Telegram Web Link
የአፍሪካ ሀገራት ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት እንደተፈፀመባቸው?

የሚገርመው ግን ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚው ነች።

ሸገር ይሄንን መረጃ የተመለከተው በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመተንተን ደረጃ የሚያወጣው ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ነው።( #ሸገር_ፕረስ )

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ሁለት አናብስት መቃብሩን ቆፈሩለትና ገንዞ ቀበረው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓተ ብሕትውናን የጀመረው አባ ጳውሊ ሲሆን አባ እንጦንስ ደግሞ ስርዓተ ምንኩስናን ጀምሯል፡፡

በምድራዊ ሃብት ባለጸጋ የነበረው የጳውሊ አባት ሲያርፍ ታላቅ ወንድሙ ጴጥሮስ የራሱንና ትንሽ ልጅ የነበረው የወንድሙ የጳውሊን ድርሻ ሰጠውና ወንድሙ አካላመጠን ሲደርስ እንዲያስረክበው አደራ አለው፡፡

ጳውሊ አካለ መጠን ደርሶ ድርሻዬን ስጠኝ ሲለው ገና ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብሎ ከለከለው፡፡ እርሱ ግን በሀሳቡ አልተስማማም፡፡ ስለዚህም ጴጥሮስ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፣ የማረባውን አስቀርቶ መናኛውን ሰጠው፡፡

ጳውሊ በሁኔታው ተበሳጭቶ ወደ ዳኛ ሲሔድ አንድ ሃብታም ሞቶ ሊቀብሩት ይዘውት ሲሔዱ አየ፡፡ ይህን ጊዜ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ፣ ይህ ሰውም ሃባታም ነበር ሞቶ እኔም ሃብት ቢኖረኝም እሞታለሁ አለና፣ ወደ ቤት ሔዶ ወንድሙ ጴጥሮስን ሀብቱን ሁሉ አንተ ውሰደው ይቅርብኝ ብሎ ትቶት ወደ አንድ መቃብር ቤት ገብቶ መጸለይ ጀመረ፡፡

ከሦስት ቀናት በኋላም ግማሽ ህብስት ከሰማይ ወረደለት፡፡ ይህን ሲያይም እዚህ ሆኜ ይህን ያሕል በረከት ካገኘሁ ከዓለም ብለይ ድንቅ ተአምር ይደረግልኛል በማለት በረሃ ገብቶ ብሕትውናን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡

የበረከት ስራ እንደንሰራበት የተሰጠን ሃብታችን ለስጋዊ መሻታችን ብቻ እያዋልን የምንኮራ ስንቶቻችን ነን? ገዳማውያኑና ባሕታውያኑ ንቀውትና ጥለውት የሚሔዱት ሃብት በዓለም ስንኖር ሰማያዊ ቤታችንን ካልሰራንበት፣ እንደ ጳውሊ ወንድም እንደ ጴጥሮስ ከወንድማችን ጋር ካጣላን መጥፊያችን ሆኖብናል፡፡ አባ ጳውሊ ለ80 ዓመታት ከሰሌን ልብስ እየለበሰ የየትኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ፊት ሳያይ በጸሎት ሲቆይ የለመደውን ግማሽ ህብስት ቁራ ያመጣለት ነበር፡፡ በፍጻሜ ዘመኑም ምንኩስናን ከጀመረው ከአባ እንጦንስ ጋር በእግዚአብሔር ፈቃድ ተገናኝተው በርካታ መንፈሳዊ ነገር ተጨዋውተዋል፡፡
በኋላም አባ ጳውሊ እንደ አባ እንጦንስ የምንኩስና ቆብ መድፋት በመፈለጉ ሊያመጣለት ወደ ገዳሙ ሔዶ ሲመለስ አርፎ አጊኝቶታል፡፡

ቆቡን አድርጎለትም ሁለት አናብስት መቃብሩን ቆፍረውለት ገንዞ ቀብሮታል፡፡ የአባ ጳውሊን ነፍስም ቅዱሳን መላእክት በዝማሬና በምስጋና ወደ ሰማይ አሳርገዋታል፡፡ እነዚህ ድንቅ አባቶቻችን ዓለምና ስጋዊ ሃብትን ጥለው ክርስቶስን ብለው ገዳም ገብተዋል፡፡ ስጋዊውን ሃብት ሲተዉት በጸሎታቸው ኃይል የማድረግ መንፈሳዊ ሃብት ታድለዋል፡፡
በረከታቸው እንዲያድርብን የዘመናችንን ጳውሊና እንጦኒ ገዳማውያን አባቶችንና እንርዳ በአታቸውንም እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ኢራን‼️

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በአደባባይ በስቅላት ገደለች!


ሞሀመድ አሊ የተባለው ይህ ኢራናዊ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በርካታ ሴቶች እንደሚያገባቸው ቃል በመግባት አስገድዶ ደፍሯቸዋል ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በተከሰሰበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ትፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መሀመድ አሊ ከ10 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከእሱ የጸነሱትን ልጅ እንዲያስወርዱ መድሃኒት ሰጥቷልም ተብሏል፡፡

ሰውየው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 200 ሴቶች ደፍሮናል የሚል ክስም ተመስርቶበታል።

በግለሰቡ ተደፍረናል ያሉ ሴቶች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍም ተደርጎበት ነበር፡፡

ሀገሪቱም ግለሰቡን በአደባባይ በስቅላት እንዲቀጣ አድርጋለች።

Via_አልአረቢያ
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
አንድ ግለሰብ በደቡባዊ ቻይና በፈጸመው የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በደቡባዊ ቻይና በተፈጸመ የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ተገደሉ። በአገሪቱ ባለፉት አሥርት ዓመታት በላይ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ እጅግ አስከፊው ጥቃት እንደሆነ ይታመናል።

ክስተቱ በቻይና ብሔራዊ ቅሬታን የቀሰቀሰ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው ወንጀል ፈጻሚው ግለሰብ "ከባድ ቅጣት" እንደሚጠብቀው ቃል ገብተው የተጎዱትን ለማከም "ሁሉን አቀፍ ጥረት" እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ሰኞ ዕለት አንድ ግለሰብ ዙሃይ በሚገኘው ስታዲየም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎችን በመኪናው ገጭቷል።

“በአስከፊው እና በአሰቃቂው ጥቃት” አዛውንቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 45 ሰዎችም መቁሰላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፖሊስ እንዳለው ከሆነ የ62 ዓመቱ አሽከርካሪ ፋን እንደሚባልና ድርጊቱን የፈጸመው በፍቺው ውሳኔ ዙሪያ ደስተኛ ባለመሆኑ የተነሳ ይመስላል ።

ግለሰቡ ከዙሃይ ስፖርት ማዕከል ለመሸሽ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን እና በራሱ ላይ ባደረሰው ጉዳት ኮማ ውስጥ እንደሚገኝ ፖሊስ በመግለጫው አክሏል።

ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር መረጃ በባለሥልጣናት በኩል አልተገለጸም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ ‼️

በሶማሊያ አንድ ታጣቂ በከፈተዉ ተኩስ ሁለት ኢትዬጲያዊያን ተገደሉ!

በሶማሊያ ጋልጋዱል ግዛት የሶማሊያ ወታደር ዩኒፎርም በለበሰ ታጣቂ በተከፈተ ተኩስ ሁለት ኢትዬጲያዊያን ተገድለዋል

ይኼን ተከትሎም በግዛቶ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዬጲያዊያን ዛሬ ከሰአት በሆላ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስባቸዉ በመስጋት ለቀዉ እየወጡ እንደሆነ ተሰምቶል ፡፡

በጥቃቱ ዙሪያ  እስካሁን የሶማሌያ  መንግስት ምንም ያለዉ ነገር የለም ፡፡

በሶማሊያ የኢትዬጲያ ኢምባሲም ይሁን የመንግስት ባለስልጣናት ስለ ዜጎቻቸዉ ሞት እስካሁን ዝምታን መርጠዋል ፡፡

via አንኳር_መረጃ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢየሩሳሌም መቅደስ ደጃፍ ላይ ስምንት ሙዳየ ምጽዋት ይቀመጥ ነበር። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔዓለም በሴቶች መግቢያ በኩል ባለው ሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ቆሞ፣ ሁሉን በሚያውቅ ባህርይው ስጦታውንና ስጦታው የተሰጠበትን ልብ ያይ ነበር። አንዳንዶች ለዝና ሰጡ፣ ሌሎች ስጦታቸውን ኑሮአቸውን ሊያናጋ እንደማይችል በማሰብ ሰጡ።

አንዲት ድሃ መበለት ግን በቤትም በእጇም የነበራትን ሁለት ሳንቲም በሙሉ ሰጠች። ከእነዚህ ከሁለት ሳንቲሞች ውጪ በምድር ላይ ምንም ጥሪት ሀብት የላትም። በዚህ ጊዜ ጌታ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድሃ መበለት ከሁሉ አብልጣ ጣለች እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች" አለ፡፡


ይህ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣1-4 የሰፈረው ይህ ቃል የመስጠትን ምንነት ጌታችን በሚገባ ያስረዳበት ነው፡፡ ሁሉ የእርሱ ሲሆን በቸርነትና በልግስና ከሰጠው ላይ ስጡኝ ብሎ ይለምናል፡፡



የዚህች መበለት በጌታችን የተደነቀ መስጠት ብዙ ይነግረናል፡፡ አለማስተዋል እንጂ እንኳን ገንዘባችን እኛ ራሳችን ዋጋ የተከፈለብን የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነን።
አንዳንዶቻችን ከሰጠን የሚጎድልብን እየመሰለን እንሰስታለን፣ እግዚአብሔር ግን ስጡኝና ፈትኑኝ፣ የጎደለውን ባልሞላ በረከቱን ባላበዛ ታዘቡኝ ይለናል። ደግሞም ስጦታ ከጉድለት እንጂ ከትርፍ አይደለም።


ስጦታችን ካልተሰማን ገና አልሰጠንም ማለት ነው። እናም ማትረፍ ከፈለግን ከጉድለታችንም ቢሆን በፍቅር እንስጥ። በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ክረምቱን እያሳለፈ ላለው ገዳምና አባቶች እጃችንን እንዘርጋ፡፡



ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ሊጨምር ነው‼️

መንግሥት ከውጭ መሉ በሙሉ ተገጣጥመው በሚገቡ በኤሌክትሪክበሚሠሩ የቤት አውቶሞቢሎች ላይ የ5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ጭማሪ አድርጓል!!

በዚህ መሠረት በተሽከርካሪዎቹ ላይ የጉምሩክ ቀረጡ ከ15 በመቶ ወደ 20 በመቶ አድጓል።

የ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ የታክስ ጭማሪው ሥራ ላይ ሲውል የተሽከርካሪ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ መንግሥት ከታክስ የሚያገኘውን ገቢ እንዲጨምር ማሳሰቡ ይታወሳል።(ሸገር ፕረስ)

@ethio_mereja_news
በሶማልያ ግዛት ስር የተጠቀለለው የኢትዮጵያ መሬት‼️

ሶማልያ በመማሪያ መጽሐፍቶቿ ላይ የኢትዮጵያን ግዛቶች በራሷ ግዛት ስር ማካተቷ ተሰማ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ‹የሕልውና ስጋቴ ናት› በመማሪያ መጽሐፍቷ ላይ አካታለች፡፡

ሶማሊያ ኢትዮጵያን የሕልውና ሥጋቴ ናት በማለት ተማሪዎቿን እያስተማረች ነው፡፡ ለዚህም የመማሪያ መጻሕፍቷን እንደገና መከለሷን ኢንሳይድ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የሶማልያ መንግስት ሶማልያውያን ታዳጊዎች እና ህፃናት ኢትዮጵያ የህልውና ስጋት እና የሶማሊያ ታሪካዊ ጠላት እንደሆነች እንዲያምኑ በትምህርት ቤት ልጆች ላይ ማስረፅ ጀምሯል።

ይህንን ትርክት ለመደገፍ የሞቃዲሾ አስተዳደር ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የታሪክ እና የጂኦግራፊ መማሪያ መፃህፍትን ከልሷል፡፡ እነዚህ የተሻሻሉት የታሪክ መማሪያ መጽሃፍት በኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሀል ጥላቻ እና ቁርሾን የሚፈጥሩ ምእራፎች የተካተቱበት ነው፡፡

በተጨማሪም የተሻሻለው የጂኦግራፊ መማሪያ መፃህፍት የኢትዮጵያን መሬት በሶማሊያ ግዛት ውስጥ እንዲካተት እና እንዲጠቀለል አድርጎ ነው ያሻሻለው፡፡ በሶማልያ ግዛት ስር እንዲካተት የተደረገው የኢትዮጵያ መሬት አብዛኛው የሶማሌ ክልል ክፍል ነው፡፡

ይህም የሶማልያ ታዳጊ ትውልድ የዚያድ ባሬ ‹የታላቋ ሶማልያ› ትርክት በውስጣቸው ለማስረጽ ታልሞ የተደረገ ሳይሆን እንዳቀረ ተገምቷል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል

'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።

ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል።

ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።

በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።

በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
መምህሩ የ2 ሚሊየን የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ አሸናፊ ሆኑ

መምህር አዳነ ደሴ ይባላሉ የመምህርነቱን ሙያ በቅርብ ነው የተቀላቀሉት ፡፡ መምህር አዳነ የቀብሪደሀር ነዋሪ ሲሆኑ በ28ኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል ፡፤ በደረሳቸውም ገንዘብ መኖርያ ቤት እንደሚገዙበት ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በመንግስት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው”- ኢሕአፓ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡

ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት አመላክቷል፡፡

በመሆኑም “ወደፊት ትውልድ እንዲከፍል በብድር በመጣ የጦር መሳሪያ ንጹሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ አግባብነት የለውም”፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ለማለት እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በዝምታ ማስቀጠል አይችልም ሲል ኮንኗል፡፡

ኢሕአፓ መንግሥት በተለይ የጦርነት አውድማ በተደረጉት በአማራ፣በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በደቡብ ክልሎች ዉስጥ የሚደረገውን ህገመንግሥቱን እየጣሱ ያሉትን፣ መንግሥት መር የዜጎች ግድያዎችን በጥብቅ ማውገዙን እና ጦርነቶቹ አሁኑኑ ይቁሙ ሲልም አሳስቧል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ጠየቀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፤ በኢትዮጵያ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ፣ የሞት ቅጣት እንዲቀርና ሕጻናትን ለውትድርና መመልመል እንዲቆም ጠየቀ

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ባደረገው ግምገማ በርካታ አገራት አሳሳቢ ባሏቸው የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ዙሪያ ለኢትዮጵያ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥተዋል።

ከምክረ ሐሳቦቹ መካከል፣ የሞት ቅጣት እንዲቀር፣ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ኾኖ እንዲደነገግና ሕጻናትን ለውትድርና መመልመል እንዲቆም የሚሉት ይገኙበታል።

በጋዜጠኞች፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሲቨክ ማኅብረሰብ ድርጅቶችና በተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች፣ የአስገድዶ መሠወር ድርጊቶችና ከሕግ ውጪ የኾኑ እስሮች እንዲቆሙና በጊዜያዊ ማቆያዎች የተፈጸሙ የሥቅየት ድርጊቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩም በርካታ አገራት ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡

Via ዋዜማ

@ethio_mereja_news
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
የአንድ ቀን ህፃን ልጅ ተጥላ ተገኘች‼️

እንሴኖ፣ህዳር 5/2017 ዓ.ም በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ጫፍ እንሴኖ ኡስሜ ቀበሌ መውጫ ለሊት ላይ በአንድ መኖሪያ ቤት ከግቢ አጥር ውጪ አጠገብ የአንድ ቀን ህፃን ተጥላ ተገኝታለች።

በዚህም የቤተሰቡ አባላት ጠዋት ከመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውጭ ያገኟትን ህፃን ለከተማው ፖሊስ ፅ/ቤት አስረክበዋል።

የፖሊስ አባላቱ ከመንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ደህንነት ጋር በመሆን ለህፃኗ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት እንዲሁም የተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንድታገኝ ያደረጉላት ሲሆን

በአንዲት አጥቢ የፖሊስ አባላት አማካኝነት ለህፃኗ ጡት እንድትጠባና እና እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑን ከፖሊስ ፅ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቀዳማዊ እመቤት ዝናሺ ታያቸዉ "የህብርተሰቡን ችግር አዉቀዋለሁ የህዝብ ልጅ ነኝ" ሲሉ ተናገሩ

ቀዳማዊ እመቤቶ በፅህፈት ቤታቸዉ ስር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዳቦ እና የትምህርት ተቆማትን በማስገንባታቸዉ የሚያመሰግኖቸዉ ወገኖች ካባ እንደሸለሞቸዉ ይታወሳል ፡፡

በሌላ ወገን ፅህፈት ቤታቸዉ ኦዲት የማይደረግ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ አሰራር የሚከተሉ ናቸዉ በማለት ቀደማዊ እመቤቶን የሚወቅሱ አሉ ፡፡

እሳቸዉ ግን "ዳቦ ብሉ ብለን አቅርበናል፣ ሰላም ማፅናት የህዝብ ስራ ነዉ"በሚለዉ ንግግራቸዉ ይታወቃሉ ፡፡

በአንድ ዉይይት መድረክ ላይ በመገኘት የህብርተሰቡን ችግር አዉቀዋለሁ ፡የህዝብ ልጅ ነኝ ፡ ወደ ላይ ሳይሆን ወደ ታችኛዉ የህብረተሰብ ክፍል ማየት ይቀናኛል ሲሉ ቀዳማዊ እመቤቶ ተናግረዋል ፡፡

ይሄን ይበሉ እንጂ አዉቀዋለሁ የሚሉት ህዝብ አብዛኛዉ ኑሮ ዉድነት ከአቅሙ በላይ ሆኖ የእለት ጉርሱን ማሞላት በተቸገረበት ግማሹም ቀዬዉ በታንክ እና በድሮን እየታመሰ ባግዳድ በሆነበት የህዝቡን ችግር ካወቁት ለምን ለመፍታት አልሞከሩም የሚለዉን ጥያቄ አለመመለሳቸዉ አጠያያቂ ያደርገዋል ፡፡

@ethio_mereja_news
2024/11/18 15:36:12
Back to Top
HTML Embed Code: