Telegram Web Link
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻
🌺         ባህረ ሐሳብ
🌻          የ፳ ፲ ፯
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተጸነሰበት ጊዜ ያለው ዓመት ዓመተ ኩነኔ ይባላል ።ክርስቶስ ከተፀነሰበት ጀምሮ አሁን እሰከ አለንበት ያለው ዘመን ደግሞ ዓመተ ምሕረት ይባላል
መላው ዓመተ ዓለም ይባላል።
ዓመተ ኩነኔ
5550 ዓመት  ነው/
ዓመተ ምሕረት /
2017 ዓመት ነው/
5550+2017=7517 ይሆናል
ይህ ማለት ዓለም ከተፈጠረ እስካሁን ያለው እድሜ 7517 ዓመት ነው ማለት ነው።

ዓመተ ወንጌላውያን እና ዕለቱን ለማወቅ 👉👉👉
ይህንን 7517ን ለ4ቱ ወንጌላውያን ትክክል መድቦ 1 ቢተርፍ ማቴዎስ
2 ቢተርፍ  ማርቆስ
3 ቢተርፍ ሉቃስ
ትክክል ቢሆን ዮሐንስ ይሆናል ማለት ነው፡
አሁን ያለንበትን ወንጌላዊው ማን እንደሆነ ለማወቅ
ይሄን 7517ን ለ4ቱ ወንጌላውያን ስናካፍለው 1879 ደርሷቸው ትርፉ (ቀሪው) 1ይሆናል
።ስለዚህም ቀሪው 1
ስለሆነ ማቴዎስ ነው:ማለት ነው
            ዕለቱ (ቀኑ) መቼ እንደሆነ ለማወቅ
1879ን ከዓመተ ዓለሙ ጋር ደምሮ
በሰባት መግደፍ (ለሰባት ማካፈል) ነው
ይህኸውም፡1879+7517=9396 ይሆናል
ይሄን በሰባት ስንገድፈው ወይም ለሰባት ስናካፍለው
1342 ደርሶ 2 ይቀራል (ይተርፋል )
ትርፉ1 ከሆነ ማክሰኞ
2 ከሆነ ረቡዕ
3 ከሆነ ሐሙስ
4 ከሆነ ዐርብ
5 ከሆነ ቅዳሜ
6 ከሆነ እሑድ
ያለምንም ትርፍ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል። ማለት ነው
ስለዚህ አሁን ቀሪው (ትርፉ) 2 ስለሆነ  2 ከተረፈ ረቡዕ ይውላል ብለናልና መስከረም 1 ቀን ረቡዕ ይውላል ማለት ነው።

የ2017 መጥቅዕ እና አበቅቴን ለማግኘት??
ዓመተ ዓለምን ማለትም 7517ን ለ14 ዐቢይ ቀመር 532፣ቢሰጡ  69 ይቀራል 69 ደግሞ ለንኡስ ቀመር   አሥራ ዘጠኝ አሥራ ቢሰጡ  ቀሪ 12 ይሆናል። አሐደ አእትት ለዘመን ይላል አንዱን አትቶ
12-1=11 ይሆናል፣11ወንበር ወጣ ይሏል በዘመነ ማቴዎስ አበቅቴውን ለማግኘት ይህንን ወንበር በጥንተ አበቅቴ ስናባዛው  ጥንተ አበቅቴ መጀመሪያ ድሜጥሮስ ያወጣበት አበቅቴ 11ስለሆነ በጥንተ አበቅቴው ስናበዘው
ማለትም 11×11=121 ይሆናል። በ4 ሠላሳ ስንገድፈው 4 ጊዜ ደርሶ 1 ይተርፋል።  የ2017 ዓመት  አበቅቴ 1 ወጣ ይባላል
መጥቅዕን ለማግኘት ?
11ን በጥንተ መጥቅዑን ማባዛት ነው
ጥንተ መጥቅዕ 19 ነው 11×በ19=209 ይሆናል ስድስት ጊዜ ሠላሳ ስንቀንስ 29 ይቀራል
ስለዚህ የ 2017 ዓ.ም መጥቅዕ 29 ነው ሆነ ማለት ነው 1+29 =30 መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ፦ አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ ከሠላሳ አይበልጡም ከሠላሳ አያንሡም ፦
መጥቅዕ ወአበቅቴ እመ ይበዝሁ ኢየዐርጉ እምሠላሳ ወኢይወርዱ እምሠላሳ ወትረ ይከውኑ ሠላሳ  እንዲል፤
መጥቅዕ 14ን አይነካም ከ14 በላይ ከዋለ ማለትም ከ15 አንስቶ ማለት ነው  በመስከረም ይውላል። ከ14 በታች ከዋለ በጥቅምት ይውላል ማለት ነው
ስለዚህ መስከረም 29 የሚውልበት ቀን ረቡዕ
ነው።
ጾመ ነነዌ
መባጃ ሐመሩ ከ30 በታች ከሆነ በጥር ይገባል። ከ30 በላይ ከሆነ ግን ገድፎ በየካቲት ይውላል።
የእለታት ተውሳክም እንደሚከተለው ነው።
የቅዳሜ ተውሳክ 8
የእሑድ ተውሳክ 7
የሰኞ ተውሳክ 6
የማክሰኞ ተውሳክ 5
የረቡዕ ተውሳክ 4
የሐሙስ ተውሳክ 3
የአርብ ተውሳክ 2

የረቡዕ ዕለት ተውሳክ 4 ነው።
    መባጃ ሐመር+መጥቅዕ የዋለበት ዕለት ተውሳክ ተደምሮ ከሠላሳ በላይ ከሆነ ሠላሳውን ገድፎ ትርፉን መያዝ ነው
     መባጃ ሐመር 29ነው =29+4=33÷30 -  ቀሪ 3  ይሆናል
   የ2017 መባጃ ሐመር 3 ነው ማለት ነው
. አጽዋማትና በዓላት የሚውሉበት ቀንን ለማወቅ መባጃ ሐመርን ከየበዓላቱና አጽዋማቱ ተውሳክ እየጨመሩ  ከሠላሳ በላይ ሲሆን በሠላሳ እየገደፉ
ማውጣት ነው
ጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም በመባጃ ሐመሩ
ነው የምትውለው
ስለዚህ መባጃ ሐመር 3 ስለሆነ
    ጾመ ነነዌ የካቲት 3
   የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ነው 14+3 =17ይሆናል  የካቲት 17 ዐቢይ ጾም
  .የደብረ ዘይት ተውሳክ  11 ነው 11+3= 14 ይሆናል መጋቢት 14 ዐቢይ ጾም
የሆሳዕና ተውሳክ 2 ነው 2+3= 5 ሚያዝያ 5 ሆሳዕና
  የስቅለት ተውሳክ 7ነው  7+3= 10 ሚያዝያ 10 ስቅለት
  የትንሣኤ ተውሳክ 9 ነው 9+3= 12 ሚያዝያ 12 ትንሣኤ
   የርክበ ካህናት ተውሳክ 3 ነው 3+3 6 ግንቦት 6 ርክበ ካህናት
  የዕርገት ተውሳክ 18ነው  18+3= 21 ግንቦት 21ዕርገት
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው 28+3 31 ሠላሳውን ሳድፉት አንድ ይቀራል ሠኔ 1 ጰራቅሊጦስ
   የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው 29+3 32 ሠላሳውን ሲገድፉት 2 ይቀራል  ሠኔ 2 ጾመ ሐዋርያት
  የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው 1+3= 4 ሠኔ 4 ጾመ ድኅነት ነው
ሌሊቱ ስንት እንዳደረ እና አሥርቆቱን ለማወቅ ደግሞ፣
ቀኑን +ሕፀፁን+ አበቅቴውን ደምሮ ሠላሳ ከሆነ ሠላሳውን መያዝ ከተረፈ ሠላሳውን ገድፎ ትርፉን መያዝ ነው
ለምሳሌ የመስከረም አንድን ሌሊት ስናሳድር
    ሠርቀ መዓልት 1+
    ሕፀፅ 1+ አበቅቴ 1+
             ሠርቀ ሌሊት  3 ማለት ነው
ሠርቀ ወርኁን ደግሞ ለማወቅ ማለትም በጨረቃ ስንት ሌሊት እንዳደረ ለማወቅ
ካደረው ሌሊት ላይ 4ን መጨመር ነው 3+4= 7
    ሠርቀ ወርኅ = 7
    ጥንተ ዖን  ማለት  ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት የተፈጠሩበት ዕለት ማለት ነው  ከሮብ ጀምሮ  መቂ
ቁጠር ነው
ጥንተ ዖን 1
    ጥንተ ቀመር ማለት ማክሰኞ ነው ከማክሰኞ ጀምሮ መቁጠር ነው  2
    ጥንተ ዕለት ማለት እሁድ ነው ከእሁድ ጀምሮ መቁጠር ነው 4
ስለዚህ እግዚአብሔርን ስናመሰግን እንዲህ ማለት አለብን  ሃሌ ሉያ በዘንዜከር ሐሳባተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሳበ ነቢያት ወሐዋርያት ሐሳበ ጻድቃን ወሰማዕት ሐሳበ ደናግል ወመነኮሳት ሐሳበ ኄራን መላእክት እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ  ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ማርቆስ ፍሥሓ ዜናዊ። በ፸፻ወ፭፻፲፯ ኮነ ዓመተ ዓለም። በ፶፻ወ፭፻ ኮነ ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ። በ፳፻፲፯ ኮነ ዓመተ ምሕረት። ዮም ሠረቀ ለነ ወርኀ መስከረም ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኀ ጥቅምት በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን። አሚሩ ሠርቀ መዓልት። ሠሉሱ ሠርቀ ሌሊት።  ሰቡዑ ሠርቀ ወርኅ። አሚሩ ጥንተ ዖን፣ ረቡዑ ጥንተ ዕለት፣ ሰኑዩ ጥንተ ቀመር። ዝ ጸሎት ወዝ አስተብቁዖት ይዕርግ በእንተ ስመ አብ ወበእንተ ተዝካረ ወልዱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ስሙ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ወበእንተ ስማ ለእግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ አሜን ካልን በኋላ ስብሐት ማለት ነው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ይቆየን
የዛሬ ዐመት በሰላም ያድርሰን

በመ/ር አስተርአየ ጽጌ

🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
መስከረም ፪
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።

ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

ከሰማዕቱ፤ ከጻድቁ፤ ከካህኑ፤ ከነቢዩ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ረድኤትና በረከት ይክፈለን: አሜን!

©ስንክሳር


🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"
1ጴጥ. 4÷3


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ይረባኛል፣ ይጠቅመኛል ብለህ የመናፍ**ቃንን መጽሐፍ አትመልከት፡፡ ከመመልከትህ የተነሳ ጸጋ ክብር ታጣለህ፡፡ አንድም የነቢያትን የሐዋርያትን መጽሐፍ በመመልከት ከሚገኘው እውቀት ተለይተህ ትጎዳለህ፡፡”

ማር ይስሐቅ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

#ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

#ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ጠላት_ተኝቶ

ትላንትን አልፈን ዛሬን ማየታችን፣ ቀኑን ተሻግረን ማምሸታችን፣ ምሽቱ አልፎልን ማንጋታችን፣ በቸር ውለን ማርፈዳችን፣ የህይወታችን ጉዞ መቅናቱ፣ ሰላም ወጥተን ስላም መግባታችን፣ የማይታለፉ ጊዜያትን ማለፋችን፣ ከባዱን ተሻግረን መቆማችን...

ጠላት ተኝቶ ስለሆነ ነውን? በእርግጥ ክፉ ዲያብሎስ እኛን ለመጉዳት ድካም ይኖረው ይሆን? በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ መሆናችንን አይቶስ አዝኖልን ይሆን? እኛን ከመፈተንስ ታክቶ ይሆን? ለተንኮል ጊዜ አጥቶ ወይም ተጨናንቆስ ይሆን? ነው ወይስ ደግ ሆኖ ይሆን? .... በጭራሽ እንደሱ አይደለም።

እርሱ ራርቶ ወይም ስራ ፈትቶ አልያም መልካም ሆኖ አይደለም። ጠላት ዘሬም እንደ ድሮው ይፈትናል የሰዎችን ውድቀት በጽኑ ይመኛል። ሰዎች በምድር ሰላም እና ደስታ እንዲርቃቸው እና እግዚአብሔር ወዳየላቸው ክብር እንዳይደርሱ እንቅፋት ያስቀምጣል።

ለተንኮል ያለመታከት ይስራል፣ ለደባ ያለመስለቸት ይተጋል፣ ለማጥፋት ፈጽሞ ይጸናል፣ ለመግደል በጽናት ይሰራል፣ ደም ለመጠጣት ያፋሽካል። ይሄ ነው ግብሩ ጨርሶ ማዘን የሌለበት እና ጥፋት ብቻ የሞላበት።

በመጽሐፍ " ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” (1ኛ ጴጥሮስ 5፥8) ተብሎ እንደተጻፈ ሊውጠን የሚዳክር ክፉ እንጂ ለጥቅማችን የማይቀርበን መሆኑ ግልጥ ነው። ስለክፋት ብናወራ ክፋት በህሪው ነው፣ ስለሀሰት ብናወራ የሀሰት አባት ተብሏል ለየትኛውም መጥፎ ነገር ምንጩ እና አስገኚው ጠላት ዲያብሎስ ነው።

እና... ጠላት ተኝቶ ሳይሆን ቅዱሱ እግዚአብሔር ጠብቆን ነው። የማይሰለች አዛኙ አዝኖልን ነው፣ የሚያፈቅረን ውዳችን እራርቶልን ነው፣ የማይደክም ምቹ መዳፉ ሰፍቶልን ነው፣ የማይጥለው ብርቱ ክንዱ ተሸክሞን ነው፣ የማይጠላ ሰፊ ልቡ ላይጥል ችሎን ነው፣ በጎነቱ በዙሪያችን ከቦን እና ጠብቆቱ በላያችን እረቦ እንጂ ጠላት ተኝቶ አይደለም።

መቆማችሁ የሚያቆም አምላክ በመኖሩ እንጂ ጠላት ስራ ፈቶ አይደለም፣ መኖራችሁ የማያኖር ጌታ በመኖሩ እንጂ ጠላት አርፎ አይደለም፣ ብንራመድ አቅም የሚሆን አምላክ ስላለ እንጂ ዲያብሎስ ቀንቶልን አይደለም፣ እያተናደ ባለው በኩል አምላክ ቆሞ እንጂ ክፉ ተዘናግቶ አይደለም፣ እየተሰበረ ባለው ነገር እጁ ጣልቃ ገብቶ እንጂ ጠላት ዲያብሎስ ዓላማውን ረስቶ አይደለም፣ እየሆነ ያለው የሆነው የሁሉ ገዢ እና አስገኚ እግዚአብሔር በመኖሩ እንጂ ሰይጣን ከክፋቱ ተዛንፎ አይደለም።

በዛ ልክ ጠላት እየከፋ ለሚያኖር እግዚአብሔር፣ ለሚረዳ እግዚአብሔር፣ ለሚያግዝ አምላክ፣ ለሚያቆም አባት፣ ምስጋናን መስጠት እና አንተ ስላለህ ነው ያ ሁሉ ማለፉ ማለት ያሻል። ማስተዋሉን ያድለን። አሜን

ክብር ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መስከረም 6 2017 ዓ.ም ተጻፈ

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ሳምራዊቷ ሴት ውሃ አጠጭኝ ሲላትም የተጠማው
ውሃን ሳይሆን የእርሷን ነፍስ ነበር እርሷ ግን የተጠማው ምን እንደሆነሳታውቅ ፣ስለዘር ልዩነት
ለመከራከር ተነሳች። መቼም የእግዚአብሔር ን ስጧታና ውሃ አጠጡኝ የሚላቸው ማን እንደሆነ የማያውቁ ሁሉ  ዘርኞች ናቸው። ከመድሐኔዓለም
ክርስቶስ ፊት ቆመውም እንኳን ዘር መቁጠራቸውን
አያቆሙም። እግዚአብሔር ግን የሚፈልገው የሰዎችን ነፍሳቸውን እንጂ ወደላይ ቢቆጠር ሄዶሄዶ
አንዱ አዳም ላይ የሚያርፈውን የዘር ሀረጋቸውን አይደለም። "
      --- ሕማማት ----
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"እግዚአብሔር ላንተ ብሎ ትሑት ቢሆንልህ፤ አንተ ለራስህ ብለህ ትሑት አትሆንምን?"

ታላቁ መቃርስ

@Finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#መሸነፍ

በህይወታችሁ ውስጥ አንዳንድ ደግ ሰዎች በደግነታቸው አሸነፈዋችሁ አያውቁም? ወይም ፍቅራቸው ከምትጠብቁት በላይ ሆኖ ተሸንፋችሁ ታውቁ ይሆን? በህይወታችሁ እንዲገቡ የማትፈልጓቸውን ሰዎች እንኳን በቅንነታቸው እና ከሚያሳዩአችሁ ፍቅር የተነሳ ተሸንፋችሁላቸው ታውቁ እንደሆን?

በበትር ያሸነፋችሁት ሰው ቀን ጠብቆ እርሱም በበትር ወይም በጉልበት እናንተን ማሸነፉ አይቀርም በመሃላችሁም የሚኖር በጎ ነገር አይኖርም። በፍቅር የረታችሁት ሰው ግን ወዳጅ ይሆናችኋል እርሱንም ገንዘብ ታደርጉታላችሁ። ላሳያችሁት ፍቅር ምላሽ እየሰጠ ቋሚ ቤተሰብ እንዲሆን ታደርጉታላችሁ።

አንዳንዴ ገጥሟችሁ ያውቃል ለሰው ፍቅር መሸነፍ ሲያቅታችሁ ሰው ተቆጥቷችሁ ለምን ትጠላዋለሁ እርሱ እኮ ይወድሃል ተብላችሁ ታውቆ እንደሆን? አንዳንዶቻችን እንዲው አይመቸኝም የምንለው ብሂል ደግሞ አለችን። ምንም አርጎኝ እኮ አይደለም በድሎኝም አይደለም ግን እንዲህ ሳየው ደስ አይለኝም፣ እንዲው አይመቸኝም ስንል እንሰማለን።

በእንከን ለተሞላው ለሰው ፍቅር ለመሸነፍ አቅማምተን እና አመንትተን ይሆናል። ባለመሸነፋችን እንደየ ምልከታችን እና እንደየ አስተሳሰባችን ልክም ልንሆን ወይም ልንስት እንችላለን። ለሰዎች ፍቅር ባለመሸነፋችን ያጣናቸው እልፍ ጥቅሞች እና ሰዎች ይኖሩ ይሆናል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ልቡን ያልረታው ሰው ለምንም አይሸነፍም።

ይህንን ትክክል የሆነውን ፍቅር እምቢ ማለት እና አልሸነፍልህም ማለት እንዴት ያለ ዕድለቢስነት ይሆን? ታላቅ የሆነው እና ምንም ህጸጽ የሌለበት የእግዚአብሔር ፍቅር የማይረታን ከሆነ የትኛውስ የፍጡር ፍቅር ሊረታን? በሰዎች ፍቅር ውስጥ ክፍተት ሰለመኖሩ የሚያሻማ አይደለም ለዛ ነው ህያው የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እምቢ ማለት የከፋ ህመም ነው የምንለው።

ምክንያቱም እግዚአብሔር የወደደን ምንም ውለታ ስለዋልንለት አይደለም ወይም ስላመነውም አይደለም ወይም የተቀመጠ መስፈርት ኖሮ አልፈን አይደለም። እንዲው የሆነውን ይሄን ፍቅር እምቢ ማለት እንዴት ይቻል ይሆን? እንዲው ወዶን፣ በነጻ አፍቅሮን፣ ያለመስፈርት ቀርቦን ይሄን ወዳጅነት መግፋት ለራስ ጉዳት መስራት ነው።

የእግዚአብሔር የፍቅሩ ማብራሪያ በቀራንዮ አንድ ልጁን ኢየሱስን መስቀል ላይ በማዋል ተተንትኖ፣ ከቋንቋ በሚሻገር መናገር ፍቅር ተስርቶልን፣ ከቃላት ባለፈ ያሁሉ ግርፋት ፍቅሩን አሳይቶን፣ የላቀው ያ ፍቅር ለእኛ ሆኖ ሳለ ይሄ እኔን አይመለከትም ብሎ ለዚህ ፍቅር ጀርባ መስጠት እንዴት ያለ ክህደት ይሆን?

ይሄንንስ ፍቅር በሌላ ፍቅር መተካት፣ ለእግዚአብሔር ለመገዛት በተገባ መገዛት ለሌላ መገዛትስ እንደምን ያለ ጠዖተ አምላኮ ይሆን? መሸነፍ ማሸነፍ የሚሆነው ለዚህ ፍቅር መሸነፍ ስንችል ነው። ለሰው ለሆነው መውደድ ልባችን እሺ ብሎ ለእግዚአብሔር ፍቅር ግን አልመረታት ካለብን የፍቅር ትርጉም አረዳዳችን ላይ ትልቅ ክፍተት አለብን ማለት ነው።

የእግዚአብሔር ፍቅሩ ከራሱ የሚመነጭ፣ ከእኛ በሆነ በየትኛውም በጎነታችን ላይ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ጥቅምን መስረት አድርጎ ከሚመጣው ከሰው ፍቅር በእጅጉ የተለየ እና ንጽጽር ውስጥ የማይገባ ነው። መወደድ ሳይገባን ተወደናል፣ መፈቀርም ሳይገባን ተፈቅረናል፣ የማይገባን ብዙ ነገር ተደርጎልናል ይህን መተው ውለታን መብላት ነው።

ይህ ፍቅር ካልረታን የትኛውስ ፍቅር ሊረታን? የቱስ እንክብካቤ ሊያሸንፈን? የቱ በጎነት ልባችንን ሊይዝ? የቱስ መውደድ ከዚህ ፍቅር ጋር ይደረደራል? የቱስ ፍቅር ከዚህ ፍቅር ይልቅ ጎልቶ ታይቶ ህጸጽ አልባ ይሆናል?... የሄ ፍቅር የበላይ ነው፣ ሁሉን ፍቅር በስሩ የሚያይ፣ የፍቅር ልኬቱ እና ቱምቢው ይሄ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።

ከዚህ ፍቅር መጉደል የጉድለት ዋና ነውና ለዚህ ፍቅር በመሸነፍ ውስጥ ያለውን ድል ማጣጣም ሲገባን ለዚህ ፍቅር ደርባ ስንሰጥ እንዳንገኝ አምላክ ማስተዋሉን ያድለን። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መስከረም 7 2017 ዓ.ም ተጻፈ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።"

አቡነ ሸኖዳ ሣልሳዊ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

(ከአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - የነፍስ አርነት መጽሐፍ)


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።"

ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
✟ የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤

✟ የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤

✟ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤

✟ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤

✟ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤

✟ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤

✟ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤

✟ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤

✟ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


  🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ልጄ ሆይ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን፤ በድኃ ላይ አትጨክን፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን፤ ስትበለጥግ ድኅነትን፤i ስትሾም ሽረትን፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት፡፡

ልጄ ሆይ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል፡፡

ለአፍህ መሐላ አታልምደው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ፡፡

ልጄ ሆይ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም፡፡

ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡

ልጄ ሆይ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና፡፡

ልጄ ሆይ፤ ጠላት በዛብኝ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ እጽፍልሃለሁ፡፡ በፍየል ነብር፤ በበግ ተኩላ፤ በአህያ ጅብ፤ በላም አንበሳ፤ በአይጥ ድመት፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው፡፡ ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡ ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት & የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡

ልጄ ሆይ፤ ቀን በሥራህ ላይ፤ ሌሊት በአልጋህ ላይ፤ የሚጠብቅህ እግዚአብሔር ነውና ማታ ስትተኛ፤ ጧት ስትነሣ እግዚአብሔርን አምላክህን መለመንና ማመስገን አትተው፡፡

(ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር)


  🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ይነበብ!!

              ✞ ሥጋ ወደም ✞

ዲያብሎስ እጅግ በጣም አብዝቶ ማራቅ የሚፈልገው ከምሥጢራት ሁሉ የበላይ ከሆነው “ከምሥጢረ ቁርባን” ነው፡፡ ምሥጢራት ሁሉ የሚደመደሙት በሥጋ ወደሙ ነው፡፡ መሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ንስሓ፣ ምሥጢረ ተክሊል የሚፈጸሙት በቁርባን ነው፡፡ ይህንን የሚያውቅ የውሸት አባት ዲያብሎስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል፡፡ አንተ ግን “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም” ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን አምናለሁና ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነሳውን ሥጋና ደም እመገባለሁ በለው፡፡ /ዮሐ6፥35/ የዘላለም ሕይወትን መውረስ እንደምትፈልግም አሳወቀው፡፡ “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል” /ዮሐ6፥41/ ስለዚህ ለዘላለም በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር ከሰማይ የወረደውን እንጀራ እበላለሁ ብለህ ጠላትህን አሳፍረው፡፡ ጠላት ግን በድፍረት እንድትቀርብ ሊፈትንህ ይችላል፡፡ የምትቀበለውን ሥጋና ደም የዕሩቅ ብእሲ ሥጋና ደም ነው ብሎ ሊያታልልህም ይሞክራል፡፡ አንተ ግን አትስማው የምቀበለው ሥጋና ደም በዕለተ አርብ የተቆረሰውና የፈሰሰውን  ሥጋና ደም ነው በለው፡፡ ሥጋና ደሙም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው እንጅ ጠላት እንደሚለው መለኮት የተለየው አይደለም፡፡ ጠላት ውጊያውን አሁንም አያቆምም “ንስሓ ሳትገባ ሳትዘጋጅ ተቀበል” ይልሃል፡፡ እርሱን ከሰማኸው የይሁዳ እጣ ፈንታ አንተ ላይም ይደርሳል፡፡ ሳይዘጋጁ ከኃጢአት ሳይነጹ ቢቀበሉት ግሩም ፍዳን የሚያመጣ የሚባላ እሳት ነው፡፡ ይሁዳ በጸሎተ ሐሙስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ከቁርባኑ ሥርዓት ተካፋይ ነበረ፡፡ ነገር ግን በልቡ የነበረው ጌታን በ30 ብር የመሸጥ ኃጢአት እንደወጣ እንዲቀር አድርጎታል፡፡ /ማቴ26፥14-29/፣ /ማቴ27÷3-9/ ሥጋና ደሙ ግሩም ፍዳ የሚያመጣ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ በንጽሕና በትሕትና ንስሓ ገብቶ ሊቀበሉት ይገባል፡፡ በዚህ መልኩ ለሚቀበለው የዘላለም ሕይወትን የሚያወርስ ጥበብን የሚገልጽ ምሥጢርን ሁሉ የሚያድል ነው፡፡ ለዚህም ነው ካህኑ በቅዳሴ ሰዓት “ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብም ያለበት ቢኖር አይቅረብ እጄን ከአፍአዊ ደም ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ፡፡ ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጅ፡፡ በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ” ብሎ እጁን የሚታጠበው፡፡ ዲያቆኑም ተቀብሎ “ይህን የቄሱን ቃል ያቃለለ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ወይም በቤተክርስቲያን በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው በእርሱም እንደተነሣሣ ይወቅ ይረዳ ስለበረከት ፈንታ መርገምን ስለኃጢአት ሥርየት ፈንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል” ይላል፡፡ ይህ አዋጅ የሚታወጀው ከክርስቶስ ሥጋና ደም ርቀን እንድንቆም ወይም የበይ ተመልካቾች እንድንሆን ተፈልጎ ወይም ለማስፈራራት ተብሎ አይደለም ንስሓ ገብተን፣ የበደልነውን ይቅር ብለን፣ የቀማነውን መልሰን፣ ተዘጋጅተን በንጽህና ሆነን እንድንቀበል ነው እንጅ፡፡ በድፍረት በኃጢአት እንደተጨማለቁ ተዘሎ የሚበላና የሚጠጣ አይደለም ፍዳ መቅሰፍት ያመጣልና፡፡ ጠላት ግን ይህንን አዋጅ እያሳሰበና እንደተመቸው እየተረጎመ “ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የበቃህ አይደለህም” ብሎ ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል፡፡ የአዋጁ ዋና መልእክት ንስሓ ገብታችሁ፣ ከንስሓ አባታችሁ ጋር ጨርሳችሁ ቅረቡ የሚል ነው፡፡ በዚህ ድል ስትነሳው ደግሞ “አንተ ገና ወጣት ነህ ሽማግሌዎች እንኳን ሳይቆርቡ ያንተ ቁርባን ምንድን ነው” ይልሃል፡፡ አንተ ምክሩን አትቀበል “ሽማግሌዎች የራሳቸው ነፍስ ነው ያላችው እኔም እንደዚሁ የራሴ ነፍስ ነው ያለኝ  ስለዚህ እነርሱ ስላልቆረቡ እኔ መቁረብ የለብኝም? በወጣትነት ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ ተባልኩ እንጅ ሽማግሌዎች የሚሠሩትን እያየህ እንደእነርሱ ሁን አልተባልኩም፡፡ በእርግጥ በጎ ሥራ ሲሠሩ ልመስላቸው ግድ ነው መጥፎ ሲሠሩ ግን ልመስላቸው አልሻም፡፡ እነርሱ የሚቆርቡበት የራሳቸው ጊዜ ሊኖራቸው ይችላል የእኔ ጊዜ ግን ዛሬ ብቻ ነው” ብለህ አሳፍረው፡፡ ይህን ሁሉ ብለህ ስታሸንፈው ደግሞ እንደለመደው ከንቱ ውዳሴን ይጨምርብሃል፡፡ ቆራቢ እንድትባል ብቻ መቁረብን ያለማምድሃል፡፡ ከዚያ በኋላ ልምድ ያደርግብህና ሳትዘጋጅ ንስሓ ሳትገባ በድፍረት መቅረብን ያለማምድሃል፡፡ ስለዚህ በጣም ጥንቃቄ ልታደርግ ያስፈልጋል፡፡ ሥጋና ደሙን ለመቀበል የግድ ንስሓ መግባት ከንስሓ አባት ጋር መወያየትን ይጠይቃል፡፡ የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ስትሻ የዘላለም ቅጣት እንዳይመጣብህ ተጠንቀቅ፡፡


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም ይስተካከላል!"

አንድ የመዋዕለ ህፃናት ርዕሰ መምህር እሁድ ጠዋት የሚያስተምሯቸውን ህፃናቶች እና ወላጆቻቸውን ሰብስበው እየተናገሩ እያለ አንድ ህፃን ልጅ ሲያስቸግራቸው የሚጫወትበት ተገጣጣሚ መጫወቻ (puzzle Game) ይሰጠዋል። ጨዋታው የተበታተነውን የአለም ካርታ ገጣጥሞ የተስተካከለ ዓለም ማምጣት ነበር። የዓለም ካርታው ውቅያኖስ እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ህፃኑ ለማስተካከል ቸገረው። ነገር ግን የካርታውን ክፍልፋዮች ሲገለበጥ የሰው አካል ቁርጥራጭ ስእሎችን አገኘ። ይህ የሰው ስእል የአለሙ ካርታ በትክክል ሥፍራውን ከያዘ በኋላ በእስኪብርቶ የተሳለ ስእል ነበር። ህፃኑ ታድያ ስዕሉን እንዲሁም አባቱን እየተመለከተ የተሳለውን የሰው ስእል ቦታ ቦታውን ያሲዘውና ገልበጥ ሲያደርገው የዓለሙ ካርታ ተስተካክሎ አገኘው።

ወዲያው ለአባቱ ያሳየዋል። አባትየውም በመገረም እንዴት እንዲህ በፍጥነት አስተካከልከው ቢለው ህፃኑም ሰውየውን ሳስተካክለው የዓለም ካርታውም ተስተካከለልኝ አለው። ያም ርዕሰ መምህር በነጋታው ጠዋት ባልደረባዎቹን ሰብስቦ ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም ይስተካከላል ሲል ተናገረ።

(ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"የክርስቶስ መስቀል እግዚአብሔር ፍቅሩን ለዓለም የሰበከበት አትሮንስ ነው፡፡"

#ቅዱስ_አውግስጢኖስ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ትልቅ

ለግዛትህ ድንበር የሌለህ፣ ለመንግስት ወሰን አልባ፣ ለአኗኗርህ ስፍራ የማይገብህ፣ ለፍቅርህ ልኬት የማይገኝልህ፣ ለርህራሬህ ምሳሌ የሌለህ፣ ለአገዛዘህ እንከን የሚታጣልህ፣ ለወሰንህ ገደብ የማይበጅልህ፣ ለሉዓለዊነትህ ተወዳዳሪ የሌለህ፣ ለአምላክነትህ ተስተካከይ የሌለህ፣ ከአለም በፊት ዘላለም የነበርክ፣ ከፊት ያለውን ዘላለም የምታይ ቅዱስ አምላካችን እግዚአብሔር ተመስገን።

ትልቅ ብልህ ትልቅነትህን አልገልጸውም፣ ቅዱስ ብልህ ቅድስናህን አላብራራውም፣ ሃያል ብልህ ሃያልነትህን አላጎላውም፣ ብርቱ ብዬ ብርታትህን አልገልጠውም አንተ ከቃላቴ የምትልቅ፣ ከንግርቴ የምትሻገር የሁሉ የበላይ ነህ።

ዝማሪያችን ቢከማች ክብርህን አይገልጠውም፣ እልልታችን የዓዕላፍ ቢሆን ክብርህ ጋር አይደርስም፣ ውዳሴያችን ቢጠራቀም ከአንተ ሃያልነት ጋር አይወዳደርም፣ ይሄ ምስጋና ይበቃዋል የማይባልልህ ምስጉን፣ ይህ ዝማሬ ይመጥነዋል የምይባልል ክቡር አንተ ነህ እግዚአብሔር።

ሰው ዘመኑን ሁሉ እያከበርህ ቢኖር፣ ጊዜውን ሁሉ ለአንተ ብቻ ቢሰጥ፣ ፍቅርህን ብቻ እያሰበ ዘመኑን ቢያሳልፍ ለክብርህ የሚመጠን ክብር ሰጥቶ አለፈ ሊባይ አይችልም ምክንያቱም አንተ የማይደረስበት ክብር ባለቤት ነህና።

ከፍጥረት ዓዕምሮ ልህቀት በላይ ትልቃለህ፣ ከሰው መረዳትም በላይ ተረቃለህ፣ በማንም የምትመረመር አምላክ አንተ ነህና ተመስገን እንልሃለን። ከጸሃፍት ጽህፈት በላይ፣ ከጠቢባንም ጥበብ በላይ፣  ከመምህራን እውቀት በላይ፣ ከመርማሪዎች ምርምር በላይ፣ ከሊቃውነት ማወቅ በላይ የሆንክ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ይሁንልህ።

መላዕክት በፊትህ ለሚስግዱልህ ለአንተ እሰግዳለሁ፣ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉህ ቅዱስ እልሃለሁ፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች ይገባለሃል የሚሉህን ይገባሃል እልሃለሁ ክብር ይገባሃል፣ አምልኮ ይገባሃል፣ ስግደት ይገባሃል፣ መገዛት ይገባሃል።

አንተን አመልካሃለሁ አንተን አከብርሃለሁ በዘመኔ ሁሉ እገዛልሃለሁ። የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ የኔም አባት እና አምላክ ለአንተ እዘምራለሁ ለአንተ እቀኛለሁ። አንተን ከፍ አደርግሃለሁ። ስምህ ዘወትር የተመሰገነ ይሁን አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መስከረም 15 2017 ዓ.ም ተጻፈ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
2024/09/28 21:22:02
Back to Top
HTML Embed Code: