Telegram Web Link
#ወንድሞቼ ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?

#ወገኖቼ በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፤ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን?

ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትግፋት።

እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ።" (ያዕ. 5፥19-20)

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


♻️ 🔔 🥰
𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖 𝕛𝕠𝕚𝕟 𝕣𝕖𝕒𝕔𝕥

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት - #ነሐሴ_24

ነሐሴ ሃያ አራት በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ።

በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶች ያደርጋቸዋል።

በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ።

ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት ባያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ።

እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ።

የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዙእ ኀረያ እንደሆነች አገኛት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱሱ ተፀንሶ በታኀሣሦ ወር በሃያ አራት ተወለደ በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ ቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው።

ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመነፈስ ቅዱስ ጸና።

ከዚህም በሗላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

ጐልማሳ በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርኩዙን ይዞ በሌሊት ወጣ።

ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሔዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣፆት የሚሠውበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ።

ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሔዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው እርሱ ግን በደኀና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው።

ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር።

ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኀነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመን ያጸናቸዋል።

ከዚህ በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር።

በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በሗላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔዶ ከእርሱም የምንኲስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሔዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ።

በዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ ከዚያም ግራርያ ወደ ሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው።

ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኲሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስበርሳቸውም አይተዋወቁም እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ሰለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እነደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም።

በዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በሗላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣ ኖረ።
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳ በአባታችን ተክለሃይማኖት ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)


♻️ 🔔 🥰
𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖 𝕛𝕠𝕚𝕟 𝕣𝕖𝕒𝕔𝕥

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
@Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል። 

(ዲያቆን አቤል ካሳሁን)

🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን?

እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"የጥንቱ ዘመን ዘመን ሰማዕትነት ከዓላውያን ነገሥታት ጋር ነበር። ዓላውያን ነገሥታት ክርስቲያኖችን ያሳድዳቸዋል። ክርስቲያኖቹም ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ይሰደዳሉ። ስለ ሀብት ንብረታቸው፣ ስለ ምድራዊ ክብራቸው፣ ስለሚስቶቻቸው፣ ስለ ልጆቻቸው፣ ስለ ምድራዊት ኑሯቸው ብዙም አይጨነቁም። ዋናው ጭንቀታቸው ነፍሳቸው ከአምላኳ፣ ከወዳጇ፣ ከሞተላት አፍቃሪዋ ርቃ እንዳትሰደድ ነበር። ታዲያ ለዚህ ብለው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ግማሾቹ ዱር ለዱር፣ ግማሾቻቸው ተራራ ለተራራ፣ ግማሾቻቸው ዋሻ ለዋሻ፣ ግማሾቻቸውም ፍርክታ ለፍርክታ ተቅበዘበዙ። ብዙ የብዙም መከራ ተቀበሉ። ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ራሳቸውን በየመቃብሩ፣ በየበረሐው ይደብቁ ነበር። በጣም የሚያስደንቀኝ ግን ይህን ያደረጉት በጣም ብዙ እናቶችም መኖራቸው ነው።

ልጆቼ! የእኛ ሰማዕትነት ግን እንዲህ አይደለም። የእኛ ሰማዕትነት እና ውጊያ በላያችን ላይ ካሉ ነገሥታት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከምኞቶቻችን ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከስግብግብነት፣ ከእንቅልፍ፣ ከዋዛ ፈዛዛ፣ ከስንፍና፣ ከውሸት ከሐሜት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ወንበራችን እስኪጎደጉድ ድረስ ፊልም ማየት ሳይሆን ቃለ እግዚአብሔር ማንበብ ነው።

ስለዚህ ልጆቼ! ከምኞቶቻችን ጋር ተጋድሎ እንግጠም!!! ነፍሳችንን ከአምላኳ ጋር ከሚያጣሉ ደግሞም ለጊዜው ሳይሆን ለዘላለም ከሚለይዋት ፍላጎቶቻችን ጋር እንጋደል። ስለምድራዊ ሀብት፣ ስለ ምድራዊ ዝና፣ ስለ ጊዜያዊ ደስታ ብለን ነፍሳችንን በዓላውያን ነገሥታት (ለምኞቶቻችን) ትንበረከክ ዘንድ አሳልፈን አንስጣት። ነፍሳችን ከእነዚህ ነገሥታት መከራ እናድናት። እነዚህን ነገሥታት ድል አድርገን ከአምላኳ እናገናኛት። ከእንቅልፍ ጋር ተዋግተን ድልም አድርገን ጧት ለስግደት፣ ለጸሎት እናበርታት። የእኛ ዘመን ሰማዕትነት ይሄ ነውና"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ሰማዕትነት_አያምልጣችሁ_እና_ሌሎች መጽሐፍ ገጽ 94)
🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
🌼አዲስ አመት🌼
መስከረም 1/1/2017 ዓ.ም

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ።
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም ።
ወይረውዩ አድባረ በድው ።
መዝ 64 ÷ 11-13
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ትርጉም ፦
በቸርነትኽ አመትን ታቀዳጃለኽ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።
የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ
ኮረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ።

#እንኳን_ከዘመነ_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወደ_ዘመነ_ቅዱስ_ማቴዎስ በሰላም አሸጋግሮ እግዚአብሔር አምላክን በሰላምና በጤና አደረሰን።

🌼ውድ
@Finote_tsidk ቻናል ተከታዮቻችን
አዲሱ አመት 🌼የሰላም
                   🌼የጤና  
                   🌼በጎ የምንሰራበት
                  🌼የምህረት ዓመት
🌼የይቅርታ ዓመት ያድርግልን።
🌼በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን

🌼 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን 🌼
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 @Finote_tsidk   🌼🌼
🌼🌼   @Finote_tsidk 🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ፍኖተ ጽድቅ
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻
🌺         ባህረ ሐሳብ
🌻          የ፳ ፲ ፯
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተጸነሰበት ጊዜ ያለው ዓመት ዓመተ ኩነኔ ይባላል ።ክርስቶስ ከተፀነሰበት ጀምሮ አሁን እሰከ አለንበት ያለው ዘመን ደግሞ ዓመተ ምሕረት ይባላል
መላው ዓመተ ዓለም ይባላል።
ዓመተ ኩነኔ
5550 ዓመት  ነው/
ዓመተ ምሕረት /
2017 ዓመት ነው/
5550+2017=7517 ይሆናል
ይህ ማለት ዓለም ከተፈጠረ እስካሁን ያለው እድሜ 7517 ዓመት ነው ማለት ነው።

ዓመተ ወንጌላውያን እና ዕለቱን ለማወቅ 👉👉👉
ይህንን 7517ን ለ4ቱ ወንጌላውያን ትክክል መድቦ 1 ቢተርፍ ማቴዎስ
2 ቢተርፍ  ማርቆስ
3 ቢተርፍ ሉቃስ
ትክክል ቢሆን ዮሐንስ ይሆናል ማለት ነው፡
አሁን ያለንበትን ወንጌላዊው ማን እንደሆነ ለማወቅ
ይሄን 7517ን ለ4ቱ ወንጌላውያን ስናካፍለው 1879 ደርሷቸው ትርፉ (ቀሪው) 1ይሆናል
።ስለዚህም ቀሪው 1
ስለሆነ ማቴዎስ ነው:ማለት ነው
            ዕለቱ (ቀኑ) መቼ እንደሆነ ለማወቅ
1879ን ከዓመተ ዓለሙ ጋር ደምሮ
በሰባት መግደፍ (ለሰባት ማካፈል) ነው
ይህኸውም፡1879+7517=9396 ይሆናል
ይሄን በሰባት ስንገድፈው ወይም ለሰባት ስናካፍለው
1342 ደርሶ 2 ይቀራል (ይተርፋል )
ትርፉ1 ከሆነ ማክሰኞ
2 ከሆነ ረቡዕ
3 ከሆነ ሐሙስ
4 ከሆነ ዐርብ
5 ከሆነ ቅዳሜ
6 ከሆነ እሑድ
ያለምንም ትርፍ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል። ማለት ነው
ስለዚህ አሁን ቀሪው (ትርፉ) 2 ስለሆነ  2 ከተረፈ ረቡዕ ይውላል ብለናልና መስከረም 1 ቀን ረቡዕ ይውላል ማለት ነው።

የ2017 መጥቅዕ እና አበቅቴን ለማግኘት??
ዓመተ ዓለምን ማለትም 7517ን ለ14 ዐቢይ ቀመር 532፣ቢሰጡ  69 ይቀራል 69 ደግሞ ለንኡስ ቀመር   አሥራ ዘጠኝ አሥራ ቢሰጡ  ቀሪ 12 ይሆናል። አሐደ አእትት ለዘመን ይላል አንዱን አትቶ
12-1=11 ይሆናል፣11ወንበር ወጣ ይሏል በዘመነ ማቴዎስ አበቅቴውን ለማግኘት ይህንን ወንበር በጥንተ አበቅቴ ስናባዛው  ጥንተ አበቅቴ መጀመሪያ ድሜጥሮስ ያወጣበት አበቅቴ 11ስለሆነ በጥንተ አበቅቴው ስናበዘው
ማለትም 11×11=121 ይሆናል። በ4 ሠላሳ ስንገድፈው 4 ጊዜ ደርሶ 1 ይተርፋል።  የ2017 ዓመት  አበቅቴ 1 ወጣ ይባላል
መጥቅዕን ለማግኘት ?
11ን በጥንተ መጥቅዑን ማባዛት ነው
ጥንተ መጥቅዕ 19 ነው 11×በ19=209 ይሆናል ስድስት ጊዜ ሠላሳ ስንቀንስ 29 ይቀራል
ስለዚህ የ 2017 ዓ.ም መጥቅዕ 29 ነው ሆነ ማለት ነው 1+29 =30 መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ፦ አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ ከሠላሳ አይበልጡም ከሠላሳ አያንሡም ፦
መጥቅዕ ወአበቅቴ እመ ይበዝሁ ኢየዐርጉ እምሠላሳ ወኢይወርዱ እምሠላሳ ወትረ ይከውኑ ሠላሳ  እንዲል፤
መጥቅዕ 14ን አይነካም ከ14 በላይ ከዋለ ማለትም ከ15 አንስቶ ማለት ነው  በመስከረም ይውላል። ከ14 በታች ከዋለ በጥቅምት ይውላል ማለት ነው
ስለዚህ መስከረም 29 የሚውልበት ቀን ረቡዕ
ነው።
ጾመ ነነዌ
መባጃ ሐመሩ ከ30 በታች ከሆነ በጥር ይገባል። ከ30 በላይ ከሆነ ግን ገድፎ በየካቲት ይውላል።
የእለታት ተውሳክም እንደሚከተለው ነው።
የቅዳሜ ተውሳክ 8
የእሑድ ተውሳክ 7
የሰኞ ተውሳክ 6
የማክሰኞ ተውሳክ 5
የረቡዕ ተውሳክ 4
የሐሙስ ተውሳክ 3
የአርብ ተውሳክ 2

የረቡዕ ዕለት ተውሳክ 4 ነው።
    መባጃ ሐመር+መጥቅዕ የዋለበት ዕለት ተውሳክ ተደምሮ ከሠላሳ በላይ ከሆነ ሠላሳውን ገድፎ ትርፉን መያዝ ነው
     መባጃ ሐመር 29ነው =29+4=33÷30 -  ቀሪ 3  ይሆናል
   የ2017 መባጃ ሐመር 3 ነው ማለት ነው
. አጽዋማትና በዓላት የሚውሉበት ቀንን ለማወቅ መባጃ ሐመርን ከየበዓላቱና አጽዋማቱ ተውሳክ እየጨመሩ  ከሠላሳ በላይ ሲሆን በሠላሳ እየገደፉ
ማውጣት ነው
ጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም በመባጃ ሐመሩ
ነው የምትውለው
ስለዚህ መባጃ ሐመር 3 ስለሆነ
    ጾመ ነነዌ የካቲት 3
   የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ነው 14+3 =17ይሆናል  የካቲት 17 ዐቢይ ጾም
  .የደብረ ዘይት ተውሳክ  11 ነው 11+3= 14 ይሆናል መጋቢት 14 ዐቢይ ጾም
የሆሳዕና ተውሳክ 2 ነው 2+3= 5 ሚያዝያ 5 ሆሳዕና
  የስቅለት ተውሳክ 7ነው  7+3= 10 ሚያዝያ 10 ስቅለት
  የትንሣኤ ተውሳክ 9 ነው 9+3= 12 ሚያዝያ 12 ትንሣኤ
   የርክበ ካህናት ተውሳክ 3 ነው 3+3 6 ግንቦት 6 ርክበ ካህናት
  የዕርገት ተውሳክ 18ነው  18+3= 21 ግንቦት 21ዕርገት
የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው 28+3 31 ሠላሳውን ሳድፉት አንድ ይቀራል ሠኔ 1 ጰራቅሊጦስ
   የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው 29+3 32 ሠላሳውን ሲገድፉት 2 ይቀራል  ሠኔ 2 ጾመ ሐዋርያት
  የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው 1+3= 4 ሠኔ 4 ጾመ ድኅነት ነው
ሌሊቱ ስንት እንዳደረ እና አሥርቆቱን ለማወቅ ደግሞ፣
ቀኑን +ሕፀፁን+ አበቅቴውን ደምሮ ሠላሳ ከሆነ ሠላሳውን መያዝ ከተረፈ ሠላሳውን ገድፎ ትርፉን መያዝ ነው
ለምሳሌ የመስከረም አንድን ሌሊት ስናሳድር
    ሠርቀ መዓልት 1+
    ሕፀፅ 1+ አበቅቴ 1+
             ሠርቀ ሌሊት  3 ማለት ነው
ሠርቀ ወርኁን ደግሞ ለማወቅ ማለትም በጨረቃ ስንት ሌሊት እንዳደረ ለማወቅ
ካደረው ሌሊት ላይ 4ን መጨመር ነው 3+4= 7
    ሠርቀ ወርኅ = 7
    ጥንተ ዖን  ማለት  ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት የተፈጠሩበት ዕለት ማለት ነው  ከሮብ ጀምሮ  መቂ
ቁጠር ነው
ጥንተ ዖን 1
    ጥንተ ቀመር ማለት ማክሰኞ ነው ከማክሰኞ ጀምሮ መቁጠር ነው  2
    ጥንተ ዕለት ማለት እሁድ ነው ከእሁድ ጀምሮ መቁጠር ነው 4
ስለዚህ እግዚአብሔርን ስናመሰግን እንዲህ ማለት አለብን  ሃሌ ሉያ በዘንዜከር ሐሳባተ ሕጉ ወትእዛዛቲሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሳበ ነቢያት ወሐዋርያት ሐሳበ ጻድቃን ወሰማዕት ሐሳበ ደናግል ወመነኮሳት ሐሳበ ኄራን መላእክት እንዘ ሀሎነ በዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ  ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ማርቆስ ፍሥሓ ዜናዊ። በ፸፻ወ፭፻፲፯ ኮነ ዓመተ ዓለም። በ፶፻ወ፭፻ ኮነ ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ። በ፳፻፲፯ ኮነ ዓመተ ምሕረት። ዮም ሠረቀ ለነ ወርኀ መስከረም ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኀ ጥቅምት በሰላመ እግዚአብሔር አብ አሜን። አሚሩ ሠርቀ መዓልት። ሠሉሱ ሠርቀ ሌሊት።  ሰቡዑ ሠርቀ ወርኅ። አሚሩ ጥንተ ዖን፣ ረቡዑ ጥንተ ዕለት፣ ሰኑዩ ጥንተ ቀመር። ዝ ጸሎት ወዝ አስተብቁዖት ይዕርግ በእንተ ስመ አብ ወበእንተ ተዝካረ ወልዱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ስሙ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ወበእንተ ስማ ለእግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ አሜን ካልን በኋላ ስብሐት ማለት ነው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ይቆየን
የዛሬ ዐመት በሰላም ያድርሰን

በመ/ር አስተርአየ ጽጌ

🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
መስከረም ፪
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።

ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

ከሰማዕቱ፤ ከጻድቁ፤ ከካህኑ፤ ከነቢዩ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ረድኤትና በረከት ይክፈለን: አሜን!

©ስንክሳር


🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"
1ጴጥ. 4÷3


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ይረባኛል፣ ይጠቅመኛል ብለህ የመናፍ**ቃንን መጽሐፍ አትመልከት፡፡ ከመመልከትህ የተነሳ ጸጋ ክብር ታጣለህ፡፡ አንድም የነቢያትን የሐዋርያትን መጽሐፍ በመመልከት ከሚገኘው እውቀት ተለይተህ ትጎዳለህ፡፡”

ማር ይስሐቅ


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

#ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

#ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
#ጠላት_ተኝቶ

ትላንትን አልፈን ዛሬን ማየታችን፣ ቀኑን ተሻግረን ማምሸታችን፣ ምሽቱ አልፎልን ማንጋታችን፣ በቸር ውለን ማርፈዳችን፣ የህይወታችን ጉዞ መቅናቱ፣ ሰላም ወጥተን ስላም መግባታችን፣ የማይታለፉ ጊዜያትን ማለፋችን፣ ከባዱን ተሻግረን መቆማችን...

ጠላት ተኝቶ ስለሆነ ነውን? በእርግጥ ክፉ ዲያብሎስ እኛን ለመጉዳት ድካም ይኖረው ይሆን? በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ መሆናችንን አይቶስ አዝኖልን ይሆን? እኛን ከመፈተንስ ታክቶ ይሆን? ለተንኮል ጊዜ አጥቶ ወይም ተጨናንቆስ ይሆን? ነው ወይስ ደግ ሆኖ ይሆን? .... በጭራሽ እንደሱ አይደለም።

እርሱ ራርቶ ወይም ስራ ፈትቶ አልያም መልካም ሆኖ አይደለም። ጠላት ዘሬም እንደ ድሮው ይፈትናል የሰዎችን ውድቀት በጽኑ ይመኛል። ሰዎች በምድር ሰላም እና ደስታ እንዲርቃቸው እና እግዚአብሔር ወዳየላቸው ክብር እንዳይደርሱ እንቅፋት ያስቀምጣል።

ለተንኮል ያለመታከት ይስራል፣ ለደባ ያለመስለቸት ይተጋል፣ ለማጥፋት ፈጽሞ ይጸናል፣ ለመግደል በጽናት ይሰራል፣ ደም ለመጠጣት ያፋሽካል። ይሄ ነው ግብሩ ጨርሶ ማዘን የሌለበት እና ጥፋት ብቻ የሞላበት።

በመጽሐፍ " ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” (1ኛ ጴጥሮስ 5፥8) ተብሎ እንደተጻፈ ሊውጠን የሚዳክር ክፉ እንጂ ለጥቅማችን የማይቀርበን መሆኑ ግልጥ ነው። ስለክፋት ብናወራ ክፋት በህሪው ነው፣ ስለሀሰት ብናወራ የሀሰት አባት ተብሏል ለየትኛውም መጥፎ ነገር ምንጩ እና አስገኚው ጠላት ዲያብሎስ ነው።

እና... ጠላት ተኝቶ ሳይሆን ቅዱሱ እግዚአብሔር ጠብቆን ነው። የማይሰለች አዛኙ አዝኖልን ነው፣ የሚያፈቅረን ውዳችን እራርቶልን ነው፣ የማይደክም ምቹ መዳፉ ሰፍቶልን ነው፣ የማይጥለው ብርቱ ክንዱ ተሸክሞን ነው፣ የማይጠላ ሰፊ ልቡ ላይጥል ችሎን ነው፣ በጎነቱ በዙሪያችን ከቦን እና ጠብቆቱ በላያችን እረቦ እንጂ ጠላት ተኝቶ አይደለም።

መቆማችሁ የሚያቆም አምላክ በመኖሩ እንጂ ጠላት ስራ ፈቶ አይደለም፣ መኖራችሁ የማያኖር ጌታ በመኖሩ እንጂ ጠላት አርፎ አይደለም፣ ብንራመድ አቅም የሚሆን አምላክ ስላለ እንጂ ዲያብሎስ ቀንቶልን አይደለም፣ እያተናደ ባለው በኩል አምላክ ቆሞ እንጂ ክፉ ተዘናግቶ አይደለም፣ እየተሰበረ ባለው ነገር እጁ ጣልቃ ገብቶ እንጂ ጠላት ዲያብሎስ ዓላማውን ረስቶ አይደለም፣ እየሆነ ያለው የሆነው የሁሉ ገዢ እና አስገኚ እግዚአብሔር በመኖሩ እንጂ ሰይጣን ከክፋቱ ተዛንፎ አይደለም።

በዛ ልክ ጠላት እየከፋ ለሚያኖር እግዚአብሔር፣ ለሚረዳ እግዚአብሔር፣ ለሚያግዝ አምላክ፣ ለሚያቆም አባት፣ ምስጋናን መስጠት እና አንተ ስላለህ ነው ያ ሁሉ ማለፉ ማለት ያሻል። ማስተዋሉን ያድለን። አሜን

ክብር ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መስከረም 6 2017 ዓ.ም ተጻፈ

   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"ሳምራዊቷ ሴት ውሃ አጠጭኝ ሲላትም የተጠማው
ውሃን ሳይሆን የእርሷን ነፍስ ነበር እርሷ ግን የተጠማው ምን እንደሆነሳታውቅ ፣ስለዘር ልዩነት
ለመከራከር ተነሳች። መቼም የእግዚአብሔር ን ስጧታና ውሃ አጠጡኝ የሚላቸው ማን እንደሆነ የማያውቁ ሁሉ  ዘርኞች ናቸው። ከመድሐኔዓለም
ክርስቶስ ፊት ቆመውም እንኳን ዘር መቁጠራቸውን
አያቆሙም። እግዚአብሔር ግን የሚፈልገው የሰዎችን ነፍሳቸውን እንጂ ወደላይ ቢቆጠር ሄዶሄዶ
አንዱ አዳም ላይ የሚያርፈውን የዘር ሀረጋቸውን አይደለም። "
      --- ሕማማት ----
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "


   🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
  @Finote_tsidk 💠 @Finote_tsidk
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"እግዚአብሔር ላንተ ብሎ ትሑት ቢሆንልህ፤ አንተ ለራስህ ብለህ ትሑት አትሆንምን?"

ታላቁ መቃርስ

@Finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#መሸነፍ

በህይወታችሁ ውስጥ አንዳንድ ደግ ሰዎች በደግነታቸው አሸነፈዋችሁ አያውቁም? ወይም ፍቅራቸው ከምትጠብቁት በላይ ሆኖ ተሸንፋችሁ ታውቁ ይሆን? በህይወታችሁ እንዲገቡ የማትፈልጓቸውን ሰዎች እንኳን በቅንነታቸው እና ከሚያሳዩአችሁ ፍቅር የተነሳ ተሸንፋችሁላቸው ታውቁ እንደሆን?

በበትር ያሸነፋችሁት ሰው ቀን ጠብቆ እርሱም በበትር ወይም በጉልበት እናንተን ማሸነፉ አይቀርም በመሃላችሁም የሚኖር በጎ ነገር አይኖርም። በፍቅር የረታችሁት ሰው ግን ወዳጅ ይሆናችኋል እርሱንም ገንዘብ ታደርጉታላችሁ። ላሳያችሁት ፍቅር ምላሽ እየሰጠ ቋሚ ቤተሰብ እንዲሆን ታደርጉታላችሁ።

አንዳንዴ ገጥሟችሁ ያውቃል ለሰው ፍቅር መሸነፍ ሲያቅታችሁ ሰው ተቆጥቷችሁ ለምን ትጠላዋለሁ እርሱ እኮ ይወድሃል ተብላችሁ ታውቆ እንደሆን? አንዳንዶቻችን እንዲው አይመቸኝም የምንለው ብሂል ደግሞ አለችን። ምንም አርጎኝ እኮ አይደለም በድሎኝም አይደለም ግን እንዲህ ሳየው ደስ አይለኝም፣ እንዲው አይመቸኝም ስንል እንሰማለን።

በእንከን ለተሞላው ለሰው ፍቅር ለመሸነፍ አቅማምተን እና አመንትተን ይሆናል። ባለመሸነፋችን እንደየ ምልከታችን እና እንደየ አስተሳሰባችን ልክም ልንሆን ወይም ልንስት እንችላለን። ለሰዎች ፍቅር ባለመሸነፋችን ያጣናቸው እልፍ ጥቅሞች እና ሰዎች ይኖሩ ይሆናል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ልቡን ያልረታው ሰው ለምንም አይሸነፍም።

ይህንን ትክክል የሆነውን ፍቅር እምቢ ማለት እና አልሸነፍልህም ማለት እንዴት ያለ ዕድለቢስነት ይሆን? ታላቅ የሆነው እና ምንም ህጸጽ የሌለበት የእግዚአብሔር ፍቅር የማይረታን ከሆነ የትኛውስ የፍጡር ፍቅር ሊረታን? በሰዎች ፍቅር ውስጥ ክፍተት ሰለመኖሩ የሚያሻማ አይደለም ለዛ ነው ህያው የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እምቢ ማለት የከፋ ህመም ነው የምንለው።

ምክንያቱም እግዚአብሔር የወደደን ምንም ውለታ ስለዋልንለት አይደለም ወይም ስላመነውም አይደለም ወይም የተቀመጠ መስፈርት ኖሮ አልፈን አይደለም። እንዲው የሆነውን ይሄን ፍቅር እምቢ ማለት እንዴት ይቻል ይሆን? እንዲው ወዶን፣ በነጻ አፍቅሮን፣ ያለመስፈርት ቀርቦን ይሄን ወዳጅነት መግፋት ለራስ ጉዳት መስራት ነው።

የእግዚአብሔር የፍቅሩ ማብራሪያ በቀራንዮ አንድ ልጁን ኢየሱስን መስቀል ላይ በማዋል ተተንትኖ፣ ከቋንቋ በሚሻገር መናገር ፍቅር ተስርቶልን፣ ከቃላት ባለፈ ያሁሉ ግርፋት ፍቅሩን አሳይቶን፣ የላቀው ያ ፍቅር ለእኛ ሆኖ ሳለ ይሄ እኔን አይመለከትም ብሎ ለዚህ ፍቅር ጀርባ መስጠት እንዴት ያለ ክህደት ይሆን?

ይሄንንስ ፍቅር በሌላ ፍቅር መተካት፣ ለእግዚአብሔር ለመገዛት በተገባ መገዛት ለሌላ መገዛትስ እንደምን ያለ ጠዖተ አምላኮ ይሆን? መሸነፍ ማሸነፍ የሚሆነው ለዚህ ፍቅር መሸነፍ ስንችል ነው። ለሰው ለሆነው መውደድ ልባችን እሺ ብሎ ለእግዚአብሔር ፍቅር ግን አልመረታት ካለብን የፍቅር ትርጉም አረዳዳችን ላይ ትልቅ ክፍተት አለብን ማለት ነው።

የእግዚአብሔር ፍቅሩ ከራሱ የሚመነጭ፣ ከእኛ በሆነ በየትኛውም በጎነታችን ላይ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ጥቅምን መስረት አድርጎ ከሚመጣው ከሰው ፍቅር በእጅጉ የተለየ እና ንጽጽር ውስጥ የማይገባ ነው። መወደድ ሳይገባን ተወደናል፣ መፈቀርም ሳይገባን ተፈቅረናል፣ የማይገባን ብዙ ነገር ተደርጎልናል ይህን መተው ውለታን መብላት ነው።

ይህ ፍቅር ካልረታን የትኛውስ ፍቅር ሊረታን? የቱስ እንክብካቤ ሊያሸንፈን? የቱ በጎነት ልባችንን ሊይዝ? የቱስ መውደድ ከዚህ ፍቅር ጋር ይደረደራል? የቱስ ፍቅር ከዚህ ፍቅር ይልቅ ጎልቶ ታይቶ ህጸጽ አልባ ይሆናል?... የሄ ፍቅር የበላይ ነው፣ ሁሉን ፍቅር በስሩ የሚያይ፣ የፍቅር ልኬቱ እና ቱምቢው ይሄ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።

ከዚህ ፍቅር መጉደል የጉድለት ዋና ነውና ለዚህ ፍቅር በመሸነፍ ውስጥ ያለውን ድል ማጣጣም ሲገባን ለዚህ ፍቅር ደርባ ስንሰጥ እንዳንገኝ አምላክ ማስተዋሉን ያድለን። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 መስከረም 7 2017 ዓ.ም ተጻፈ

  🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
"አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።"

አቡነ ሸኖዳ ሣልሳዊ


  🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
  ✥     @AtronoseZetewahdo      ✥
⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⎓⍟
2024/09/20 16:21:43
Back to Top
HTML Embed Code: