Telegram Web Link
ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ያለህ እግዚአብሔር ቸርነትህን ይጠብቃል!


ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ስለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ  ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!

ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው  ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው  ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።


እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን  ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ  ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
                       
የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ ተተኪን በተመለከተ ድምጽ ሊሰጥ ነው ተባለ፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) የሚተካው ሌላኛው ተልዕኮ ላይ ድምጽ ለመስጠት ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

በምክር ቤቱ ጊዜያዊ የአሰራር ደንብ መሰረት በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአትሚስ ተልዕኮ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 31፣ 2024 ድረስ ተራዝሞ ነበር።

በዩናይትድ ኪንግደም የተዘጋጀው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ፤ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት አትሚስን በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ለመተካት ያሳለፈውን ውሳኔ የሚደግፍ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት አባላት በዚህ ረገድ ለ12 ወራት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ይሰጣል።

ረቂቁ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እስከ መጪው የአውሮፓውያኑ ሰኔ መጨረሻ ድረስ 1 ሺሕ 40 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እስከ 12 ሺህ ገደማ መለዮ ለባሽ የጸጥታ አካላት እንዲያሰማሩ ፈቅዷል።

የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ከተለያዩ አገራት የተወጣጣ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለስድስት ወራት በሶማሊያ እንዲቆይ ማሰማራቱ ይታወቃል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ዳቦ ለመግዛት የሄደች 5 ዓመት ሕጻንን አስገድደው የደፈሩ ሁለት የዳቦ ቤት ሠራተኞች በ19 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት መቀጣታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ተከሳሾች አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ ሁለቱም ግለሰቦች የዳቦ መጋገሪያ ቤት ሠራተኞች ናቸው።

ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን፤ ተበዳይ የ5 ዓመት ሕጻን ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት በሁለት ዳቦ ቤት ሠራተኞች መደፈሯ ተገልጿል።

ይህም ወንጀል መፈጸሙን ክሱ የደረሰው የወናጎ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ታሕሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን አሐዱ ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ሕጸን ርኆቦት በለጠ ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድ ቤት በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገልጿል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በምስራቅ ወለጋ ዞን በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የተከሰተው በተለምዶ ሲኖ ትራክ በሚል የሚታወቅ የጭነት ተሸከርካሪ እና የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ በመጋጨታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአደጋው የ11 ሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ 12 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት መድረሱን የሲቡ ሲሬ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ፈዮ ቡሊ ገልጸዋል፡፡

Via ፋና
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
#ሠላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጣችሁ


ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ መስጠትን ከዘር ጋር አነጻጽሮ በምሳሌ ያስተምራል፡፡

ዘር በእጅ የያዙትን ይበዛልኛል፣ ስለ አንዷ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ አፈራለሁ ብሎ በእምንት በእርሻ ቦታ መበተንን ይጠይቃል፡፡

መስጠትም ይህን ይመስላል፡፡ በእጅ ያለውን በልግስና አሳልፎ ሰጥቶ ከእግዚአብሔር ሰፊ በረከት አገኛለሁ ብሎ በእምነት መስጠት፡፡

ይህን ቅዱስ ቃል አምናችሁ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘውና ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ላሉበት ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ያደረጋችሁት በአይነት የእህል ልገሳ በዚህ መልኩ ተጭኖ ለገዳሙ ተልኳል፡፡


“በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ያጭዳል፤ በበረከትም የሚዘራ ደግሞ በበረከት ያጭዳል፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2ኛ ቆሮ 9፥7) እንዲል፤ ስለ መስጠትና መቀበል በሰፊው አስተምሮበታል፡፡

የዘራ እንደሚሰበስብ፣ የሰጠም ዋጋውን አያጣምና የተዘራባት ምድር የዘሩባት አብዝታ እንደምትሰጥ፣ በልግስና የሰጣችኋቸው ገዳማውያን በጸሎታቸው ትልቅ ዋጋ፣ በሚያልፍ ስጦታ የማያልፍ በረከት፤ በሚያልቅ ልግስና የማያልቅ ዋጋ ያስገኛሉና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ምጽዋትን በዘር መስሎታል፡፡


እኛም እንላለን፣ ስለሰጣችሁት እያንዷንዷ ቅንጣት የእህል ዘር ስለአንዱ ፋንታ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጥልን፡፡ በወጣ አብዝቶ ይተካ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተሰራው ከታቀደው አንጻር ገና ብዙ ይቀረዋልና ገዳማውያኑን በዚህ መልኩ በአይነት ማለትም ቀለብ በመስፈር፣ የግንባታ እቃዎች ጠጠር፣ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት በልባችሁ እንዳሰባችሁ በመስጠት መደገፍ የምትፈልጉ ካላችሁ በደስታ እንቀበላለን፡፡ በገንዘብ ድጋፍ ለምታደርጉም የገዳሙ አካውንት ከታች ተቀምጧልና የቻላችሁትን እንድታደርጉ ገዳማዊያኑ እየተጣሩ ነው።



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ወደ መቶ ብር ከፍ ያለው የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት የተለየ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም ተባለ

የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 100 ብር ሆነ ማለት ድሮ ተማሪዎች ሲመገቡ ከነበረበት የምግብ አይነት የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት በቀን ከ22 ብር ወደ 100 ብር መሻሻሉን ተከትሎ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ተመኑ ሲያድግ በተቃራኒው ግን የሚቀርበው የምግብ አይነትና መጠን ያነሰ በመሆኑ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ አሐዱም ይሄንን የተማሪዎች ቅሬታ በመያዝ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል።

በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ በሰጡት ምላሽ፤ የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው፣ "የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም" ሲሉ ገልጸዋል።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ እንዳልቆዩ የሚገልጹት ዶ/ር ሰሎሞን፤ "ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል" ብለዋል።

አሐዱም "የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ማሻሻያ በቂ ነው ወይ? አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርስ ተመጣጣኝ ነው?" ሲል ዩኒቨርስቲዎችን ጠይቋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ የትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች የቀን ምግብ 22 ብር ቢመደብ፤ ከዛ በላይ ወጪ እንደበረው እና ተቋማቱ ለሌላ ሥራ የሚያገኙትን ገንዘብ ለምገባ የሚያውሉበት ሁናቴ መኖሩን ገልጸዋል።

"ዩንቨርስቲዎች በሚመደው 22 ብር ብቻ ተማሪዎቻቸውን አይመግቡም ነበር" ሲሉ ዶ/ር ሰሎሞን ያነሱትን ሃሳብ ተጋርተዋል።

"አሁን የተሻሻለው በጀት በተወሰነ ደረጃ ችግርን ይቀርፋል ተብሎ የሚጠብቅ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የተደረገው ማሻሻያ ቁጥሩ ትልቅ ቢመስልም ቀድሞ ሲወጣ ከነበረው ወጪ አንጻር ሲታይ አሁንም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በአንጻሩ ሌላው አሐዱ ያነጋገራቸው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ቶሎሶ ዳኒ፤ "አሁን ካለው የዋጋ ንረት አንጻር 22 ብር ተማሪዎችን መመገብ አይችልም ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት መሰረት ወደ መቶ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ የተመደበው በተማሪ 100 ብር በቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ ከነበረው 22 ብር ወደ መቶ ብር ከፍ መደረጉ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ መሆኑን አንስተዋል።

ዶ/ር ሰሎሞን የዩንቨርስቲዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሃሳብ ሲያጠናክሩ፤ ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ እንደነበረ ጠቅሰው፤ "ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር" ሲሉ አክለዋል።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ሀላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የወጣቱን የሥራ አጥነት ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በፖለቲካ ሽኩቻው ላይ ትኩረቱን አድርጓል ሲል ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ወቀሰ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የወጣቱን የሥራ አጥነት ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በፖለቲካ ሽኩቻው ላይ ትኩረቱን አድርጓል ሲል "ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ" የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅት ወቅሷል፡፡

ድርጅቱ "በክልሉ ያሉ ተቋማት መውደማቸው ለሥራ አጥነት ችግር መንስኤ ናቸው" ሲልም ገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ከሰው ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም በተጨማሪ በወጣቱ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ይገለጻል፡፡
በተለይም በቅርቡ የትግራይ ወጣቶች ማህበር እንዳስታወቀው ከሆነ፤ በክልሉ ሥራ ያላቸው ወጣቶች ከ20 በመቶ ያነሱ ናቸው፡፡

አሐዱም ይህንን የወጣቱን ችግርና በክልሉ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በሚመለከት በክልሉ የቅድሚያ ሰብዓዊ መብቶች ለኢትዮጵያን ምክትል ፕሬዝዳንት መብሪህ ብርሃኔን ጠይቋል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በምላሻቸው በክልሉ አብዛኛውን ችግር የፈጠረው ጦርነት መሆኑን በማንሳት፤ "በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ተቋማት መውደማቸው ለዚህ ምክንያት ነው" ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር አቀፍ የሥራ ዕድል ችግሮች መኖራቸውን ያነሱት አቶ መብሪህ፤ ይሁን እንጂ በትግራይ ክልል ያለው ችግር ከሁሉም የከፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"ይህንን ችግር ለመቅረፍም የግዚያዊ አስተዳደሩ በርካታ ሥራዎች መስራት ሲጠበቅበት በውስጥ ፖለቲካዊ ሽኩቻ ውስጥ ተጠምዷል" ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

የትግራይ ክልል በድህረ ጦርነት ወቅት ላይ ያለ መሆኑን የሚያኑሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ "ወደ ቅድመ ጦርነት መመለስ ከባድ ሊሆን ቢችልም ቀስ በቀስ ለመመለስ ፖለቲካ ሽኩቻውን መቀነስ አለበት" ብለዋል፡፡

"ለዚህም በግዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓት መካከል ያለው ሽኩቻ መቆም አለበት፤ ስልጣንም ከምርጫ ውጪ ሊገኝ አይችልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"በአሁኑ ወቅት በክልሉ ትልቅ ችግር ፈጥሮ የሚገኘው የፖለቲካው ውጥረት በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የፌደራል መንግሥትም በመልሶ ግንባታ ላይ ሊሳተፍ ይገባል" ሲሉም ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ መሆኑንም ነው በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ለፋና ዲጂታል ያረጋገጡት፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለትም በዚሁ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን አውስተው÷ ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንከር ማለቱን አስረድተዋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press
ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመላኩ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ❤️

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
#መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ !!!


#የአራተኛው መልክ ደግሞ የአማልክትን መልክ ይመስላል


ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸው የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር፡፡

ከባቢሎናውያን ይልቅ ጠቢባን የነበሩት ሶስቱ ሕጻናት በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ በምናገኘው ታሪካቸው እንደሚግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር።


ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል፣ ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም" አሉት፡፡

በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠለስቱ ደቂቅን ግን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።


በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል፤ የአራተኛው መልክ ደግሞ የአማልክትን መልክ ይመስላል" አለ።

የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ይስገድ ተብሎ የነበረው አዋጅ ተሽሮ "ጉልበት ሁሉ ለሰለስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" የሚል አዋጅ ታወጀ፡፡

ይህ ድንቅ ተአምር የተገለጠበት ቀን ታህሳስ 19 የታላቁ አለቃ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው፡፡

የስሙ ትርጓሜ ታማኝ አገልጋይ ማለት የሆነው ቅዱስ ገብርኤል በዘመናችንም ለበርካቶች ታላቅ ተአምራት ሰርቷል፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፤የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየንና ገዳማውያን አባቶችና እናቶች እንደ ባቢሎን እሳት በነደደው ስጋዊ ፍላጎት ውስጥ አሸናፊ እንዲሆኑ የሚረዳቸውም ነው፡፡ ገዳማውያኑ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሲሉትም በረከታቸው አብሮን እንዲሆን ገዳማቸውንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በህንድ መሀንነቱን ለማከም ጫጩት ከነነፍሷ የዋጠው ህንዳዊ መሞቱ ተነገረ


እንደ ኢንዲያን ቱደይ ዘገባ ከሆነ ቻቲስጋርህ በተባለ የህንድ ግዛት ወስጥ የሚኖረው አንድ የ35 ዓመት ሰው መሃንነትን ለመቅረፍ በሚደረገው የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ አንዲት ጫጩት ከዋጠ በኋላ ነው ሀኪሚ ቤት ሲሄድ ህይወቱ ያለፈው።

ጫጩቷ ጉሮሮው ላይ ተሰንቅራ ትንፋሽ በማጣቱ የሞተ ሲሆን ጫጩቷ ከጎሮሮው ስትወጣ በህይወት መገኘቷ ተነግሯል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/08 04:16:28
Back to Top
HTML Embed Code: