Telegram Web Link
ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።

በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡

መስከረም 3ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡ ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች በማሳመን߹ በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ በሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡

ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ እኔ ነኝ የገደልኳት ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።

የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤቱ እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

@አዲስ አበባ ፖሊስ

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ዛሬ ማምሻውን በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠው የመብራት ኃይል አገልግሎት ወደነበረበት እየተመለሰ ነው

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

ስለሆነም የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

@Sheger_press
@Sheger_press
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ዩ በአርባምንጭ ጎዳና በሞተር እየተንሻር ዛሬ‼️

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
BUMS‼️

በርግጠኝነት ይህ ኤርድሮፕ ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን  አትጠራጠሩ።

ቶሎ ጀምሩ ጊዜው ሳያልፍ

በኤርድሮፕ አለም ሁሌም ጥሩ የሰራ ሰው ተጠቃሚ ነው።እናንተ ብቻ ወጥራቹ ስሩት።

አሰራሩ በጣም ቀላል ነው።

ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇👇
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ውክልናቸውን አንስቼባቸዋለኹ ባላችው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትት ጌታቸው ረዳ ምትክ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጄኔራል ታደሠ ወረደ እንዲተኩ ሰሞኑን ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር በተደረገ ስብሰባ ጠይቆ እንደነበር መስማቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ዐቢይ ግን የደብረጺዮን ቡድን ያቀረበውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉት ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ዐቢይ በዚኹ ስብሰባ ላይ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራውን እንዳይሠራ የደብረጺዮን ቡድን እንቅፋት ኾኗል በማለት ወቅሰዋል ተብሏል።

የደብረጽዮን ቡድን ግን፣ ጌታቸው ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነታቸው መነሳት አለባቸው በሚለው አቋሙ አኹንም እንደጸና መኾኑን ምንጮቹ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በጌታቸው ምትክ ማን መሾም እንዳለበት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እየተነጋገረ መኾኑን የደብረጺዮን ቡድን ለወራት በተደጋጋሚ ሲናገር እንደነበር አይዘነጋም።

@Sheger_press
@Sheger_press
በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።ከ22 ብር ወደ 100ብር አድጓል

ለትምህርት ሚኒስቴር በተፃፈው ደብዳቤ
"የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።"ተብሏል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#የምርኩዝ ድጋፍ የነደለውና ማታ ላይ የሚያበራው እጅ

በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱ ነገስታት ዓለምን ሲቆጣጠሩ መነሻቸውን ሮም ያደረጉ ትውልዳቸው ከአብያ መንግስታት ቢሆንም በክርስትናቸው ስጋት የገባቸው ዘጠኝ ቅዱሳን አባቶች ወደ ግብጽ አቀኑ፡፡ ከዚያም በ470ዎቹ ዓ.ም አካባቢ በንጉስ አልአሜዳ ዘመነ መንግስት በአቡነ አረጋዊ መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን በመባል የሚታወቁት እነዚህ ታላላቅ ቅዱሳን በአክሱም ቤተ ቀጢን በሚባ አካባቢ በሕብረት ተቀምጠው በመጀመሪያ የግዕዝ ቋንቋ ተማሩ፡፡ ከዚያም ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ግዕዝ ቋንቋ መተርጎም ጀመሩ፡፡ በሕብረት ይጸልዩና ወደ አካባቢው በመውጣት ወንጌልን ያስተምሩም ነበር፡፡ ከእነዚህ አንዱ ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ናቸው፡፡

ወንጌል ከማስፋፋት በኋላም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወት ለመመስረት ተስማሙ፡፡ ይህን ጊዜም መለያየት ግድ ሆነ፡፡ የአክሱም ሕዝብ ግን አባ ጰንጠሊዎንንና አባ ሊቃኖስን እባካችሁ አትለዩን በማለቱ በከተማዋ አቅራቢያ ገዳማቸውን መስርተዋል፡፡ አባ ሊቃኖስ የሚለው ስማቸውም በእውቀታቸው የተደመመው የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው፡፡ አባ ዸንጠሌዎን ከአክሱም ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት ወይም “እንዳባ ዸንጠሌዎን” በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚህ ስፍራ 1 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል ወይም “የቀበሮዎች ተራራ” ላይ ዐርፈዋል፡፡

አባ ሊቃኖስ በደብረ ቆናጽለር ገዳማቸውን ካነጹ በኋላ በትምህርታቸው በርካታ ደቀመዛሙርትን ያፈሩ ሲሆን ከሶሪያና ከግሪክ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስንና ቅዱሳት መጻሕፍትን ተርጉመዋል፡፡ ለ21 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸውም ከተራራው እየተነሱ ወንጌል ይሰብኩ፣ በከሳቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ ወይም አባ ሰላማ ክርስትናን ተቀብለው የደከሙትን ክርስቲያኖችም ያጸኑ፣ አዳዲስ ክርስቲየኖችንም ያጠምቁ ነበር፡፡ ታዲያ ሁልጊዜም ከእጃቸው የማይለየውን በትረ ሙሴያቸውን ሲሰብኩም ሲጸልዩም የሚደገፉበት መዳፋቸው በዘመን ብዛት ሊነደል ችሏል፡፡ አስገራሚው ነገር ማታ ማታ ለጸሎት የሚያነሷቸው እጆቻቸው እንደ ፋና ቦግ ብለው ሲያበሩ መታየታቸው ነው፡፡

በ1928 ዓ.ም ጣሊያን ሀገራችንን በወረረበት ወቅት ሕዝቡ እንዳይገዛ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያላትን ትልቅ ሚና ስለሚያውቅ በርካታ ጥቃት አድርሶባታል፡፡ የአባ ሊቃኖስ ደብረ ቆናጽል ገዳምም በወረራው ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አንዱ ነው፡፡ ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ የገዳሙ መስራችና ታላቅ ሐዋርያዊ ተጋድሎ ያደረጉት፣ ወንጌል የሰበኩት፣ ክርስትናን ያስፋፉትና በርካታ መጻሕፍትን የተረጎሙት ጻድቁ ቅዱስ አባ ሊባኖስ ሕዳር 28 ቀን የእረፍታቸው መታሰቢያ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡

ቅዱሳን አባቶች በስጋችን መንገድ የጀመርነው ሩጫ አላዳርስ ብሎን ከነፍሳችን ገበያ ለራቅነው ለኛ ጸሎትና ምልጃ ያለማቋረጥ ያቀርባሉ፡፡ ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብዓ አጋንንቱን ታግሰው ስለሀገር፣ ስለ ሕዝብ እየጸለዩ በየገዳማቱ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች ያሳልፋሉ፡፡ እኛም ከበረከታቸው ተሳታፊ ለመሆን ገዳማቱን እናግዝ፣ በአታቸውን እናጽና፡፡         


ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
መረጃ‼️

የሶሪያው ፕሬዚዳንት ዋና ከተማዋን አስረክበው ፈረጠጡ

የሶሪያ አማፅያን የአገሪቱን መዲና ደማስቆን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተከትሎ  ፕሬዝዳንቱ መሸሻቸው ተነግሯል።

ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ያወጁት አማፅያኑ  አሁን ከተማዋ ከአሳድ ነፃ ነች ብለዋል።

የአገሪቱ ጦርም ይሄንኑ አረጋግጧል ።

ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ከተማዋን ለቀው መሸሻቸውን አርቲ ዘግቧል ።
በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?

- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል

- በአምቦ ከተማም በተመሳሳይ በተባራሪ ጥይት ተመትተው ሁለት ሰዎች ሞተዋል

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ገርጂ፣ ጃክሮድ፣ ሾላ፣ 6 ኪሎ፣ መነን፣ ጎሮ ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተኩስ ሲሰማ ነበር።

በርካታ ነዋሪዎች በድምፁ ተደናግጠዋል፣ መረጃ የሰጠ የመንግስት አካልም የለም።

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት ተኩሱ ከሰሞኑ ከመንግስት ጋር እርቅ ፈፀሙ በተባሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት የተተኮሰ ነው።

መገናኛ አካባቢ አንዲት ሴት በተኩሱ ምክንያት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉም ታውቋል። በተመሳሳይ ባለፉት ጥቂት ቀናት በአምቦ ከተማ በታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት ሁለት ሰዎች በተባራሪ ተመትተው እንደሞቱ ታውቋል።

ታጣቂዎቹ የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከሸገር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ወደ ሰማይ እየተኮሱ እንደገቡ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

"ታጣቂዎቹ በቅጥቅጥ አና በሃይሉክስ መኪና ተጭነው ሾላ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ተኩስ አየተኮሱ እየተጓዙ ነበር" ያለን አንድ የአይን ምስክር በሁኔታው በርካቶች እንደተደናገጡ ገልጿል።

ህዝብ በሚንቀሳቀስበት ጎዳና ላይ ድርጊቱ መፈፀሙ እንዳሳዘናቸው የገለፁት ነዋሪዎች ህዝብን በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ ቀድሞ ባልተገለፀበት ሁኔታ ማሸበር አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

መሠረት ሚድያ ሾላ ፖሊሲ ጣቢያ ከሚገኙ አንድ የፖሊስ አባል ድርጊቱን ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶች ከተኮሱ ቦታ በድንጋጤ ሲሸሹ ይታይ እንደነበር ገልፀዋል። (meseret media)

@Sheger_press
@Sheger_press
#የድንጋይ ወጋግራና የድንጋይ ምሰሶ

ተራራ የከፍታ፣ የታላቅነት፣ ቀና የማለት ምሳሌ ነው፡፡ የጽኑዕ ልብ፣ የትልቅ ራዕይ የጠንካራ ሀሳብ ማሳያ፡፡ ከመናገሻችን አዲስ አበባ በ622 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኝ አንድ ድንቅ ሀገራዊ ሀብት የያዘ ጥንታዊ መዳረሻ ላይ ከትመናል፡፡ ጣሪያው፣ ግድግዳው፣ ወለሉ፣ ወራጅና ማገሩ፣ ምሰሶና ወጋግራው ዓለት፣ ከዓለትም የተዋበ ዓለት የሆነበትን ድንቅ የጥበብ ስራ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ የሰራ ካሕን ወንጉስ ቅዱስ ላሊበላ፡፡ የሕንጻ አሰራር ከመሰረቱ ተጀምሮ ወደላይ የሚቆለል ሲሆን ቅዱስ ላሊበላ ግን ከጣራው ተነስቶ ወደ ታች በመፈልፈል ልዩ ጥበብ አሳይቷል። ይህም አይነት አሰራር ከሕንጻ ስራ ይልቅ ቅርጻ ቅርጽ ከመቅረጽ ጋር ይነጻጸራል።

11ዱን ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት በ22 ዓመታት ውስጥ ሲያንጽ ከየትኛውም ሰራተኛ ክፍያ አላስቀረም፡፡ ንጉስ ነኝና ብሎ ማንንም አላስገደደም፡፡ በቤተ ማርያም ጀምሮ ድንቆቹን አብያተ ክርስቲያናት ሰርቶ ሲያጢናቅቅ ኢየሩሳሌምን ለመሳለም በእግራቸው በረሀውን አቋርጠው የሚሔዱ ኢትዮጵያውያን ኢየሩሳሌምን እዚሁ ሀገራቸው ላይ እንዲያገኙ በማድረጉ አምላኩን አመሰገነ፡፡ ለዚያም ነው በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ማየ ዮርዳኖስና የአዳም መቃብር ሳይቀር በሕንጻዎቹ ውስጥ ያካተተው፡፡ ድንቅ ስራውን አይተው ካደነቁ የውጪ ሀገራት ዜጎች አንዱ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተባለው ፖርቹጋላዊ የካቶሊክ ቄስ ይገኝበታል፡፡

አልቫሬዝ በላሊበላ ያየውን ሁሉ ከጻፈ በኋላ ሲያጠቃልል እንዲህ ይላል፣ “እዚህ መጥቼ ያየሁትን ሁሉ ብጽፍ ማንም አያምነኝም፤ እናም ያየሁትን ሁሉ አልጻፍኩላችሁም፡፡ ምናልባትም ይህን የጻፍኩትን ራሱ አታምኑኝ ይሆናል፤ ነገር ግን በልዑል እግዚአብሔር ስም እምላለሁ የጻፍኩላችሁ እውነት ነው፡፡ በግራኝ መሀመድ ወረራ ጊዜም አካባቢው ላይ የደረሰው ይህ ጦረኛ ሰው ፍልፍልና ውቅር አብያተ ክርሳቲናት ሲመለከት እጅግ መደመሙን የታሪክ መዛግብት ያስነብባሉ፡፡ ግራኝ መሐመድ ያየውን ከአእምሮ በላይ የሆነ ስራ በማድነቅ በፍጹም ሳይነካው እንደሔደ አብረውት የነበሩት የጦር አበጋዞቹና ጀሌዎቹ ጽፈዋል፡፡  

በዩኔስኮ የዓለም ህዝብ ቅርስ ተብሎ የተመዘገበውን ይህንን ድንቅ የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ላሊበላ ክብር መገለጫ መሳለም ኢየሩሳሌምን መሳለም ነው፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ በሕይወቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ ውቅር አብያተ ክርስቲናቱን መጎብኘትም አለበት፡፡ በተለይ ከጌታ ልደት ጋር በሚከበረው የቅዱሱ ንጉስ የልደት ቀ29 ታሕሳስ 29 ላልይበላ መገኘት፣ የድንጋይ ወጋግራውንና የድንጋይ ምሰሶውን ለማየት ልዩ አጋጣሚ ነው፡፡

የቅዱሱ ንጉስ የመጀመሪያ ስራ በሆነችው ቤተ ማርያም ዙሪያ በሚገኘው ማሜ ጋራ አባቶች ሊቃውንት “ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ” የሚለውን ዝማሬ ልብን በሚመስጥ፣ ዜማ ሲያቀርቡ በዚያ መሆን መልካም ነው፡፡ የቅዳሴውን ልዩ ዜማና ምስጢር፣ የሌሊቱን ማሕሌት መታደም፣ በመላዕክት ዝማሬ ካሕናት ሲያሸበሽቡ መመልከት፣ ልደትን በኢየሩሳሌም የማክበር ያህል ድንቅ በረከት አለው፡፡ መንፈሳዊውን ነገር ብቻ እያሰቡ በዓሉን እንዲያሳልፉ ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ተዘጋጅቷል፡፡   

ለአረጋውያን፣  ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ምቹ ማረፊያም አዘጋጅተናል፤ ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17 ዓ.ም

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17 ዓ.ም

የጉዞ ዋጋ ምግብን ፣ ማረፊያንና መስተንግዶን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
ቻይና - ቤይጂንግ

📌የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያዋን ደብር ሰየመች፡፡

በቻይና ምድር የተከፈተው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም” የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አዲስ የተከፈተችውን ቤተ ክርስቲያን ከሰየሙ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን ማቁረባቸውም ተነግሯል።

በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን መሾማቸውም ነው የተገለጸው።

በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ መሳተፋቸውም ተነግሯል።

ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ በቻይና የሚገኙት ብፅዕ አቡነ ያዕቆብ ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ሀገሪቱ መዲና ቤይጂንግ ከተማ ማቅናታቸውም ነው የተገለጸው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
አዲስአበባ‼️

"ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ እንጠይቃለን" - የአዲስ አበባ ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
****

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
BUMS‼️

በርግጠኝነት ይህ ኤርድሮፕ ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን  አትጠራጠሩ።

ቶሎ ጀምሩ ጊዜው ሳያልፍ

በኤርድሮፕ አለም ሁሌም ጥሩ የሰራ ሰው ተጠቃሚ ነው።እናንተ ብቻ ወጥራቹ ስሩት።

አሰራሩ በጣም ቀላል ነው።

ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇👇
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
https://www.tg-me.com/bums/app?startapp=ref_cC18eXCc
ሰላም ‼️

ሰላም በጣም ጥሩና አስፈላጊ ነው። ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ መንገድ መምጣትም በጣም ደስ የሚል እና የሚበረታታ ተግባር ነው ። አገሩ በጦርነት ተዳክሟል። ህዝቡ ታክቶታል ።
.
ወደሰላም መንገድ የገቡ ታጣቂዎች የሚስተናገዱበት መንገድ ግን በደንብ ሊታሰብበትና ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል።
መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች መሃል ከተማ ከነትጥቃቸው እንዲገቡ ማድረግ ዛሬ የተፈጠረውን አይነት ችግር ይፈጥራል።
.
በመሰረቱ እነዚህን ታጣቂዎች የፈጠራቸውና ወደ ትጥቅ ትግል ያስገባቸው ብዙ ምክንያት ቢኖርም ከዚህ ቀደም ከአስመራ ስምምነት በኋላ የትጥቅ መፍታት እና ወደማህበረሰቡ የመቀላቀል ሂደቱ በአግባቡ አለመካሄዱም ነው ።
.
መንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ እና አገሩና ህዝቡ እፎይታ እንዲያገኝ ጥረት ማድረጉ ትልቅ ነገር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ታጣቂዎች ከስምምነት በኋላ የሚኖራቸው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ግን ሊታሰብበት ይገባል ።
.
ታጣቂዎች ወደ ሰላም ስለመጡ የከተማው ነዋሪ ሰላም ማጣት የለበትም ።

ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በጋሻው

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#ለታተመው መጽሐፍም ሦስት ጊዜ ይሰግዳሉ

ቅዱሳን መላእክት ምግባቸው ምስጋና፣ ምስጋናቸው ምግብ ሆኗቸው የሚኖሩ ከእሳትና ከነፋስ የተፈጠሩ ዘለዓለማዊ ረቂቃን መናፍስት ናቸው፡፡
የአምላካችን የእግዚአብሔርን ኃያልነት ይህን ያህላል ይህንንም ይመስላ ብለን ልንናገር የማንችለው መሆኑን ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ እነዚህ ረቂቃን፣ ኃያላን የሆኑ ፍጡራን የሚገዙለት መሆኑ ነው፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት ብለን እንናገር እንጂ በየነገዱ ስር ያሉት ቆጥረን የማንዘልቃቸው፣ እልፍ አእላፋት ናቸው፡፡

ከእነዚህ ነገዶች አንዱ ሱራፌል ወይም ሃያ አራቱ ካሕናተ ሰማይ ናቸው፡፡ የዚህ ነገድ አንዱ መልአክ ሱራፊ የሚባል ሲሆን ሱራፌል የሙሉ ነገዱ ስም ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ካህናተ ሰማይ በመባል ይጠራሉ፡፡ በዘመነ ኦሪት በሰው አምሳል በመገለጣቸውም ሽማግሌዎች ተብለው ተጠርተዋል፡፡   

በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሳያርፉ፣ ሳያቋርጡ የሚያጥኑት ካህናተ ሰማይ ምስጋናቸው ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ፡፡ በቅድስት ሥላሴ ስዕል ዙሪያ ከምናያቸው ገጾች ውስጥም ገጸ ሰብእና ገጸ አንበሳ ከኪሩቤል ነገድ፣ ገጸ ንስርና ገጸላሕም ደግሞ ከሱራፌል ነገድ ካሉ መላዕክት በመውሰድ ፊታቸውን ወደ ውጪ  ጀርባቸውን ወደ ውስጥ አዙረው መንበሩን እንዲሸከሙ አድርጓል፡፡ ይህም የእርሱን የፈጣሪያቸውን ፊት ማየት እንደማይቻላቸው ሲነግራቸው ነው፡፡

ሃያ አራቱ ካሕናተ ሰማይ ደግሞ መንበሩን እየዞሩ ያጥናሉ፡፡ ራዕይ 4÷6 እና 5÷8 ላይ እንደተጻፈው “ዙሪያውም ሃያ ዐራት ካህናት አሉ፡፡ በፊታቸው የበጉን ሥዕል፣ ደምን የተረጨች ልብስንም፣ የታተመ መጽሐፍንም ያያሉ፡፡ መንበሩን በዞሩ ቍጥር ለዚያ ለበጉ ሥዕልና በደም ለታለለችዋ ልብስ፣ ለታተመው መጽሐፍም ሦስት ጊዜ ይሰግዳሉ፡፡” ይህም ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድ ላይ ባለበት በዙፋኑ ይሰግዱለታል የሚለውን እውነታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

ይህ ምስጋና የማያቋርጥ፣ ዘመን የማይገድበው፣ የወቅቶች መፈራረቅ፣ የፀሐይና የጨረቃ መመላለስ የመይገድበው ነው፡፡ በሃያ አራቱ ካሕናተ ሰማይ ምሳሌነት በምድር ያሉ ካሕናት በቅዳሴ ጊዜ መንበሩን እየዞሩ በማጠን አምላካችን እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፡፡ “መንበሩን በዞሩ ቍጥር ለዚያ ለበጉ ሥዕልና በደም ለታለለችዋ ልብስ፣ ለታተመው መጽሐፍም ሦስት ጊዜ ይሰግዳሉ፡፡” እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ “ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለሥላሴ ምስጋናና ክብር ይገባል” እያሉ በመስገድ የዙፋኑ ምሳሌ የሆነውን መንበሩን ያጥናሉ፡፡ ሕዝቡም እውነት ነው ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ይላሉ፡፡


ይህ ምስጢር የሚፈጸምባት ቅዳሴው ውዳሴው የሚካሔድባት ቤተ ክርስቲያን ስትፈርስ፣ ገዳማትና ገዳማውያን ሲቸገሩ ማገዝ የዚህ ድንቅ ምስጢር በረከት ተካፋይ መሆን ነው፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ይኖራሉ፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን አባቶች እናግዝ ገዳማቸውን እናጽና ስብሐተ እግዚአብሔር የሚደርስበት ቤተ ክርስቲያኑንም እናንጽ፡፡   


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
የ28 ሰዎች ህይዎት የቀጠፈ የሱዳን ቦምብ ጥቃት

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 28 ሰዎች ሲሞቱ 37 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የደቡብ ካርቱም የድንገተኛ አደጋ ክፍል በሰጠው መግለጫ፤ በነዳጅ ማደያው ላይ በተወረወረ ቦምብ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

ይህም የ28 ሰዎችን ህይዎት በመቅጠፍ ከ37 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ባለፈ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማስከተሉ ተነግሯል፡፡

ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የዥንዋ ዘገባ አመልክቷል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
"መንግስት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ አለበት"- ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ ) ባወጣው መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት እየገቡ ካሉ ታጣቂ ሀይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት መንግስት ለህዝቡ ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ኢዜማ በመግለጫው አክሎም "ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሐድሶ ሥልጠና የሚገባ ታጣቂ ኃይል በሙሉ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ መሆን አለበት" ብሏል::

በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡

"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም" ሲልም አሳስቧል::

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/01 00:36:37
Back to Top
HTML Embed Code: