Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ!

ጤናችን በምርታችን !


በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚብሽን ከ ሰኔ 15 - 20 /2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በዚህ ታላቅ ኤግዚብሽን ፤-

• በሀገራችን በባህላዊ እና በዘመናዊ መድሀኒት፤
• በህክምና መገልገያ መሳሪያ
• የጤና እና የግል ንጽህና መጠበቂያ ማምረት ላይ የተሰማሩ ከአነስተኛ አስከ ከፍተኛ አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤
• የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶች ይቀርባሉ
• የሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ የንግድ ትስስሮች እና የልምድ ልውውጦች ይደረጋሉ፡፡
• ዓለም ዓቀፋዊ ተሞክሮዎችና አሰራሮችላይ ያተኮረ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፤

እርስዎ፡- መጥው ሲጎበኙ ሀገራችን እያከናወነች ያለውን እና ወደፊት የምትደርስበትን የህክምና ግብዓት አምች ኢንደስትሪ ዘርፍ ሁለንተናዊ እድገት ይመለከታሉ፤ በርካታ ኢንቨስትመንት እድሎችም እንዳሉ ይገነዘባሉ፡፡

ይምጡ፤ ይካፈሉ፤ ይጎብኙ

ጤና ሚኒስቴር ከመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አምራች ዘርፍ ማህበራት ጋር በመተባበር
ለበለጠ መረጃ 011 518 6262 / 952 ላይ ይደውሉ!! ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ!!
https://pharma-exhibition.moh.gov.et/
#ጤናችን በምርታች
#our health by our products
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: twitter.com/FMoHealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: @mohethiopia
ከችግር ለመውጣት ተስማምተንና አንድ ሆነን መሥራት መቻል አለብን – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከችግር ለመውጣት ተስማምተንና አንድ ሆነን መሥራት መቻል አለብን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። በውይይቱ መልዕክት…

https://www.fanabc.com/archives/250704
በቦንጋ ከተማ ለሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በቦንጋ ከተማ ለሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልል ደረጀ በቦንጋ ከተማ የሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት ከመጽሐፉ ሽያጭ በሚገኝ ገንዘብ የሚሰራ ነው፡፡ የቤተ መጽሐፍቱ ፕሮጀክት ከመደመር…

https://www.fanabc.com/archives/250707
Live stream finished (38 minutes)
የኢትዮ-ቻይና የንግድና ኢንቨስትመንት ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የቻይና የንግድና ኢንቨስትመንት ትውውቅ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴዔታ ሃሰን መሃመድ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የሥራ ሃላፊዎችና የቻይና የንግድ ም/ቤት ልዑክ ተሳትፈዋል፡፡ አቶ ሃሰን መሃመድ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ኢትዮጵያና ቻይና ለረጅም ዓመታት የዘለቀ…

https://www.fanabc.com/archives/250713
ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የት/ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት10 ወራት 7 ነጥብ 88 ሚሊየን ተማሪዎችን የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡ አገልግሎቱ በ10 ወራት በትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ÷ በት/ቤት ምገባ መርሐ ግብር 9 ሚሊየን ተማሪዎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ 7 ነጥብ 88 ሚሊየን ተማሪዎችን ተደራሽ ማድረግ…

https://www.fanabc.com/archives/250719
የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚከናወነው ሥራ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲል የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጠየቀ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷ መንግስትና ህዝቡ የሚፈልጉትን ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መሥራት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/250736
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ከሆኑት ክላቨር ጋቴትን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ በመጭው ሐምሌ ወር የምታስተናግደው 4ኛዉ ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ በጋራ መሰራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ “አፍሪካ አዳራሽ “የተሰኘው የኮሚሽኑ…

https://www.fanabc.com/archives/250743
ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡

በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡

ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡፡
ከንቲባ አዳነች ከቤጂንግ ኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ዋና ጸሃፊና የቤጂንግ የአመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ዋና ጸሃፊ እና የቤጂንግ የአመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ሊ ዌይ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም ÷ሁለቱ እህትማማች ከተሞች በቀጣይ በትራንስፖርት፣ በቤቶች ግንባታ፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/250746
በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ከመመራት ተነስቶ አዳማ ከተማን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ኤልያስ ለገሠ እና ዮሴፍ ታረቀኝ ለአዳማ ከተማ እንዲሁም የአብሥራ ተስፋዬ፣ ወንድወሰን በለጠ እና ፍቅሩ ዓለማየሁ (በራስ ላይ) ለጣና ሞገዶቹ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብር ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ፡፡
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቤላሩስ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የቤላሩስ አምባሳደር ፓርቬል ቪዚያትኪ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷ መደበኛ የፖለቲካ ምክክር በማካሄድ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል። ኢትዮጵያና ቤላሩስ በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ግብርና፣ ትምህርት እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/250751
ዩክሬን ስሎቫኪያን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ዩክሬን ስሎቫኪያን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ስሎቫኪያ 17ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ጎል ስትመራ ቆይታ፤ ዩክሬን በ54ኛው እና በ80ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ…

https://www.fanabc.com/archives/250755
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ ይጠብቁን! #ፋናላምሮት
በትግራይ ክልል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በተያዘው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑ ወጣቶችን ለማሳተፍ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። ከሰኔ 20 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መስከረም አጋማሽ 2017 ዓ.ም ድረስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ የሚሆኑ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች በ14…

https://www.fanabc.com/archives/250758
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት(ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ በሆኑት አቡበከር ካምቦ(ዶ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱን አስመልክቶ አቶ ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”በአቡበከር ካምቦ(ዶ/ር) ከተመራው ልዑክ ጋር በክልላችን የትምህርት ጉዳዮች ላይ ባደረግነው ውይይት፣ ድርጅቱ መንግስታችን ለትምህርት ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በበጎ መረዳቱንና…

https://www.fanabc.com/archives/250761
Live stream finished (1 hour)
2024/09/28 16:19:33
Back to Top
HTML Embed Code: