Telegram Web Link
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ ዛሬ በጀመረው 23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ እና አትሌት ውብርስት አስቻለ ተከታትለው በመግባት ለሀገራቸው የወርቅና የብር ሜዳሊያ አምጥተዋል።

https://www.fanabc.com/archives/250775
ኦስትሪያ ፖላንድን በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ዕድሏን አለመለመች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ አራት የተደለደሉት ኦስትሪያና ፖላንድ ባደረጉት የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ኦስትሪያ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

በዚህም ኦስትሪያ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ዕድሏን አለምልማለች።

በምድቡ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ኦስትሪያ በፈረንሳይ 1 ለ 0፤ እንዲሁም ፖላንድ በኔዘርላንድስ 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል።
“ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት በ2011 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠነሰሰው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በየአመቱ የችግኝ ተከላ ስራ ስታካሂድ ቆይታለች። ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ2016ቱን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ጅማሮ መርሃ ግብር አካሂደናል።

በተካሄደውም የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ሁነት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት ይፋ ሆኗል። በመቀጠልም የሀገራዊውን የአረንጓዴ አሻራ ይዘት እና የስራ ውጤት በሰዋዊ ተረክ የሚያቀርብ አለምአቀፍ ዘጋቢ ፊልም የምረቃ እይታ ተካሂዷል።

ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት እንዳመለከተው የደን ሽፋናችን በ2011 ዓመተ ምህረት ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ብሏል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመርሃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ይህን የዕድገት ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
Live stream finished (49 minutes)
በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ 2ኛ ዙር የምድብ ጨዋታ ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ተጠባቂው የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግብ ያልተቆጠረበት የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኗል።

ውጤቱን ተከትሎ በምድብ አራት የሚገኙት ፈረንሳይና ኔዘርላንድስ በተመሳሳይ 4 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በዚሁ ምድብ ቀደም ሲል ምሽት 1ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ኦስትሪያ ፖላንድን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታወሳል።

በምድብ አራት የመጨረሻ መርሐ ግብር ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድስ ከኦስትሪያ የሚጫወቱ ይሆናል።
2024/09/28 18:16:08
Back to Top
HTML Embed Code: