Telegram Web Link
Live stream finished (1 hour)
ያሉንን የተፈጥሮ ጸጋዎች ወደ ልማት ለመቀየር በትኩረት ይሰራል – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ያሉንን የተፈጥሮ ጸጋዎች ወደ ልማት በመቀየር ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በሀዲያ ዞን ጊቤ ወረዳ የሀንዶሼ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክ መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ አቶ እንዳሻው በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ የሀዲያ ዞን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ…

https://www.fanabc.com/archives/250632
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ የ1500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሐይሉ በፖላንድ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸንፋለች፡፡ አትሌቷ በፖላንድ ባይድጎሽ ከተማ በተካሄደው የ1500 የሴቶች ሩጫ ውድድር 3፡58.59 በሆነ ሰዓት በመግባት ማሸነፏን ከዎርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/250635
የመከላከያ ጀኔራል መኮንኖች አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ጀኔራል መኮንኖች አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በዛሬው ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የአማራ ክልል የሰላም ኮንፈረንሰ ውይይት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተደርጓል፡፡ ወይይቱን የመሩት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ ÷ የፌደራል…

https://www.fanabc.com/archives/250644
ተጠባቂው የስፔንና ጣልያን ጨዋታ በስፔን አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር በምድብ ሁለት የሚገኙት ስፔን እና ጣልያን ተገናኝተው በስፔን አሸናፊነት ተጠናቋል።

ቡድኖቹ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ባደረጉት ተጠባቂ ጨዋታ ስፔን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች።

በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጣልያን አልባንያን 2 ለ 1 እንዲሁም ስፔን ክሮሺያን 3 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም ስፔን ስድስት ነጥብ በመያዝ ምድቡን እየመራች ሲሆን ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቷንም አረጋግጣለች።
በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ እና ኔዘርላድስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሰረትም በምድብ አራት የሚገኙት ፈረንሳይ እና ኔዘርላድስ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ፈረንሳይ ኦስትሪያን 1 ለ 0 እንዲሁም ኔዘርላንድስ ፖላንድን 2 ለ 1 በሆነ…

https://www.fanabc.com/archives/250653
በጅግጅጋ የእንስሳት መኖ ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የእንስሳት መኖ ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡ ፋብሪካውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እስኮት ሆክላንደር እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ኡመር ፋሩቅ መርቀው ከፍተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በክልሉ ተወላጅ…

https://www.fanabc.com/archives/250657
ለሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ት/ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ተገንብቶ በቅርቡ ለተመረቀው ሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፀጋዬ አሰፋ እንዳሉት÷ የትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና ስትራቴጂክ ዕቅድ በትምህርት ባለሙያዎችና መምህራን እየተዘጋጀ ነው፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተገኝተው ባለሙያዎቹ እያዘጋጁ የሚገኘውን መተዳደሪያ ደንብ፣ ስትራቴጂክ ዕቅድና መዋቅራዊ አደረጃጀት ሂደትን ተመልክተው የሥራ አቅጣጫ መሥጠታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ቦርዱ የ6ኛው ዙር ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚያስፈጽመውን የ6ኛው ዙር ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚያስፈጽመውን የ6ኛው ዙር ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

https://www.fanabc.com/archives/250662
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማይክሮ አልጌ ምርምርና ማምረቻ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነው የማይክሮ አልጌ (ስፓይሩሊና) ምርምርና ማምረቻ ማዕከል ተመርቋል፡፡ ማዕከሉ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ነው የተገነባው፡፡ ባለፉት 3 ዓመታት የምርምርና የልማት ሥራው ሲጠና የቆየው የምርምር ማዕከሉ ግንባታው ተጠናቅቆ በአዳሚ ቱሉ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት…

https://www.fanabc.com/archives/250668
የደቡብ አፍሪካ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ትምህርት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ በታሪኳ ሁለት የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን አስተናግዳለች፡፡ ኮዴሳ (Convention for a Democratic South Africa – CODESA) በመባል የሚታወቀውና እና እ.አ.አ ከ1991 እስከ 1993 የተካሄደው የምክክር ሂደት የመጀመሪያው የሀገሪቱ የምክክር እርምጃ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሂደቱ ዋነኛ ዓላማ በወቅቱ የነበረውን ስርዓት ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማስወገድ ከዘር መድልዎ…

https://www.fanabc.com/archives/250669
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ ለሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ልትልክ ትችላለች አሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን ዩክሬንን እንደሚያስታጥቁት ሁሉ ሀገራቸውም ለሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ልትልክ እንደምትችል አስታውቀዋል። በቬትናም ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት ፑቲን÷ ምዕራባውያን ሰሜን ኮሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጣለባትን ማዕቀብ በመቃወም የኒውክሌር እና የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ሰርታለች በሚል ያገለሏት ሀገር እንደሆነች ጠቅሰዋል። ምዕራባውያኑ በሞስኮ እና በፒዮንግያንግ…

https://www.fanabc.com/archives/250682
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአውሮፓ ዋንጫን ከፋና ጋር! #EURO2024
በቢሾፍቱ በሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት ይሰራል – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች የገጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሃና አርዓያስላሴና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም÷ በፍሬንድሺፕ ፍላወርስ፣ ጆይቴክ፣ ሆላንድ ዴይሪ፣ ሪፍትቫሊ የውሃ ቴክኖሎጂ ድርጅት እንዲሁም…

https://www.fanabc.com/archives/250695
ሐሰተኛ የቅጣት ማቅለያ አቅርበው ቅጣት እንዲቀልላቸው ያስደረጉ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አሳሳችና ሐሰተኛ የቅጣት ማቅለያ ማስረጃ በማቅረብ ቅጣት እንዲቀልላቸው አስደርገዋል ያላቸውን ሦስት ተከሳሾች በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ በረከት ብርሃኑ ሞሲሳ፣ ዮናስ ካሳ በጋሻው እና ዳግም ውብሸት ወንድማገኝ የተባሉት ተከሳሾች÷ በሌላ ችሎት አቅርበውት የነበረው ሕዝባዊና…

https://www.fanabc.com/archives/250698
የብሪክስ ሀገራት ዐቃቤ ሕግ ሐላፊዎች ስብሰባ የጋራ ስምምነት መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በብሪክስ አባል ሀገራት የዐቃቤ ሕግ አመራሮች መካከል ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ የጋራ የስምምነት መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል፡፡ ከሰኔ 10 እስከ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የብሪክስ ሀገራት የዐቃቤ ሕግ ሐላፊዎች ፎረም ዲጃታል መፍትሔ ለወንጀል መከላከል እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚል መሪ ሃሳብ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ…

https://www.fanabc.com/archives/250700
2024/09/28 18:17:00
Back to Top
HTML Embed Code: