Telegram Web Link
''ተመስገን''

መላእክቱና እረኞች በአንድነት ሆነው ''በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን...'' ብለው ያመሰገኑትን ጌታ እኛም  እንዲሁ እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 በቦሌ ደ/ሳ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ተሰብስበን ''ተመስገን'' በተሰኘው የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ ቁጥር 2  የዝማሬ አልበም የተወለደውን አምላክ እናመሰግናለን::

በዕለቱም 16 መዝሙራትን የያዘው የዝማሬ አልበም ለሽያጭ ይቀርባል::


መዝሙራቱ በማኅቶት ቲዩብ የሚለቀቁ ሲሆን በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::


በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::


ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሳዛኝ ክስተት!

በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የ179 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከታይላንድ ወደ ደቡብ ኮሪያ እየበረረ እያለ #ሙዓን ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ነው የተከሰከሰው። በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩ 181 ሰዎች ውስጥ ሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ በህይወት ተርፈዋል።

ከሁለት ቀን በፊት የአዘርባጃን አውሮፕላን በሩሲያ ሚሳኤል ተመትቶ 38 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

ዛሬ ታህሣስ 20/2017 ዓ.ም ከደቂቃዎች በፊት ረዘም ላሉ ሰከንዶች የቆየውና አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት  አዋሽ ፈንታሌ ከማለዳው 12:58 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን 10km ጥልቀት አለው።

ሰሞኑን ተከታታይ ቀናት እየተከሰተ እንደሚገኝ ይታወቃል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ሹመት‼️

የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ምክትል አዛዥ የነበሩት እና በቅርቡ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈፀሙት አቶ ጃል ሰኚ ነጋሳ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ቢሮ ሐላፊ በመሆን በዛሬው መሾሙ ተዘግቧል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የሱማሌያው ኘሬዝዳን ከጂቡቲ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን አየር ክልል ላለመጠቀም ወይም ለመሸሽ በሶማሌ ላንድ በኩል በማለፍቸው ሶማሌ ላንድ የአየር ክልሌ ተጥሷል በማለት ከሳለች ።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶማሌላንድን ሉዓላዊ የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሰው በመግባት ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የሶማሊላንድን የግዛት መብቶች በመጣስ እየተከሰሱ ነው።

ፎከር 70 5Y-KBX በሚል ስም የተመዘገበ እና በኬንያ አየር መንገድ ስካይዋርድ ኤክስፕረስ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ከሶስት ሰአት በፊት የሶማሌላንድን የአየር ክልል አልፎ ወደ ሞቃዲሾ ሲመለስ የኢትዮጵያን ግዛት በመሸሽ ነው።

ሶማሊያላንዳዊያን<< ይህ ያልተፈቀደ ወረራ አፋጣኝ እርምጃ ይጠይቃል። አየር መንገዱ ይህንን ጥሰት በማቀላጠፍ ቅጣት ሊጣልበት ይገባል፤ ወደፊትም የሶማሊያ ባለስልጣናት የሶማሌላንድን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ መታገድ አለባቸው። የሶማሌላንድ አየር ክልል ሉዓላዊ ነው፣ እና ማንኛውም ያልተፈቀደ አጠቃቀም የራስ ገዝ ግዛቷን እና አስተዳደርን የሚነካ ነው።>>እያሉ ነው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ አቶ ሰለሞን ጎበዜና እሸቱ የተባሉ ግለሰቦችን ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ የቻሉት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሀና ማርያም ቀለበት አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ ሁለት የልደት ሰርተፍኬትና አንድ ያገባ ያለገባ ሰርተፍኬት፣ ሀሰተኛ ዲጅታል የቀበሌ መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ እጅ ከፍንጅ ተይዞ የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ

1ኛ.1 ሰርተፍኬቶች መስሪያ ማሽኖች
2ኛ. 3 የማሽን ቀለም ብዛት
3ኛ. 4 ላፕቶፖች
4ኛ. 6 የልደት ካርድ እና ሌሎችም ንብረቶች መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

በመሆኑም ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ ወንጀል ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን አሳልፎ ለፀጥታ አካላት በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ EFPapp በመጠቀም መረጃ በምስል፣ በቪዲዮ እና በፅሑፍ በመላክ ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መልዕክት በመላክ ጥቆማ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡

በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡


በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል ፡፡ ገዳማት የቤተክርስቲያን ስውር ጓዳዎችና የሚስጥር መዝገቦች ናቸው ፤ ገዳማት የመማፀኛ ከተማ ናቸው ፤ ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸው ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በተለያዩ አዝማናት በሀገሪቱና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በደረሱ ውጪያዊና ውስጣዊ የጥፋት ዘመቻዎች ቀጥተኛ ተጠቂዎችም ነበሩ፡፡

ተፈጥሮአዊ በሆኑ ችግሮችም እንደየአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጋላጭ ሆነው ኖረዋል፡፡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በየጊዜው በተለያየ ስልት የገዳማውያኑን አኗኗር፣ ሥርዓትና ትውፊት ለመበረዝ ሲንቀሳቀሱና ገዳማቱን ሲዋጉ እንደኖሩ ግልጽ ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡


በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የእናት ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ አመስጋኝ ልብ የአንድ አማኝ ቀዳሚ መለያ ባህሪ ነውና በመልዓኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡


አሁን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አኳያ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ያህል ባይሆንም " ጋን በጠጠር ይደገፋል " እንዲሉ የተቻለውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል  አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ ከላይ እንዳልነው ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸውና አሁንም ከጎናቸው በመቆም አለን እንበላቸው ፡፡  


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በአዋሽ አካባቢ ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ!

በዛሬው ዕለት ከተሰሙ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች አንዱ በአዋሽ አካባቢ ተመዝግበዋል። በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ርዕደ መሬት ዛሬ እሁድ ምሽት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታወቀ።

በአካባቢው ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ እንደሆነ የማዕከሉ መረጃ አመልክቷል። በሬክተር ስኬል የመለኪያ መሳሪያ ከ2.5 እስከ 5.4 መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት ይገልጻሉ።

በዚህ መጠን የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ንዝረታቸው በበርካታ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች ጭምር የሚሰማ እንደሆነም የተቋማቱ መረጃ ያሳያል። የምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ጭምር ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየ ንዝረት አስከትሏል። ከአዋሽ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ የተከሰተው የምሽቱ ርዕደ መሬት፤ በዛሬው ዕለት ብቻ በአካባቢው የተመዘገቡ መሬት መንቀጥቀጦችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ

እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
Update‼️

በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 71 ሰዎች ህይወት አለፈ።

@Sheger_press
@Sheger_press
2025/01/05 03:19:50
Back to Top
HTML Embed Code: