋው መሥዋዕት (እርሱም ክርስቶስ ነው) ወደ አንተ እቀርባለሁ ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ዳግመኛም በዕርገቱ ምክንያት እኛንም ይዞን ዐረገ፤ ይኸውም ባሕርያችንን (ሰውነትን) ነው፡፡ ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን ጸሎት ካህኑ “ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ” ሲለን፤ “ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን” ብለን እንመሰክራለን (መጽሐፈ ምሥጢር፤ የዕርገት ምንባብ)፡፡ ይህ የሆነው በክርስቶስ በዕርገቱ ነው፡፡ የእርሱ ዕርገት የምዕመናንን (ቅዱሳንን) ዕርገት የሚያሳውቅ፡ የሚያረጋግጥ ሆነ፡፡ ከሰማያት በአምላክነቱ ኀይል በረቂቅ ምሥጢር ወረደ (ሰው ሆነ)፤ ከምድር በአምላክነቱ ኀይል ያዳናቸውን ምርኮ ይዞ ወደ አባቱ ዐረገ፡፡ ምስጋናው ገነት የሆነችለት ቅዱስ ዳዊት “ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ፡ ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው፤ ወደ ሰማይ ዐረግኽ፡ ለሰው ልጆችም ጸጋን (መንፈስ ቅዱስን) ሰጠህ” (መዝ 67: 18) ብሎ አስቀድሞ ተናገረ፡፡ በክርስቶስ መስቀል ድኅነትን የተቀበሉ፤ መቀበላቸውን እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ እንዲያጸኑ የሚያደርጋቸው መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ዕርገት የወረደ ጸጋ ነው፡፡ ክርስቶስ ጸጋ ሆኖ እንደተሰጠን (ለሕማም እንደተሰጠልን)፤ እንዲሁ መንፈስ ቅዱስንም ለሃይማኖት መጽናት፤ ለምግባር መቃናት፡ ለትሩፋት ሥምረት ለቤተ ክርስቲያን (ለምዕመን) ጸጋ ሆኖ ተሰጠ፡፡ በእውነት ከክርስቶስ ያልሆነ፤ ከመንፈስ ቅዱስ ዕድል ፈንታ የለውም፡፡ ከክርስቶስ ሃይማኖት፤ ከእርሱ ጋር ሕማምና መከራን ከመቀበል ያልሆነ፤ ከትንሳኤውና ከዕርገቱ አይሆንም፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ሰላምና ደስታ ጋርም ዕድል አይኖረውም፡፡ መንግሥተ ሰማያት የመንፈስ ቅዱስ ሰላምና ደስታ ናትና፡፡ የክርስትና ምግባር ሁሉ መደምደሚያው እውነተኛውን የልብ ሰላምና ደስታ ማግኘት ነውና፡፡ ጸጋ ሁሉ ፍጹም ሆና ለቤተ ክርስቲያን እንድትሰጥ መድኅን ክርስቶስ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ ዘወትር በጸሎት እና በንስሐ ወደ ሰማይ መውጣትን የተለማመደ፤ በእውነት ወደ እግዚአብሔር ማረግ ይሰጠዋል፡፡ በሃይማኖትና በምግባር በመታመኑ በጸጋ ያደረበት ክርስቶስ ወደ ሰማያዊ አባቱ ያሳርገዋል፤ በዚያም በብዙ ማደሪያዎች ውስጥ ያሳድረዋል፡፡ በአምላካዊ ሥልጣኑ ሰውነታችንን ከታችኛይቱ ሲዖል ያድናት፤ በምሕረቱም ወደ አባቱ መንግሥት ያሳርጋት፡፡

በመልካሙ ዋሉ !

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
+ የተሠጠህን ቁጠር +

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ።

ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።

@Finote_tsidk
@Finote_tsidk
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም

እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

╔═══|◉❖•❀•❖◉|═══╗
      @Finote_tsidk
╚═══|◉❖•❀•❖◉|═══╝
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ነገ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም
(JUNE 23/2024 G.C) ይገባል፡፡

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
✝️በዓለ ጰራቅሊጦስ✝️

ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣
ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም *እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤* /ሉቃ. ፳፬፥፵፱/ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡
በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ /ሐዋ.፪፥፩-፬/፡፡ ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሰን።

♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
ጰራቅሊጦስ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ነው:: በትንሣኤው ተፀንሳ እስከ ዕርገቱ ድረስ ለዐርባ ቀናት ተሥዕሎተ መልክእ (Organ formation) የተፈጸመላት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የተወለደችበት ቀን ነው:: እግዚአብሔር በባቢሎን ሜዳ የበተነውን ቋንቋ የሰበሰበበትና እንዱ የሌላውን እንዳይሰማው እንደባልቀው ያሉ ሥሉስ ቅዱስ አንዱ የሌላውን እንዲሰማ ያደረጉበት ዕለት ዛሬ ነው:: ሰው ወደ ፈጣሪ ግንብ ሰርቶ በትዕቢት ለመውጣት ሲሞክር የወረደው መቅሠፍት ዛሬ በትሕትና ፈጣሪን ሲጠባበቁ ለነበሩ ሐዋርያት ፈጣሪ ራሱ ያለ ግንብ ወርዶ ራሱን የገለጠበት ዕለት ነው::

ዛሬ እስራኤል ከግብፅ በወጡ በሃምሳኛው ቀን በሲናን ተራራ የወረደው እሳትና በጽላት ላይ የተጻፈው ሕግ የተሠጠበት ቀን ነው:: ፋሲካችን ክርስቶስ በታረደ በሃምሳኛው ቀን በሐዲስ ኪዳንዋ ደብረ ሲና በጽርሐ ጽዮን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በሐዋርያት በልባቸው ጽላት ቃሉን የጻፈበት ቀን ነው:: በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በርግብ አምሳል በትሕትና የወረደው መንፈስ ቅዱስ ዛሬ በእሳትና በነፋስ አምሳል ወደ ሐዋርያቱ የወረደው ዛሬ ነው:: ርግብ ሆኖ የወረደው ሊመሰክርለት እንጂ ኃይል ሊሠጠው ስላልነበረ ነው:: ዛሬ ግን ለሐዋርያቱ ኃይል ሊሠጣቸው ፈልጎ በእሳትና በነፋስ ኃይሉን ገለጠ::

መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ በዚያ መገኘት ከፈለጋችሁ በቅዳሴው መካከል ተገኙ:: ካህኑን "ይህች ቀን ምን የምታስፈራ ናት? ይህች ቀን ምን የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከመልዕልተ ሰማያት የሚወርድባት?" ሲል ታገኙታላችሁ:: ኢሳይያስ ያየውን ራእይ ማየት ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴ ገስግሱ:: ሱራፊ በጉጠት ፍሕም ይዞ ኃጢአታችሁን የሚተኩስበትን ደሙን ለመቀበል ከፈለጋችሁ ወደ ቅዳሴው ገስግሱ:: "ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ" እያላችሁ የምታዜሙበት ዕለታዊው ጰራቅሊጦስ ቅዳሴው ላይ ተገኙ:: በአዲስ ቋንቋ ትናገራላችሁ:: የእናንተ ቋንቋ ሳይቀየር የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ሰምቶ ይረዳችሁዋል::

ለሐዋርያት የተሠጠኸውን ሠጥተኸን ከሐዋርያት ያገኘኸውን ያላገኘህብን ሆይ ቅዱስ መንፈስህ ከእኛ አትውሰድብን:: የማዳንህን ደስታ ሥጠን:: በእሺታም መንፈስ ደግፈን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 16 2016 ዓ.ም.

#share

╔═══|◉❖•❀•❖◉|═══╗
      @Finote_tsidk
╚═══|◉❖•❀•❖◉|═══╝
2024/06/26 03:07:42
Back to Top
HTML Embed Code: