Telegram Web Link
''ተመስገን''

መላእክቱና እረኞች በአንድነት ሆነው ''በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን...'' ብለው ያመሰገኑትን ጌታ እኛም  እንዲሁ እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 በቦሌ ደ/ሳ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ተሰብስበን ''ተመስገን'' በተሰኘው የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ ቁጥር 2  የዝማሬ አልበም የተወለደውን አምላክ እናመሰግናለን::

በዕለቱም 16 መዝሙራትን የያዘው የዝማሬ አልበም ለሽያጭ ይቀርባል::


መዝሙራቱ በማኅቶት ቲዩብ የሚለቀቁ ሲሆን በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::


በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::


ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ

👉 የስርቆት ወንጀል ለመፈፀም ሙከራ ያደረጉ ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል


በዛሬው ዕለት በድምቀት የተከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የፖሊስ አባላት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተጠናከረ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበረ የገለጹት የመምሪያው ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ናስር ሙሀመድ፤ የፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል በበዓሉ ዕለት ቦታው ላይ በመገኘት የስርቆት ወንጀልን ለመፈፀም ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል።

ከዚህ ውጪ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር  መጠናቀቁን ገልጸው፤ ሕዝቡ በዓሉን አክብሮ ወደ መጣበት እየተመለሰ እንደሚገኝ አክለዋል። "መንገዶቹም በጥንቃቄ እንዲጠበቁ ትዕዛዝ አስተላልፈናል" ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት እስከዛሬ ከነበረው ቁጥር ከፍተኛ የሆነ የሰው ብዛት የተገኘበት በመሆኑ ከሰው ብዛት አንፃር መኪና ለማንቀሳቀስ እንኳን ረጅም ሰዓት እንደወሰደ የገለጹት የመምሪያው ሃላፊ፤ "ያም ሆኖ ግን የህብረተሰቡ እርስ በርስ የመከባበርና የእንግዳ ተቀባይነት መኖር ስለረዳን ያለ ስጋት ማንቀሳቀስ ችለናል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የትራፊክ አደጋን በተመለከተ ምንም ያጋጠመ ጉዳት እንደሌለ በመናገር፤ አሽከርካሪዎች በሌላ ጊዜም እንደዚሁ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ማሽከርከር እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታ ጥምር ኃይል፤ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ንግሥ ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ገልጿል።

በዓሉን አስመልክቶ የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት በሞባይል እና በጫማ የስርቆት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔን ተከትሎ፤ ወንጀለኞቹን ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት አንድ ዓመት ከአራት ወር እስከ አንድ ዓመት ከሁለት ወር የሚደርስ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል።
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባ ታጣቂ ቡድን  ከ83  በላይ ሰዎችን ገደለ!

ሪፖርተር እንግሊዘኛው በዛሬው እትሙ ከሶማሌላንድ በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባ ታጣቂ ኃይል የበርካቶችን ህይወት መቅጠፉን አስነብቧል፡፡

ጋዜጣው የክልሉን መንግስት እና ገለልተኛ ወገኖችን አነጋግሮ ባወጣው ሰፊ ዘገባ ታጣቂ ቡድኑ ከባድ መሳሪያዎችን ታጥቆ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት አደገኛ ጥቃት መፈጸሙን ነው የገለጸው፡፡

ከ30 ያላነሱ የሶማሌ ክልል ፖሊስ አባላት እና 53 ንፁሀን ዜጎች ከሶማሌላንድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ሀርሺን ወረዳ  በገቡ ታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌ ክልል አመራሮች አረጋግጠዋል ያለው ዘሪፖርተር ሌሎች ምንጮች ግን በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መግለፃቸውን ነው የዘገበው።

የክልሉ ፖሊስ 6 የታጣቂ ቡድኑን አባላት የማረከ ሲሆን ምርኮኞቹ የሲቪል ልብስ የለበሱ የሶማሊላንድ ጦር አባላት መሆናቸው መረጋገጡንም ነው ያስነበበው፡
Reporter

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ

እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
ጅቡቲ ገቡ‼️

ሰሞኑን አስመራ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ዛሬ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል። ፕሬዝዳንቱ ወደ ጅቡቲ ያቀኑት በጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋባዥነት ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ይወያያሉ ተብሏል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች

• የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር - ኤላ ትሪክ
• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ
• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi
• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት - ሲሳይ
• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ
• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮንቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ
• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ /Miss Fendisha/
• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ - ጃዝሚን/jazmin_hope1/
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት - ኤላ Review
• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ - Baes
• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ
• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ
• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu
• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ
• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ /Elatick/
• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ - I did it በዘነዘና
• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ - አቤል ብርሃኑ
• የዓመቱ ምርጥ ኢንፎርማቲቭ ኮንቴንት አዋርድ- ሙሴ ሰለሞን
• የዓመቱ ምርጥ ኢመርጂንግ ኮንቴንት አዋርድ-ስኬት ቤስት ሾርት ሙቪ ቪዲዮ አዋርድ
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በወንድ አሸናፊ- ከርተንኮል
• የኢቨንቱ ምርጥ አለባበስ በሴት አሸናፊ - ማሂልት ኢብራለም

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/06 23:29:08
Back to Top
HTML Embed Code: