Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‹‹እንጦጦ ፓርክ አምስተኛው የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ስያሜን ያገኘንበት ማሳያችን ነው - ከማህደራችን።

እንጦጦ ፓርክ በእንጦጦ ተራሮች የሚገኝ ተፈጥሯዊ የመዝናኛ ስፍራ ነው። በ2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ድንቅ ፓርክ ጥቅጥቅ ደን፣ ድንቅ እይታ፣ እንደ ተራራ መውጣት፣ የአየር ላይ የገመድ ጉዞ እና የፈረስ ግልቢያ ያሉ የተለያዩ የመዝናኛ ተግባራትን አገልግሎት የሚሰጥ ስፍራ ነው።

ለቤተሰብ ምቹ የሆኑ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች፣ የጥበብ ማዕከል፣ የሕፃናት የመጫወቻ ሜዳዎችም ያሉበት ስፍራ ነው። ፓርኩ ተፈጥሮን ከዘመናዊ መገልገያዎች ያቆራኘ የቤት ውጭ አዝናኝ ተግባራትን መፈፀም የሚያስችል ነው።›› - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
የ2017 ዓ.ም የከምባታ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ በዓል አከባበር በምስል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትንፋሼ- የመስቀል ዕለት ይጠብቁን!
ፓርኩ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ለማምረት ማቀዱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በበጀት ዓመቱ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ተኪ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ፓርኩ እቅዱን ለማሳካትና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ይበልጥ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉልላት አበበ እንደገለፁት÷ ፓርኩ ውስጥ ከገቡት…

https://www.fanabc.com/archives/263432
ስራኤል በሂዝቦላህ ዒላማዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ስትፈፀም ታጣቂ ቡድኑም ምላሽ እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሊባኖስ በሚገኙ የሂዝቦላህ ኢላማዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈፀሟ ሲነገር ሂዝቦላህም በምላሹ በእስራኤል ግዛት የሮኬት ጥቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የእስራኤል ጦር እንዳስታወቀው÷ በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመው የአየር ጥቃት በርካታ የሂዝቦላህ ኢላማዎችን ማውደሙን አስታውቋል፡፡ በአየር ጥቃቱ ከ558 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ አካባቢያቸውን…

https://www.fanabc.com/archives/263405
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) አመራሩ በይበልጥ የአገልጋይ አመራር ሰብዕና ተላብሶ እንዲሠራ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የመሻገር ትልሞችን በቅንጅት በማሳካት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አመራሩ የአገልጋይ አመራር ሰብዕና ተላብሶ እንዲሠራ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ።

ብልጽግና ፓርቲ ላለፉት 12 ቀናት በአዳማ ያካሄደው የከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።

ፓርቲው “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሐሳብ ከክልሎች፣ ከተማ አሥተዳደሮችና ከፌዴራል ተቋማት ለተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውም የነገዋን ኢትዮጵያ ብልጽግና በማረጋገጥ የትውልዱን መፃኢ እድል ምቹና ስኬታማ ማድረግ በሚያስችሉ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው ሐሳቦች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ሀገራዊ የመሻገር ትልሞችን በርብርብና ቅንጅት በማሳካት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አመራሩ ከምንጊዜውም በላይ የአገልጋይ አመራር ሰብዕና ተላብሶ በውጤታማነት እንዲሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልጠናው ማጠቃላያ ላይ አቅጣጫ በሰጡበት ወቅት አሳስበዋል፡፡

አመራር አባላቱ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም የሕዝብ ችግሮችን በየደረጃው በመፍታት በተግባር አንድነት የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ በስልጠናው በቂ አቅም ማግኘታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የነገዋን ኢትዮጵያ መሥራት የሚያስችል ግንዛቤ የጨበጡበት ስልጠና መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

ስልጠናው ሀገር ቀያሪም ሀብት ፈጣሪም ሰው በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች፣ ከተሞችና የፌዴራል ተቋማት ያለው ከፍተኛ አመራር በተመሳሳይ ...https://www.fanabc.com/archives/263438
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥር የተቋቋመውን የሬድ ፎክስ ማዕከል ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ጋር በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ በጋራ ለመስራት እና በፌደራል ፖሊስ ሥር የተቋቋመውን የሬድ ፎክስ ማዕከል በማቴሪያልና በስልጠና ለማጠናከር ያለመ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በውይይቱ ወቅት÷ ከእንግሊዝ የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ ጋር እየተጠናከረ የመጣውን ትብብር…

https://www.fanabc.com/archives/263446
በኢሬቻ በዓል መሳተፍ የሚፈልጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢሬቻ በዓል መሳተፍ የሚፈልጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሁነቶች ላይ ለመታደም ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ፡፡

ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከተያዙ ዝግጅቶች መካከል በመስከረም ወር የሚከበሩ ዋና ዋና በዓላት የሚገኙበት ሲሆን÷ከእነዚህ መካከልም የኢሬቻ በዓል አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ገልጿል፡፡

ከበዓሉ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በበዓሉ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማስተናገድም ክልሉ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችን ማዘጋጀቱ ነው የተገለጸው፡፡

ለተጓዦች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የትኬት ቅናሽ መደረጉ እንደተገለጸም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጓዦች በቆይታቸው ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስህቦችን የሚጎበኙበት፣ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት የሚያደርጉበትና በልዩ ልዩ የኢቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚሳተፉበት ዕድል መመቻቸቱም ተጠቅሷል፡፡

ስለሆነም በበዓሉ ላይ መታደምና ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በተመቻቹ ልዩ ልዩ ሁነቶች ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም እንዲመዘገቡ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡፡

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf5Rj5qIdElunjrVniyjDGTp5RcWl3kRepEpN6kPJQxX6Wj3g/viewform?pli=1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‘’ሃላላ ኬላ ሪዞርት ስድስተኛው የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ስያሜን ያገኘንበት ማሳያችን ነው - ከማህደራችን።

ሃላላ ኬላ ሪዞርት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንደስትሪ ለማጎልበት እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻ ለማድረግ በማሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት በ2013 ዓ.ም. ይፋ በሆነው የ”ገበታ ለሃገር” ፕሮጀክት ስር ከሚገኘው የኮይሻ ቅርንጫፍ አንዱ ነው፡፡

አለማቀፍ የቱሪስት መዳረሻ የሆነውና ሰፊ አካባቢን የሚያካልለው የኮይሻ ልማት ፤ በደቡብ መዕራብ ክልል ውስጥ፤ በኮንታ ልዩ ወረዳ እና በዳውሮ ዞን የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ 450 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡’’ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
2024/11/16 11:49:15
Back to Top
HTML Embed Code: