ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የሚገጣጥሙ አምራቾችን እንደሚያበረታታ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን የሚገጣጥሙ አምራቾችን እንደሚያበረታታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የገጣጠማቸውን በኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀሱ የከተማና መካከለኛ አውቶብሶች አስረክቧል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) እንዳሉት÷የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችን ለማበረታታት እየተሰራ ነው፡፡ የቢኬጂ…
https://www.fanabc.com/archives/263455

የቀድሞ የእግር ኳስ አሰልጣኝ አዳነ ገብረየሱስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ስም ካላቸው አሰልጣኞች መካከል አንዱ የነበሩት አሰልጣኝ አዳነ ገብረየሱስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሰልጣኝ አዳነ በኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን፣ ሙገር ሲሚንቶና ሀዋሳ ዱቄትን ጨምሮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ለረጅም ዓመታት በመስራት የሚታወቁ አንጋፋ የእግር ኳስ አሰልጣኝ ነበሩ፡፡ በተለይም…
https://www.fanabc.com/archives/263458

አምባሳደር ታዬ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን በመግለጽ በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባደረጉበት ገለጻ በተለይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው አንስተዋል።
ሶማሊያን በተመለከተም ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በመዋጋት ረገድ በምታደርገውን የተጠናከረ ጥረት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የስምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ሞሊ ፊ በበኩላቸው፥ አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና አጠቃላይ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ውይይቱ ኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው።

ለደመራና መስቀል በዓል መስቀል ዐደባባይን የማጽዳት ሥራ ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመስቀል ዐደባባይ የፅዳት ሥራ አከናወነ፡፡
በጽዳት ሥራው ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች እና ምዕመናን ተሳትፈዋል፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት÷ የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖትነቱ ባሻገር የኢትዮጵያውያን መገለጫና የጋራ ሀብታችን ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በበኩላቸው÷ የመስቀል በዓልን የምናከብረው በመስቀሉ የተሠራልንን ድንቅ ተዓምር ለመግለጽ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ቤተክርስቲያኗ በመስቀሉ የምታስተምረው ሰላምን መሆኑን በመግለጽ÷ ይህንን ሰላም በትብብር ማፅናት የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ከቤተክርስቲያኗ ጎን መሆናቸውን ለመግለጽ የተገኙትን ሁሉም በቤተክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።
https://www.fanabc.com/archives/263476