Telegram Web Link
በወላይታ ሶዶ የ15 ዓመት ታዳጊዋን ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾ በጽኑ እስራት ተቀጡ

በወላይታ ሶዶ ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የወረዳው ፍ/ቤት አስታውቋል ።ተከሳሾቹ በቁጥር አምስት ሲሆኑ ጉርዛ ጉቡላ፣ጉቴ ጴጥሮስ፣ሙርቴ ሙኩሎ፣ወጣት ጩምቡሎ ጩጩሞ እና  ወጣት ካፍቴ ኢዮና  የተባሉ ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ በወላይታ ዞን በዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ሻላ ጽጾ ትፌ ቀበሌ ክልል ውስጥ ልዩ ሥሙ ጽጾ ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀባቸው ተገልፆል፡፡ የግል ተበዳይ የሆነችው በየነች ሞርካ የተባለች የ15 ዓመት ታዳጊ ስትሆን የጓደኛዋ ሠርግ ቤት ሄዳ ስትመለስ ተከሳሾች ሆን ብለው በቡድን ተደራጅተው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀሙባት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ተከሳሾቹን  ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል በሰውና በህክምና ሰነድ ማስረጃ አደራጅቶ ለአቃቤ ህግ ያቀርባል፡፡አቃቤ ህግም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ፍ/ቤት ያቀርባል።

በዚህም መሰረት የወረዳዉ ፍርድ ቤት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍ/ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። (ዳጉ_ጆርናል)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው::

ታላቁ አባት አባ ሕርያቆስ ፍቅርና ደግነት እንጂ ትምህርት ያልነበረው አባት ነበር፡፡ በብሕንሳ ገዳም የሚኖርው ይህ አባት ለጸሎት ያህል መዝሙረ ዳዊትንና አንዳንድ መጻሕፍትን ብቻ ነበር የሚያውቀው ብዙዎች ግን በአንድ ነገር በሚገባ ያውቁታል፤ ለእቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያን ባለው ፍቅር፡፡ ታዲያ በተለይ ከመዝሙረ ዳዊት መዝሙር 44ን ፈጽሞ ይወደው ነበር፡፡ በየሔደበትም ይህን ስለ እመቤታችንና ስለጌታችን የሚያወሳ መዝሙር በቃሉ ይጸልይ ነበር፡፡ ብዙዎችም በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ ይዘባበቱበት ነበር፡፡

ዛሬም በዘመናችን እኛ እውቀት ያልነውን ዘመናዊነት ባለማወቃቸው የምንንቃቸው ገዳማውያን አባቶች የሚሉንን ብንሰማ ሀገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ለእነዚህ ገዳማውያን አባቶች ክብር ቢኖረን፣ ገዳማቸውን ለማጽናትና በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያለውን ሙትአንሳ  ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም አቅማችን በፈቀደ ብናግዝ በጸሎታቸው በረከት እንጠቀማለን፡፡

////////////////////////////////////////////////////////////////////////
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፤ አንድ ቀን ታዲያ አባ ሕርያቆስ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::

በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር:: "እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::

እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራልና በሰዎች ዘንድ ደካማ መስለው የሚታዩትን ይመርጣቸዋል፡፡ ዓለምንና ኮተቷን ትተው የወጡ ገዳማውያን አባቶች ጥሪያቸው አንድና አንድ ነው፤ ለስጋ ገበያችሁ ስትሮጡ በነፍሳችሁ እንዳትጎዱ በገንዘባችሁ የበረከት ስራ ስሩበት፣ በሰማይም ብል የማይበላው መዝገብ ይኖራችኋል ነው፡፡

////////////////////////////////////////////////////////////////////////
አባ ሕርያቆስ የሁልጊዜም ምኞቱ የእመቤቴ ምስጋና በዝቶልኝ፣ እንደ እንጀራ ተመግቤው፣ እንደውሃ ጠጥቼው ባየሁ የሚል ነበር፡፡ እመብርሃን ምኞቱን አሳክታለትም አሁን ድረስ የምንጠቀምበትን ቅዳሴ ማርያምን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ቅዱሳን ድርሰቶችን ደርሷል፡፡

እርሱ ሳያውቅ ምስጋናዋን ብቻ እያሰበ ወደ ገደል ሲወድቅ በቀሚሷ ዘርፍ እንዳዳነችው ሁሉ ገዳማውያን አባቶችን የአባ ሕርያቆስን መንገድ ተከትለዋልና እርሷ ትባርካቸዋለች፡፡ እርሱ ቅዳሴ ማርያምን ለእመብርሃን ምስጋና በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ አዘጋጀ እኛ ደግሞ ቅዳሴዋን እየሰማን ነፍሳችን ትለመልማለች፡፡

ገዳማውያን አባቶችም የሚያለሙት ገዳም ነገ የምንባረክበት፣ ለሀገር ለወግን የሚጸለይበት ነውና እንዳቅማችን እናግዝ፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ :- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
መረጃ ‼️

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አክሰም አይጓዙም

የኅዳር ጺዮን ዓመታዊ ክብረ በዓልን በማስመልከት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጺዮን እንደሚጓዙ ተደርጎ በተለያዪዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የሰነበተው ዜና ፍጹም መሰረተ ቢስና በቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ለመጓዝ የተያዘ ምንም አይነት መርሐ ግብር አለመኖሩን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል።(fastmerja)

የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በየዓመቱም በ2 ሚሊዮን ይጨምራል።

የተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት 129.7 ሚሊዮን ደርሷል።

ይህ ቁጥር በ28 ዓመታት ውስጥ እጥፍ ሊሆን እንደሚችልም ሪፖርቱ ትንበያውን አስቀምጧል።

@ቢቢሲ

@ethio_mereja_news
የአፋልጉን ተማጽኖ

እህታችን ሲስተር አዲስዓለም ተስፋዬ ከመኖሪያ ቤቷ አዲስ ዓለም ልዩ ስሙ ኤጀሬ ከወጣች አንድ ዓመት የሆናት ሲሆን አለችበት ፣ ታየችበት በተባለችበት ቦታ ሁሉ ብንፈልጋትም የውሃ ሽታ ሆና ቀርታብናለች።

ተስፋ ባለመቁረጥ ከዛሬ ነገ ትመጣ ይሆናል ብለን ብንጠብቅም አልተመለሰችም።

ከዚያም ባለፈ በአካባቢያችን ለሚገኘው የፖሊስ ጣቢያ ያመለከትን ቢሆንም ምላሽ አላገኘንም።

እህታችን የአይምሮ ህመምተኛ መሆኗ በህክምና የተረጋገጠ ሲሆን ሲስተር አዲስዓለምን ያያችሁ ወይም የምትኖርበት የምታውቁ ከስር ባስቀመጥነው ቁጥር እንድታሳውቁን በፈጣሪ ስም በተማፅኖ እንጠይቃለን ።

ፈላጊ ቤተሰቦቿ
+251986573832
+2510986370995

ሼር በማድረግ ለሁሉም ተደራሽ እናድርግ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል ተሸልሟል፡፡

ሽልማቱ በዘርፉ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመታት የተገኘ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ከሽልማቱ በኋላም አየር መንገዱ ደንበኞቹ ለሰጡት ድጋፍ ምሥጋና አቅርቧል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተረፈ

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

Via: መናኸሪያ ሬዲዮ
ቤተመንግስት ተገኘ የተባለው ወርቅ ከተሸጠ የመንግስት አካላት ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው እናት ፓርቲ ገለፀ

ፓርቲው ባወጣው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” በሚል ያቀረቡት ገለፃ ላይ ለህዝብ ማብራርያ እንዲሰጡ ጠይቋል።

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም" ያለው ፓርቲው "ከእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አስቀድሞ ለ44 ዓመታት ደርግ እና ኢህአዴግ ሲመሩ ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" የሚለው ምላሽ እንደሚፈልግ ገልጿል።

ፓርቲው አክሎም "የተጠቀሰው ወርቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተነገረው ወርቅ ሳይሆን ከወርቅ የተሠሩ የተለያዩ መገልገያዎች ከሆኑ ወደ ብሔራዊ ባንክ እየተላለፈ ያለው ወርቅ ሳይሆን ከወርቅ በላይ የሆነ የአገር ቅርስ የትላንት እኛነታችን መገለጫ ከሆኑ ነገሮች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ መጠየቅ አግባብነት ይኖረዋል" ብሏል።

እናት ፓርቲ በመግለጫው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም ብሏል።

ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡ እናት ፓርቲ በጽኑ ያሳስባል በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

መሠረት ሚድያ በቅርቡ በሰራቸው ተከታታይ ዘገባዎች ይህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ የተነገረለት ወርቅ ጥፍጥፍ ወርቅ ሳይሆን የኢትዮጵያ ነገስታት ለዘመናት ሲገለገሉባቸው የነበሩ ከከበሩ ማእድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ዘውዶች እና የወርቅ እቃዎች እንደሆኑ ይፋ አድርጎ ነበር።

ጉዳዩ የበርካታ ዜጎች መነጋገርያ ቢሆንም መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ዙርያ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጠም። (meseret media)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዳማ‼️

ሰዉ ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆኖበታል
ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ወላጆች ተሳቀዋል ፡፡

አፈሳዉ ብሄር ሃይማኖት የትምህርት ደረጃ ሳይለይ በከተማዉ ሁሉም አካባቢ ቀጥሎል ፡፡

የአዳማ ነዋሪዎች የምሬት ድምፅ ነዉ፡፡


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Dogs Notcoin ያመለጣቹ ሰዎች Paws በፍፁም እንዳያመልጣቹ

- ሁለተኛ ዕድል ዳግም አይገኝም

- በሶስት ሳምንት ውስጥ 40 ሚሊዮን ሰዎች ገደማ ጀምረውታል።

ካለፈ እንዳይቆጫቹ ቶሎ ጀምሩ👇 👇
https://www.tg-me.com/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=gCb0B62i
https://www.tg-me.com/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=gCb0B62i
መረጃ ‼️

አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መንግሥት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመለ ይገኛል በማለት አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል!

ቡድኑ፣ በርካታ ወጣቶች ከግዳጅ ውትድርና ለመቅረት ለመንግሥት ባለሥልጣናትና ለገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ከፍተኛ ገንዘብ እየከፈሉ ይገኛሉ ብሏል።

ገዥው መንግሥት የክላሉን ሕዝብ የሰላም ጥያቄ በመጥለፍና የሰላም ጥሪ የሚደረግባቸውን ሕዝባዊ ሰልፍች በማዘጋጀት ለራሱ ፖለቲካዊ ዓላማ እየተጠቀመባቸው ይገኛል በማለት የወቀሰው ቡድኑ፣ ሕዝቡ መንግሥት ያልፈቀደውን ሰልፍ ሊያደርግ እንደማይችል ይታወቃል ብሏል።

በተያያዘ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ ትናንት በክልሉ በርካታ ዞኖች በተካሄዱት የሰላም ጥሪ የተንጸባረቀባቸው ሕዝባዊ ሰልፍች እጁ እንደሌለበት ዛሬ በኮምኒኬሽን ቢሮው በኩል አስታውቋል።

ሰልፎቹ ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ያካሄዳቸውና በክልሉ ያለው አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ የተጠየቀበት መድረክ መኾኑን የጠቀሰው የክልሉ መንግሥት፣ የክልሉ መንግሥት ለድጋፍ እንዳዘጋጀው ተደርጎ በተለያዩ አካላት የሚናፈሰው አሉባልታ ግን ከእውነት የራቀ ነው በማለት አስተባብሏል።

አሉባልታው በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሕዝቡ የሰላም ጥሪ እንዳይደርሳቸው በሚፈልጉ አካላት ኾን ተብሎ የተደረገ መኾኑን እንደሚያውቅ የክልሉ መንግሥት ጨምሮ ገልጿል።(ዋዜማ)

@Sheger_press
@Sheger_press
ነባር የሙስሊም መካነ መቃብር በኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ ገጠመው

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ጌዲዮ ዞን፣ ይርጋጨፌ ከተማ ነባር የሆነ የሙስሊም መካነ መቃብር የተወሰነ ክፍሉ ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎች እና የከተማው የእስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ ተናገሩ።

በከተማው የሚገኘው የቢላል መካነ መቃብር የመንገድ ማስፋፊያን ጨምሮ “ለሕዝብ መዝናኛ” ግንባታ 15 ሜትሩ እንደሚፈልግ የከተማው አስተዳደር ማሳወቁን ተናግረዋል።

መንገድ ዳር የሚገኘው እና ለ50 ዓመታት ዘላቂ ማረፊያ የሆነው መካነ መቃብሩ ለመንገድ ማስፋፊያ የተፈለገውን አምስት ሜትር ገደማ “አገራዊ ነው” በማለት ለኮሪደር ልማቱ እንዲውል ይሁንታ ቢያገኝም፤ ተጨማሪ የመካነ መቃብሩን 10 ሜትር መፈለጉ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል።

የከተማው አስተዳደር በይርጋጨፊ ከሚገነቡ አራት ዘላቂ ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሶ ‘ልማቱ አይቀሬ ነው’ ብሏል።

አንድ ለጉዳዩ ቀረብ ያሉ የአካባቢው ነዋሪ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ “ከሚፈለገው በላይ” አንሰጥም እያለ ነው በማለት፤ ቅራኔው ለመዝናኛ ከተባለው ተጨማሪ ክፍል ጋር የተያያዘ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከመካነ መቃብሩ የሚፈለገው ስፍራ “ፋውንቴን፣ ማረፊያዎች፣ መዝናኛ፣ በጎን ሱቆች” እንደሚሠሩበት መነገሩን ለጉዳዩ ቀረብ ያሉ ነዋሪ ገልጸዋል።

Via- BBc amharic

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በህንድ ሆስፒታል ውስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ የ10 ጨቅላ ህጻናትን ህይወት ቀማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ “ልብን በሚሰብረው አደጋ ህጻናት ልጆቻቸውን ላጡ ወላጆች መጽናናትን እመኛለሁ" ብለዋል
በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 10 አዲስ የተወለዱ ህጻናት ህይወት አለፈ። አርብ ምሽት በማሃራኒ ላክስሚ ባይ ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የደረሰው የእሳት ቃጠሎ በኤሌክትሪክ ችግር የተከሰተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#የጠየከውን አታገኝም?  


ሰው መሆን በራሱ ወደ ላይ ማንጋጠጥ፣ አንዱ ጥያቄ ሲመለስ ሌላ መጠየቅ፣ አንዱ ፍላጎት ሲሟላ ሌላኛው ላይ ማተኮር ያለበት ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ እጅግ አጥብቀን ፈጣሪያችንን ጠይቀን የማናገኛቸው ነገሮች ያጋጥሙናል፡፡

ሌሎች በቀላሉ የሚያገኟቸው እኛ ግን ነጋ ጠባ ፈጣሪያችንን ወትውተን ያላገኘነው ነገር ይኖራል፡፡ አልፎ ተርፎም ይህ አጥብቀን የምንሻው ነገር ሊኖረን እንደሚገባ በበርካቶች ዘንድ የሚታመንበት፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም እርግጠኛ ሆነው እንዳለን የሚያስቡት ይሆናል፡፡
   

ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከቱ ይደርብንና እንዲህ ይለናል፡፡ “እግዚአብሔርን ደጋግመህ ጠይቀኸው ያልሰጠህ ነገር ካለ፣ አንተን ደጋግመው ጠይቀውህ ያልሰጠሃቸው ሰዎች እንዳሉ አስብ፡፡” እግዚአብሔር “ፈታሒ በጽድቅ ኮናኒ በርትዕ“ ነውና እንደየስራችን ይከፍለናል፡፡


እገዛችንን ልንሰጣቸው እየቻልን አልፈናቸው የሔድን ስንቶች ናቸው? ጩኸታቸውን እንዳንሰማ መስኮታችንን የዘጋንባቸው፣ ወይም ዳንኪራችንን ከፍ አድርገን ጩኸታቸውን የዋጥንባቸው ስንቶች ናቸው?


የትኛውን ጥሪ ነው በአጽንኦት የሰማነው? ስለበደላችን በቀራንዮ አደባባይ “ኤሎሔ… ኤሎሔ… ላማ ሰበቅታኒ” አባት ሆይ ለምን ተውኸኝ ያለው ጥሪ የኛ አይደለምን? እርሱ የሁሉ ባለቤት ሲሆን “ተጠማሁ” ማለቱ የኛን መጠማት ለማርካት ደሙን ሲያፈስ ያሰማው ነው፡፡ ሞቱ፣ ግርፋቱ… የኛን ሞትና ግርፋት የተቀበለበት ፍጹም ፍቅሩ የተገለጸበት ድንቅ ስጦታው ነው፡፡

ይህን ያህል ዋጋ ከከፈለልን ለጥቂቷ ዓለማዊ ጥያቄያችን ደጋግመን ጠይቀን ካልተሰጠን ወደ ራሳችን እንመልከት፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታ የበረሀው ሐሩር የሌት ቁር የሚፈራረቅባቸው፣ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን ጸብአ አጋንንቱን ታግሰው፣ ዓለምን ንቀው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘውና ሙትአንሳ  ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ይኖራሉ፡፡


መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነውና በአታቸውን ለማጽናት እጃችንን እንድንዘርጋ ደጋግመው ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡ እንስማቸው!!!   



የሙትአንሳ  የማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም የኛን እገዛ ከመቼውም ግዜ በላይ ይፈልጋል።

                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000442598391

                        አቢሲኒያ ባንክ
                        141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
መረጃ‼️

በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ኤርፖርት ዛሬ ቀትር አካባቢ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር በአውሮፕላን መንደርደሪያ መንገድ ላይ እያለ በቴክኒክ ችግር መጠነኛ አደጋ እንዳጋጠመው ተዘግቧል ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
""ሥልጣን በቃኝ፤ በድጋሚ አልወዳደርም!"

🏃‍♂ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለህዝቡ የገባችውን ቃል እጠብቃለሁ አለች

"🏃‍♂"የስልጣን ዘመኔን ስለጨረስኩ በድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት አልወዳደርም ስልጣኔንም እለቃለሁ አለች

"🏃‍♂"እኔም በቃኝ፤አዲስ ሠው ወደ ኃላፊነት ይምጣ"አትሌት ገዛኸኝ አበራ

በእርግጥ ዛሬ በነበረው የባለድርሻ አካላት ስብሠባ አመራሮቹ ላይ የትችት ዝናብ ቢወርድም ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በስልጣን ዘመንዋ ስሟን ከፍ አድርጎ የሚያስጠራ ስራ መስራቷን መደበቅና መካድ አይቻልም፤

ምንአልባት ከኦሎምፒክ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ ችግሮችና በያዘችው አቋም እነዚህ መልካም ነገሮቿ ቢሸፈኑም በእሷ የስልጣን ዘመን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣በአለም የወጣቶች ሻምፒዮና፣በሀገር አቋራጭ፣በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች እጅግ አስደማሚ የሀገርን ስምና ባንዲራ ከፍ ያደረጉ አንፀባራቂ ውጤቶች መመዝገባቸው የፕሬዝዳንቷን የአመራር ብቃት ጠቋሚ ናቸው።

አሁን ግን ነገሮች የመጨረሻው ሠዓት ላይ የደረሱ ደራርቱም የቀድሞ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በሚል ለመጠራት የተቃረበች ይመስላል፤ላለፉት ስድስት አመታት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንትነት ወንበር ላይ የተቀመጠችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ "ተርሜን ጨርሻለሁ፤ስልጣን በቃኝ"በማለት ቀደም ሲል ለህዝቡ የገባችውን ቃል እንደምታከብር በዛሬው ስብሰባ ማሳወቋ ከብዙዎች አርአያነት ያለው በጎ ተግባር በሚል ውዳሴ እየቀረበላት ነው።

ለወንበራቸው ሲሉ ሀገርንም፣ስፖርቱንም ዋጋ የሚያስከፍሉ ሠዎች ባየንበት የስፖርቱ መንደር ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ"ተርሜን ጨርሻለሁ፤ከዚህ በኃላ በአመራርነት ወደ ፌዴሬሽኑ አልመጣም፤አንድም ሁለት ወር እንዲሁም ሁለት ዓመት የሠራ ሙሉ ተርሙን እንደሠራ ነው የሚቆጠረው"በማለት በዛሬው የባለድርሻ አካላት ስብሰባ ላይ የተናገረችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ"ተርሜን ጨርሻለሁ፤በቃኝ"ካለች በኋላ "በቀጣይ ለሚኖረው የስራ አስፈፃሚና የፕሬዝዳንት ምርጫ የምትልኳቸው ሶስት ሶስት ሠዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ፤ስፖርቱንና ሀገሩን የሚጠቅም ትክክለኛ ሠው መርጣችሁ ላኩ"በማለትም የጉባኤው አባላትን መክራለች።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ "ስልጣኔን እለቃለሁ"ከማለቷ በፊት ብዙ ያልተረጋገጡ ወሬዎች ሲናፈሱ የነበረ ሲሆን ከኦሮሚያ ውክልና የተነፈገችው ደራርቱ ቱሉ ከአዲስ አበባ ውክልና አግኝታ ለፕሬዝዳንትነት እንደምትወዳደርም በስፋት ሲናፈስ የነበረው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆኑን ደራርቱ በውሳኔዋ አሳይታለች።

ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ደራርቱ ሌላ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አትሌት ገዛኸኝ አበራ በስራ አስፈፃሚው ላይ የቀረበውን ትችት አምኖ በመቀበል እሱም በተመሳሳይ"እኔም ስልጣን በቃኝ፤አዲስ ፊት ወደአመራርነት ይምጣ"ሲል መናገሩም ታውቋል።

በተያያዘ ዜና የዕለቱ ትኩሳት የነበረው የአትሌቶች ማህበር ሁለት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውክልናን የማስነሳት አጀንዳ በተፈጠረው ከፍተኛ ተቋውሞ በታሠበው መልኩ ለውይይት ያልቀረበ ሲህን ጉዳዩን አስመልክቶ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ማብራሪያ ሠጥታበታለች"እኔ ውክልናየው ይነሳ አላልኩም ከመቼው ወደሚዲያ ሄደ ትንታኔ እንደተሠጠበት ሳይ ገርሞኛል፤ እባካችሁ ባልተረጋገጠ ነገር ወደ ሚዲያ አትሩጡ" በማለት ወቀሳ ያቀረበችው ፕሬዝዳንቷ"እኔ ያልኩት የአትሌቶች ውክልና ይነሳ ሳይሆን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ደንብ ላይ ያለ ድምፅ ይሳተፉ የሚለው በድምፅ እንዲሆን እንዲደረግ እንስራ ነው ያልኩት እንጂ እንዴት እኔን ወደስልጣን ያመጣኝ ማህበር ውክልና እንዲነጠቅ አደርጋለሁ"በማለት አስረድታለች።

ዛሬ ሙሉ ቀን በፍሬንድሺፕ በነበረው ስብሰባ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ላይ ውርጅብኝ የወረደ ሲሆን በተለይ አመራሩ የዓሣ ግማቱ ከአናቱ በሚል ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ነው በሚል የሠላ ትችት የቀረበበት ሲሆን ፌዴሬሽኑም ያቀረበው የጥናት ሠነድ የነበረባቸውን ጉድለት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ጥናቱን ያዘጋጁትም እንዲዘጋጅ የፈቀዱትም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

የደራርቱ "ሥልጣን በቃኝ፤ በድጋሚ አልወዳደርም"ካለች በኋላ ማን ቀጣዩ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ይሆናል? የሚለው የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን የቀድሞ አትሌቶች ስለሺ ስህንና አትሌት አሠፋ መዝጠቡን ወደኃላፊነት ለማምጣት ስራዎች መጀመራቸው ተሠምቷል።

Via በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/18 17:45:30
Back to Top
HTML Embed Code: