Telegram Web Link
ኢትዮጵያ ቃል የገባችባቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶች ቆጥራ የምታስረክብ ሀገር መሆኗን ተመድ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቃል የገባችባቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነቶች በሙሉ ቆጥራ የምታስረክብ ሀገር እንደሆነች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ገለፀ፡፡ ከዱባይ እስከ ባኩ ያለፈውን አንድ አመት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሰራቻቸውን ስራዎች በተመለከተ በኢትዮጵያ ፓቪሊዮን ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም…

https://www.fanabc.com/archives/270962
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ፋና80 - ሁሉም ይጨበጨብላቸዋል- እሁድ ከቀኑ 9፡00 ይጠብቁን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተደረገው የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በፖሊስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሃዲ ከሀገሪቱ ፖሊስ ሃላፊ ጄነራል አተም ማሮል ቢያር ኩክ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ፖሊስ ተቋማት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቅርቡ ለደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኦፊሰሮች በሰጠችው የስልጠና እድል ዙሪያና በሌሎች የትብብር ዘርፎች መወያየታቸውንም የኤምባሲው መረጃ…

https://www.fanabc.com/archives/270968
በአፋር ክልል የጤፍ ሰብል የማምረት ባህል እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የጤፍ ሰብል የማምረት ባህል እያደገ መምጣቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሀመዱ መሀመድ ለፋና ብሮድክሳቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ በአፋር ክልል ያለው የጤፍ ሰብል ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የጤፍ ሰብል ማልማት ተግባርን በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ለማስፋት…

https://www.fanabc.com/archives/270967
የቻይና -አፍሪካ የኢኮኖሚና ንግድ ትብብር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና- አፍሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ትብብር ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በኮንፈረንሱ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ እና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ አቶ አሕመድ ሽዴ÷ የቻይና-አፍሪካ ኮንፈረንስ ታሪካዊ…

https://www.fanabc.com/archives/270974
በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት ባስተናገደችው ስፔን ሺዎች ተፈናቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት ባስተናገደችው ስፔን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ ተፈናቅለዋል፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት በስፔን ቫሌንሺያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለትም ሀገሪቱ በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት በማስተናገዷበሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ መፈናቀላቸው ተሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ ማላጋ አካባቢ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ÷ከ1 ሺህ በላይ ቤቶች ደግሞ በጎርፉ አደጋ ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን በአንዳሉሺያ የጎርፍ አደጋ ፕላን ዳይሬክተር አንቶኒዮ ሳንዝ አስታውቀዋል።

አሁንም ከባድ ዝናብ እስከ ምሽት ድረስ ከማላጋና ግራናዳ እስከ ቫሌንሲያ እና ታራጎና ሊቀጥል እንደሚችል መመላከቱን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጂያንሱ ግዛት ዋና ገዥ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይናዋ ጂያንሱ ግዛት ዋና ገዥ ሹ ኩሊን ከተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በቻይናዋ ጂያንሱ ግዛት ዋና ገዥ ሹ ኩሊን የተመራ የግዛቷ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል፡፡
Live stream finished (1 hour)
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በአብአላ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኪልበቲ ረሱ አብአላ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝት መርሐ ግብሩ በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን አሊሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/270990
Live stream finished (1 hour)
የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
2024/11/16 11:01:18
Back to Top
HTML Embed Code: