Telegram Web Link
ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀት እየተጓጓዘ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የስድስተኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው ክልሎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መጓጓዝ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ÷ ሰኔ 2013 ዓ.ም እና መስከረም 2014 ዓ.ም 6ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ መካሄዱን ጠቅሰው፤ በጸጥታ ምክንያት ምርጫ ያልተካሄደባቸው እንዲሁም ድጋሚ…

https://www.fanabc.com/archives/249407
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሁሌም ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት ፋና ላምሮት! የምዕራፍ 17 የአምስተኛ ሳምንት አጓጊ ውድድር ቅዳሜ ከቀኑ 6፡ 00 በቀጥታ ስርጭት ይጠብቃችኋል!
ኤምባሲው በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ የጃፓን ባለሀብቶችን ቁጥር ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር የተወያዩት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፤ የጃፓን ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ…

https://www.fanabc.com/archives/249413
እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ ተገደለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ ታሌብ አብደላህ ተገደለ፡፡ ታሌብ አብደላህ የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት በደቡባዊ ሊባኖስ ጆዩያ በተሰኘ አካባቢ በፈጸመው የአየር ጥቃት ነው የተገደለው፡፡ በቅጽል ስሙ አቡ ታሌብ ተብሎ የሚጠራው ታሌብ አብደላህ በደቡብ ሊባኖስ ቀጣና የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን አዛዥ እንደነበር…

https://www.fanabc.com/archives/249417
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ የተደረገው በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው፡፡ ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/249422
ማስታወቂያ

የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የዳሰሳ ጥናት መጠይቅ
************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የማኅበራዊ ሚዲያ ሥራውን ለማሻሻል ከሚያደርገው ጥረት ጋር በተያያዘ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ባንኩ ለዚሁ ጥናት ከማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ግብዓት ለመሰብሰብ በበይነ መረብ (online) ያዘጋጀውን መጠይቅ በመሙላት ለጥናቱ ስኬት የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እየጠየቅን፣ መጠይቁን ቀድመው ለሚሞሉ በርካታ ተሳታፊዎች የአየር ሰዓት ስጦታ ያዘጋጀን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

እባክዎ ወደ መጥይቁ ለመግባት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (link) ይጫኑ፡፡ ስለሚያደርጉልን ትብብር እናመሰግናለን፡፡

https://forms.gle/SGRFpeQWCZCBJ8Z46
ኢትዮጵያ በማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማትን ሐዘን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የሐዘን መግለጫ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ለማላዊ መንግሥት እና ሕዝብ የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

በዚህ የሐዘን ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ከማላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

የማላዊ መከላከያ ኃይል አውሮፕላን ከትናንትና በስቲያ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ከራዳር ውጭ መሆኑን ተከትሎ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ዕድል- ዓርብ ምሽት ይጠብቁን
ከአማራ ክልል 19 ሺህ 950 ኪሎ ግራም ኦፓልና ወርቅ ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 19 ሺህ 950 ኪሎ ግራም የኦፓልና ወርቅ ማዕድናትን በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ታምራት ደምሴ እንደገለጹት÷ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የክልሉን የማዕድን ሃብትና ፀጋ በጥናት በመለየት በስፋት እንዲለማ እየተደረገ ነው። በዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ጥናቶችን በማከናወንና ባለሃብቶች በዘርፉ…

https://www.fanabc.com/archives/249433
በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች 24 የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም ኤሌክትሪክ አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ስር በሚገኙ 24 የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ በአካባቢዎቹ በጸጥታ ችግር ምክንያት የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ተጠግነው ነው ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም አገልግሎት መስጠት የጀመረው፡፡ በምዕራብ ሸዋ በችግሩ ሳቢያ…

https://www.fanabc.com/archives/249438
በኦሮሚያ ክልል ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች መሰራጨታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው የዘንድሮው የንብ እርባታና የማር ሀብት ልማት የዕቅድ ክንውን ግምገማና የዘርፉ የ2017 በጀት ዓመት ላይ ያተኮረ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ…

https://www.fanabc.com/archives/249442
የሚኒስትሮች ም/ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ጎን ለጎን ይፋ የተደረገውን ‘ከለውጡ ማግስት - የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች’ መጽሐፍ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ ፡-https://www.pmo.gov.et/media/other/Cabinetbook.pdf
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ የሥነ-ስርዓትና ፍሬ ነገር ሕጎች እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ለመተግበር በአዋጁ የተጠቀሱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ-ስርዓትና ፍሬ ነገር ሕጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የበጀት ዓመቱ የመጨረሻው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን÷ በዚህም የፍትሕ ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ 100 ቀናት የሕግና…

https://www.fanabc.com/archives/249447
የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶች በማልማት ተመፅዋችነትን ማስቀረት የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶች በማልማት ተመፅዋችነትን ማስቀረት የሚያስችል ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ÷የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማው በማክሮ ኢኮኖሚና ዋና ዋና ዘርፎች…

https://www.fanabc.com/archives/249456
በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች መንግሥት ቃልን በተግባር እየፈጸመ መሆኑን ያመላክታሉ- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች መንግሥት ቃልን በተግባር እየፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለፁ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻው የ100 ቀናት የአፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። አቶ አደም ፋራህ ግምገማውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷…

https://www.fanabc.com/archives/249459
የኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በይፋ ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁዲት ሱሚንዋ ቱሉካ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመው በይፋ ሥራ ጀምረዋል፡፡ ከቤልጂየም ዩኒቨርሲቲ ሊብሬ ዴ ብሬክስልስ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ቱሉካ፥ ከፈረንጆቹ 2020 እስከ 2023 የፕሬዚዳንት ስትራቴጂክ ክትትል ካውንስል ምክትል አስተባባሪ በመሆን ሲያገለግሉ፤ በ2023 መጋቢት ወር የፕላን ሚኒስትር…

https://www.fanabc.com/archives/249446
Live stream finished (48 minutes)
2024/11/16 12:52:06
Back to Top
HTML Embed Code: