Telegram Web Link
መረጃ‼️

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና እናት ፓርቲ፣ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙ የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሲያልፉ በተኮሱት ተኩስ መገናኛ አካባቢ የአንዲት እናት ሕይወት ማለፉን ማረጋገጣቸውን ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ ነው የተባሉ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞችም የጥይት ተኩስ ሲያሰሙ እንደነበር ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

የስምምነቱ ግልጽነት ማጣትና ታጣቂዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባቱ ሂደት ጥርጣሬ እንደፈጠረባቸው የገለጡት ፓርቲዎቹ፣ ስምምነቱ ትጥቅ ማውረድን አይጨምርም ወይ? በማለት ጠይቀዋል።

መንግሥት የስምምነቱን ሂደትና ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ የጠየቁት ፓርቲዎቹ፣ በአዲስ አበባ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ተኩስ ኾን ተብሎ የሕዝቡን ሥነ ልቡና ለመስለብና ለማስፈራራት የተደረገ መኾኑን ሕዝብ ማወቅ አለበት ብለዋል።

በታጣቂዎቹ ተኩስ ሕይወታቸው ያለፉትን እናት ቤተሰቦች መንግሥት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍልም ፓርቲዎቹ መጠየቃቸው ሸገር ፕረስ ከመግለጫው ተመልክቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ትናንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ሮብ ገበያ በተባለ ቦታ ባንድ ተሽከርካሪ ላይ በፈጸሙት ድንገተኛ ጥቃት፣ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሠ ሥዩምን መግደላቸውን ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

ቡድኑ፣ የኮማንደሩ አጃቢዎች የነበሩ ቁጥራቸውን ያልተጠቀሱ የመከላከያ ሠራዊት እባላትና የክልሉ ፖሊሶች በዚሁ ጥቃት መግደላቸውንም ጠቅሷል።

በጥቃቱ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሲሳይ ባሻዳ እንደቆሰሉና ወደ ጫንጮ ሆስፒታል እንደተወሰዱም ቡድኑ ገልጧል። ከኮማንደሩ ጋር የነበሩ ቁጥራቸው ያልተገለጠ ሰዎች በቁጥጥሩ ሥር እንደሚገኙም ቡድኑ አስታውቋል።

ቡድኑ፣ ሟቹ ለገሠ እና ቆስለው የተረፉት ሲሳይ ባካባቢው በሚንቀሳቀሱ ተዋጊዎቼ ላይ ተደጋጋሚ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ይመሩ ነበር ብሏል።

የቡድኑ ታጣቂዎች በዚሁ ጥቃት፣ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ መግደላቸውንና የፓርቲውን ሃላፊ ማቁሰላቸውን ሸገር ፕረስ ዋዜማ ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

#Sheger_press

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ተስማሙ‼️

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሶማሊያው መሪ ጋር ከስምምነት ደረሱ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ፣ በባሕር በር ውዝግብ ሳቢያ በአገሮቻቸው መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቁርሾ ለመፍታት ትናንት ምሽት በፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ኹለቱ አገራት አንዳቸው የሌላኛቸውን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማክበር፣ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የንግድ ማዕቀፎችን ለመፍጠር እና በአንዲት ሱማሊያ ማዕቀፍ ሥር ለኢትዮጵያ ዘላቂ የኾነ የባሕር በር ለማስገኘት ተስማምተዋል።

ዐቢይና ሞሐመድ፣ በኹለቱ አገሮች መካከል በባሕር በር ውዝግብ ዙሪያ ውጥረት ከተፈጠረ ወዲህ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አቀራራቢነት ለመጀመሪያ ጊዜ እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል። መሪዎቹ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአንካራ ስምምነት' ዝርዝሩ ምን ይሆን?

"በሶማልያ መንግስት ባለመብትነት ስር በሚከናወን የንግድ ውል፣ ሊዝ እና ሌላ አሰራር ሁለቱም ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ይከናወናል፣ ይህም ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር የመጠቀም እድል ይኖራታል።

ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም ከመጋቢት 2017 ዓ/ም በፊት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሙ የማመቻቸት ስራ ይሰራል፣ በአራት ወር ውስጥ ደግሞ ስምምነት ይፈረማል።"

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን መሀመድ በመግለጫው ሀገራቸው የኢትዮጵያን የባህር በር የኪራይ ፍላጎት እንደሚረዱና ለዚህም ለመተባበር ፈቃደኛ ነን ብለዋል።

መሀመድ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት ሀገራቸው ዕውቅና እንደምትሰጥ አውስተው ምስጋናም አቅርበዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የሶርያው በኤርትራ ይደገማል ሲሉ ቲቦር ናጊ ተናገረ

ይህን ያሉት ከዚህ ቀደም የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን በኢትዮጲያና በጊኒ ያገለገሉት ዲፕሎማቱ ቲቦር ናጊ ሲሆኑ አነጋጋሪውን አስተያየት በኤክስ ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።

"የባሽር አል አሳድን ውድቀት ሶርያውያን በደስታ እንዳከበሩት ሁሉ አምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ ሲወድቅም ኤርትራውያን በተመሳሳይ መንገድ ደስታቸውን ይገልፃሉ ሲሉ ዲፕሎማቱ በኤክስ ላይ መፃፈቸውን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

አክለውም "ከጥቂት ቀናት በፊት የባሽር አልአሳድ ደጋፊዎች የነበሩት አሁን ስርዓቱን ሲቃወሙት እንደነበር የተናገሩ ሲሆ፤ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው ይህ በኤርትራ ላይ ይደገማል ሲሉ የአሜሪካ መንግስትን ለበርካታ ዓመታት ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉት ቲቦር ናጊ ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#ጠብታው ሲጠራቀም  

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ልዩ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡

ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ ገዳማውያን የተጠለሉበት፣ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡

ይሁንና መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት ድርቅ በመኖሩ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆኋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበት በአታቸውን ማጽናት የሚችል እገዛ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን አፍ መሻሪያና የአመት ልብስ ልናቀርብላቸው ይገባል። በዚህ የበረከት ስራ ገዳሙንና አባቶችን ብቻ ሳይሆን በጸሎታቸው ሀገራችንንም ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የእያንዳንዳችን ጠብታ ድጋፍ ሲጠራቀም ዋጋ አለው፣ የሕሊና እርካታም እናገኛለን፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
የምንዛሪ ተመኑ ከባንክ ጋር ከ3 እስከ 5 ብር ልዩነት እንዳለው ሮበስት የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ገለፀ።

በቅርቡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ ፍቃድ ከተሰጣቸው 5 ቢሮዎች አንዱ ነው።

የ ሮበስት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌቱ ሙሊሳ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የምንዛሪ ተመኑ ከዕለት ዕለት ቢለያይም ከባንክ አንፃር ከ3 እስከ 5 ብር ልዩነት እንዳለው ነግረውናል።

ይህን የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በኤርፖርት ውስጥ ለመክፈት ዕቅድ እንዳለ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ በመቀሌ ቅርንጫፍ መከፈቱን ተናግረዋል።

የመቀሌው ቅርንጫፍ ስራ ከጀመረ ሶስት ሳምንት አከባቢ መሆኑንም አንስተዋል።

የውጭ ምንዛሪ ይገኝባቸዋል ተብሎ በሚታሰቡ አከባቢዎች ላይ ቢሮዎችን እንደሚከፍቱ የነገሩን አቶ ጌቱ፤ መቀሌ የተመረጠችው ከወርቅ ንግድ ጋር ተያይዞ መሆኑን ገልጸዋል።

ከመቀሌ በተጨማሪ በአዳማ እና ድሬዳዋ ቅርንጫፎችን ለመክፈት መታቀዱንም ነው የነገሩን።

ቢሮው ያለ ጉምሩክ ፍቃድ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መግዛት የሚችል ሲሆን፤ የጉምሩክ ፍቃድ በሚያቀርቡት ጊዜ ደግሞ ከዛ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል።

ቱሪስቶች 5 ሺህ እና የቢዝነስ ተጓዦች ደግሞ ያለ ጉምሩክ ማዘዣ እስከ 10 ሺህ ብር ከቢሮው መግዛት እንደሚችሉም አንስተዋል።


በተጨማሪም ለአስመጪ እና ላኪ ድርጅቶች LC መክፈትን ጨምሮ ለግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥ በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የግል ድርጅቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ መስጠት መጀመራቸው ይታወቃል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ታገደ!!

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ ተጣለባቸው፡፡

ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል" ብሏል በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ።

ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሥራ አመራር ቦርድ የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press
በአዲስ አበባ ለበርካታ ዓመታት ያለ አገልግሎት ተቀምጠዋል የተባሉ የባቡር ሀዲዶች በሽያጭ እንዲወገዱ ተደረገ!

በአዲስ አበባ ከተማ ለበርካታ አስር አመታት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የባቡር ሀዲዶችን በሽያጭ የማስወገድ ሂደት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተሰምቷል።በዚህ የመጀመሪያ ዙር ለረዥም ዓመታት የቆዩና ያለአገልግሎት የተቀመጡ ነባር የባቡር ሀዲጆችን የማስወገድ ስራ በኃላፊነት እየሰራ የሚገኘዉ የከተማዋ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት " እነዚህ የባቡር ሀዲዶቹ  ከ2ሺ ቶን  በላይ  የሚመዝን ክብደት ያላቸውና ከዚህ  ያልተናነሰ በቶን የሚቆጠር  ጭነት የመሸከም አቅም እንዳላቸው አስታውቋል ።

የግዢና ንብረት ማስወገድ ዘርፍ የንብረት ማስወገድ ክትትል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ኃይለመስቀል አቶ አሰፋ እንደተናገሩት ከተማ  አስተዳደሩ እነዚህ የባቡር ሀዲዶች ለከፋ ዘረፋ መዳረጋቸውን ብቻ ሳይሆን የሚያስገኙትን  ከፍተኛ ገቢ ታሳቢ በማድረግ ጭምር  በሽያጭ እንዲወገዱ የውሳኔ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።በዚህም በመጀመሪያ ዙር የባቡር ሀዲዶችን በሽያጭ የማስወገድ ሂደት አገልግሎቱ እስካሁን 24 ሚሊዮን 677 ሺ 985 ብር ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ እንዲሆን ማድረጉን አስታዉቀዋል።

Via Capital

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
BUMS‼️

በርግጠኝነት ይህ ኤርድሮፕ ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን  አትጠራጠሩ።

ቶሎ ጀምሩ ጊዜው ሳያልፍ

በኤርድሮፕ አለም ሁሌም ጥሩ የሰራ ሰው ተጠቃሚ ነው።እናንተ ብቻ ወጥራቹ ስሩት።

አሰራሩ በጣም ቀላል ነው።

ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇👇
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጁ መሠረት የንብረት ታክስ ከመክፈያው ቀነ ገደብ አንድ ቀን ካለፈ ባለ ንብረቶች ከሚከፍሉት የታክስ ተመን ላይ 5 በመቶ ጨምረው እንዲከፍሉ በሚያስገድደው ድንጋጌ ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ትናንት በተደረገው የአስረጂዎች መድረክ፣ የገንዘብ ሚንስቴር ተወካዮች የቅጣት ድንጋጌው ባለ ንብረቶች በፍጥነት ታክስ እንዲከፍሉ ያግዛል በማለት ተናግረዋል። ረቂቅ አዋጁ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዳይጎዳ የታክሱ መጠን በሀብት ደረጃ ተለይቶ እንዲቀመጥም ቋሚ ኮሚቴው ጠይቋል።

ረቂቅ አዋጁ፣ የሐይማኖት አገልግሎቶች የሚሰጡባቸውን ቦታዎችና የመቃብር ሥፍራዎችን ከታክስ ክፍያ ነጻ ያደረገ ሲኾን፣ የሐይማኖት ተቋማት ለንግድ ሥራ የሚያውሏቸው ንብረቶች ግን ታክስ እንደሚጣልባቸው ደንግጓል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ አካል ጉዳተኞች፣ የመድሃኒት አምራቾችና ኢንደስትሪዎች ከታክስ ነጻ እንዲደረጉ የጠየቁ ሲኾን፣ የገንዘብ ሚንስቴር ተወካዮች ግን ኹሉንም አካላት ከታክስ ነጻ ማድረግ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮችን ገቢ በማሳነስ መሠረተ ልማቶችን እንዳያሟሉ ችግር ይፈጥራል በማለት ጥያቄውን ሳይቀበሉ ቀርተዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ኢጋድ የአንካራውን ስምምነት እንደሚደግፉ አስታወቁ!!

የአውሮፓ ኅብረትም የአንካራውን ሥምምነት እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡ ኅብረቱ ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውጥረት ከማርገብ ባለፈ የመከባበር እና የመነጋገር አስፈላጊነትን እንደሚያንጸባርቅ አመላክቷል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ስምምነቱ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ኃላፊነት የሚሰማቸው መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ሊቀመንበሩ በቱርክዬ ፕሬዝዳንት አቀራራቢነት የተደረሰው ስምምነት የሚበረታታ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሥምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የቆየውን ማኀበራዊ መስተጋብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካ ስምምነቱ ትብብርን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይነት ምክክር እንደሚያስፈልግ ጠቁማለች፡፡ በስምምነቱ ሂደት ጉልህ ሚና ለተጫወተችው ቱርክዬም ምስጋና አቅርባለች፡፡

በተመሳሳይ ዩናይትድ ኪንግደም የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለጋራ ልማት እና ብልፅግና ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩበት መሆኑን ገልፃለች። በአፍሪካ ቀንድ ትብብርን፣ መረጋጋትን፣ ልማትን እና የጋራ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምትደግፍም አረጋግጣለች። ለስምምነቱ እውን መሆን ቱርኪዬ እና የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለተጫወቱት ሚናም ምስጋና አቅርባለች፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/01 00:07:40
Back to Top
HTML Embed Code: