በየቀኑ የሚሰማው ነገር ግራ ያጋባል። ያስደነግጣልም።
ከላይ ያለችው ልጅ ትላንት ሰይፉ ሾ ላይ ቀርባ ነበር።
እናም ኩላሊቷን ታማ እያለች ድንገት ከተዋወቀችው ልጅ ጋር ፍቅር እንደ ጀመረች'ና ኩላሊቱን እንደሰጣት ተናግራ ህዝቡን ስታስገርመውና ስታስደንቀው ነበር።
እኔም የተቆራረጠ ቪዲዮ አይቼ በልጁ ልብ እየተገረምኩ ነበር።
ሰይፉ ፋንታሁን በታሪኩ ተገርሞ በተደጋጋሚ 'ይሄ እኮ በፊልም መሰራት ያለበት ታሪክ ነው....' ሲል ነበር።
ልጅቷ ስለባሏ ስታወራ 'ያኔ ዲያሌሲስ በማደርግበት ሰዓት በደንብ እንኳን ሳንተዋወቅ ለሰዓታት ከጎኔ አይለየኝም ነበር። ያኔ ከስቼ በገረጣሁ ሰዓት ነው ፍቅሩን ያሳየኝ...' ምናምን ስትል ነበር !
አሁን እራሱ ባለታሪኩ በለቀቀው ቪዲዮ ግን እንደዛ ስታሞግሰው የነበረው ልጅ ከስቶ'ና እራሱን ጥሎ 'ኩላሊቴን እሟ ቀሊጦ ካለቺኝ በኋላ ልጅቷ ትታኛለች። ከተለያየንም 3 ወር አልፎናል። እኔ በተራዬ ታምሜ አስታማሚ አጥቻለሁ። በዚህ ሰዓት እኔ ለቤት ኪራይ እንኳን የምከፍለው ነገር የለኝም....' እያለ ነው።
Via ሙስተጃብ
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news

ሱሌማን አብደላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ ተዘገበ
በሳዑዲዓረቢያ መቀመጫዉን በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችን በማቅረብ የሚታወቀዉ ሱሌማን አብደላ ለበርካታ ጊዜያት በሀገሪቱ መንግስት በቁጥጥር ስር ዉሎ በእስር ላይ ይገኝ ነበር።
ሱሌማን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም ሲያንጸባርቅ የነበረ ሲሆን በሳዑዲዓረቢያ መንግስት ተይዞ እስር ላይ ቆይቷል።
ሱሌማን ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠቱን መሠረት ሚዲያ ዘግቧል። ሱሌማን በኢትዮጵያ ምን እንደሚጠብቀዉ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። እስካሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ሱሌማን አብደላን መረከቡን አላሳወቀም።
Via መሠረት ሚደያ

የዓለማችን ረዥሙ ሾፌር አልባ የባቡር የጉዞ መስመር ስራ ጀመረ‼️
በሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ በቅርቡ ወደስራ የገባውና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዘው ሾፌር አልባ የመንገደኞች የባቡር አገልግሎት ፈጣን፣ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም ደህንነቱ አስተማማኝ ነዉ ተብሎለታል፡፡
የትራፊክ ምልክቶችን መረዳት፣ የባቡሩን ፍጥነት መቆጣጠር፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ አስቀድሞ ማሳወቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ለባቡሩ ከሚሰጠዉ ጥቅም ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተሳፋሪዎችን የጉዞ ሁኔታ መከታተል ያስችላል፡፡
አገልግሎቱ በቀን 3.6 ሚሊዮን መንገደኞችን በሙሉ አቅሙ በስድስት የጉዞ መስመሮች የማጓጓዝ አቅም እንዳለው ገልፍ ቢዝነስ ዘግቧል፡፡ በዚህም ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ በማቅረብ በሪያድ ያለውን የካርቦን ልቀት ለመቀነስ እና የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
በ23 ቢሊዮን ዶላር በጀት ወደስራ የገባው የባቡር አገልግሎት 176 ኪ.ሜ ገደማ የሚሸፍን ሲሆን የሀገሪቱን የትራንስፖርት ስርዓት አዲስ መልክ እንደሚሰጠዉ ይጠበቃል፡፡

#ለድንቅ ስራ የተመረጠ እጅ፣ የተቀባ ራስ
በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገድለ ላሊበላን የጻፉት የውቅር አቢያተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ቅርጽና አሰራር ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡፡ “በላሊበላ እጅ እኒህ አብያተ ክርስቲያናት ከምድር ልብ ወጥተው የሚሠሩበት ጊዜ ደረሰ… ምድርን ከፈጠረ ጀምሮ ተሠውሮ የነበረውን ሕንጻ እንዲገልጥ እግዚአብሔር ወዷልና።” የልዩ ጥበባዊ መገለጥ፣ የድንቅ አእምሯዊ ሀሳብ፣ የመጠቀ የስነ ሕንጻ ጥበብን የመረዳት አቅም ውጤት የሆኑት እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት እውን ለመሆናቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳለበት ይህ አገላለጽ ማሳያ ነው፡፡
ይህን መነሻ አድርገው ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ሲወቅር የመላዕክት እገዛ እንዳለበት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያብራራሉ፣ አንድም እነዚህ የጥበብ ውጤቶች ልዩና የማይደገሙ ተደርገው ቢሰሩም በሰው እጅ መሰራታቸውን መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ያም ሰው እግዚአብሔር ስራውን ሊገልጽበት ፈልጎ ይህን እውቀት በአእምሮው ያኖረለት እጁንም የባረከለት ንጉሱ ቅዱስ ላሊበላ ነው ይላሉ፡፡
ቅዱስ ላሊበላ ገድሉ በንግስና ስሙ ጠቅሶ ስራውን ሲያብራራ “ገብረ መስቀልም ልዩ ልዩ የሆኑ የብረት መሣሪያዎችን አሠራ። ለመጥረብም የተሠራ አለ። ለመፈንቀልም የተበጀ ብረት አለ። ለመፈልፈልም የተሠራ አለ። እነዚህን ቋጥኝ ድንጊያ የመቅደስ ሕንጻ የሚፈጸምባቸውን አሠራ። ገብረ መስቀልም ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምድራዊ ሐሳብን፣ ሚስቱንም ደስ ለማሰኘት ፈቃድ ቢሆንም አላሰበም። ሁሉንም በሙሉ መንፈስ ስለ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት አሰበ እንጂ።” ይላል፡፡ መጽሐፉ ከዚህ ጋር አያይዞ በንጉሥ ላሊበላ አዛዥነት በሀገሬው ሰዎችና በመላእክት እገዛ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ እንደተሰሩ ይነግረናል፡፡
“ንጉሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደ እርሱ ሰብስቦ በአብያተ ክርስቲያናቱ ሕንጻ ሥራ የምትረዱኝ ሁላችሁም የምትቀበሉትን ደሞዛችሁን ተናገሩ አላቸው፣ እግዚአብሔር እንድሠራ አዞኛልና። እናንተም በአንደበታችሁ ደመወዛችሁን እንዴት እንደምትቀበሉ ተናገሩ። በጠራቢነትም ሥራ የሚረዳ፣ ጥራቢውንም በማውጣት የሚረዳ ሁላችሁም በአንደበታችሁ ተናገሩ። እንደ አላችሁኝ እሰጣችኋለሁ” ሲልም አወጀ፡፡
ያለ ፈቃዳችን አስገደደን እንዳትሉኝ። በአጉረመረማችሁ ጊዜ ድካማችሁ ብላሽ እንዳይሆን። “ሁላቸውም ልባቸው እንዳሳሰባቸው ነገሩት። እርሱም ስጦታቸውን ሳያጓድል እንዳሉት ሰጣቸው። የአብያተ ክርስቲያናቱን ሕንጻ ሥራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ፈጸመ ድረስ ለሚፈለፍልም ሆነ ለሚጠርብ የቤተ ክርስቲያኑን ጥራቢ ለሚያወጣም ሆነ ደሞዛቸውን በጊዜው ይሠጣቸው ነበር።” ይላል ገድለ ቅዱስ ላልይበላ፡፡
ይህን ድንቅ ስፍራ መጎብኘት በተለይ በልደቱ ቀን ታሕሣስ 29 በስፍራው መገኘት ልዩ እድል ታላቅ በረከትም ነው፡፡ ይህን ልዩ ቀን ላስታ ላይ ለማሳለፍ ለምትፈልጉም ልዩ የጉዞ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
ለአረጋውያን፣ ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ምቹ ማረፊያም አዘጋጅተናል፤ ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።
የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17 ዓ.ም
የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17 ዓ.ም
የጉዞ ዋጋ ምግብን ፣ ማረፊያንና መስተንግዶን ጨምሮ :-6,500
ለበለጠ መረጃ:-0938944444
አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም

ፋና ቴሌቪዥን ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሰላም ስምምነት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ በሚባል መልኩ የኤርትራዉን ፕሬዚዳንት የሚያጣጥል ዘገባ ሰራ
ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበዉ ረዘም ያለ ቃለምልልስን ሰጥተዉ ነበር።
በወቅቱ በጎረቤት ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ጉዳይ ላይ ፕሬዚደንቱ አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ስለ ህገመንግስት ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሀገራቸዉ ከሶማሊያ እና ግብጽ ጋር የገባችዉ ስምምነት ኢትዮጵያን የማያሰጋ ነዉ ብለዉ አስተያየት ሰጥተዉባቸዉ ነበር።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም ለመፍጠር የተደረጉ ሂደቶች ተቀዛቅዘዋል ተብሎ መረጃ መናፈስ ከጀመረበት አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚመስል መልኩ ታድያ በትናንትናው እለት በመንግስታዊ ሚዲያ ፋና ሚዲያ በኩል "የአስመራው መንግስት ነገር-የራሷ አሮባት" በሚል ርዕስ ፕሬዚዳንቱን የሚያጣጥል ዘገባ ተሰርቷል።
#ዳጉ_ጆርናል
@Sheger_press

ትላልቅ የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠሩ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡
በስብሰባው የምክር ቤት አባላት ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
በዚህም የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ውስብስብ ችግሮች እንዳሉ በመጥቀስ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ እና እየተገነቡ ባሉ የመስኖ ፕሮጀክት ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሚኒስቴሩ ምን እየሰራ ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
እንዲሁም የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠሩ መሆናቸውን አንስተው÷ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉና አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ እንዲገለጽም ጠቁመዋል፡፡

104 ጋዜጠኞች በአንድ ዓመት ውስጥ መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌደሬሽን አስታወቀ
ፌዴሬሽኑ 60 በመቶዎቹ ሟቾች ከጋዛው ጦርነት ጋር በተገናኘ መሆኑን ገልፆል።
የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (አይኤፍጄ) ዓመታዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በ2024 ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ሌላ የሞት ዓመት ነበር ብሏል።
እ.ኤ.አ. በታህሳስ 10 ቀን 2024 ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ መሰረትም በዓለም ዙሪያ 104 ጋዜጠኞች ተገድለዋል ያለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም 55 ጋዜጠኞች በጋዛ ውስጥ መገደላቸው ይፋ አድርጓል።
ዲሴምበር 10 ላይ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማክበር አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌደሬሽን (IFJ) በስራ ላይ እያሉ ስለተገደሉ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች የ2024 አመታዊ ዘገባ የመጀመሪያ ግኝቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን እስካሁን ባለው ያልተሟላ መረጃ መሰረት ከጥር 1 ጀምሮ 104 የሚዲያ ባለሙያዎች ተገድለዋል ከነዚህ ውስጥም 12 ሴቶች መሆናቸውን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከሪፖርቱ ተመልክቷል።
አይኤፍጄ እ.ኤ. አ ከ1990 ጀምሮ የተገደሉትን ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር ማተም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 14 ሴቶችን ጨምሮ 129 ሰዎች መሞታቸውን የመዘገበበት ዓመት የምን ጊዜም ከፍተኛ ቁጥር ሆነ ተቀምጧል።
በጋዛ እና ሊባኖስ ውስጥ ያለው ጦርነት በፍልስጤም 55 ፣ በሊባኖስ 6 እና በሶሪያ 1 የሚዲያ ባለሙያዎች መገደላቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ቁጥሩ 60 በመቶውን ይይዛል።
በሚሊዮን ሙሴ

#ሰማይን የለጎመውና እሳት ያዘነመው ቅዱስ
ንጉሱ አክአብና ሚስቱ ንግስቲቱ ኤልዛቤል አብያተ ክርስቲያናትን ዘግተው አብያተ ጣኦታትን በመክፈት ነቢያትና ካሕናትን ያስገድሉ ጀመር፡፡
በዘመናቸው የነበረው ነቢዩ ቅዱስ ኤሊያስ “ተው” ቢላቸው አልሰማ አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ" “በፊትህ የቆምኩ ሕያው እግዚአብሔር አምላክ ሆይ እኔ ካልተናገርኩ በስተቀር በዚህች ምድር ዝናም አይዝነም” ብሎ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ዘግቷል፡፡
ቤል የተሰኘውን ጣኦት አምላካቸውን እሙን ይዩት ብሎ፣ አንድም እግዚአብሔር የሰጣቸውን እየበሉ እንዴት ጣኦት ያመልካሉ የሚል የሃይማኖት ቅንአት ይዞት ነው፡፡
በተለይ የደሀውን ናቡቴ ርስት በመውሰዷ የገሰጻት ንግስቲቱ ኤልዛቤል ናቡቴን ስታስገድለው "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም፡፡ የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" ብሏት ነበርና በእልህና በጥላቻ 900 ነቢያትና ካሕናት አስፈጅታለች፡፡ አንድ መቶ የሚሆኑትን ግን የአካአብ የጦር ቢትወደድ አቢድዩ በአንድ ዋሻ ደብቆ አድኗቸዋል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ900 ዓ.ዓ የተወለደው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤልያስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ርዕሰ ነቢያትም ተብሎ ይጠራል፡፡ ሲወለድ አራት ብርሃን የለበሱ ሰዎች መጥተው ወደ ቤታቸው መጥተው በእሳት መጎናጸፊያ ሲጠቀልሉት ቤቱ ብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ወላጆቹ ይህን ነገር በጊዜው ለነበሩ ነቢያትና ካሕናት ነግረዋቸዋል፡፡
በመጨረሻም ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ አክአብንና ቢትወደዱን አብድዩን አገኛቸው፡፡ “እስከመቼ በሁለት ልባችሁ ታነክሳላችሁ እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ እርሱንም ተከተሉ፣ ቤል አምላክ ከሆነ ደግሞ እርሱን አምልኩ እርሱንም ተከተሉ፤ ይህ እንዲሆንም መስዋዕት ሰውተን መስዋዕት ከሰማይ ወርዶ የበላለት አምላክ ነው” አላቸው፡፡ በዚህ ተስማምተውም በመጀመሪያ የጣኦቱ ካሕናት መስዋዕት ቢሰዉ ከሰማይ እሳት ወርዶ የማይበላላቸው ሆነ፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስም ያሾፍባቸው ጀመር፡፡ አምላካችሁ እንቅልፋም ነውና ተኝቶ ይሆናል ጮኻችሁ ጥሩት፣ አምላካችሁ እንጂ ዋዘኛ ነውና ከእረኞች ጋር ይጫወት ይሆናል” እያለ፡፡
በኋላም የሰር መስዋዕት ጊዜ ደረሰ ይበቃችኋል አላቸው፡፡ እርሱም መስዋዕቱን አዘጋጅቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ “አምላከ እስራኤል እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እከብርበት፣ እበላበት፣ እጠጣበት ብዬ አይደለም ለአምልኮትህ ቀንቼ እንጂ ይህነ መስዋዕት ተቀበል” ብሎ ቢያመለክት ከሰማይ እሳት ወርዶ ከመስዋዕቱና ከተረበረበው እንጨት እልፎ መሬቱን እስኪልሰው ድረስ በልቶለታል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ታላቅ ነቢይ እግዚአብሔር ስለሰጠው ሦስት ጸጋዎች ታከብረዋለች፡፡ ስለድንግልናው፣ ስለምንኩስናው (እጅግ ጥቂት ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ ይመገብ ነበርና)፣ ስለ ብሕትውናው (ከሰዎች ርቆ ይኖር ነበርና፡፡
ከሰማይ እሳት ያወረደ፣ ዝናም እንዳይወርድ ሰማይን የለጎመ ድንቅ ባህታዊ ነው፡፡ በመጽሐፈ 1ኛ ነገስት 17፣2 የሰፈረው ታሪኩ እንደሚሳየውም ወደብሔረ ሕያዋን በእሳት ሰረገላና በእት ፈረስ አርጓል፡፡ በመጨረሻም በዘመነ ሐሳዌ መሲህ መጥቶ በሰማዕትነት ያርፋል፡፡ መታሰቢያው ታሕሳስ 1 ነው፡፡ የዘመናችን ባሕታውያንም ስጋዊውን ዓለም ትተዋልና መንፈሳዊ በረከት የታደሉ ናቸው፡፡ ገዳማቸውን በማገዝ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ከሀላፊነት ለቀቀች!
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ባደረገው ስብስባ አዲስ ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ የአርቲስት ሀረገወይን አሰፋን ጥያቄ ተቀብሎ በሌላ ሀላፊነት መመደቡ ታውቋል።
አርቲስት ሀረገውይን የስራ መደራረብ ስላለበኝ ከአቃቤ ነዋይነት ሌላ ሀላፊነት ስጡኝ ብላ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በአዲሱ ስራ አስፈፃሚ የማርኬቲንግ ሀላፊው የአቶ ኢሳያስ ተፈሪ ምክትል ሆና እንድትሰራ ተመድባለች።
በአርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ምትክ የአቃቤ ነዋይ ቦታን ወ/ሮ አሰፋሽ ታገሰ ተክታ እንድትሰራ መመደቧ ተረጋግጧል ።
ምክትል ፕሬዝዳንት ተዋናይነት ማስተዋል ባለችበት ስራዋን እንድትቀጥልም ስራ አስፈፃሚው ወስኗል።
@ባላገሩ ስፖርት

#BreakingNews
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሰ ሥዩም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን መገደላቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።
ከፖሊስ አዛዡ በተጨማሪ የወረዳው የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲሳይ በሻዳ ተመትተው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ሰምተናል፡፡
በጥቃቱ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል በድምሩ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ዋዜማ ማረጋገጥ ችላለች።
አማጺ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ሮብ ገበያ በተባለ ስፍራ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ፖሊስ አዛዡና የጸጥታ ኃይሎቹ ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊው ወደ ጫንጮ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለዋዜማ አረጋግጠዋል።
አማጺ ቡድኑ <<የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለናል>> በማለት ቀድመው ማሳወቃቸውን ተከትሎ አመራሮቹና የጸጥታ ኃይሎቹ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
ሆኖም በስፍራው ሲደርሱ በአማጺ ቡድኑ በኩል በተከፈተባቸው ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ የፖሊስ አዛዡና የጸጥታ አባላቱ ሕይወታቸው ማለፉት ምንጮች ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ አመራሮቹ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ፓትሮል ተሽከርካሪ አቃጥለው ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸውንም ዋዜማ ሰምታለች።
አማጺ ቡድኑ ከዚህ ቀደምም የውጫሌ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪና ከሃምሳ በላይ የጸጥታ አባላትን መግደሉን ዋዜማ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በፊትም የሱሉልታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በተመሳሳይ በታጣቂዎቹ መገደላቸው ተጠቁሟል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው የክልሉ መንግሥት በቅርቡ ከአማጺ ቡድኑ አንድ ክንፍ ጋር አደረኩት ባለው የሠላም ስምምነት በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ነው። [ዋዜማ]

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት አሻራ መስጫ ቀን ያለፈባቸውን ደንበኞች የቅጣት ክፍያ በማስቀረት በአዲስ ምዝገባ 5 ሺጭ ብር እና 6 ወር ቀጠሮ መጠበቅ ግዴታ እንዲኾን ማድረጉን አስታውቋል።
ቀደም ባለው አሠራር፣ የአሻራ መስጫ ቀን ያለፈባቸው ቅዳሜ ቀን በመሄድና 1 ሺሕ ብር የቅጣት ክፍያ በመክፈል ይስተናገዱ ነበር።
ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች በአዲስ ምዝገባ ማለትም 5 ሺሕ ብር ከመክፈልና 6 ወር ከመጠበቅ በቅጣት 1 ሺሕ ብር መክፈል ይሻላል በማለት ወደ ውስጥ ለመግባት እየተጠባበቁ መኾኑን ለዋዜማ ተናግረዋል።
የፓስፖርት አሻራ መስጫ ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች የመጨረሻ ቀን ባለፈው ቅዳሜ በመኾኑ፣ እጅግ በርከታ ሰዎች ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሲስተናገዱ ዋዜማ ተመልክታለች።
ተቋሙ፣ ገንዘብ ሚንስቴርን ሳያስፈቅድ በግለሰብ ስም አካውንት በመክፈት ከ1 ሺሕ እስከ 1 ሺሕ 500 ብር ቅጣት ሲያስከፍል እንደነበርና በዚኹ አካውንት 17 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ ስለመደረጉ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኦዲት ሪፖርት መረጋገጡ ይታወሳል።

በአማራ ክልል በፋኖ ሀይሎች ተረሸኑ ስለተባሉት ከ30 በላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የፀጥታ አባላት ጉዳይ!!
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 በላይ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን እና የአካባቢው አስተዳደርን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
በዞኑ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም. ለሁለት ወራት ለመንግሥት "መረጃ እና ድጋፍ ሰጪ" በሚል ተጠርጥረው በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የነበሩ በርካታ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት "መረሸናቸው" ታውቋል። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አለማየሁ 20 ከሚሆኑ የወረዳው ካቢኔዎቻቸው ጋር የግድያው ሰለባ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።
መስከረም መጨረሻ በአካባቢው "ከባድ ውጊያ" መደረጉን ተከትሎ መስከረም 29/2017 ዓ.ም. ወረዳው በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱን እና የመንግሥት ኃይሎች ወረዳውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ "[መከላከያ] የሚሊሻ፣ የፖሊስ አባላትን እንዲሁም ካቢኔዎችን በሙሉ መስመር ላይ ነው ጥሏቸው የሄደው" ሲሉ አንድ ነዋሪ፤ 'ባልተለመደ ሁኔታ' የወረዳው አስተዳደር ከተማዋ ውስጥ መቅረቱን ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም 20 የሚሆኑ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መከላከያ ሠራዊት "ለስምሪት" አካባቢውን ለቆ ሲወጣ "ተቆርጠው" መቅረታቸውን ተናግረዋል። በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት የአካባቢ አመራሮች "ፈረስ ቤት ሚካኤል" በተባለ የከተማው መውጫ ላይ ተወስደው መረሸናቸውን ሦስት ነዋሪዎች እና የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የቡና ዋጋ በዓለም ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጭማሪ አሳየ!
የዓለማችን ዋነኛ ቡና አምራች ሀገራት የሆኑት ብራዚል እና ቬትናም በጎርፍ እና በድርቅ መጠቃታቸው በዓለም ቡና ዋጋ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡አንድ ኪሎ ቡና በዓለም ገበያ ላይ በ6.8 ዶላር በመሸጥ የቡና ዋጋ በታሪክ ከፍተኛው ላይ መድረሱ ተገልጿል።
በተለይም ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የአረቢካ ቡና በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው ከ80 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል።ለቡና ዋጋ መናር የአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የቡና ጠጪዎች ቁጥር መጨመር እና፣ ቡናን ከተለያዩ ምርቶች ጋር በመቀላቀል ማምረት መለመዱም እንደ ምክንያት ተጠቅሷል።
የቡና ጠጪዎች ቁጥር እድገት አሁን ባለበት ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ የዋጋ መናሩ ሊጨምር እንደሚችልም ተጠቁሟል።በቻይና የቡና ጠጪዎች ቁጥር ከፍ ያለ ሲሆን ሀገሪቱ ከአፍሪካ እና ሌሎች አህጉራት ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና እያስገባች መሆኑ ተገልጿል፡፡ይህ ለኢትዮጵያ ቡና መልካም ዜና ሲሆን በዚህ አመት ከቡና 2ቢሊየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ከወደብ ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገናኙ ነው ተባለ፡፡
ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ውዝግብ ውስጥ ያስገባቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመሪዎቻቸው አማካኝነት በቱርክ ተገናኝተው በመካከላቸው በሰፈነው ልዩነት ዙሪያ ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ''ኢትዮጵያ የስብሰባ ጥያቄውን አቀረበች፤ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ተቀበሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህንንን ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በአንካራ የሚደረገውን ስብሰባ ለመታደም ወደ ቱርክ አቅንተዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስለ ውይይቱ እስካሁን የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ (ዶ/ር) ወደ ቱርክ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
VOA AFRICA

ኢትዮ መረጃ - NEWS
Video
#ሳይበሉ የሚጠግቡት፣ ሳይቀቡ የሚወዙት
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመተ ዓለም ግንቦት 10 ቀን የእረፍታቸው መታሰቢያ ሲሆን፣ በየዓመቱ ታሕሣስ 02 ደግሞ ዓመታዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡ በትንቢተ ዳንኤል ታሪካቸው በሰፊው ተጽፎ የሚገኘው “ሠለስቱ ደቂቅ” ወይም ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የባቢሎኑ ንጉስ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ባጠፋት ጊዜ ማርኮ ከወሰዳቸው እስራኤላውያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡
በንጉሱ ቤት እንዲቀመጡ ከተመረጡት ምርኮኞች ውስጥም እነዚህ የይሁዳው ንጉስ የኢዮአቄም ልጆችና ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የሀገራቸው ነገር ዘወትር ያሳስባቸዋልና በጾምና በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ እናም በቤተ መንግስት ከሚዘጋጀው ምግብ ይልቅ ጥራጥሬ መብላት ነበር የመረጡት፡፡ በንጉሱ ፊት የሚቀርቡብት ቀን ሲደርስም ከሌሎቹ ሕፃናት ይልቅ ወዝተውና አምረው ይታዩ ነበር፡፡ በቤተ መንግስቱ ከሚኖሩ ወጣቶችና ከባቢሎናውያን ወገንም የእነርሱን ያህል ጥበበኛ አልተገኘም፡፡
ንጉስ ናቡከደነጾርም ወዷቸዋልና በአማልክቱ ስም ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ብሎ ሰየማቸው፡፡ ይህ በንጉሱ ዘንድ ያገኙት ተቀባይነት በባቢሎናውያኑ የቤተ መንግስቱ ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅናት ፈጠረ፡፡ እናም ነገር መጎንጎን ጀመሩ፡፡
ንጉሱ ለክብሩ መገለጫ ቁመቱ 60 ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አቁሞ ሕዝቡን ሁሉ እንዲያሰግድ፣ የማይሰግድ ቢኖር እስከ ሞት በሚደርስ ቅጣት እንዲቀጣ ምክር አቀረቡና አስተገበሩት፡፡ ሦስቱ ሕጻናት ግን ለመስገድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡
ይህን ጊዜም በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተፈረደባቸው፡፡ 49 ክንድ የሆነ እሳት ነዶም ወደዚያ ተጣሉ፡፡ እነርሱ ግን በእሳቱ ውስጥ ሆነው አምላካችን እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡ በዚህ መካከል ንጉሱ በእሳት ውስጥ አራት ሰዎች እየተመለከተ እንደሆነ ገለጸ፡፡
አራተኛወር ሊያድናቸው የመጣው ሊቀ ማላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነበር፡፡ ከልብሳቸው አንዲት ክር፣ ወይም ከጸጉራቸው አንዲት ነቁጥ ሳትቃጠል ወጥተዋል፡፡ ወደ እሳቱ የጣሏቸው ሰዎች ግን በወላፈኑ ተለብልበው ሞተዋል፡፡
በእሳቱ ላይ ሆነው ያደረሱት ምስጋና ዛሬም ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “የሶስቱ ሕጻናት ምስጋና” “ጸሎቱ ሰለስቱ ደቂቅ” ተብሎ ከመዝሙረ ዳዊት ጋር ይጸለያል፡፡ ታሕሣስ 2 ቀን መታሰቢያቸው የሚደረግላቸው እነዚህ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ በዚያው በባቢሎን ተቀብረዋል፡፡
አስገራሚው ነገር ንጉሱ ናቡከደነጾር እጅግ ይወዳቸው ነበርና ሲሞት በመካከላቸው እንዲቀብሩት ትዕዛዝ በማስተላለፉ በእነርሱ መቃብር ነው የተቀበረው፡፡ ሳይበሉ የሚጠግቡት፣ ሳይቀቡ የሚወዙት ባደረባቸው መንፈሳዊ ኃይልና በእግዚአብሔር ቸርነት ነበር፡፡
አሁን በዘመናችንም ዓለምና አምሮቷን ንቀው፣ በገዳማትና በየዋሻው ያሉ አባቶቻችን በቀን አንድ ጊዜ መናኛ ነገር እየተመገቡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ጸንተው የሚኖሩት፡፡ የበረከታቸው ማሳያ የሆነው ደግሞ የጸሎታቸው ኃይል ነው፡፡ ድውያን ይፈወሳሉ፣ ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን ገዳማት በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡

ሳውዲ አረቢያ የ2034 የአለም ዋንጫ አስተናጋጅ ሆነች!
ሳውዲ አረቢያ የ 2034ቱን አለም ዋንጫ ውድድር ለማዘጋጀት በብቸኝነት ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ዛሬ በነበረ የፊፋ ጉባኤ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ሳውዲ አረቢያ ማሸነፏን አረጋግጠዋል።
ለብዙዎች የሳዑዲ ዓለማቀፍ ዋንጫ ማፅደቁ ሀገሪቱ አሁን በስፖርታዊ ጨዋነት የምትጠቀምበት ኃያልነት የመጨረሻ መግለጫ እና ከዚ ጋር ተያይዞ የመጣው ዕድል፣ መቋረጥ እና ውዝግብ ይሆናል።
እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ መንግሥቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ኢንቨስት አድርጓል። መንግሥቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፎርሙላ 1ን፣ የእግር ኳስ የስፓኒሽ እና የጣሊያን ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎችን፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫን እና ከፍተኛ ደረጃ ቦክስን፣ ጎልፍን፣ የፈረስ እሽቅድምድም እና ቴኒስን አስተናግዷል።
የሀገሪቱ የህዝብ ኢንቬስትመንት ፈንድ የተለየውን አራት የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቦችን ተቆጣጥሮ ኒውካስል ዩናይትድን ገዝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የዴንማርክ ድርጅት ፕሌይ ዘ ጨዋታ ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ አረቢያ ከ900 በላይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን መፈራረሟን ገልጿል፣ ውጪያዊ እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ተጽእኖዋን እያሰፋች ትገኛለች።
በግንቦት እና በሴፕቴምበር መካከል፣ አማካኝ የየቀኑ የሙቀት መጠን ከ27C እስከ 43C በውስጥ አካባቢ፣ እና በባህር ዳርቻዎች ከ27C እስከ 38C መካከል ይደርሳል።
የሳውዲ ስፖርት ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዘጋጆቹ በበጋው ዝግጅት ይቻል እንደሆነ በእርግጠኝነት እያጠኑ ነው።
"በበጋው ወቅት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለምን አትታይም? በበጋም ሆነ በክረምት ለኛ ምንም ለውጥ አያመጣም, እንደዚህ አይነት ክስተት ለማስተናገድ ትክክለኛውን ከባቢ አየር እንደሰጠን እስካረጋገጥን ድረስ." በማለት ተናግሯል።
የአለም ዋንጫው እየተስፋፋ ሲሆን ከ2026 ጀምሮ 48 ቡድኖች ይሳተፋሉ። ይህም በኳታር ከተወዳደሩት 32 ጭማሪዎች ነው።